Get Mystery Box with random crypto!

😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂

የቴሌግራም ቻናል አርማ zeget77 — 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂 ዝ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zeget77 — 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂
የሰርጥ አድራሻ: @zeget77
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.16K
የሰርጥ መግለጫ

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, 0902410718
° ° [ ዝገት ከ ከሌላጋ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Abusmovies

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-05 21:48:36 #ፊልም ከፍቼ ስልክ ላይ እሚያስፈጥጠኝ መንፈስ ወጋውት


Join @Zeget77
Share  & Invite ur Friends
396 views 𝒜ℬ𝒟 , 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:48:16 ለወደፊት #Computer_science እና #ኑሮ ሲያወሩ

#ኑሮ ለወደፊቱ ግን ለልጆችህ ምን ልታደርግላቸው ነው?

#Computer_science በስማቸው folder እከፍትላቸዋለው


Join @Zeget77
Share  & Invite ur Friends
375 views 𝒜ℬ𝒟 , 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:46:18 ከተጋቡ ገና 3ት ቀናቸው ነው ግን እየተቧቀሱ ነው

ኧረ ላጤነት ይለምልም!


@zeget77
417 views 𝒜ℬ𝒟 , 07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:45:49 ታክሲ ላይ ወያላ ሆነህ እየሰራክ ፓይለት ነኝ
ብለህ የተዋወካት ቺክ ስታይክ


እንግሊዝ እንግሊዝ ጀርመን ጀርመን !

@Zeget77
388 views 𝒜ℬ𝒟 , 07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:28:07 ብቀላ

ምዕራፍ 16

ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.

ጊዜው ሳይታወቅ ከነፈ ። አንድ ወር ከዚያም ስድስት ሳምንት አለፈ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ግን የሀብቴ ስፋት ፤ የአኗኗሬ ምላት ፤ የትልቅነት ዝናዬ በመላው ኔፕልስ ታወቀ ።
ሀብታም ሆኜ መገኘቴ ብቻ በየትኛውም ከበርቴ ቤተሰብ ሁሉ ተቀባይነትን ሰጠኝ ። ከዚያ ሁሉ አድናቂዬ መሀል ብልሁን ሞሮን ሰይጣን ልሁን መልአክ ማንነቴን
ለማጣራት የከጀለ አንድም ጠርጣሪ አልነበረም ። አስፈላጊው ብዙ ሀብት መያዝ በምርጥ ሰረገላ መጓዝ ነው ። ምርጥ በልቼ ምርጥ ለብሼ በቲያትር ቤትና ስብሰባ የክብሩን ቦታ ይዤ መቀመጤ በኔፕልስ ከተማ መታወቅ ያለበት ባለፀጋ አደረገኝ ። ጨረቃ በሰረቀ ቁጥር ለደስታዬ እየተጨነቁ ጣዕመ ዜማ የሚያሰሙ ሙዚቀኞችን ማዘዜ በአጭር ጊዜ በኔፕልስ መታወቅ ያለበትን ሁሉ በቅርብ እንዳውቅና እኔንም ማወቅ በሰዎች ዘንድ እንደብርቅ ነገር ተገመተ ። ስሜ የትም ተወራ ፡ ዕለታዊ ሥራዎቼ አለ በሚባለው ትልቅ ጋዜጣ በየጊዜው ይወጡ ጀመር ። የለጋስነት ዝናዬ እንዲህ
በየአደባባዩ ፤ በየመጠጥ ቤቱና መገናኛው ሲዛመት ከኔ ጋር ለመተዋወቅ ብቻ ነጋዴዎች ለግል ሠራተኛዬ ለቪቼንዞ ጉርሻ ሳይቀር ይሰጡት ጀመር ። እርሱም የተቀበለውን ጉርሻ ልክና የሰጠውን ሰው ጥልቀትና ቅሌት ዘርዝሮ ሳይደብቅ ይነግረኛል ።

ሀብታምነቴ ካመጣልኝ ልዩ መስተንግዶ አንዱ አንዳንድ ወጣቶች እየመጡ የጡት አባታቸው እንድሆን መጠየቃቸው ነው ። ገና ለጋ ቆንጆ ሴቶች በሰበብ አስባብ እየተዋወቁኝ ማዳም ኦሊቫ ሊሆኑ የሚችሉበትን መንገድ በረቀቀ
ጥበብ ይሞክሩ ጀመር ። የፈላጊዎቹን ሴቶች ጥረት መመርመሩ ብቻ ለኔ የጊዜ ማሳለፊያ ጊዜያዊ ሥራ ሰጠኝ ። ሽበቴን ሳይቀር ውብ ነው እያሉ የሚያወድሱኝ የልጃገረድ ዕድሜ ሴቶች ቋቅ እስኪሉኝ አጋጥመውኛል ። እንደ ኮከብ የሚያበራ የልጅነት ዐይናቸው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይጠቅሰኛል ። ክንዳቸው ያልተሸፈነ ቆነጃጅት ሴቶችን ዳበስ ሳደርግ «አታድርግ» ከማለት የሚቆጠቡ አላጋጠሙኝም ። ሀብት የሚሰጠው እንዲህ እንዲህ ያለውን ድብቅ
እድል ሁሉ መሆኑ ገባኝ ።

