Get Mystery Box with random crypto!

😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂

የቴሌግራም ቻናል አርማ zeget77 — 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂 ዝ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zeget77 — 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂
የሰርጥ አድራሻ: @zeget77
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.16K
የሰርጥ መግለጫ

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, 0902410718
° ° [ ዝገት ከ ከሌላጋ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Abusmovies

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-04 22:26:45 ብቀላ

ምእራፍ 13

ደራሲ ማርኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.

«አላልኩዎትም…አላልኩዎትም በውበትዋ መሽነፍዎ
ገባኝ። »

ሲጃራዬን እያቦነንኩ በሀሳብ እንደሚሟገት ሰው ካመነታሁ በኋላ በውበትዋ እንኳ መሽነፍ አልተሸነፍኩም፤
ብቻ እንደርስዋ ያለች ውብ ሴት አይቼ አላውቅም ።»

«እኔም አስቀድሜ ነግሬዎታለሁ ። ከእንግዲህ ግን አስጠነቅቆታለሁ ።»

«አስጠነቅቃለሁ?» ከመጠን በላይ ተደንቄ ፊቴን ቅጭም አደረግሁና ፡ «ከምኑ ፡ ከማንስ እንድርቅ ነው?
መቸም ከእመቤቲቱ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ። ምክንያቱም ያስተዋወቅኸን አንተው ነህ ። መቼም ተላላፊ በሽታ
ወይም ለሕይወት አስጊ የሆነ ነገር የለባትም ። በሽታ አለባት እንዴ?»

በሀሳቤ አመጣጥ ተደንቆ ሳቀ ፡ «የለም ሴትየዋ ስሜትዋ ስለሚለዋወጥ ዳግመኛ ሲያይዋት ቀዝቀዝ ትልቦት
ይሆናል » አለ ።

ስቄ ትከሻውን መታ ካደረግሁት በኋላ «ለመሆኑ በየትኛው እድሜዬ ነው እርስዋን የመሰለ የተወደሰች ሴት
መማረክ የምችለው?>>

«እንዴ! ሽበትዎ የእድሜዎን ማርጀት አይገልጽም አላለችዎትም እንዴ? ብቻ ይቅርታ ያድርጉልኝ ወይዘሮዋ ለኔ እንደ እህት ናት። ያለፈው ጓደኛዬ ፋቢዮ ከባለቤቱ ጋር የወንድምና የእህት ፍቅር እንድናጠናክር አድርጎ ነው ያለፈው። አሁንም ያው እየሳበኝ ልጠብቃት ስሜቴ ይገፋፋኛል።

አካሄዱ ገባኝ። እርሱ የመሬቱ ባለርስት ለመሆን ነው ሀሳቡ ። ምንም ዓይነት ተካፋይ እንዳይነሳበት ነው ጥረቱ።
በርሱ አስተሳሰብ ትክክል ነው ። ግን የመሬቱ ባለቤት እኔ ነኝ። ስለዚህ የኔ አስተሳሰብ ደግሞ ከእርሱ ለየት ይላል። ጨዋታችንን አውቄ አቀዘቀዝኩት ።

አርእስቱ የሰለቸኝ አስመስዬ ስሜቴን አስከፋሁኝ። ፌራሪ በሁኔታዬ ተደስቶ ግብዣውንም ቀልዱንም እንደገና ሕይወት ዘራበት። በሚከተለው ቀን ከቀትር በኋላ በጌታ ሮማኒ ግቢ እንደምንገናኝ አስታውሶኝ ስለ ኔፕልስ
ሰው አለባበስ መወያየት ጀመርን ። ስለኔፕልስ ነዋሪዎች የሞራል መላሸቅ አስተያየት ሰነዘርኩ። ሊሰጠኝ የሚችለውን አስተያየት እያወቅሁ ጆሮዬን ሰጠሁትና መለፍለፉን ቀጠለ።

<<እባክዎ ይተውት የሞራል ነገር» አለ የያዘውን ሲጃራ አምዘግዝጎ ወረወረና ። «ሞራል አልባ ፤ ሞራለ ቢስ ፤ የሞራል ውድቀት ፤ ምንድነው ይኸ ሁሉ መያዣ መጨበጫ የሌለው ነገር። አንድ ወንድ ሀያ የማፍቀር ችሎታ እያለው በአንዲት ሴት እንዲታሰር የሚደረገው ለምንድነው ። ሲያገብዋት ቆንጆ የነበረች ልጃገረድ ከሠርጉ በኋላ ቀፈታም ፤ ሻካራ ወይም እንደ ሲባጎ የመነመነች ነጭናጫ ትሆናለች። በሕይወት እስካለች ድረስ እንግዲህ የሞራሉ ግዴታ የወንድ ፍትወት በርዕዋ ታስሮ እንዲኖር ነው። ሕጉ ጤነኛ
አይመስለኝም። ደረቅ ነገር መጨረሻው መሰበር ነው።
ሕጉ ሲጣመም ደሞ ኅብረተሰቡ ጉድ ይላል። ራስን ማታለል ነው ። አንዳንዱ ሀገር ይህን ሁሉ ድክመት ሸፋፍኖ
መያዝ ይችላል ። የእንደኛ ያለው ደግሞ ፊት ለፊት ይጋጠመዋል ።>>

«በዓለም የሚፈለገው ግን ይኸ ብቻ አይደለም ብዬ ጀመርኩ። «ሰው ማለት የአራዊት ባሕሪውን ያሸነፈ
ማለት ነው ።»

