Get Mystery Box with random crypto!

አዳብና መልቲ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ adabnamidea — አዳብና መልቲ ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ adabnamidea — አዳብና መልቲ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @adabnamidea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 817

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-09-24 15:59:09
አገና ከተማ ጉራጌ የመስቀል ድባብ ዛሬ


አዳብና መልቲ ሚዲያ Telegram https://t.me/Adabnamidea

አዳብና ሚዲያ ዩቱብ https://youtube.com/channel/UCbihhwTdI6hy-e7Kj6T_J8g
231 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 15:37:03
ውቢትዋ ቡታጀራ ለመስከረም 30 የአዳብና ፌስቲቫል ካሁኑ እንዲ ዝግጅቱዋን ጨርሳለች።
መስከረም 30 #አዳብና በዶቢ ክስታኔ ገበያ አልቀርም!!

አዳብና መልቲ ሚዲያ Telegram https://t.me/Adabnamidea

አዳብና ሚዲያ ዩቱብ https://youtube.com/channel/UCbihhwTdI6hy-e7Kj6T_J8g
249 viewsedited  12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 15:26:50 'አዳብና' በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ
*ከዘፀአት ቱቼ # Zetseat Tuchie
==============
በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ በጉጉት ከሚጠበቁ የወጣት ወንዶችና ልጃገረጆች ጨዋታዎች መካከል 'አዳብና' አንዱና ዋነኛው የባህል ጨዋታ ነው። ይህ የወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች ጨዋታ ከመስቀል ደመራ ዕለት ጀምሮ እስከ ጥቅምት ዐምስት ዕለት ድረስ በየገበያ ሥፍራዎችና በየደብሩ በደማቅ ኹኔታ ይቀጥላል።
'አዳብና' ከመድረሱ በፊት ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች በተለያየ መንገድ 'አዳብናን' ለማክበር ይዘገጃጃሉ።ያላገቡ ወጣት ወንዶች፣ የቡሄ ዕለት በየአባቢያቸው ባለ ሰፊ መስክ ላይ ደመራ (ምጅር) ያቆማሉ። በዛው ክረምቱ ማለፉንም ጅራፍ በመተኮስ ያበስራሉ ። ሆያሆሄም በመጨፈር 'አዳብና' ጨዋታ ላይ ልባቸው ለከጀላት ኮረዳ ስጦታ ገዝቶ (ሎሚ፣ ማስቲካ)ለመስጠት ገንዘብ ያጠራቅማሉ።
ልጃገረዶችም በበኩላቸው በዐዲስ ዓመት ዋዜማ ቀን "አዬ አዬ ሆ አዬ አዬ ሆ አዬ ንብለ" እያሉ እንጊጫ በመንቀልና ለዐዲስ ዓመት እንቁጣጣሽ በመጨፈር 'ለአዳብናቸው' ገንዘብ ያጥራቅማሉ ፣ 'የአዳብና' ዕለት አምሮ ለመታየት አዲስ ልብስና ጌጣጌጣቸው ያዘጋጃሉ ፣ ፀጉራቸውን በልዩ ኹኔታ ይሠራሉ።
ወንዶችም፤ ሴቶችም ከዐዲስ ዓመት (አክራሚ) ዋዜማ ቀን ጀምሮ መስቀል እስኪደርስ ድረስ በየአካባቢው ባቆሙት ደመራ (ምጅር) ምሽት ምሽት ተሰብስበው ይጨፍራሉ። ይህ 'አዳብና' ከመድረሱ በፊት ጓደኝነታቸው የሚያጎለበቱበት 'አዳብና' የት የት እንደሚሄዱ የሚቀጣጠሩበት ጊዜ ነው።እንዲሁም ታዳጊ ልጆች አጨፋፈሩን የሚማሩበትና ልምድ የሚወስዱበት ጊዜም ጭምር ነው።
'አዳብና' የተለያዩ የጨዋታ መልኮች ቢኖሩትም፣ ወንዶች እና ልጃገረዶች አብረው ክብ ሰርተው፣ ወንዶች በጉረሮ በሚያወጡት ልዩ ድምፅ እና በጭብጨባ፣ ልጃገረዶቹ በከበሮና በጭብጨባ፣ የተወሰኑት ወንዶችና ልጃገረዶች ደግሞ በክቡ መሐል በመግባትና በመጨፈር የሚያሳዩት ትርኢት አንዱና ዋነኛው ነው።
የጨዋታውን የመስጀመሪያ ግጥም በማውጣት ወንዶቹም ልጃገረዶችም ሊሳተፉ ይችላሉ ። ለምሳሌ፦ ወንዱ ከጨዋታው ማሐል በፀባይዋና በመልኳ ቀልቡን የሳበችው ልጅ ካለች እንዲ ብሎ ሊገጥም ይችላል።
በማለሲ ቂልጡ ወፊ ይንጊሊጡ፣ (2)
ዚ የማና ቅንጡ እጅዲ ያረጡ፤
*ትርጉም፦ በትሿ ዋርካ ወፏ ትዘፍናለች፣
የማናት ልጅቷ ቅንጡ የኾነች፤
የቱሉ እንቁቦሆም ቶናም ጡብየኢ፣(2)
የአቢዲ ዲሞፍተር የመስሉ ላባኢ፤
*ትርጉም፦
እንደ ጋራ እንጉዳይ ቁጭ ብለዋል ጡቶቿ፣ የአባቴን
ዲሞፍተር ይመስላል ዳሌዋ፤
ግጥሞቹ ቅኔ ለበስ በኾነ መልኩ አድናቆት፣ ሽሙጥ እና ወቅታዊ ኹኔታዎችንም ያነሣሣሉ።
'አዳብና' ላይ ወንዶች ተሳታፊዎች "አጋት"የሚባል ሌላ ጨዋታም ጨምረው ይጫወታሉ። በመጀመሪያ አንድ ተጫዋች ከፊት ለፊት ቀጥ ብሎ ይቆማል ።ሌላኛው ተጫዋች ደግሞ በግምት ከ20 ሜትር ላይ በመንደርደር የቆመውን ተጫዋች ከእጁ በስተቀር ትክሻውና ጭንቅላቱ ሳይነካ ዘሎ ያልፋል።
ተጫዋቱ ጭንቅላቱን ሳይነካ ማለፍ ካቃተው፣ እሱ በተራው ቋሚ ይኾናል።ማለፍ ከቻለ ግን ቆሞ የነበረው ተጫዋች ትክሻ ላይ ወጥቶ በመቀመጥ ሎሚ ወደ ላይ ይወረውራል። ሎሚዋን ተሻምቶ የያዘ ሰው የሚቀጥለው ዘላይ ተጫዋች ይኾናል።አዳብና ላይ ከሚታዩ ጨዋታዎች መካከል የበትር ዝላለ፣ነጆ አራጆ፣ሰባ የሚጠቀሱ ናቸው።
አጋቲ፣የበትር ዝላለ፣ሰባ ወጣት ወንዶቹ ብቻ የሚጫወቱት ሲሆን ልጃገረዶቹ እጮኛዋ ሊሆን የሚችል ወንድ አቅምና ጥንካሬ የሚታይበት ጨዋታዎች ናቸው።