ለክብሬ ስል ብዙ ግብዣዎችን ደግሼ ስጠራ ቆነጃጅት ሴቶች ለሀብቴ ሲሉ በግብዣዬ ላይ ለመገኘት ጥረት
አድርገው ይመጣሉ ። በአብዛኛው ግብዣ ላይ ኒና እና ጉዶ አይጠፉም ። ባለቤቴ በመጀመሪያዎቹ ግብዣዎቼ ላለመገኘት ሞክራ ነበር ። ነገር ግን ይህን ልጅነት ይዘሽ በሀዘን መጨበጡ ዋጋ የለዉም ስለምላት «እርስዎን በማክበር ብቻ ፤ የሮማኒ ቤተሰብ የቅርብ ወዳጅ በመሆንዎ ፤ ባለቤቴን በልጅነቱ ያውቁት ስለነበር ብቻ ነው የምመጣው»
እያለች ትመጣለች ።

ጉዶን በብዙ ዓይነት ስጦታ ልቡን ሰለብኩት ።
ከኔ ወዲያ የሚመካበት ሰው የሌለ እስኪመስለው ድረስ በየጊዜው ዉለታዬን አከበድኩበት ። ሕይወቱን እንደምፈልግ እንዳይጠራጠር ዐይኑን በስጦታ ሸፈንኩት ፣ ሚስጥሩን ሁሉ አውጥቶ ይዘረግፍልኝ ጀመር ። በማን እጅ
ውስጥ እንዳለ አዘናጋሁት ። ሊኖረው የማይገባውን የረጅም ጊዜ እቅዱንና ውጥኑን ሲያወራልኝ እገረማለሁ ። ለጥፋት ቅጣት መኖሩን ፤ በሰፈሩት
ቁና መሰፈርን መዘንጋቱ ያስገርመኛል ። አልፎ አልፎ ፍጹም ራሴን ዘንግቼ ሀጥያተኛነቱን ፡ ለቅጣት የቀረበ መሆኑን ፡ ቀኑ የተቆረጠች ጉድጓዱ የተማሰች መሆንዋን ንገረው ንገረው የሚል ግፊት ከውስጤ ለመውጣት እንደ እሳተ ገሞራ ልፈትለክ ይልና እኔው እንደ ብልሀቴ ራሴን በራሴ አቀዘቅዘዋለሁ ። አንድ ቀን ግን ስሜቴ እንዳያጋልጠኝ እፈራ ነበር ። ብዙ ጊዜ ጉሮሮው ላይ ነክሼ ማንነቴን ለመንገር ቃጥቶኝ የመጨረሻዋን
ሰዓት በመጠበቅ ብቻ ትእግስትን በግድ እገዛና ራሴን አቀዘቅዛለሁ ። ጉዶ ጥሩ ወይን ጠጅ መውደዱንም ስለማውቅ
ክፍሌ በመጣ ቁጥር መስከሪያውን አስመርጠዋለሁ ። በእድሜ ጓደኞቹ ፊት ሚስጢሩን በአደባባይ እንዲናገር አደርጋለሁ ። ሰክሮ ሲመሰስ ኒና እንዴት አድርጋ እንደምታስተናግደው ሁሉ እውነቱን ከውሸት ሳይለይና ሳይደብቅ
በመጠጥ አፍ እንዲለፈልፍ አደርገዋለሁ ። ኒና ከነገር ሁሉ ሰካራም ሰው እንደሚያንገሸግሻት ስለማውቅ አስከሬ እልክላታለሁ ።

የሮማኒን ግቢ እንደልቤ በፈለግሁበት ሰዓት ገብቼ መውጣት ቻልኩ ። የፈለግሁትን ያህል ተጫውቼ መመለስ ለመድኩ ። እገዛ ንባብ ቤቴ የገዛ መጽሐፎቼን አንብቤ ፤ ውሻዬን ፈትቼ በራሴው የአትክልት ቦታ እንደልቤ እንሸራሸራለሁ ። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አንዲት ቀን እንኳን ሮማኒ ቤት አድሬ አላውቅም ። በእድሜ አንጋፋ ሰው ሊጠነቀቅበት የሚገባውን ሁሉ ሳላጓድል ተጠነቀቅሁ ። ጉዶን ከሚያስቀና ነገር ሁሉ ተወገድኩ ። በየማለዳው ሆቴል
ክፍሌ ድረስ ኒና በሴት ሠራተኛዋ የምትልክልኝን ፍራፍሬና የእንደምን አደርክ ሰላምታ ለጉዶ ፌራሪ አልነግረውም ነበር ።

ባለቤቴ ሌሎች ቆንጆ ሴቶች እንደሚከታተሉኝና እንደሚፈልጉኝ ማወቅ ስትጀምር ራስዋ በድብቅ ሆቴሌ ድረስ
መምጣት ጀመረች ። ጉዶ እኔን በቀላሉ የሚደለልና የማይጠራጠር ምስኪን ነበር ባለው ዓይነት እኔም እርሱን ዓይኑ
ሥር አታለልኩት ። እኔ እርሱን እንዳመንኩት እርሱም እኔን እንዲያምነኝ አደረግሁት ። አወዳደቁ ግን የተውተበተበና ጥልቅ አዘቅት ውስጥ እንዲሆን ከወደቀ የሚንኮታኮትበት እንጂ የሚተርፍበት እንዳይሆን ሸረብኩለት ።

ሮማኒ ግቢ በተመላለስኩ ቁጥር የልጄን የስቴላን ናፍቆት እስክረካ በድብቅ የአባትነት ፍቅሬን ሰጠኋት ።
ሕጻንዋ በኔ መምጣት የተፈጥሮ ደስታዋ ሁሉ ተመለሰ ።
በተፈጥሮ ማንነቴን ተረድታ ከሀዘንዋ ፍጹም ዳነች ። አንዳንዴም ሞግዚትዋ ሕጻንዋን ሆቴሌ ድረስ እያመጣች
አንድ ሁለት ሰዓት ከኔ ጋር እንድትጫወት ታደርጋት ጀመር ። ጉልበቴ ላይ አስቀምጬ የሕጻናት ታሪኮችን ሳወጋላት ልጄ በበለጠ ትደሰታለች ። የነሐሴ ወር መግቢያ ድረስ ደህና ታዳጊና ደስተኛ ሆነች ። ከዚያ በኋላ አንዳንድ ሁኔታዋ የሕመም ምልክት አመጣ ። እየከሳች መሄድ ጀመረች ። ሰውነትዋ መገርጣት ያለወቅቱ ድካም ታየባት ። ሞግዚትዋ የሕጻንዋ ሁኔታ መለወጡን ለእመቤትዋ ብትነግርም እመቤቲቱ ደንታም እንዳልሰጣት ሰምቼ እኔ ራሴ አንድ ቀን ለኒና አነሳሁባት ።

