Get Mystery Box with random crypto!

" የዞስካለስ እይታዎች "

የቴሌግራም ቻናል አርማ zooskales_views — " የዞስካለስ እይታዎች "
የቴሌግራም ቻናል አርማ zooskales_views — " የዞስካለስ እይታዎች "
የሰርጥ አድራሻ: @zooskales_views
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 166

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-07-28 15:56:47
ሰውየው .
52 views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 00:04:56 ይቅርታ መጠየቅ የሚቻልበት መንገድ
( የሁለተኛው ክፍል )

ስለ ትዳር ጓደኛህ አስብ። ከዚህ በፊት አንድ ሰው ይቅርታ ሲጠይቅህ ምን እንደተሰማህ ለማስታወስ ሞክር። ታዲያ የትዳር ጓደኛህም ለምን እንዲህ እንዲሰማት አታደርግም? ጥፋተኛ እንደሆንክ ባይሰማህም እንኳ የትዳር ጓደኛህ እንደዚያ ስለተሰማት ወይም ድርጊትህ ያላሰብከውን ውጤት ስላስከተለ ብቻ ይቅርታ መጠየቅ ትችላለህ። እንዲህ ማድረግህ የትዳር ጓደኛህ ቅሬታ ቶሎ እንዲወገድ ሊረዳ ይችላል።—የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ ሉቃስ 6:31

ስለ ትዳርህ አስብ። ይቅርታ መጠየቅን እንደ ሽንፈት ሳይሆን እንደ ድል ቁጠረው። ምክንያቱም ምሳሌ 18:19 ቅሬታን ይዞ የሚቆይ ሰው “ከተመሸገች ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው” ይላል። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሥር መልሶ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ደግሞ ከባድ ምናልባትም ጨርሶ የማይቻል ነገር ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ግን ይቅርታ የምትጠይቅ ከሆነ በመካከላችሁ የተፈጠረው አለመግባባት ወደከፋ ችግር እንዳያመራ ማድረግ ትችላለህ። በሌላ አባባል ከራስህ ስሜት በላይ ትዳርህን ታስቀድማለህ ማለት ነው።—የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ ፊልጵስዩስ 2:3

ይቅርታ ለመጠየቅ ፈጣን ሁን። እርግጥ ነው፣ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ ላልሆንክበት ጉዳይ ይቅርታ መጠየቅ ከባድ ሊሆን እንደሚችል አይካድም። ሆኖም የትዳር ጓደኛህ ጥፋተኛ መሆኗ አንተ ተገቢ ያልሆነ ምግባር እንድታሳይ ሰበብ ሊሆንህ አይገባም። ስለዚህ ጉዳዩ ውሎ አድሮ መረሳቱ አይቀርም ብለህ በማሰብ ይቅርታ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበል። ቅድሚያውን ወስደህ ይቅርታ መጠየቅህ የትዳር ጓደኛህም ይቅርታ መጠየቅ ቀላል እንዲሆንላት ያደርጋል። ደግሞም ይቅርታ በጠየቅክ ቁጥር ለሌላ ጊዜ እንዲህ ማድረግ ቀላል እየሆነልህ ይሄዳል።—የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ ማቴዎስ 5:25

ከልብህ እንደሆነ አሳይ። ላደረግከው ነገር ሰበብ አስባብ መደርደር ይቅርታ እንደመጠየቅ አይቆጠርም። በተጨማሪም “ጉዳዩ እንኳ ይህን ያህል የሚያስቆጣ አይመስለኝም! ለማንኛውም ይቅርታ” በማለት የለበጣ ይቅርታ መጠየቅም ቢሆን ተገቢ አይደለም። ጥፋትህን አምነህ ተቀበል፤ እንዲሁም የትዳር ጓደኛህ ቅር መሰኘቷ ተገቢ እንደሆነ አመንክም አላመንክ ዞሮ ዞሮ ያስከፋት ነገር እንዳለ ተረዳላት።