«መጽሐፉ ምንድነው የሚለው?» ብሎ አቋረጠኝ።

<<ብላ ፤ ጠጣ ፤ ተደሰት ነገ ትሞታለህ አይደለም እንዴ የሚለዉ?>>

«የኔፕልስ መጽሐፍ ፤ አዎን ይላል አልኩት።» የሚያውቀውን እንዲያነብ እንጂ ልከራከረው ስለማልፈልግ «የዘመናዊ ስልጣኔ ሞራል ጠንቃቃ መሆንን አይጠይቅም ፡ አስፈላጊው በሕዝብ ፊት ቀሎ ያለመገኘት ብቻ ነው።
ይኸ ደግሞ ቀላል የቀላል ቀላል ነው» አልኩት ።

በአስተያየቴ ተደስቶ ራሱን ነቀነቀ ። «ትክክል አስቀመጡት ። ይኽ ደግሞ የሚቻል ነው ። የሴትን ስም ወይም
ክብር እንውሰድ። ይህ ስምዋ ከማግባትዋ በፊት በቀላሉ ሊጠፋ የሚችል ነው ። ነገር ግን አግብታ ትዳር ከመሰረተች በኋላ ነጻ ነች። አስራ ሁለት ውሽማ ልትይዝ ትችላለች። አያያዙን ካወቀችበት ባልዋም ላያውቅባት ይችላል ። ባል በሚማግጥበት ሀገር ሚስት የማትማግጥበት ምን አጥጋቢ ምክንያት አለ?»

የልቡን ሴሰኝነት ሁሉ አውጥቶ ሲዘበዝብ አተኩሬ አየሁት ። ያ ትክልክል ብሎ የተሰራው ፊቱ ቢከፍቱት ብልግና ብቻ ሆኖ ታየኝ ። የሚያስከብር ባሕል የሌለው ወፍ ዘራሽ ሻካራ አረም ነው ። ስሜቴ በሙሉ በአፈጣጠሩ ተቅለሸለሽ ። የሕመም ስሜት ተሰማኝ ። የፊት ገጽታዬ ተኮማተረ ። ትንፋሼ ከመጠን በላይ ከበደ ። ሁኔታዬ ፌራሪን አስደነገጠውና «ምነው አመሞት እንዴ ጌታዬን?» አለኝ ።

«አልፎ አልፎ እንደዚህ ያመኛል ። ሄጄ ልረፍ !»ብዬ ብድግ አልኩ : ስሜቴን በሙሉ ብልግናው ስላስቆጣኝ እንዳይከተለኝ ተከላከልኩ ። ጥቂት ቃላት ከተለዋወጥን ማንቁርቱ ላይ መወርወሬ ስለማይቀር ስሜቴን በብቸኝነት
ለማቀዝቀዝ ተጣደፍኩ። በስዕሉ ባለቤትነት መበልጸጌን ባጭሩ ገልጬ ! ወዲያው ከፈልኩት። አመስግኜ አዲዮስ
ብዬ ተለያየን ።

ቤቴ ስገባ ሌላ ሕመም ጠበቀኝ ። በጥንቃቄ ተመርጦ የተለቀመ ልዩ ልዩ ፍሬ በቅርጫት ተሞልቶ መሀል ጠረንጴዛ ጠበቀኝ ። በግል እንዲያገለግለኝ የቀጠርኩት ሠራተኛዬን ቪንቼንዞን ፍሬው ከየት እንደመጣ ስጠይቀው «ክብርት ማዳም ሮማኒ» አለኝ። ስምዋ የታተመበትን ካርድ አውጥቶ አሳየኝ። አገላብጬ አየሁት። የሚስቴ የእጅ ጽሕፈት አርፎበታል።

<<ጌቶች ቃል የገቡልኝን የነገውን ጉብኝት ለማስታወስ» ይላል ። ንዴት ሳይሆን ብሽቀት አደረብኝ ። ወረቀቱን ጨምድጄ ፤ ፍሬውን በንዴት በተንኩት ። ቪንቼንዞን
«ይህን ፍሬ ቶሎ አውጣና ለሆቴል ጠባቂው ልጅ ስጥ»
ስለው ሠራተኛዬ በትህትና ፍሬውን ሰብስቦ ወጣ ።»
ከራሴ ግቢ የተለቀመ የፍሬ ስጦታ ተላከልኝ ። ራሴን መቻል አቅቶኝ ሶፋው ላይ ተወረወርኩ ። በመገረምና በብሽቀት ልቤን እስኪያመኝ ከት ብዬ ሳቅሁ ።

ማዳም በቅጽበት ወጥመድዋ ገባች ። ሀብቱን እንጂ ምንነቱን ለማታውቀው ሰው ተሸነፈች። ይህ ወርቅ የሚሉት
ቢጫ የመጠንቆያ ብረት ምን የማይሠራው አለ ። ኩሩውን
ሰው ማማ ያስልሳል ። የሴት ፍቅር ለወርቅ የሸቀጥ እቃ ነው ። ወርቁ በተለቀ ቁጥር የፍቅር ሸቀጡ በርከት ይላል ።
ያዘጋጀሁት በቀል ብዙ የሚያደክም ውጣ ውረድ ያለው መስሎኝ ነበር ። ወጥመዱን ገና ከመዘርጋቴ የምፈልጋት
ጅግራ ሰተት ብላ ገባች ። ወርቄ እነኝህን ውሽታሞች ፤ ራሳቸውን የሚያታልሉ ድልሎች ከንቱ ቁመናቸውን አራቆተልኝ ። ሚስቴ እኔን ብቻ አይደለም የከዳችው ። ተፈጥሮዋ በሙሉ የጽናት ሳይሆን የክዳት ፡ የሴሰኝነትና የወረት ነው ። ፌራሪን ካሁኑ ሰልችታለች ፡ ልውጫው ይቀጥላል። እንደ ጓደኛዬ ፌራሪ እና እንደ ሚስቴ ኒና ያሉ ከአውሬ የባሱ አራዊቶች በኅብረተሰቡ ውስጥ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል? አውሬ ምን ጥፋት አለው ። አይዋሽም ከሞቱም በኋላ ቆዳቸው ያገለግላል። የውሸታም ሰው ግን ምላሱ ሆነ አስከሬኑ አየሩን ከመበከል ሌላ የሚሠራው ፋይዳ የለም።