በደግ አስተሳሰቤ አመስግና ልጅቱ ምንም የጠና እንከን እንደሌለባት ልትነግረኝ ስለሞከረች ጫን ብሎ መከራከሩ ማንነቴን የሚያስጠረጥር ስለሆነብኝ ለጊዜው ጨክኜ ዝም አልኩ ።

የነሐሴ ወር እንደተጋመሰ ሰው ከሽርሽሩ የመመለሽያው ጊዜ ስለሆነ አንድ የዳንስ ግብዣ ለወዳጆቼ ለመስጠት ስዘጋጅ አንድ ቀን ማለዳ ጉዶ ክፍሌን ለሚጠብቀው ቪንቼንዞ መምጣቱን ሳይናገር አንኳኩቶ ማረፊያ ክፍሌ ጥልቅ
አለና ቀጥታ ሶፋው ላይ ውድቅ አለ ። በሁኔታው የደነገጥኩ መስዬ ፦

«ምንድነው ችግሩ» ብዬ የተጨነቀ ፊቱን ለማንበብ እየሞከርኩ «የገንዘብ ችግር ከሆነ እንደራስህ ባንክ ልትተማመንብኝ ትችላለህ» አልኩት ። ውለታየ መብዛቱ እየከበደው አስር አስሬ እጅ እየነሳ «የለም የገንዘብ ችግር አይደለም ጌታዬ» ብሎ በዝምታ ዋጠው ። እንደገና ነገሩን ለማወቅ ፤

«እንዴት ነው ወይዘሮዋ አላገባህም ብላ አስደነገጠችህ እንዴ?>> አልኩት።

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየት Any Comment @Abusmovies


╔═══❖• •❖═══╗
@Zeget77
╚═══❖• •❖═══╝
392 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:47 ካም ነው ። የሚሰጠኝ እልማዝ ደግሞ ሌላ ኃይሉ ነው፡፡
ይልቅ ጨመርመር ቢያደርግልኝ እንዴት በወደድኩት::>>

«ጨመርመር ቢያደርግልሽ የምታፈቅሪው ይመስልሻል ኒና?» እንደ ቀና በድምጹ ያስታውቃል ።« እኔ መቼም የምታደርጊው አይመስለኝም ። በዚህ ላይ በጣም በራሱ ይመካል ። ለምሳሌ ሴት አስቀድማ ካልጠየቀችኝ እኔ አልጠይቃትም የሚለው አነጋገር አለው ።»

ከት ብላ የዘማዊት አሳሳቅ ከሳቀች በኋላ «ጥንታዊ አነጋገር ነው ። ድንቅ ሰው ነው ። ተነስ እንግባ ይልቅ ብርዱ መጣ ።» እቅፍ አድርጐ አነሳት።

«ያንን ሽማግሌ አያትሽን በፍቅር ዓይን ስላየሽ አንድ መቶ ከንፈር ትቀጫለሽ ትንሽ ብልግና አለብሽ ከአያትሽ ጋር ትቀብጫለሽ ።»

«ስማ ይልቅ ጉዶ ሰውየው አንዳንድ ነገሩ ፋቢዮን እይመስልህም ። እኔ ብዙ ሁኔታው ፋቢዮን ቁርጥ ሆኖብኛል፡፡>>

«እኔም እንዲህ ያለ ስሜት ከአንድ ሁለቴ መጥቶብኝ ነበር ። ግን ምን ሊሆን ይችላል ። አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን የሚመስል ጥላ ዓይነት ምስያ ኣላቸው ይባላል በኔ አስተሳሰብ ሰውየው የቅርብ ዝምድና ከሮማኒ ቤተሰብ ጋር ያለው ይመስለኛል ። የፋቢዮ አጎት ሊሆን ይችላል ።ደግሞ በጣም ሀብታም ነው ። ለኛ መቸም ጥሩ ጥገት ሊሆነን ይችላል ።» ተያይዘው ወደ ቤት ሲገቡ መስኮቱን ዘጉት። ማንነቱን ባለመረዳታቸው ደስ አለኝ። የመጥመዱ ቁልፍ አሁንም በእጄ መሆን አስደሰተኝ። እስከአሁን ከእቅዴ አንድም የተበላሸብኝ ነገር ያለመኖሩ ልበሙሉ አደረገኝ....
ይቀጥላል.....

