2022-06-20 18:36:34
ጸሀይን መመልከት..!
አዲሱ አስተማሪ ክፍል ውስጥ እንደገባ ተማሪዎቹ ራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ እና ስለራሳቸው አንድ ነገር እንዲናገሩ ያዛቸዋል።
መምህር፦እሺ አንተ ከፊት ያለኸው ጀምር...
ስሜ ካኑ ይባላል በትርፍ ጊዜዬ ጸሀይ ስትገባና ስትወጣ ማየት ደስ ይለኛል።
መምህር፦በጣም ጥሩ አንተኛው ቀጥል....
ስሜ ወልዴ ነው ሆቢዬ ጸሀይን መመልከት ነው።
መምህር፦አንተስ...
ኑርየ እባላለሁ፤ ጸሀይን መመልከት በጣም ያስደስተኛል...
እያለ እያለ ሁሉም ወንድ ተማሪዎች ራሳቸውን አስተዋውቀው ጨረሱ
ስማቸው ከመለያየቱ በስተቀር የሁሉም ተማሪዎች ትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ ጠራራ ጸሀይ መመልከት መሆኑ ያስገረመው አስተማሪ
"እሺ በጣም ጥሩ! አሁን ደሞ ልክ እንደወንዶች ሴቶች ተማሪዎች ራሳችሁን እያስተዋወቃችሁ ደስ የሚላችሁን ነገር ትነግሩኛላችሁ" አለና
ከፊት ተቀምጣ ወደነበረችው በጣም ቆንጅዬ ልጅ ጠቆመ።
እሺ ጀምሪ አለ አስተማሪው
.
.
.
.
እኔ ፀሀይ እባላለሁ በትርፍ ጊዜዬ..
@WubTarikoch
424 views15:36