የአንበሳ ሀቁ አባሮ የያዘውን ፊት ለፊት በመዳፉና በጥርሱ ማድቀቅ ነው። ሰው ግን ተደብቆ በመሳሪያ ኃይል ፍርሀቱንና ጨካኝነቱን ያስመሰክራል። ስለዚህ ለኔ ከሰው ይልቅ አራዊት ክብረት ይገባዋል።

<<ጌታ ሮማኒ ግቢ እንኳን ደህና ገቡ» ብላ ስትቀበለኝ፡
ለጆሮዬ ያልተለመደና ያልተጠበቀ አነጋገር ሆነብኝ። እኔው ራሴ እገዛ ግቢዬ መስክ ላይ መቆሜን ተጠራጠርኩ። በደመነፍሴ የራሴን ሚስት እጅ ስነሳ ፤ ፍልቅልቅ ብላ ተውባ ተቀበለችኝ ። ለአንድ አፍታ አእምሮዬ ውሉን ሳተ ። የግቢው አጸድ ዋዠቀብኝ። በክብረ ሞገስ የቆመው ዋና ቤት ፡ የሕጻንነት ጊዜዬን ያሳለፍኩበት ቤቴ በአንድ አፍታ ክምብል የሚል ሆኖ በዓይኖቼ ስር ከመቅጽበት ተንኮታኩቶ የሚወድቅ መሰለኝ ። ጉሮሮዬን ድርቅ
197 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:45 ስተኛ
ነው።»

ግብዣውን መቀበሌን ከአንገቴ ዝቅ ብዬ ገለጽኩ ። ጉዶ ፌራሪ የሚያሾፍ መሆኑ እየታወቀበት «ጌታዬ ሴቶችን እንደማይወዱ ማዳም ሮማኒ አታውቅም" አለ ።

እንዳላሳፍረው «ትክክል ብሏል ሲኞር ፌራሪ ፤ ሴትን የሚቋቋም ጉልበት የለኝም ። መልአክ የምትመስል ሴት ፈገግ ስትል መድረሻ ይጠበኛል» አልኩት ።

ነገውኑ ከቀትር በኋላ ቤትዋ ልመጣ ፤ ጉዶ መጥቶ ሊወስደኝ ፤ በቀጠሮ ላላሳፍራት እርስዋም ልጅዋን (ልጄን)
ስቴላን ልታሳየኝ ቀጠሮ ተቆርጦ ተስማማን ። እንደ መላእክት ጉብኝትዋ አጭርና ጥፍጥ ያለ ሆነብኝ ።

እጅዋን ለሰላምታ ዘረጋችልኝና ጎንበስ ብዬ በከንፈሬ ነካሁት ። መነጽሩን አተኩራ ካየች በኋላ ዐይንዎን ያምዎታልን?» አለችኝ ።

«ብርሀን አይደፍርልኝም ። ከእድሜዬ ጋር የተያያዘ ነው ።»

«እድሜዎ እንኳ ይህን ያህል የገፋ አለመሆኑ ግልጽ ነዉ ።"

«ፀጉሬ እንዲህ ጥጥ መስሎ ከዚያ ወዲያ ምን ይጠበቃል ።»

«ብዙ ወንዶች በወጣትነት በነጭ ፀጉር ይሸፈናሉ ። ሽበት እኮ የእርጅና ምልክት አይደለም ።»

ይህን እየተባባልን ሰረገላዋ ደረስን ። ጉዶ ፌራሪ እጁን ዘርግቶ እያለ የኔን እጅ ይዛ ሰረገላዋ ወጣች ። ልብስዋን አስተካክላ ሰረገላው ትቶን ተሽከረከረ ። ዘወር ብዬ
የጉዶን ፊት አየት ባደርግ ቅናት በልቡ መጠንሰሱ በጉልህ ይታያል ።

«ምነው ስሜትህም ጨዋታህም ድንገት እንደጨለመ ብርሀን ደብዘዝ አለብኝ ። ሴትየዋ እንዳልከው ተወዳዳሪ የሌለው ውበት ነው ያላት» አልኩት ።

ይቀጥላል...

ሀሳብ አስተያየት Any Comment @Zeget77


╔═══❖• •❖═══╗
@Abusmovies
╚═══❖• •❖═══╝
195 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:44 ብቀላ

ምእራፍ 12

ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.

«እውነት ከአንጀትዎ ነው ግብዣዋን አይቀበሉም?»
«በእውነት ነው የምልህ እኔ ምንም ያህል ቢዋቡ የቆንጆ ሴቶችን ፍቃድ የምከታተልበት ጊዜ የለኝም። በኔፕልስ የሚያስቸኩሉ ብዙ ጉዳዮች አሉኝ፡፡ይህ ከተጠናቀቀ ከዚያ ወዲያ ምናልባት ለእንዲህ ያለው ጉዳይ ጊዜ ሊኖረኝ ይችላል። ግን አትጠራጠረኝ ወዳጄ እመቤቲቱን እጅ የምነሳበት ጊዜ ወደፊት አላጣም።እኔ ለጊዜዉ ሴት ወይዘሮ ለማነጋገር እቅዱም ሆነ ጊዜዉ ስለሌለኝ ይቅርታ እንድታደርግልኝ በተገቢዉ ምርጥ ቃል እንዲገለፅልኝ ጠይቄ እንደገና አስደነቅሁት።