ሀሳብ አስተያየት Any Comment @Abusmovies


╔═══❖• •❖═══╗
@Zeget77
╚═══❖• •❖═══╝
276 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:46 ብቀላ

ክፍል 15

ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.
ዋንጫውን ብድግ አድርጐ የሞላውን ጠጅ በአንድ ትንፋሽ ጠጣው «እንግዲያውስ የልቤን አውጥቼ ልንርዎት ። ወይዘሮዋን አፍቅሬአታለሁ። ፍቅር ስል የስሜትን ግለት ሁሉ አውጥቶ ሊገልጽልኝ ቃሉ ላይ ድክመት አለው ። ጣቶችዋ ሲያርፉብኝ አጥንቴ ድረስ ይሞቀኛል ድምጽዋ ነፍሴን ጭምር ያረካዋል ዐይኖችዋ በውስጤ ይቀልጣሉ ያለብኝን ሕመም ሁሉ እኔም ልገልጽልዎት አልችልም ። እርስዎም በትክክል ሊረዱልኝ አይችሉም ።»

«ራስህን ረጋ አድርግ» አልኩት ። በለስ እጄ ውስጥ የከተተውን ጠላቴን ራሱን በራሱ ሲያራቁት በደንብ ተመለከትኩት ። «ደምህ በስሜትህ ንዳድ ሞቅ ሲልብህ ራስህን ቀዝቀዝ ለማድረግ መሞከር አለብህ ። ለመሆኑ ወይዘሮዋ የምታፈቅርህ ይመስልሀል?>>

«መምሰል? ለምን መምሰል ብቻ » አመነታ ።
«የለም የለም ይህን ጥያቄ እኔ መንካት የለብኝም ። ብቻ ለባልዋ ግድ እንደሌላት አውቃለሁ ።»
«ይህንንም አውቃለሁ ዳተኛ ተመልካች እንኳን ይህን መመልከት አያቅተውም ።»

«ይኸ ሊያስደንቅ አይችልም ። ስሜቱን ገልጾ ሊወስድና ሊቀበል የሚገባውን ፍቅር መገመት አይችልም ነበር ጓደኛዬ እንዲህ ያለው ሰው ይህችን የመሰለች አልማዝና እንቁ ለማግባት ምን ችግር ውስጥ ከተተው መጀመሪያውኑ?>>

ንዴቴ በግዝፈት መጥቶ እቅዴን ሊያበላሽብኝ ታገለኝ ። ድምፄንም እንቅስቃሴዬንም ሰከን ካደረግሁ በኋላ«አሁን ሞቷል ። ነፍሱ በሰላም ትረፍ። ጥፋቱ ምንም ቢተልቅ ባለቤቱ እስከ ሕይወቱ ማለፊያ ታማኙ ነበረች አይደለም እንዴ?>>

«አፈር ብሎ አንገቱን ሰበር ኣድርጉ በፈራ ተባ ድምጽ» ትክክል ነው አለ።

«አንተም ታማኝና የልብ ወዳጁ ነበርክ። የዐይናማዋ ባለቤቱን ስበት ሁሉ አሸንፈህ የጓደኝነትን ወሰን ጠብቀህ ትኖር ነበር ።»
«አሁንም ትክክል ነው» ሲል ዘና ብሎ የተዘረጋው እጁ በጭንቀት እንደመንቀጥቀጥ አለ ።

«በኔ አስተያየት አሁን ከወይዘሮዋ ጋር ያለህ ፍቅር ይበል ይበል የሚያሰኝ እንጂ እንከን ያለበት አይመስለኝም ። እኔም ይቅናህ ከማለት ሌላ የምጨምረው የለኝም።

እተቀመጠበት የሚጨብጠውን አጥቶ ተቁነጠነጠ ።ዐይኑን ወደግድግዳ ሲወረውር የፋቢዮአባት አፈጠጠበት ወደእኔ ዞሮ እርስዎ ግን የወይዘሮዋ ፍቅር እንደማይማርኮት እርግጠኛ ነዎት» ብሎ እንደገና ጠየቀኝ ። «ይቅርታ አድርግልኝ ወይዘሮዋ መማረክ ትማርካኛለች ግን እንዳንተ ባለው ዓይነት አይደለም ። አንተን ደስ ካለህ ማረጋገጫ ልስጥህ ወይዘሮዋ እንተኛ ብላ ካላ ስገደደችኝ እኔ....»

«እህ እርስዎ » መልሴን ለማግኘት አሾተላ ።

«እኔ እንተኛ ብዬ አልጠይቃትም ።»

«ይህማ ሊሆን አይችልም ።»

«ያውልህ እንግዲህ ልትተማመንብኝ ትችላለህ ።በል ቡናችንን እንጠጣ» ብዬ እጁን ይዤ አስነሳሁት ።

በረንዳ ወጥተን እኔ ከጋባ አጠገብ በተዘጋጀልኝ ወንበር ተቀመጥኩና ቡናው መቀዳት ተጀመረ ። ሰማዩ የሙሉ ጨረቃ ብርሀን ተጐናጽፏል ። የሌሊት ወፎች እያ
ለፉ ይጮሀሉ አንድ የሆነ የሕመም ዓይነት ጩሀት እያረፈ ጆሮዬ ጥልቅ ይላል ።

ምሽቴ ሠራተኛ ጠርታ «ዊቪስን ፈተህ ልቀቀው»አለችው ።

ውሻዬ ከመቅጽበት ጩኸቱን አቁሞ እየፈነደቀ ሜዳውን አቋርጦ ወደ እኛ ሲገሰግስ አየሁት ። እመቤቲቱንና ፈራሪን አልፎ እኔን ይሳለም ጀመር ። ጭራው ተወራጨ
ምራቁ ጫማዬ ላይ ተዝረበረበ ። በጭንቅላቱ ጉልበቴን እያሸ በእፎይታ ተነፈሰ ኒናና ፌራሪ እንዳይጠራጠሩ መላ መፍጠር ነበረብኝ ።«ይኸውላችኋ አልነገርኳችሁም መሰለኝ ውሾች ሲባሉ በደረስኩበት ሁሉ እንዲህ ሆነው ተጨንቀው ነው የሚ ቀበሉኝ ። እኔ ራሴ ይገርመኛል ።»

ማጅራቱን ይዤ በትእዛዝ ዓይነት ወደ መሬት ጫን ሳደርገው ስልጡን ውሻዬ እግሬ ሥር ተኛ ። አልፎ አልፎ ብድግ እያለ ናፍቆቱን ይወጣል ። የደረሰብኝን የሰውነት
ለውጥ ምን እንደፈጠረው የሚመረምር ይመስል ፊቴን ትክ ብሎ ያያል፡፡

ኒና በሁኔታው የተረበሸች መስላ ታየችኝ።
«ውሻው ድንገት ችግር እንዳያመጣብኝ አሰብሽ እንዴ እመቤት» አልኳት ።

«የለም እንዲያው ገርሞኝ ነው ። ውሻዬ እንግዳ ይፈራ ነበር ። እንዲህ ያለ አቀባበል የሚያደርገው ለባለቤቴ ብቻ ነበር ...»

