Get Mystery Box with random crypto!

😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂

የቴሌግራም ቻናል አርማ zeget77 — 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂
የቴሌግራም ቻናል አርማ zeget77 — 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂
የሰርጥ አድራሻ: @zeget77
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.16K
የሰርጥ መግለጫ

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, 0902410718
° ° [ ዝገት ከ ከሌላጋ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Abusmovies

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-24 19:45:34 ታክሲ ውስጥ ሌባ ኪስህ ገብቶ ምንም ሲያጣ ነካ ያረግህና


ቆይ ግን ለመሆኑ ሒሳብ ማን ሊከፍልልህ ነው

@Abusmovies@Abusmovies
593 views , 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:34:06 ​​ የባከነች_ነብስ
#እውነተኛ ታሪክ
#ክፍል1⃣
የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

... ማታ ከጠጣሁት ወይን ጋር ስለቀላቀለብኝ ነገር እርቃኔን ስላነሳኝ ፎቶና ስለቀረፀኝ ቪዲዮ እያፌዘ ያወራልኛል። በጣም አፀያፊ ቃላቶችን እየተናገርኩና እርቃኔን እየደነስኩ የቀረፀኝን የቪዲዮ ምስል ሲያሳየኝ ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ በሀይል ድዉ ድዉ እያለች በጉሮሮዬ ልትወጣ ምንም አልቀራትም ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ።
<<አ.ም.ኜ.ህ ነ.. ነበ.. ነ.በ.ር! እንደ ህፃን ልጅ ተንተባተብኩኝ!
<<ደሞ እናንተ ምናችሁ ይታመናል? ሴትን ማመን መጨረሻዉ ለፍትህ አልባ ህመም መዳረግ እንደሆነ ከእኔ በላይ ምስክር አይኖርም!>>
እጅግ በጣም የሚያፈቅራት ሴት ከድታዉ እንደሄደችና በእሷ ምክንያት ሴቶችን መበቀል እንደሚያስደስተዉ እየተመፃደቀ ሲናገር አዉሬ እንጂ የሰዉ ልጅ አልመስልሽ አለኝ! በፍፁም ያልጠበኩትን ያልገመትኩትን ማንነትን ነበር የተላበሰዉ ልክ በለሰለሰ ቆዳ እንደተሸፈነ መርዛማ እባብ!። በ ሶስት ቀናት ዉስጥ 50ሺ ብር እንድሰጠዉ ካልሆነ ግን ፎቶዉንና ቪዲዮዉን በማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ እንደሚበትነዉ እየዛተበኝ ነገረኝ
<<እባክህ...በሴት ልጅ...አምላክ!...ስለ እናትህ ብለህ... ስለወደድኩህና ስላመንኩህ እንዲ ልታረገኝ አይገባም እባክህ...>>
የዓይኖቼ መስኮቶች ተከፍተዉ እንባዬ ገላዬን እስከሚያርስ ድረስ ለመንኩት!
<<አንድ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ገንዘቡን ካላመጣሽ...>>
ንግግሩን ሳይጨርስ ከለቅሶዬ ጋር ትቶኝ ወጣ! ዓለም በምን አይነት ክፉና አስመሳይ ሰዎች እንደተሞላች ዛሬ ገና ገባኝ! ክህደትና ዉርደቴን ተከናንቤ ከነበርኩበት ክፍል ወጣሁ ማታ እራት ለመብላት የገባንበት ሆቴል ነበር። ለእየሩስ ደዉዬ ያለሁበትን ቦታ በምልክት አስረድቼ በፍጥነት እንድትመጣልኝ እያለቀስኩ ነገርኳት ከ 30 ደቂቃ በሗላ እየሩስና አባቷ ኮንትራት ታክሲ ይዘዉ ያለሁበት ቦታ ደረሱ! እየሩስ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ
<<አይዞሽ የእኔ ቆንጆ ሁላችንም ከጎንሽ ነን! እኛ እንደዉም ማታ የእረፍቷን ዜና ሰምተሽ በድንጋጤ ከእየሩስ ጋር መለያየታችሁን ስትነግረን ማታዉኑ ጉዞ የጀመርሽ መስሎን ነበር!>> የእየሩስ አባት ነበር! ስለ ምን እንደሚያወራ አልገባኝም! እየሩስን አየሗት አይናን ከእኔ ለማሸሽ ስትሞክርና እንባ በአይኖቿ ግጥም ሲል አስተዋልኩ!
<<መቼም እግዚአብሔር የፈቀደዉ ነዉ የሚሆነዉ! በርታ ማለት ይኖርብሻል ገዜ ስለሌለን ለቀብር እንድንደርስ በፍጥነት ጉዞ መጀመር ይኖርብናል!>> አለኝ
<<የ.ም.ን ቀ.ብ.ር?>>...