እውነታውን አምነህ ተቀበል። እንደማንኛውም ሰው አንተም ስህተት እንደምትሠራ በትሕትና አምነህ ተቀበል! በተፈጠረው ችግር ውስጥ የአንተ እጅ እንደሌለበት ቢሰማህም እንኳ ሁኔታውን ከራስህ አንጻር ብቻ አትመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ “ክሱን አስቀድሞ ያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ ይህም ሌላው ወገን መጥቶ እስኪመረምረው ድረስ ነው” ይላል። (ምሳሌ 18:17) ስለ ራስህና ስለ ድክመትህ ትክክለኛ አመለካከት መያዝህ ይቅርታ መጠየቅ ይበልጥ ቀላል እንዲሆንልህ ያደርጋል።

አርታኢ :- ዞስካለስ ጥላሁን
20/11/2014 ዓ,ም
Join us ----
:- @zooskales_views
:- @Literary_revolutionaries
58 views21:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 00:04:51
45 views21:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 00:03:39 ይቅርታ መጠየቅ የሚቻልበት መንገድ
( የመጀመሪያው ክፍል)

ተፈታታኙ ነገር

አንተና የትዳር ጓደኛህ በሆነ ጉዳይ ተጋጭታችኋል። ‘ይቅርታ መጠየቅ አያስፈልገኝም፤ ጭቅጭቁን የጀመርኩት እኔ አይደለሁም!’ ትል ይሆናል።

ያጨቃጨቃችሁን ጉዳይ ብትተዉትም በመካከላችሁ ግን ውጥረት እንደሰፈነ ነው። አሁንም ይቅርታ ስለመጠየቅ ታስባለህ፤ ሆኖም “ይቅርታ” የምትለዋን ቃል ማውጣት ይተናነቅሃል።

ምክንያቱ ምንድን ነው?

ኩራት። “በውስጤ ኩራት ቢጤ ስላለብኝ አንዳንድ ጊዜ ‘ይቅርታ’ የሚለውን ቃል ማውጣት ከባድ ይሆንብኛል” በማለት ። አንተም ኩራት ካለብህ ለተፈጠረው ችግር የተወሰነ አስተዋጽኦ እንዳደረግክ አምነህ መቀበል ሊያሳፍርህ ይችላል።

አመለካከት። ይቅርታ መጠየቅ የሚያስፈልግህ ጥፋተኛው አንተ ከሆንክ ብቻ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል። ፦ “ሙሉ በሙሉ ጥፋቱ የእኔ እንደሆነ ካመንኩ ‘ይቅርታ’ ማለት ቀላል ይሆንልኛል። ሆኖም ሁለታችንም ትክክል ያልሆነ ነገር ከተናገርን ይህን ማድረግ ይከብደኛል። ያጠፋነው ሁለታችንም እስከሆንን ድረስ እኔ ይቅርታ የምጠይቅበት ምን ምክንያት አለ?”

ጥፋቱ ሙሉ በሙሉ የትዳር ጓደኛህ ከሆነ ደግሞ ይቅርታ ላለመጠየቅ በቂ ምክንያት እንዳለህ ይሰማህ ይሆናል። አንድ ባለትዳር “ምንም ጥፋት እንደሌለብህ እርግጠኛ ከሆንክ ንጹሕ መሆንህን ለማሳየት የምትሞክረው ይቅርታ ባለመጠየቅ ሊሆን ይችላል” ብሏል።

አስተዳደግ። ምናልባት ያደግከው ይቅርታ መጠየቅ እምብዛም ባልተለመደበት ቤተሰብ ውስጥ ሊሆን ይችላል። ከሆነ ደግሞ ጥፋትን አምኖ መቀበልን አልተማርክ ይሆናል። በዚህ ረገድ በልጅነትህ ጥሩ ሥልጠና ካላገኘህ አዋቂ ከሆንክ በኋላ ከልብ ይቅርታ መጠየቅ ሊከብድህ ይችላል።

 በቀጣይ :- ምን ማድረግ ትችላለህ?