ከት ብሎ ከሳቀ በኋላ "በእዉነትም የሚያስደንቁ ሰዉ ነዎት ። የሴት ጥላቻዎ ከፍተኛ መሆን አለበት።"

"ጥላቻ ማፍቀርን ተከትሎ የሚመጣ ነዉ። እኔ ሴትን አፍቅሬም ጠልቼም አላዉቅ ። በኔ አስተያየት የሚጠሉበት አይታየኝም። ጥላቻ ከማፍቀር ይጠነክራል። የኔ ስሜት ሴቶችን በሚመለከት ለፍቅሩም ሆነ ለጥላቻዉ ግድ የለሽነት ነዉ።"

በሀሳቤ ያለመስማማቱ ግንባሩ ላይ እየተነበበ "ምንም ቢሆን በጊዜዎ ሴት አፍቅረዋል ። የሴት ፍቅር እንደ ፀሀይ ጨረር ነዉ ። በወቅቱ ለፍቅሩ ጨረር መጋለጥ በግድ ያስፈልጋል ።"

"አፍቅሬስ ነበር ።" አልኩት ። "ብቻ የኔ ፍቅረኛ ሳልጠግባት የቅድስናን ህይወት መርጣ ምናኔ ገባች ። "

"በራስዎ ጥፋት ነዉ። ሳይጠግቧት እንዴት ለቀቋት?"

"ይልቅ ስላንተ ስእል እንጫወት ዛሬ ልጎበኝልህ ብችል ከዘጠኝ እስከ አስር ጊዜ ነበረኝ። "

ፊቱ በደስታ ፈክቶ “ዝግጁ ነኝ ። ብቻ ዛሬ ዛሬ ስዕሌ እጅግም የሚያመረቃ ስላልሆነ ክብርዎን የሚመጥን ላይሆን ይችላል ።»

"ግዴለም የወዳጄን የእጅ ሥራ ማየት ደስታን ይሰጠኛል» አልኩት ። ከገበታ ላይ ብድግ ብዬ «ለፋቢዮ ባለቤት የተዘጋጀውን የአልማዝ ስጦታ ማየት ትፈልግ እንደሁ..."

ጥግ የተቀመጠውን ሳጥን ከፍቼ ለእንቁ ማስቀመጫ ፓሌርሞ ያሠራሁትን የእንጨት ሙዳይ ከፍቼ የአንገት ፤ የፀጉርና የእጅ አልማዝ አውጥቼ አሳየሁት ። አፉን ከፍቶ ራሱን መቆጣጠር እስኪያቅተው አደነቀ ። እያንዳንዱ አልማዝ በመልክ በመልኩ ያስደረግሁት ፖሌርሞ ሆኜ ነው ።
እጁ ላይ ካደረግሁለት በኋላ «ስለኔ ሆነህ ለማዳም ሮማኒ ስጥልኝ አልኩት።"

ካመነታ በኋላ «ግን ሊጐበኝዋት ይገባል ። ምስጋናውን እድትገልጽልዎ እድል ይስጥዋት ። ያለዚያ ይህን የሚያህል ስጦታ ተቀብላ ዝም ማለቱ ያሳፍራታል» አለ ።

እንጨት ሙዳይ ውስጥ አስገብቼ እንደገና ከረጢት ውስጥ ከከተትኩት በኋላ ከነቁልፉ ሰጠሁት ።

"በቅርብ ቀን ታስተዋውቀንና አናግራታለሁ ። ዛሬ ግን ያንተን ስቱዲዮ አያለሁ ። ለጊዜው ብቻዬን መሆን
ሰላለብኝ ሳሰናብትህ ይቅርታህን እየለመንኩ ነው ።"
ስለዉ ፈጥኖ ተነስቶ ተሰናብቶኝ ወጣ ። ያን ሀብት ይዞሲወጣ ሰው ሳይሆን አጥንት ተሰጥቶት ይዘህ ውጣ የተባለ ውሻ መስሎ ታየኝ ። የበቀል ግርፋት እንዲህ በረጅሙ ሲደግስ በዓለም የመጀመሪያ ሰው እኔ ነኝ ለማለት በልቤ ውስጥ ቃጥቶኝ ኩራት ተሰማኝ ።

ቀኑን ብቻዬን በፀጥታ ውዬ በቀጠሮው ሰዓት ወደ ፌራሪ ቤት አዘገምኩ ። ቤቱ ደርሼ አንኳኳሁ ። ተንደርድሮ ከፈተልኝና እየተርበተበተ የፎቁን ደረጃ እንድወጣ ጋበዘኝ ። ወዲያው ስዕሎቹን ማድነቅ ጀመርኩ ። እንዳለውም አንድም አዲስ ሥራ የለውም ። ሁሉም የማውቀው ነው።
ዘና ብዬ ተቀምጬ ስዕሎቹን ካየሁ በኋላ በመሬት አቀማመጥ ውበት ሥራው ላይ አተኮርኩ ። ሥራው የባለሙያ
ሳይሆን የተማሪ ነው ። ቢሆንም በጣም አድንቄ ያየሁትን በአምስት መቶ ፍራንክ እንደምገዛ ገለጽኩለት ። በዚህች
ብቻ የሕጻን ዓይነት ደስታውን ለመቆጣጠር እስኪያቅተው
እየገለፈጠ ሌሎች አራት ስዕሎች እንዳይ ጋበዘኝ ። እነኝያንም እርሱን ለማስደሰት ስል ገዛሁለትና እንደ ህጻን ፈነደቀ ። ቪኖ ጋብዞኝ የሚያስቁ ቀልዶች ሲያወራልኝ የሰረገላ ድምጽ ሰማሁ ። ቀጥሎም የበሩ ደወል አንቃጨለ ።