...........ይቀጥላል.........

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል እንዳይረሳ

ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ @Abusmovies አድርሱን


Join&share
@Zeget77
ማንበብ ባህላችን ይሁን
697 views , 05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:33:45 ​​ የባከነች_ነብስ
#እውነተኛ ታሪክ
#ክፍል9⃣
የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

... አቤል የሚሰራበትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫና መጠገኛ የሆነዉን ሱቅ አስጎበኘኝ ሱቁ የታላቅ ወንድሙ እንደሆነ ነገር ግን ከጅማ ድረስ እየመጣ ለመቆጣጠር ስለማይመቸዉ እሱ በሀላፊነት እንደሚያስተዳድርለት ነገረኝ።
ሱቁ አነስ ያለ ነገር ግን በርካታና ጥራት ያላቸዉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለዓይን በሚማርክ ሁኔታ ተደርድረዉበታል የሱቁን ጉብኝት እንደጨረስን እራት እንድንበላ ጠየቀኝ ብዙ ማምሸት እንደማልችልና ነገ ተጓዥ ስለሆንኩ በጊዜ ገብቼ እረፍት ማድረግ እንዳለብኝ አስረዳሁት
<< ለተወሰነች ደቂቃ ብቻ! ተረጋግቼ ላወራሽ የምፈልገዉ ነገር ስላለ ነዉ?>>
ሰዉን ቶሎ ከሚያምኑት ወገን ባልመደብም ብቻ አቤል ምን አይነት አስማት እንዳለዉ አልገባኝም ልቃወመዉ አልቻልኩም። ከሱቁ ወጥተን እዛዉ ቦሌ አካባቢ ከሚገኝ ተለቅ ያለ ሆቴል ገባን! ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሮ ስለነበር በተለያዩ አይነት ከለር ብልጭ ድርግም የሚሉት መብራቶች ለስለስ ብሎ ከሚንቆረቆረዉ የእንግሊዘኛ ሙዚቃ ጋር ተዳምረዉ ለሆቴሉ ልዩ ዉበት አጎናፅፈዉታል። እኔና አቤልን ለተመለከተን በፍቅር ረጅም ጊዜ ያሳለፉ ጥንዶች እንጂ በጣት የሚቆጠር የትዉዉቅ ቀናቶች ያለን አንመስልም። <<በእኔ ምርጫ>> ብሎ ከታዘዘዉ የበግ ጥብስ ላይ ደጋግሞ አጎረሰኝ ለሴት ልጅ ያለዉ አክብሮትና ጨዋታ አዋቂነት አቤልን ያለ ምንም ፍርሀት ግልፅ ሆኜ በነፃነት እንዳወራዉ እያደረጉኝ ነዉ! የመጠጥ ተጠቃሚ አለመሆኑን ነገር ግን ይህ ምሽት ያለ ወይን አይደምቅም ብሎ ወይን ታዘዘ! በሁለታችንም ብርጭቆ ልዩ ስሜትን በሚሰጥ እርጋታ ወይኑን ቀዳዉ
<<እንግዲህ እኔ ጋር የረሳሽዉ...>> ንግግሩን እንደጀመረ ስልኬ ጠራ እየሩስ ነበረች አቤልን ይቅርታ ጠይቄ ላናግራት ወደ መፀዳጃ ሄድኩ ከ30 ደቂቃ በሗላ እንደምጨርስ ነግሬያት ተመለስኩ
<<ለጥሩ ምሽታችንና እኔ ጋር ለረሳሽዉ ነገር ፅዋችንን እናንሳ!>> እሱ ጋር ምን ልረሳ እችላለሁ? ዉስጤ የበለጠ ለማወቅ ስለጓጓ ብርጭቆዉን አንስቼ ተጎነጨሁ አቤል ምን እንደሚያወራ ባይገባኝም የሆነ ነገር ያወራልኛል ምስሎች ብዥዥ...ብዥዥ... እያሉብኝና የእንቅልፍ ስሜት ሲጫጫነኝ ይታወቀኛል
...ጠዋት እራሴን ከማላዉቀዉ ክፍል አልጋ ዉስጥ አገኘሁት ፊት ለፊቴ ካለዉ ወንበር ላይ አቤል ሲጋራ እያጨሰ ነበር መንቃቴን ሲመለከት ከት ብሎ ሳቀብኝ
<<ወፏ ወደ ወጥመዷ ገብታለች!>> አለኝ የማየዉ የምሰማዉ ህልም እንጂ እዉነት አልመስልሽ አለኝ
<<የት ነኝ?>> አልኩት
<<ሲኦል>>...

.............ይቀጥላል.........

