2022-08-26 16:05:08
የጢያ ትክል ድንጋይ
#ጉራጌን_እንወቅ
--------ክፍል- 2-------
የአንዳንዶቹ ትክል ድንጋዮች ቁመትም ከ1-5 ሜትር ሊረዝም እንደሚችል የአርኪዮሎጂ አጥኚዎች ሥራዎች ያመለክታሉ፡፡
በድንጋዮቹ ላይ የተቀረጹት ምስሎችም የጎራዴ ወይም የሰይፍ ወይም የጩቤ፣ የጦር፣ የትራስ እንጨት፣ ክብ ዳቦ ወይም ፀሐይ መሰል ቅርጾች፣ የግማሽ ጨረቃ ምስሎች እጆቹን ወደላይ የዘረጋ ሰው ክንዶች ናቸው : :
በቅድመ ታሪክ ይኖሩ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ድንጋዮቹን ለምን እንደተከሏቸው ባይታወቅም ትልቅ የጦር መሪዎች፣ ገዥዎችና ታላላቅ ሰዎች የተቀበሩባቸው ሥፍራዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡ ሊቃውንቱ ይህን ግምት የወሰዱት በአሁኑ ጊዜ በሶዶ፣ በስልጢና በጌድኦ ካሉት የመቃብር ድንጋዮች እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡
ምንም እንኳን ትክል ድንጋዮቹ መች እንደተተከሉ በትክክል ማወቅ ባይቻልም አንዳንድ አጥኝዎች ከ800 ዓመት በፊት እንደተተከሉ ይገምታሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ከቅድመ ታሪክ በፊት የነበሩ ኢትዮጵያውያን የተሠሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገምታሉ፡፡
የተወሰኑ ትክል ድንጋዮቹ ለብዙ ዓመት ሳይወድቁ የቀሩበትን ምክንያት ሲያብራሩም ከመሬት በታች ስምንት ሜትር ርዝመት ስላላቸው እንደሆነ ይገልጣሉ፡፡ በድንጋዮቹ ላይ ያለው የሰይፍ ብዛት ሟች ምን ያህል ልጆች እንዳሉት እና ምን ያህል አውሬ እንደገደለ ያሳያሉ፡፡
............ይቀጥላል………
ምንጭ #ኬር_ጉራጌ
#አዳብና በጥያ አለም አቀፍ ቅርስ ቅጥር ግቢ ውስጥ አልቀርም! ቻሌንጅ
335 viewsሮዛ ታደለ, 13:05