ማን እንደ መጣ ልቤ ነገረኝ ። መነጽሬን አስተካክዬ እንደተቀመጥኩ የምድር ቤቱ በር ተከፈተ ። ደረጃውን ክብደት የሌለው ፈጣን ጫማ ሲረግጠው ሰማሁ ። ክፍሉን የሴት ሽቶ ጠረን አወደው ። ባለቤቴን ፊት ለፊት ቆማ
አየኋት ።

ውበትዋ ለአንድ አፍታ አፈዘዘኝ ። መጀመሪያ ሳያት የማረከኝ ውበት እንደገና ስሜቴን ለመማረክ ቃጣው ።
በጥንቃቄ የተሰፋው የሀዘን ልብስ ውበትዋን በይበልጥ አጉልቶ አውጥቶታል ። ለጥቂት ሰኮንዶች በማራኪ ፈገግታዋ ካየችኝ በኋላ በአክብሮት «ሳልሳሳትጌታ ሲዛር ኦሲ ቫ ይመስሉኛል» አለች ።

ሀዘኑም ፡ ድንጋጤና እልሁም በአንድጊዜ ስለተባበሩብኝ አፌን አላውሼ የምናገርበት ልሳኔ ክው ብሎ ደረቀ።
እንዲያው ከአንገቴ ጎንበስ ብዬ አወንታዬን ገለጽኩ ።

ደርበብ ብላ ሁለት እጅዋን ለሰላምታ ዘረጋች ።
«እመቤት ሮማኒ ነኝ ። የሲኞር ፌራሪን ስቱዲዮ የመጐብኘት እቅድ እንዳለዎት ሰምቼ ለላኩልኝ ከግምት በላይ ውድ
ስጦታዎ ላመሰግንዎ መጣሁ።ልባዊ ምሥጋናዬን እባክዎ ይቀበሉኝ ።» ብላ ከአንገትዋ በአክብሮት ዝቅ አለች ።

እጅዋን ጥርቅም አድርጌ ጨበጥኳት ። ቀለበትዋ ስጋዋን ከፍሎ እንደሚገባና እንደሚያማት አድርጌ ጨበጥኳት " ስሜትዋን ተቆጣጠረች እንጂ አፍ አውጥታ መጮህ ነበረባት ።

«ይልቅስ ምስጋናው ከእኔ ሊደርስሽ ይገባል” ብዬ በሻከረ ድምፅ ለምሥጋና ጐንበስ አልኩ። «አልማዝ ዋጋ
በማይሰጥሽ የሀዘን ወቅት የማይረባ ስጦታዬን በመቀበልሽ ማመስገን የሚገባኝ እኔ ነኝ ። ሀዘንሽ ግን የኔው ነው ። ባለቤትሽ በሕይወት ቢኖር በእጁ አልማዙን አንገትሽ ላይ ያጠልቅልሽ ነበር። ከኔ እጅ በመቀበልሽ ምስጋናዬ ጥልቅ ነው ።»

አስተያየትዋ አስደነገጠኝ ። ደንግጣ ያስደነገጠችኝ ትክ ብላ በመነጽሬ ውስጥ ለማየት ስትሞክር ለማደናገር ፈጥኜ የመዝናኛውን ወንበር አቀረብኩላትና ሁሉን ትታ እንደ ንጉሥ ሚስት ደልቀቅ ብላ ተቀመጠች ። ፊትዋ ግን
በድንጋጤ ወዲያው ወየበ ። ካለማቋረጥ በሀሳብ ተውጣ ታስተውለኛለች ። ፌራሪ አዲስ የወይን ጠጅ እያዘገጃጀ የባጥ የቆጡን ይለፈልፋል ። «እህ ተነቃብዎት አይደል ጌታዬ?» አለ ወደ እኔ እያተኮረ ። «ይህን ሚስጢራዊ ቀጠሮ
እኛ ሆን ብለን ነው ያዘጋጀነው ። ልናስደንቆትም ፈልገን
ነው ። ወደ ሮማኒ ጊቢ የሚሄዱበት ቀኑ ሚስጢር ሲሆንብን ማዳም ሮማኒ ደግሞ ለተላከላት ስጦታ ሁሉ ምስጋናዋን እስክታቀርብ እንቅልፍ የሚወስዳት ስላልሆነ ይህን የሚስጢር ግንኙነት አዘጋጀን ። ታዲያስ በእመቤቲቱ
ውበት ምን ያህል ነው የተደነቁት?»

«ማነው በእንዲህ ያለው ውበትና ልጅነት የማይደነቅ? በዚህ ላይ ደግሞ እመቤቲቱ በእኔ ላይ ያላትን ስሜት ስመለከት ልቤ በኩራት ተሞልቷል ። በተለይ ሀዘን ልብዋን በሰበረበት በአሁኑ ወቅት እኔን ለማስተናገድ መነሳትዋ በጣሙን የተለየ ውለታ ነው ያደረብኝ ። »

ሀዘንዋን ስጠቅስ ስሜትዋ ጠውለግ ካለ በኋላ “ዋ ያ ፋቢዮ እዚች ቦታ አሁን ቢኖር ምንኛ ደስ ባለውና በሞገስ ባስተናገድዎ ። እኔ እኮ አሟሟቱ ድንገት ስለሆነ ላምን
አልቻልኩም ። እስከ መቼም ሀዘኑ የሚወጣልኝ አይመስለኝም ።» ዐይንዋ በእንባ ሲሞላ ቀና ብዬ ፌራሪን አየት አደ
ረግሁትና አፈር አለ ። ጓደኛዬ የባለቤቴን ያህል ማስመሰል አይችልም ።