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል እንዳይረሳ

ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ @Abusmovies አድርሱን


Join&share
@Zeget77
ማንበብ ባህላችን ይሁን
552 views , 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:33:45 ​​ የባከነች_ነብስ
#ክፍል_8⃣
የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

... መሸትሸት ሲል ከእንቅልፌ ነቃሁ እየሩስ ከአጠገቤ ጋደም ብላለች። ስልኬ ላይ አምስት ሚስኮል አገኘሁ ሁለቱ የእናቴ ሲሆን የተቀረዉ አዲስ ቁጥር ነበር በቀጥታ ወደ እናቴ ደዉዬ ስለ አባቴ አዲስ ዜና ካለ ጠየኳት ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ በሀዘን ተዉጣ ነገረችኝ እኔም እሷን ትቼ አዲስ አበባ ብዙ መቀመጥ እንደማልችል እንደዉም በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ ከእየሩስ ጋር ወደ ጅማ እንደምመለስ አሳምኛት ስልኩን ዘጋሁት።
<<...ምሳ እንኳን አልበላሽም አሁን ተነሺና እራት እንብላ>>
<<ይቅርብኝ አራበኝም! ...ይልቅ ነገን እዚህ አሳልፌ ከነገ ወዲያ መመለስ ይኖርብኛል አብረን እንሄዳለን?>>
እየሩስ ሀሳቤን አልተቃወመችኝም። ስልኬ ላይ ወዳገኘሁት አዲስ ቁጥር ደወልኩ አቤል ነበር ድምፁን ስስማ ልቤ ድንግጥ አለ! ልክ እንደተማረከ ወታደር ለምን የልቤን እንደምናዘዝለት ባላዉቅም አዲስ አበባ ከደረስኩ በሗላ የገጠመኝን ሁሉ ምንም ሳላስቀር ነገርኩት!
<<ከቻልሽ ነገ ላግኝሽ እኔ ጋር የረሳሽዉ እቃ አለ>> አለኝ!
ግራ ገባኝ እስከማስታዉሰዉ ድረስ እሱ ጋር የረሳሁት ምንም ነገር የለም ቢሆንም ነገ ከእየሩስ ጋር ትኬት ለመቁረጥ ወደ መስቀል አደባባይ እንደምንመጣና በዛዉ ላገኘዉ እንደምችል ነገርኩት የሚሰራበት ቦታ ቦሌ አካባቢ እንደሆነ ነግርኝ እሱ ያለበት ቦታ ለመገናኘት ተቀጣጥረን ስልኩ ተዘጋ። እየሩስ እራት እንድበላ ብታስጨንቀኝም ፍቃደኛ ልሆንላት ስላልቻልኩ እሷ ጋር ያለዉን ለእኔ እኔ ጋር ያለዉን ደግሞ ለእሷ እያጫወትኳት እንቅልፍ ወሰደን... እንደሌላዉ የሀምሌ ቀን ዝናብ ያስጨነቀዉ ሳይሆን ቀለል ያለ ብሩህ ጠዋት ነበር ከእየሩስ ጋር አርፍደን ተነሳን ጥሩ ቁርስ...የሚገርም ምሳ...ቤተሰባዊ መስተንግዶ ስለተደረገልኝ በትንሹም ቢሆን ሀዘኔን ቀለል አደረገዉ።
ወደ ጅማ የምንሄድበትን የጉዞ ትኬት አክስቴ ከምትደክሙ ብላ ሰዉ አስልካ አስቆረጠችልን። ሲኒማ ፊልም ልናይ ነዉ በሚል ሰበብ ከእየሩስ ጋር 11:30 ላይ ተያይዘን ወጣን! ለአቤል ደዉዬ እየመጣሁ እንደሆነ ስነግረዉ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ አሳወቀኝ ስደርስ እንደምደዉል ነገርኩት...
እየሩስ<<ምናልባት ብቻሽን ሊያገኝሽ አስቦ ይሆናል እኔ እዛዉ አካባቢ ከአንዷ ጓደኛዬ ጋር ልቆይና ስትጨርሺ አብረን እንመለሳለን አይሻልም?>> አለችኝ!
ልቤን ፍርሀት... ፍርሀት እያለዉ እሺ አልኳት...

.............ይቀጥላል.........