ፌራሪ ከሀሳብዋ ጋር ተስማምቶ በነገሩ ግራ የገባው መስሎ ጉችር ብሎ ተቀመጠ ።

«እኔም በጣም ገርሞኛል» ብሎ ፌራሪ ሲናገር ውሻው ቀና ብሉ እምም በማለት ሊያጉተምት ሲል በእግሬ ረገጥ አደረግሁትና ተመልሶ ተኛ ያሁኑ ሁኔታው ለኔም
ገረመኝ ከመሞቴ በፊት ውሻዬ በፌራሪ ላይ እንዲህ ያለ የጥላቻ ምልክት አያሳይም ነበር ሁኔታቸውን ማረጋጋት ስለነበረብኝ <<እኔ በሕይወቴ ውስጥ ብዙ ውሾች እይቻለሁ ብዙ ውሾች በእጄ አድገው ስላለፉ ውሾች ደግነትን በእጄ ላይ የሚያሸቱ ይመስለኛል ስለዚህ የዚህም ውሻ ሁኔታ ይኸው ይመስለኛል ጌታው የሞተበትን ውሻ እንኳ እኔ ሄጀ ሳጽናና ውሻው የሀዘን ድምጹ ይቀንሳል።
ዛሬም ከመሄዴ በፊት ብትፈቅዱልኝ እኔው ባስረውና ብዳብሰው ከሀዘነተኛ ድምጹ እፎይታን ታገኛላችሁ>>አልኩ፡፡

ለመሄድ ስነሳ ውሻውን አስሬ ተመለስኩ ሆቴሉ ድረስ አብሮኝ ለመሄድ የተነሳውን ፌራሪን ብቻዬን እንድሄድ ጠይቄ መለስኩት ። ራሴን ዝቅ አድርጌ እጅዋን ስሜ
ተለያየን ። ፌራሪ በሩ ድረስ ሸኘኝና ዋናውን መንገድ እሰኪይዝ ቆሞ አየኝ እንደሽማግሌ እግሬን እየጐተትኩ ቀስ ብዬ አዘገምኩ ። በሩ መዘጋቱን ስሰማ ዋናውን መንገድ ትቼ ወደጐን ሸውጄ በምሥራቅ በኩል ተክሉን እየከፋፈልኩ ግቢው ትይዩ ጐብታ ላይ ተደበቅሁ ። በረንዳው ፊት ለፊት ከመታየቱም በላይ የጊቢው ኮሽታ ሳይቀር ይሰማኛል፡፡

ኒና እና ፌራሪ ጐንለጐን ተቀምጠዋል ። እርስዋደረቱ ላይተደግፋ እርሱ እጁን በወገብዋ አዙሮ ተደላድለው ተቀምጠዋል ። በዚህ ዓይነት እቅፍ ለእቅፍ ለጥቂት ጊዜ ዝም ብለው ከተቀመጡ በኋላ

«አንቺ ኒና በጣም ጨካኝ ነሽ ያንን ሽማግሌ የፈለግሽው መስሎኝ ነበር ።»
«ልክ ነውና አሁንም እፈልገዋለሁ ። ሽማግሌውያንን አስቀያሚ መነጽር ባያደርግ እንከን የሌለው መልከመል
224 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:46 "እና እርስዋ እኔ ይህችን ሴት..... ይህችን ሴት ......"

«አዎን ታፈቅራታለህ እንጂ ለምን አታፈቅራትም ።የሟች ባለቤትዋ ምርጥ ጓደኛ ነህ » አማልክት እንኳን የሚፈቅዱት ነው የሚመስለኝ ። መልካም የፍቅር እድል እንዲ
ገጥምህ ዋንጫዬን እንዳነሳልህ ፍቀድልኝ ።» ዋንጫዬን ግልብጥ አድርጌ አጋባሁ ። አሁን ደግሞ ጭድ አይቶ ገደል የገባ በሬ ሆነብኝ እኔን የሚጠራጠርበት ልቡ ጭልጥ ብሎ ገደል ገባ ፊቱ ከቅናት ሁሉ ነጽቶ ቁልጭ አለ እጄን አንስቶ ጫን አለው ።

«ይቅርታ ያድርጉልኝ ጌታዩ ተሳስቼ ነበር ። ልጅቱን ራስዎ የፈለግዋት መስሎኝ ተሳስቼ ነበር በእውነት ዝቅ ብዬ ይቅርታ ልለምኖት ይገባል" ግን እኔ የእሷን ውሽማ ሳይሆን ሕይወቱን መፈለጌን ሊጠራጥር አልቻለም፡፡

«ልትፀፀት አይገባም ። ፍቅረኛች ሁሉ ሲገጥማቸውና ሊያንፀባርቁት የሚገባውን ነው ያሳየኸው ብቻ ያለ ምክንያት ነው ራስህን የጎዳኸው ። በኔ እድሜ ደግሞ ስትደርስ ከሴት ፍቅርና ከንፈር ይልቅ የብርና የወርቅን ቅጭልጭልታ ትመርጣለህ ። እመነኝ ወዳጄ እኔን የፍቅር ሱስ አይማርከኝም ።»

ዋንጫውን ብድግ አድርጐ የሞላውን ጠጅ በአንድ ትንፋሽ ጠጣው «እንግዲያውስ የልቤን አውጥቼ ልንርዎት ። ወይዘሮዋን አፍቅሬአታለሁ ....

