2022-09-25 23:25:46
" ------ "
በይኝ በሽመሉ
ምቺኝ በከዘራ
የቀረሽ እሱ ነው
ካየሁት መከራ
አትያዢ ነገር
የተልባ እግር
እንቆቅልሽ ሆነ
የአንቺማ ነገር
ይታይሽ ጉዳቴ
ነግ በእኔ በይና
አስታውሺው ችግሬን
እንደ ራስ እዪና
ትዝ ይበልሽ እንጂ _ _ የቀድሞ ቃልሽ
እንደ ሐምሌ ዝናብ _ _ አይሁን አመልሽ
12/01/2015 ዓ,ም
ቴሌግራም ይቀላቀሉን እና ያካፍሉን :- CHANNEL :- @zooskales_views
ቡድን: - https://t.me/Literary_revolutionaries
41 views20:25