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል እንዳይረሳ

ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ @Abusmovies አድርሱን


Join&share
@Zeget77
@Zeget77
ማንበብ ባህላችን ይሁን
473 views , 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:33:45 ​​​ የባከነች_ነብስ
#ክፍል_❼
እውነተኛ ታሪክ

የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

...እዉነትም ሀዘን ከእኔ ፍቅር ይዞታል! አልያም ደግሞ በእኔ ይቀናብኛል ማለት ነዉ! ትንሽ ፈገግ ስል ደስታዬን የሚያጠፋ ሳቄን የሚገድል ችግር መፍጠሩን ተያይዞታል። አባቴ <<ሰላም ሁኑ>> የሚል መልዕክት በቁራጭ ወረቀት ላይ አስፍሮ የት እንደሄደ አለመታወቁን እናቴ ነገረችኝ! ያለችበት ሁኔታ ከባድ ሊሆን ስለሚችል ዛሬን አድሬ ነገ እንደምመጣ ብነግራትም አሷ ግን መምጣቴን አጥብቃ ስለተቃወመች የተወሰኑ ቀናትን አዲስ አበባ ለመቆየት ወሰንኩ።
አድካሚ ህይወት...አድካሚ መንገድ...አድካሚ ቀን!... የእየሩስ ክፍል ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ!
<<ምናልባት በስራ ምክንያት የሄደበት ጉዳይ ሊያቆየዉ ስለሚችል ሊያስጨንቃችሁ ስላልፈለገ ይሆናል መልዕክት የተወላችሁ!>>አየሩስ ነበረች!
መልስ ልሰጣት አልቻልኩም! ምን አይነት ምላሽ ልሰጣትስ እችላለሁ? በወቅቱ አልነበርኩ ሰዉ ስላልነበረበት ሁኔታ እንዴት በእርግጠኝነት መናገር ይቻለዋል?
<<ደ.ክ.ሞ.ኛ.ል! በህይወቴ የሚፈጠሩ ተደጋጋሚ ችግሮች አድክመዉኛል!>> አልኳት! እንባዬ ያለ ከልካይ ይወርድ ስለነበር ሁኔታዬ እየሩስን አሳዘናት የተወሰነ እረፍት እንዳደርግ ከአልጋ ዉስጥ አስገብታኝ
<<አንድ ሁለት ቀናትን እዚህ እናሳልፍና ወደ ጅማ አብረን እንሄዳለን! አሁን ግን ተረጋግተሽ እረፍት ማድረግ ይኖርብሻል!>> ብላ ተሰናብታኝ ወጣች!
እኔ ቀጥ ብዬ መቆም ስፈልግ ህይወት ታንገዳግደኛለች! ይነጋል ሰዉም አብሮ ከንጋቱ ጋር ይነቃል፤ይመሻል ሰዉም አብሮ ከምሽቱ ጋር ይተኛል!... ህይወት በድግግሞሿ ዉስጥ የሰዉን ልጅ አቅፋ ትሽከረከራለች... የሰዉ ልጅም በህይወት አዙሪት ዉስጥ ይዞራል! ድካም...ለቅሶ...ሀዘን...ተደራርበዉ ለእንቅፍ አሳልፈዉ ሰጡኝ... ሽልብ አደረገኝ...

..............ይቀጥላል.........

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል እንዳይረሳ

ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Zeget77 አድርሱን


Join&share
@Zeget77
@Zeget77
ማንበብ ባህላችን ይሁን
474 views , 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 08:18:21 የመብራት ሀይል አጥር ስር እየሸናህ ሰራተኞቹ ሲገቡ


ደሞ ዘነበ ብላችሁ እንዳታጠፉት!

@Zeget77
218 views 𝒜ℬ𝒟 , 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:05:32 #እሷ፡ እኔ እና ባሌ እኮ በሳምንት 3 ጊዜ ነው ሚናረገው
#ጓደኛዋ፡ እኔ ደሞ 1 ጊዜ ቢቻ ነው ሚናረገው
#እሷ፡ እንዴ ከማን ጋ ባል እኮ የለሺም ?
#ጓደኛዋ፡ እንዴ ስለ ባልሽ እያወራን መስሎኝ
351 views 𝒜ℬ𝒟 , 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:05:11 ለቅሶ ቤት ሄጄ ለሶስተኛ ጊዜ ምግብ ሲያስጨምር አይታው....

#ማነህ_ወንድም#ማነህ_ወንድም ሟች ራሱ እንዳንተ ቢበላ አይሞትም ነበር
347 views 𝒜ℬ𝒟 , 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:44:03 አንድ ጥናት እንዲህ ይላል ወንድ ልጅ እንዳፈቀረሽ ምታውቂበት አንዱ መንገድ አንቺን ሲያይ ያልበዋል ይላል።

#ወንድሜ
የሚያልበውማ ሻይ ልጋብዝሽ ብለህ ወስደሀት ግማሽ ጥሬ አንድ ኪሎ ጥብስ ስታዝብህ ነው
365 views 𝒜ℬ𝒟 , 07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:43:54 ይሄ ደግሞ ለየት ያለ ሊስትሮ ነው... የጫማዬን ክር ፈቶ ካጠበው በኋላ እንዲደርቅ ትከሻዬ ላይ ጣል አደረገው
344 views 𝒜ℬ𝒟 , 07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