የወዶቹ አይን ውስጥ ለመግባት ከልጃገረዶቹ የሚጠበቀው አምሮ መታየትና ጎበዝ ጨፋሪ መሆን ነው:
Butajira and Dobi kistany
215 views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 15:26:48
189 views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 12:11:22
ሀቅ አይደበቅም፡፡እውነት አይሸሸግም፡፡ጉራጌ ያልቆረቆረው ከተማ ጉራጌ የሌለበት ከተማ ባዶ ነው፡፡
       የኢትዮጵያ ከተሞች በሙሉ በመስከረም ወር ያዝናሉ፡፡ምድር አረንጓዴ ለብሳ በአበቦች ስትፈካ ከተሞች ያዝናሉ ያነባሉ፡፡
         የመሰረቷት;ቆርቋሪዎቿ በረከት;ምርቃት ፍለጋ;ዘመድ አዝማድ ፍለጋ;ጨርቄን ማቄን;ሱቄን ቤቴን
ሳይሉ እንደ "ያቆብ"ሄደዋል፡፡
               ያ የሰላም ሰው ከተማ የለም፡፡
                ያ ታታሪ ሰው ከተማ የለም፡፡
               ያ ትጉህ ሰው የለም ገብቷል፡፡
ስራ አክባሪው;ሰው አክባሪው;ከተማው አስለቅሷት ሄዷል፡አሳዝኗት ሄዷል፡፡
               መዲናችን ሸገር; መርካቶ;ኮልፌ አጠና ተራ;ሾላ  ልጆቿ ጥለዋት ሄደዋል፡፡ስራው ሞቷል፡፡
                      በኬር ግበም
                      በኬር ተዘበርም
        ሙሌ ከአይመለል፡፡


አዳብና መልቲ ሚዲያ Telegram https://t.me/Adabnamidea

አዳብና ሚዲያ ዩቱብ https://youtube.com/channel/UCbihhwTdI6hy-e7Kj6T_J8g
238 views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 10:15:00
#አዳብና_ክብረ_በዓል_ is_Loding
#አዳብና_ደረሰ
#አዳብና_ሰላልኖ
አዳብና+ጢያ ትክል ድንጋይ +ጉሎ ፏፏቴ
310 viewsዘፀአት የዘጌ ገቾ, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:30:00
በአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ፕሮዲዩሰርነት በዚየን ዛየን ፊልም ፕሮዳክሽን ሲካሄድ የነበረው ሁለተኛው 'አዳብና' የተሰኘው የድምፃዊ የጃጋማ ኮርማ ሙዚቃ ቪዲዮ ቀረፃ ዛሬ አጠናቀናል።
በዚህ መዚቃ ክልፕ አዳብናን ከማስተዋወቅ ባሻገር የአካቢያችን የቱሪስት መስቦች የሆኑትን ጢያ ትክል ድንጋይና ጉሎ ገነተ ማሪያም ፏፏቴ ለማስተዋወቅ ሞክረናል።

ምስጋና
*****
ለሶዶ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት
ለቡኢ ኪነት ጥበብ ክበብ
በቀረፃው ለተሳተፋቹ የቀረፃ ባለሙያዎች በሙሉ
በማስተባበርና በተለያየ መንገድ ስታግዙን ለነበራቹ የማህበራችን አባላቶች።

#አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር
231 viewsዘፀአት የዘጌ ገቾ, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 20:49:58
196 viewsዘፀአት የዘጌ ገቾ, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 13:22:51
ቲሸርቱን የምትፈልጉ ሻሸመኔ አካባቢ ያላቹ የማህበራችን አባላቶች

የማህበራችን የሻሸመኔ አስተባባሪ
ዘሪሁን ጋሻውን ደውሉ
0995415674
324 viewsዘፀአት የዘጌ ገቾ, 10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:04:33
226 viewsዘፀአት የዘጌ ገቾ, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