«እባክሽን ለመጽናናት ሞክሪ ። ከሀዘን የሚገኝ ነገር የለም። ልጅ ስለሆንሽ መጪው ዘመን ያንቺው ነው ።
ባንቺ እድሜ ያለ ሰው ሀዘን ሊያበዛ አይገባም ።» ይህን እንዳልኳት እንባዋ ድርቅ ጥርስዋም ፍልቅቅ አለ ።

«ሀዘኔን ሊያጽናናኝ የሚችል ከእንግዲህ የእርስዎ ጉብኝት ነው ። መላው ቤቴ እርስዎን ለመቀበል ደ
213 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:44 መንገዱን ቀጠለ ። ጨረቃዋ የቁመናውን ግርማ ሙልጭ አድርጋ እስክታሳይ ድረስ ከጠራው ሰማይ ጋር የተዋጣለት ሰዓሊ ሥራ ይመስል ነበር ። የአደን አውሬን በመነጽር እንደሚያይ አዳኝ እኔ ስለቴን እያደራጀሁ ከየሁት ። አሁን ፍጹም ወጥመዴ ውስጥ ገብቷል ። ነፍሱን በማይምረው አጥፊው እጅ ገብቷል ። እንድምረው የሚያደርገኝ አንድም የፀፀት ንስሀ የመግባት ፍንጭ ስላልሰጠኝ ቅጣቱን ያለ ይቅርታ ደገስኩለት ። በሁለቱም ከሀዲዎቼ መሀል የሚሽቴ ሀጥያት ማመዘኑን ግን አልተጠራጠርኩም ። ራስዋን ለማስከበር የቅንጣት ያህል ፍላጐት ቢኖራት ኖሮ የዓለም ፈተና ቢፈታተናት እንኳ ማለፍዋ አይቀርም ነበር ። ስለዚህ በሁለቱም ላይ የበቀል ስለቴ የሚያርፍ መሆኑን አረጋገጥኩ ። ይህን ሁሉ እያሰብኩ በመስኮት ከዐይኔ ርቆ እስኪሄድ ድረስ አየሁት ። ወዴት እንደሚሄድ አውቃለሁ ።የባል ሀዘን ያደቀቃት አልቃሽ ለማጽናናት ነዋ! የበቀል ጀምሬ በእንዲህ ዓይነት ተከናወነና መስኮቱን ጥዬ አረፍት ወሰድኩ ።
ይህ በሆነ ማግስት ፌራሪ ከቁርስ ገበታ ሳልነሳ ተመልሶ መጣ " የሮማኒ ባለቤት ስጦታውን ከመቀበልዋ በፊት የባለቤትዋ እንግዳና ወዳጅ በመሆኔ በአስቸኳይ ተቀብላ ልታነጋግረኝ መፈለግዋን ነገረኝ እንዲቀመጥ ጋበዝኩት እህ ትናንትና ማታ እንዳልከው አገኘሀት?"አልኩት
«አዎ ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ነው መልእክትዎን ሰጠኋት ። በጣም ተደስታለች ። ብቻ ስጦታው ከመቀበልዋ በፊት እንዲያነጋግርዋት አበክራ ጠይቃለች በሀዘንዋ ምክንያት እንግዶችን እንደልብዋ ለመቀበል ባትችልም የባለቤትዋን ወላጆች ወዳጅ ለመቀበል ትፈልጋለች »በአክብሮት አንገቴን ዝቅ አድርጌ «በእውነት ከሚገባኝ በላይ ነው ወይዘሮዋ የምታከብረኝ » እንዲህ የሚያጓጓ ግብዣ እምብዛም ደርሶኝ አያውቅም ። ግን አዝናለሁ ግብዣውን ለመቀበል ያዳግተኛል ። በተለይ በቅርብ ጉብኝቱን ለመፈጸም አይመቸኝም ። እባክህ አስተዛዝነህ አለመቻሌን ንገርልኝ ።» በጣም ተደንቆ ግራ የተጋባ መሰለ «እውነት ከአንጀትዎ ነው ግብዣዋን አይቀበሉም?».....
ይቀጥላል.....




ሀሳብ አስተያየት Any Comment @Abusmovies


╔═══❖• •❖═══╗
@Zeget77
╚═══❖• •❖═══╝
226 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:44 ብቀላ

ምእራፍ 11

ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.