ይቀጥላል.....

ሀሳብ አስተያየት Any Comment @Abusmovies


╔═══❖• •❖═══╗
@Zeget77
╚═══❖• •❖═══╝
202 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:46 ብቀላ

ክፍል 14

ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.
«ሁሉም ትዝ ይለኛል» አልኩ ። ፌራሪ ደንግጦ «ትዝ ይለኛል ነው ያሉት?» አለኝ።
«አዎን ከፋቢዮ አባት ጋር ብዙ ጊዜ እዚህ እንጫወት ነበር ። የፋቢዮ እናት በልጅነትዋ ነው የሞተችው» ብዬ
ቤተሰቡን በዝርዝር ማወቄን ገለጽኩ ።

«ቤተሰቡን እንዲህ የሚያውቁ ከሆነ ልጄን ስቴላን ቢያዩዋት ፡ ወይስ ልጅ ሰልችቶዎታል?» አለችኝ ።

«እኔ ለልጅ ያለኝ ፍቅር ከፍተኛ ነው» ብዬ ስሜቴን በቀላሉ አቀዝቅዤ የልጄን መምጣት እጠባበቅ ጀመር ።
በሩ በቀስታ ተከፈተ ። ልጄ ብቅ ስትል ልቤ ሀዘኑን አልችለዉ አለ ።

«አይዞሽ ነይ አትፍሪ» ብላ እናቲቱ አበረታታቻት ።
ልጄን በተለየኋት ጥቂት ቀናት ሁኔታዋ በብዙ ተለዋውጧል ፤ ተጫዋችነትዋ ተቀንሷል ፤ ተጠራጣሪና ዐይናፋር
ሆናለች። በዕድሜዋ ሊኖር የማይገባው ጠርጣሪነት ፊትዋ ላይ ይነበባል ። ጠቅላላ ሁኔታዋ ለኅሊናዬ ብዙ ነገር
አዋየኝ ። ልጄ መዘንጋትዋን ነፍሴ ነገረችኝ ። ወደእኔ መምጣት ከጀመረች በኋላ መሀል መንገድ ቆማ ፌራሪን
አየት አደረገች ።

«ነይ እንጂ ስቴላ ። እኔ እኮ ባለጌ ካልሆንሽ አልቆጣሽም ። ጭራቅ መስዬኮ ነው የምታያት ። ነይና እኝህን
የአባትሽን ወዳጅ ሰላም በያቸው።»

ልጄ የአባትዋ ስም ሲጠራ ዐይንዋ ፋኖስ መስሉ እርምጃዋ መተማመኛ አገኘ ። ሮጣ ትንሽ እጅዋን በአንገቴ አዙራ ጥምጥም አለችብኝ ። እንደሚስም ሆኜ ፀጉርዋ ሥር ቆየት ብዬ ፍልቅ ብሎ የመጣውን የወላጅ እንባዬን መለስኩት ። ጥቁር መነጽሬን የምትፈራው መስሎኝ ነበር ። እርስዋ ንቅንቅም አላለች ። በረካ መንፈስ ጉልበቴ ላይ ተደላድላ ተቀመጠች ። የትኩረት አመለካከትዋ ግን የውስጥ ስሜቴን የመቆጣጠር ኃይሌን እንደማናጋት አደረገው። ብዙ ካየችኝ በኋላ አንድ ለንባብ የሚያስቸግር ፈገግታ ፊትዋ ላይ ተቀረፀ ። እንደገና ልትስመኝ ወደ አፍ ስትጠጋ ነገሩ እንዳያስታውቅ ብዬ እቅፍ አደረግኋት ። የቻልኩትን ያህል
ድምጼን ጐርነን አድርጌ «ስቴላ ፡ አንች በጣም ደስ የምትይ ሕጻን ነሽ ፡ ስቴላ ማለት ትንሽ ኮከብ ማለት ነው ።>>
ብዬ ሳጫውታት ትከሻዋን ክንዴ ላይ አስደግፋ ፤

«አባቴን አይተውታል ፡ በቶሎ ይመጣል?» አለችኝ ። ፈጥኜ መልስ ለመስጠት ስላልቻልኩ ፌራሪ መልሱን ወዲያው ወረወረ ።

«ቅዠትሽን አታምጪ እንግዲህ ፤ አባትሽ ርቆ መሄዱን ታውቂ የለ ። በጣም ባለጌ ስለሆንሽ ነው ጥሎሽ የሄደው ። እረፍት የማይሰጡ ጨቅጫቃ ልጆች ወደሌሉበት
አገር ነው የሄደው አባትሽ ።» አላት ።

በትዝብትና በፍርሀት ልጄ ፌራሪን በጥላቻ ስታስተውለው አየኋት ። እኔም ሰው ስታዘብ እንዲህ ያለ አስተያየት ስላለኝ ገረመኝ ። ምን እያሉ እንደሚያደድቡዋት
ግን ገባኝ ። ሆን ተብሎ ልጅቱ ግራ እንድትጋባና ራስዋን እንድትጠላ የተደረገ ደባ ነው ።

