( በድጋሚ የተለጠፈ ) ተፃፈ ለ:- ልደት ሐይሌ ' ተዋዶ ይለያያል ' ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ | " የዞስካለስ እይታዎች "
( በድጋሚ የተለጠፈ )
ተፃፈ ለ:- ልደት ሐይሌ
" ተዋዶ ይለያያል "
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
የለኝም ቅሬታ
የለኝም ወቀሳ
ከቆረጠ አንጀትሽ
ልብሽ ከተነሳ
ይብላኝ እንጂ ለአይኔ
አንቺን ለለመደ
ለካስ ሰው ይለያል
እየተዋደደ
ይለያያል ሰው
እየተዋደደ..
ምን ይሆን መሓላ ?
ምን ይሆን ቃልኪዳን ?
ቃሉስ ኖሮን ነበር
እኛ ተከዳዳን
ቃሉስ እውነት ነበር
እኛ ተከዳዳን
የተነጋገርነው
ነበር ወይ ውሸት
ያሳለፍነው ግዜስ ?
ወራት እና አመት ?
ይበቃል ይበቃል
ካልሽስ ይበቃናል
ኑኖ ኑሮም
ለካ ይለያያል
እንግዲህ ገላዬ
አይድላ አይመቸው
የወደደውን ሰው
አጥቶ ከሚቆጨው
ምን ይኖራል ህመም
ከዚህ ደግሞ የከፋ
የካቡትም ሲናድ
ያመኑት ሲጠፋ
------- / /------------
10/11/2014 ዓ,ም
Join us ----
:- @zooskales_views
:- @Literary_revolutionaries