አርታኢ :- ዞስካለስ ጥላሁን

20/11/2014 ዓ,ም
Join us ----
:- @zooskales_views
:- @Literary_revolutionaries
58 views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 22:46:20
19/11/2014 ዓ,ም
Join us ----
:- @zooskales_views
:- @Literary_revolutionaries
55 views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 20:48:10
" ተዋዶ ይለያያል "
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

የለኝም ቅሬታ
የለኝም ወቀሳ
ከቆረጠ አንጀትሽ
ልብሽ ከተነሳ
ይብላኝ እንጂ ለአይኔ
አንቺን ለለመደ
ለካስ ሰው ይለያል
እየተዋደደ
ይለያያል ሰው
እየተዋደደ..
ምን ይሆን መሓላ ?
ምን ይሆን ቃልኪዳን ?
ቃሉስ ኖሮን ነበር
እኛ ተከዳዳን
ቃሉስ እውነት ነበር
እኛ ተከዳዳን
የተነጋገርነው
ነበር ወይ ውሸት
ያሳለፍነው ግዜስ ?
ወራት እና አመት ?
ይበቃል ይበቃል
ካልሽስ ይበቃናል
ኑኖ ኑሮም
ለካ ይለያያል
እንግዲህ ገላዬ
አይድላ አይመቸው
የወደደውን ሰው
አጥቶ ከሚቆጨው
ምን ይኖራል ህመም
ከዚህ ደግሞ የከፋ
የካቡትም ሲናድ
ያመኑት ሲጠፋ
------- / /------------

10/11/2014 ዓ,ም
Join us ----
:- @zooskales_views
:- @Literary_revolutionaries
42 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 21:06:30
ከዋክብትን ዝገኚ
አለምን በመዳፍሽ..
ምድርን ሞላዋን
ይሁኑ ትራስ ለክንድሽ
ፀሐይ ትንፀባረቅ
ትብራ በአንቺ ዙሪያ
ታዛዋ ይሁን
ግዛትሽ የእሷ መጠሪያ
ከዋክብቶች ...
ከጀርባሽ አድብተው : የአንቺን መጥለቅ ነቅተው ይጠባበቃሉ .የቀኗ ፀሐይ መሆንሽን ዘንግተው : አንቺ ግን ከዳመናው በላይ ከአድማስ ጥልቅ ርቀሽ ያለሽ ሰማይ ነሽ ብያለሁ ።


እንኳን ተወለድሽልኝ እህት አለሜ ( ሕያብ )


ዞስካለስ ጥላሁን
176 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 22:02:40
ህመሙ ቢበዛ
ምን ያስጨንቀኛል
ምህረት ብታገኚ
ምንስ ያስከፋኛል
ደግሞስ ብትተኚ
አልጨነቅ ብዙ
አጠገብሽ አልሆን
አሉሽ ሰዎች ብዙ
ደግሞ ብትሞቺ
ፈፅሞ አላለቅስም
አፈርም አይብለሽ
እላለሁኝ እኔ ዝም
ዝምታዬ ለምን እንደሆነ
ሲያምሽ ታምሜያለሁ
ስትተኚም ማቀቅሁ
ስታጣጥሪብኝ ቀድሜሽ
ነው የሞትሁ .


28/09/2014
ለ ዮርዲ
181 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 21:50:09
' ምድሪቱ አሉኝ ከምትላቸው ውብ እንስቶች በላይ ከውብም በላይ ፀዳል የሞላት አንዲት ሴት አለች እርስዋም የእኔ እህት ዓለም ነች ( ሕያብ ) እንኳንስ ተወለድሽ ።

:- ሳቋ እንደ ፎስ ፈረስ በጭለማ የሚያበራ
:- ረዥም ዘንፋላ ፀጉር ያላት
:- ስሟ በክፉ የማይነሳ
:- መሲ የምትባል

አለ አይደል እንደ ንጋት ኮከብ
171 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 11:49:32 መልካም ልደት !!