ለመጨበጥ እጁን ዘረጋልኝ ለዚያ ሁሉ ወሮታዬ ጥላቻ ከመለሰልኝ ከሀዲ ጋር መጨባበጡ የሲኦልን ያህል ከበደኝ ። ግን በትንሽ ስህተት እቅዱ ሁሉ ከሚበላሽ የኢዮብን ትእግስት ልዋስ ብዩ ከነጓንቴ ጨበጥኩት ። ተደሰተ መጠጥ አዞ ጽዋውን አነሳልኝ ስለሠዓሊነቱ ስለድህነቱ እየነገረኝ ወርቅ የሲጋራ መያዣውን ከኪሱ አውጥቶ ጋብዘኝና የገዛ ፊርማዬን እያነበብኩ አንዲት ሲጋራ አውጥቼ አቀጣጠልኩ ስለካውንት ሮሚ ባለቤት ውበት ጠየቅሁት እንደርስዋ ያለች ውብ ሴት በኔፕልስ ታይታ አትታወቅም ምታሰኝ ቆንጆ ናት አለኝ እንደውነቱ ከሆነ ለፋቢዮ ሮማኒ የምትገባት ሴት አይደለችም አለና እንደገና የውስጥ እሳቴን ቀሰቀሰብኝ
እኔ ልጅ ሆኖ ብቻ ስለማውቀው የቅርብ ሁኔታው አላውቅም በልጅነቱ አንባቢ ተመራማሪና ሰው ሚያምን ነበር አልኩት፡፡ አዎን የሞራል ሰው ነው ሞራል በሌለው ሀገር የሞራል ሰው መሆን ጅልነት ነው» አለኝ ።የሞራል ሰው ያለመውደዱን አድንቄት ዋንጫዬን አነሰሁለትከአንተ ጋር ጓደኝነትን በእርግጥ እመርጣለሁ» አልኩት ካውንት ሮማኒ እንዴት እንደ ሞተ ተረከልኝ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የጅል አሞሞት እንደሞተ አድርጉ ተረከልኝ የካውንቱን ልጅ ሁኔታ ጠየቅሁት እንደአባትዋ አይነት ጅል ናት አለኝ ልጄ በአንድ ወር ዕድሜ ከቤቱ አንድ የሚወዳት ሊገኝ ያለመቻሉን ከአነጋገሩ ተረድቼ እልህና የተስፋ መቁረጥ ላብ በጀርባዬ ኮለል ብሎ ወረደ የቀብር ሥነሥርዓቱ እንዴት እንደነበር ጠየቅሁት፡፡
"እኔ ራሴ ቀብሩ ላይ ተገኝቼ ነበር"
"አንተም አንተም በቀብሩ ላይ ተገኘህ?"ብዬ ጥንቃቄዬ ሁሉ ከዳኝ።"እኔ እኮ ከወንድም የቀረብኩ ጓደኛው ነበርኩ እንዴት ቀብሩ ላይ መገኘት የለብኝም?" «ይቅርታ አድርግልኝ እኔ ተስቦ ስለምፈራ አንተም ይህንኑ አስበህ እንደሁ ብዬ ነው » «የለም ተስቦ እንኳ እንደማያሰጋኝ በልጅቴ የማውቀው ነገር አለ ።» «ምን ዓይነት ነገር?»በተስቦ እንደማልሞት ተረጋግጦልኛል' እኔን የሚያሰጋኝ የቅርብ ወይም
ከወንድም የቀረበ ጓደኛ ሕይወቴን እንደሚያጠፋ ነበር ። ከወንድ የቀረበው ጓደኛ
አሁን ሞቶአል።ከእንግዲህ የሚያሰጋኝ ነገር ያለ አይመስለኝም»
ተደላድዬ ሲጃራውን እያጨስኩ ተቀመጥኩ እርሱም እንዲሁ ተደላድሉ በመተማመን እግሩን አነባብሮ ተቀመጠ አንድ ቦታ ብዙ ስለተቀመጥን በእግራችን እየተንሸራሸርን አየር እንድንቀበል ሀሳብ አቀረብኩና ቡና ቤቱን ትተን ወጣን «እና ጓደኛህን ታፈቅረው ነበር ማለት ነው?"
«ማፍቀር እንኳን አይደለም ስዕሎቼን ይገዛኝ ስላነበር እወደው ነበር መውደድም ቢሆን ከልቤ የነበረው ሚስት እስካገባ ድረስ ነበር »
«ሚስቲቱ በመሀላችሁ ገባች መሰለኝ ።»ወዲያው አርእስቱን ለመለወጥ ተቻኮለ ።
እድሜ እንዳስቸገረው ሽማግሌ እግሬን ጐተት አደረግሁና« ብርሃን ሲበዛብኝ እንደምታየው የዐይኔ ሕመም ይነሳብኛል »ካልኩት በኋላ "አንድ ቀን እንግዲህ ስዕሎችህን ታስጐበኘኛለህ ።»
በጣም ተደስቶ እንድጐበኘው ጋበዘኝ ። ምናልባትም በስዕሎቹ ደስ የሚለኝ ቢኖር በስጦታ መልክ እንደሚያበረክትልኝ ገለጸልኝ ። በስድስት ወር ውስጥ ሙያውን እስከ ጭራሹ ለመተው እንዳቀደ ሲጠቅስልኝ
«አሃ የሆነ ሀብት አገኘህ መሰል»
«ሀብት እንኳን አይደለም " ሀብት ያላትን ላገባ አቅጃለሁ ። »ስድስት ወር የሀዘን መፈጸሚያ አጭሩ ጊዜ ነው ።ከስድስት ወር በኋላ ሚሽቴን ሊያገባ ነው ። ስድስት ወር ድረስ ስንት ነገር እንደሚፈጸም ሳይገባው መቅረቱ ገረመኝ ። ጉሮሮውን አንቄ እዚያው ልጨርሰው ከጀልኩ ጣቶቼ በእልህ ተቆለፉ ስሜቱን የሚያረሳሳ ጥያቄ አመጣብኝ
«ጌታዬ ብዙ ሀገር የመጐብኘት እድል አጋጥሞታል
ለመሆኑ የመጨረሻዋን ቆንጆ ያገኙት በየትኛው ሀገር ነውአለኝ "
እኔ ሕይወቴን ያሳለፍኩት ቆንጆ ሴት በመምረጥሳይሆን ሀብት በማግበስበስ ነው ሀብት ቆንጆ ሴት ጭምር ይገዛል የሚል ፈሊጥ ስለነበረኝ ልቤ ወደሴት መስመሩን