ፌራሪ የልጅቱን ሁኔታ አስተውሎ ከት ብሎ ከሳቀ በኋላ እንደታቀፍኳት ፀጉርዋን ከግራና ቀኝ ጠምዞ ጢም ለማስመሰል አፍንጫዋ ሥር እየጐተተ «ጠቅላላውን እኮ የፋቢዪ ሮማኒ ፎቶ ናት» አለ ። ፀጉርዋን በጨመደደ ቁጥር
ልጅቱ ደረቴ ውስጥ ሽሽትዋን ቀጠለች ። ሚስቴ ምንም አስተያየት አትሰጥም ። እኔ ብዙ ከተከላከልኩ በኋላ ድምጼን እንደመቀለድ አገርሜ «ከሕፃን ጋር ገራገሩን መጫወት ነዉ የሚበጀዉ።
ያለዚያ እንደ ጭራቅ መታየትን ያስከትላል>> አልኩት።

<<ይህቺን እንከን የለሽ ስታድግ እንዲህ

አንድ ወንድ ስላሾፈባት በወንዶች ሁሉ ላይ ለማሾፍ ምክንያት ታገኛለች። አይመስልሽም እመቤቴ?>> አልኩ ወደ ሚስቴ ዘወር ብዬ

<<አንድ ወንድ ስላሾፈባት ሌላዉ ወንድ ደግሞ ደግ ስለሆነላት ነገሩ ይማታባታል እንጂ አታሾፍም>> አለች።

ድንገት አሽከሩ የእልፍኙን በር ከፍቶ ራት መዘጋጃቱን ተናገረ። ልጅቱን ከጭኔ ላይ አወረድኳትና ወደ ክፍሏ ሄደች ። ሶስታችንም ወደ ገበታ ቤት አመራን። ስለ እንግድነቴ በክብር መቀመጫዉ ላይ ተጋብዤ ተገቢ ቦታዬን ያዝኩ። ከአባቴ ጀምሮ ቆሞ የሚያበላኝ ሰራተኛዬና ጓደኛዬ ከኋላዬ ቆሞ ዋንጫዬን በሞላልኝ ቁጥር በመነፀሬ ዉስጥ እየፈራ ማንነቴን አየት ያደርጋል ። ከተቀመጥኩበት ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ የአባቴን ገፅታ ትክ ብሎ እኔን ልጁን በሀዘን እያየ ሚስኪን የሚለኝ እየመሰለኝ ትክ ብዬ ፎቶዉን እያየሁት ከንፈሬ እየተንቀጠቀጠ ስሜቴ ከዳኝ።

<<ፎቶዉ በትክክል የፋቢዮን አባት ይመስላል? >> ብሎ ፌራሪ ጠየቀኝ።

ክዉ ብዬ ከደነገጥኩ በኋላ ስሜቴን ዋጥ አድርጌ <<እንዴታ ባልሳሳት ጌታ ሮማኒን ቁርጥ ይመስላል ፤ ልቤ የተጠራቀመውን ትዝታ ሁሉ ፈንቅሎ አወጣው እኮ ። አብረን
ያሳለፍነውን ደጉንና ክፉውን ጊዜ ሁሉ በአንድ አፍታ ከፊቴ አምጥቶ አነጠፈው እኮ ። ዋ! ምንኛ የሚያኮራ ትልቅ
ሰው እንደነበር ብነግራችሁ አታምኑኝም።»

«ፋቢዮም የሚያስኮራ ግን በስሜቱ ቀዝቃዛ የሆነ ሰው ነበር » አለች ሚስቴ ።

ውሸታምነትዋ እንደገና ሊያዋርዳት ነው። ደፋር ውሸታም ናት ። ስሜቴ ለእርስዋም ሆነ ለሌላ ቀዝቅዞ አያውቅም ። ስሜትዋን በደስታ ለመሙላት የምከታተል ባሪያዋ እንጂ ስሜት የሌለኝ የበረዶ ቅርጽ አልነበርኩም ። ድምጼን ከፍ አድርጌ «ስለ ጓደኛዬ ስሜት በትክክል አውቃለሁ ። ባጠቃላይ የሮማኒ ቤተሰብ ስሜት ቁጡ እንጂ ስሜተ ቀዝቃዛነት እንኳ የለባቸውም» አልኩ ።

እዚህ ላይ ከኋላዩ የቆመው መጋቢ በትህትና ለመናገር መፈለጉን ገልጾ ሊናገር ሲል ፌራሪ ዋንጫውን እያስሞላ «ይልቅ የቤቱን አሮጌ ሊቅ እናድምጥ ፡ እርሱ ሁለቱንም ጌታ ሮማኒዎች ያውቃል» በማለት ተንከትክቶ ሳቀ ።

ዘወር ብዬ የመጠጥ አሳላፊውን ፈት አተኩሬ ካየሁ በኋላ «ፊትህ ትዝ አይለኝም ምናልባት እኔ ከሄድሁ በኋላ
ይሆናል እዚህ መሥራት የጀመረከው አልኩት ።»

አወንታውን እጅ በመንሳት ገለጸልኝ ። «አዎን ጌታዬ እኔ እዚህ ሥራ የጀመርኩት እሜቴ የጌታ ፋቢዮ ሮማኒ እናት ከመሞታቸው አንድ ዓመት አስቀድሞ ነው ።» ስሜቱ ገላለጻለን» አለች ጉዶ ኣየት ሲያደርጋት በዐይንዋ እኔን ጠብቃ በግልምጫ አቀለጠችው ።