1. ግንቦት 1 ቀን 1947 ዓ.ም ከእናታቸው ከወይዘሮ አለማሽ ገብረልዑልና ከአባታቸው ከአቶ ዜናዊ አስረስ በአድዋ ከተማ ተወለዱ።

ትምህርት

2. እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በዓድዋ ንግሥተ ሳባ ትምህርት ቤት ተማሩ፡፡ ከ1961 እስከ 1964 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጄነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት አዲስ አበባ ተከታተሉ።
3. በ1965 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ የሕክምና ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ።

የፖለቲካ ተሳትፎ

4. በ1966 መጀመሪያ በተማሪዎች መማክርት ምርጫ ላይ በመወዳደር የሣይንስ ፋኩልቲን በመወከል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምክር ቤት (Student Council) አባል በመሆን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ አመራርን ተቀላቀሉ።

5. በመስከረም ወር 1967 ዓ.ም የብሔረ ትግራይ ተራማጆች ማህበር (ማገብት) እንደተመሠረተ የንቅናቄው አባል ሆኑ።

6. በ1967 ዓ.ም አምባገነኑን የደርግ ሥርዓት ለመታገል ወደ ትጥቅ ትግል በመውጣት የተሃህት/ህወሓት አባል ሆኑ፡፡ ከ1967 እስከ 1969 በህወሓት ታሪክ የድርጅት ህልውናን የማረጋገጥ ምዕራፍ ፈተናዎች በፅናት ተሻገሩ።
7. በ1969 ዓ.ም የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ተወካይና የከፍተኛ አመራር አባል ሆኑ።

8. በ1971 ዓ.ም በህወሓት 1ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ፡፡
9. ከ1971-1975 ዓ.ም የትግራይን ሕዝብ በብሔራዊና ህዝባዊ ትግሉ በስፋት ለማሳተፍ በተደረገው እንቅስቃሴ በአመራርነት ተሳተፉ።

10. በ1975 ዓ.ም በሁለተኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴና የፖሊት ቢሮ አባል ሆነው ተመረጡ።

11. ከ1976-1981 ዓ.ም የህወሓት የትግል እንቅስቃሴን ከኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ጋር ለማስተሳሰር ከፍተኛ የጥናትና የአመራር ሚና ተጫወቱ።

12. በ1981 ዓ.ም በሦስተኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ የህወሓት ዋና ጸሐፊ በመሆን ተመረጡ።
13. በ1983 ዓ.ም ህዳር ወር በኢህአዴግ የመጀመሪያ ጉባኤ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።

መንግሥታዊ የአመራር ተሳትፎ

14. በ1983 ዓ.ም ግንቦት ወር ኢህአዴግ አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት ወቅት የኢህአዴግ ጊዜያዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ሆነው ለአንድ ወር ያህል አገለገሉ።
15. ከሐምሌ ወር 1983 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1987 ዓ.ም መጨረሻ የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚዳንት በመሆን አገለገሉ።

16. በ1987ዓ.ም የተካሄደውን የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ተከትሎ በመስከረም 1988 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ተመረጡ።

17. በ1992 ዓ.ም ሁለተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በመስከረም 1993ዓ.ም ተመረጡ።

18. በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን ሦስተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በ1998ዓ.ም መስከረም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ለ3ኛ ጊዜ ተመረጡ።

19. በ2002 ዓ.ም የተካሄደውን አራተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በ2003 ዓ.ም መስከረም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ለአራተኛ ጊዜ በመመረጥ እስከ ዕለተ ህልፈታቸው አገራቸውንና ሕዝባቸውን አገልግለዋል፡፡

20. ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘና በሌሎች ጉዳዮች የአፍሪካን ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ፣በቡድን 8 እና ቡድን20 ሃገራት ስብሰባ በማስተጋባት የአፍሪካ ቃል አቀባይ (Spokesman of Africa) የሚል ስያሜ ያገኙ ድንቅ የአፍሪካ ልጅም ነበሩ።

21. እአአ በ1995 ዓ.ም ከዩናይትድ ኪንግደም ኦፕን ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣በ2004 ዓ.ም ደግሞ ከኔዘርላንድስ ኢራስመስ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ሠርተዋል። እአአ በ2002ዓ.ም ደግሞ ከደቡብ ኮሪያ ሃናማ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሣይንስ የክብር ዶክትሬት ተቀብለዋል።

22. ለኢትዮጵያ ልማት፣ለዓለም ሰላም፣ለምሥራቅ አፍሪካ መረጋጋት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከ10 ያላነሱ የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ከተለያዩ ተቋማት ተቀብለዋል።


ዞስካለስ ጥላሁን
join us telegram :- @zooskales_views
251 views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