ሳይለውጥ እርጅናው መጣ» አልኩት ከት ብሎ ከሳቀ በኋላ «ፋቢዮ ሮማኒም ከማግባቱ በፊትእንዲሁ የሚለው ነገርነበረው » አለ
«ለመሆኑ የፋቢዮ ባለቤት ቆንጆ ናት?» ብዬ ጠየቅሁት ።
«ቆንጆ የቆንጆ ቆንጆ ናት እንጂ ብቻ የሟች ባልዋ አባት ጓደኛ ስለሆኑ አንድ ቀን ሊጐበኝዋት ይገባል ። እኔ አስተዋውቃችኋለሁ ።»
«ለምን ? አስፈላጊ አይደለም በሀዘን የተጨበጠች ሴት ለሌላ ሰው ደንታ የላትም ። »አነጋገሬ እንደተዋጣልኝ ገባኝ ። ቸልተኛ በሆንኩ መጠን ፌራሪ እኔን ለማስተ
ዋወቅ ቋመጠ " የገዛ ሚሽቴን ለማስተዋወቅ መነሳሳቱን ውስጥ ውስጡን አንገበገበኝ «ያውም በአክብሮት ነው የምትቀበልዎት " በሀዘን የምትጨበጥበት ምክንያት ደግሞ ምንም የለም በአፍላ ወጣት እድሜዋ ላይ ናት፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ፋቢዮን የምትወደው ሰው አልነበረም ። የመጽሐፍ ሰው እንጂ ፍቅርን የሚለግስ ሰው አልነበረም ። ከዚህ በላይ ደግሞ አባትዋ ለሀብትሲሉ አጋብዋት እንጂ እርስዋ ወዳውአልተጋቡም።»
ሆቴል ደረስን ። ክፍሌ ውስጥምርጥ ቪኖ ጋበዝኩት ።ክፍሌ ውስጥ ባለው ዕቃ በጋበዝኩት ቪኖ ውድነት ተገረመ ሀብቴን አይቶ «ቀናሁብዎት» አለኝ ። «ልትቀናብኝ
አይገባም» አልኩት «አንተ ወጣት ነህ ፍቅር እጣ ፈንታህ ናት እኔ ግን የድሎትና የቅንጦት እንስሳ ብቻ ነኝ »አልኩት ።
ትኩር ብሎ ከተመለከተኝ በኋላ «ጌታዬ በልጅነቶ በጣም መልከ ቀና እንደነበሩ ሁኔታዎ ይናገራል» አለኝ ።አንገቴን ዝቅ አድርጌ ለአስተያየቱ ካመሰገንሁ በኋላ
«ለወንድ እንኳ በመጀመሪያ ደረጃ አስፈላጊው ጉልበቱ ነው ከዚያ መልከ ቀናነቱ ሁለተኛ ደረጃ ነው ይመስገነው ጉልበት ዛሬም አለኝ» አልኩት ።
«አጋጣሚነቱ ይገርሞት ይሆናል ! አንዳንድ ሁኔታዎና ለዛዎ ያንን ሟች ጓደኛዬን ፋቢዬ ሮማኒን ይመስላል።» ነገር ለማደናገር ወይን ጠጁን ሞላሁላት የመጨረሻውን ጠጥቶ«ይቅርታ ያድርጉልኝ አሁን ልሂድ እንግዲህ ለሮማኒ ባለቤት የሚልኩት ሰላምታ ካለ በዚህ ምሽት የማገኛት ስለሆነ ለመላክ ቸል እንዳይሉ ።»የምልከው ሰላምታ እንኳ የለኝ። አየህ ቆንጆ ሴቶች የሀቅ ሚዛን ስለሚጎድላቸው ላናግራቸው አልወድም ብቻ አንግዲህ ልቸገር ካልክ ሟች ባለቤትዎ ባለ ውለታዬ ስለሆነ በዋጋ ለመተመን የሚያስቸር እንቁ ስጦታ አዘጋጅቻለሁ ። ፋቢዮ ሮማኒ በሕይወት ቢኖር ለእርሱ ነበር የምሰጠው ዞሮ ዞሮ የእርስዋው ስለሆነ ይህንኑ ብታስረዳልኝ እወዳለሁ »
«በደስታ እታዘዛለሁ » በአክብሮት ከቀመጫው ተነስቶ ለመሄድም እየተዘጋጀ እንዲያውም እንዲህ ላለው የታላቅ ሽልማት መልእክተኛ መሆን የሚመረጥ
ነው ሴቶች ብርቅና ድንቅ ጌጥ ይወዳሉ ደግሞ አይፈረድባቸውም
የሚያማምር ዓይንና የአልማዝእክብል ይፈለጋል አሁን ልሂድ ከእንግዲህ ብዙ ጊዜ እንገናኛለን”ብሎ ሊጨብጠኝ እጁን ዘረጋ
"እንዴታ መገናኘታችን አያጠራጥርም" ብዬ የተዘረጋ እጁን ጨበጥኩትና ከክፍል እየተቻኮለ ወጣ የሆቴሉን ደረጃ ወርዶ የአትክልቱ መስክ አልፎ የዋናውን መንገድ ሲያያዝ በመስኮት ይታየኛል ትኩር ብዬ ሳየዋው እስኪያቅለሸልሸኝ ድረስ ጠላሁት»ትክልክል ብሎ የተሰራው ቁመናውን ሁሉ አጥንቴ ድረስ እስኪነዝረኝ ረገምኩት ። አካሄዱ ግን አስገረመኝ ። ነገ ተነገወዲያ የሚጠብቀውን ባለማወቅ ዕድሉ የደስታ
ፈረስ ያስጋለበችው ይመስል አካሄዱ የልቡን ደስታ ይገልጽ ነበር ። ባረማመዱ ከስድስቱ ወር የጓደኛ ሞት ሀዘን በኋላ መጪው ዘመን ለርሱ የዘንባባ አክሊሉን ይዞ የሚጠብቀው ይመስል ነበር ።አንድ ጊዜ ብቻ እንደመቆም አለና ወደክፍሌ ዞር በማለት እያመነታ ባርኔጣውን ብድግ ፊቱን እንደማራገብ አድርጎ
308 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