ደርበብ ብላ በልዕልታት ግርማ ብድግ አለችና «ወይን ጠጃችሁን እስክትደግሙ ብቻችሁን ልተዋችሁ አንዳንዴ ወንዶች ቀልዳችሁ የሴቶችን አብሮ መቀመጥ ስለማ
ይፈልግ ብቻችሁን ልተዋችሁ ጌታዬ እንደተመችዎት በረንዳ ቡና ተዘጋጅቶ
ይጠብቃል» ብላ ልትወጣ ስትል ፈጥኘ በእክብሮት በሩን ከፈትኩላት ። ለሁለታች
ንም ወይን ጠጁን ቀድቶ ብሽቀቱን መደበቅ የማይችለው የጥንት ጓደኛዬን አየት አደረግሁት ። የመጠጥ አሳላፊው ጂያኮሞ ቀደም ብሎ ወጥቶ ስለነበር ገበታው ቤት ብቻችንን ቀረን ። ብቻዬን ከጠላቴ ጋር መቀመጤ የግጥሚያው መጨረሻ እንዲሆን ሁኔታዎች ገፋፉኝ፡፡

ለአንድ ሁለት ደቂቃዎች ስለበቀል እቅዴ ማውጣት ማውረድ ጀመርኩ ። እንደገበጣ ጫወታ ግጥሚያው ልብን የሚስብ ሆነልኝ ። እንደመሰሪ ተጋጣሚ በቆራጥነት እርምጃዬን ቀጠል አድርጌ ወጋሁ ።

«ምንኛ የምትፈቀር ቆንጆ ሴት ናት! በዚህ ላይ ብልህ ናት የውበት ምርጫህ ያስደንቀኛል ሲኞር» አልኩት የወይን ጠጁን እየተጐነጨሁ ።እንደመደንገጥ
እንደመቆጣትና እንደመደነቅ እያለ ምን? ምን ማለትዎ ነው ጌታዬ» አለ
«አይ ወጣትነት» አልኩ እራሴን እየነቀነቅሁ «የወጣትነት ትኩስ ደም እንደምንም የፈለገውን ያገኛል፡፡ ሰማህ ወይ ወዳጄ ትኩስ ስሜትህ ሊያሳፍርህ አይገባም ። ላዝንልህ የሚገባኝ ሴትየዋም ያንተው ዓይነት የመውደድ ስሜት ባይኖራት ነበር ። እንዲህ ከሆነች ደግሞ ጂል ናት። አጋጣሚው እንዲህ ተስተካክሎ ቀርቦላት እምቢኝ የምትል ከመቶ አንድ ሴት ናት ።»
195 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:26:45 አነቀው ። የወንድ ልጅ እምባ በዋዛ አይመጣም ። ያን አፍታ ግን እዬዬ ብዬ አንብቼ ማልቀስ ከጀለኝ ። ዋ ውድ ቤቴ! ምነው እንደጌታው ተነኳክቶ መቃብር በገባ የሚልም ምኞት መጣብኝ ።
ይኸ የማነው ቤት ዛሬ? የሚል ጥያቄ ተመላለሰብኝና ፌራሪን አየት አደረግሁት ። እርሱ የቤቴ ጌታ አይሆናትም
አልኩ ። ተወልጄ ያደግሁበትን ቤቴን በስስት በሀዘን ስሜትና በፍቅር ዐይን ቃኘሁት ። አንዳንድ ነገሮች ተለዋውጠዋል ። ደስተኛ የነበረው መጠጥ አሳላፊዬ ከዚህ በፊት
ያልታየበት የአካል ጉስቁልናና የውስጥ ስሜት ጉዳት ይታይበታል ። ሰውነቱና ውስጣዊ ስሜቱ ተጎድቷል ። ተጎሳቁሎአል ። ከበረንዳ ተነስቶ የማያውቀው የግል የመዝናኛ ወንበሬ ከቦታው የለም ። ያሳደግሁት ውሻዬን ወዴት እንዳደረሱት አላውቅም ። ስሜቴን በመቆጣጠር ረገድ ግን ብርቱ ጥንቃቄ አደረግሁ ።

የፊቴን ማዘን ካጤነች በኋላ ቀልድ በተቀላቀለው ስሜት «ግቢዬ ድረስ መጥተው ስለጐበኙኝ ሀዘን ተሰማዎት መሰለኝ» አለችኝ ።

«ይቅርታ እመቤቴ ። በእውነት ይህ ከታየብኝ ከወንዶች ሁሉ በደለኛ ነኝና እክሳለሁ ። ግን እኔም ጥያቄ ላቅርብልሽና ዳንቴ ገነትን እንዲጐበኝ ሲፈቀድለት ሀዘን ነው ደስታ የተሰማው?»

ፊትዋ እንደማፈር አለና ጠወለገ ። ፌራሪ የተስፋ መቁረጥ ዓይነት የቅናት ስሜት አንፀባረቀ ። እቤት ገብተን የቤቱን ውስጥ ድርጅት ታሳየኝ ጀመር ። የመዝናኛ ክፍሉ መስኮት በሰፊው ተከፍቷል ። ፒያኖው በቅርብ እንደተዘፈነበት ያስታውቃል ። አበባ በየባዙ ፈክቶ ተንተርኳል ።
ሶፋው ላይ አረፍ ካልኩ በኋላ ፡

«ሁሉም ትዝ ይለኛል» አልኩ ። ፌራሪ ደንግጦ «ትዝ ይለኛል ነው ያሉት?» አለኝ።

ይቀጥላል...

ብቀላ እንዴት ነዉ..? እንደወደዳችሁት ተስፋ አለኝ። ይሄን ምርጥ ድርሰት የምታዘጋጅልንን elu jaznንም ላመሰግናት እወዳለሁ። አመሰግኑልኝ አበርቱልኝ!!

ሀሳብ አስተያየት Any Comment @Abusmovies

╔═══❖• •❖═══╗
@Zeget77
╚═══❖• •❖═══╝
188 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