ስተኛ ነው።» ግብዣውን መቀበሌን ከአንገቴ ዝቅ ብዬ ገለጽኩ ። ጉዶ ፌራሪ የሚያሾፍ መሆኑ እየታወቀበት «ጌታዬ ሴቶችን እንደማይወዱ ማዳም ሮማኒ አታውቅም" አለ ። እንዳላሳፍረው «ትክክል ብሏል ሲኞር ፌራሪ ፤ ሴትን የሚቋቋም ጉልበት የለኝም ። መልአክ የምትመስል ሴት ፈገግ ስትል መድረሻ ይጠበኛል» አልኩት ። ነገውኑ ከቀትር በኋላ ቤትዋ ልመጣ ፤ ጉዶ መጥቶ ሊወስደኝ ፤ በቀጠሮ ላላሳፍራት እርስዋም ልጅዋን (ልጄን) ስቴላን ልታሳየኝ ቀጠሮ ተቆርጦ ተስማማን ። እንደ መላእክት ጉብኝትዋ አጭርና ጥፍጥ ያለ ሆነብኝ ። እጅዋን ለሰላምታ ዘረጋችልኝና ጎንበስ ብዬ በከንፈሬ ነካሁት ። መነጽሩን አተኩራ ካየች በኋላ ዐይንዎን ያምዎታልን?» አለችኝ ። «ብርሀን አይደፍርልኝም ። ከእድሜዬ ጋር የተያያዘ ነው ።» «እድሜዎ እንኳ ይህን ያህል የገፋ አለመሆኑ ግልጽ ነዉ ።" «ፀጉሬ እንዲህ ጥጥ መስሎ ከዚያ ወዲያ ምን ይጠበቃል ።» «ብዙ ወንዶች በወጣትነት በነጭ ፀጉር ይሸፈናሉ ። ሽበት እኮ የእርጅና ምልክት አይደለም ።» ይህን እየተባባልን ሰረገላዋ ደረስን ። ጉዶ ፌራሪ እጁን ዘርግቶ እያለ የኔን እጅ ይዛ ሰረገላዋ ወጣች ። ልብስዋን አስተካክላ ሰረገላው ትቶን ተሽከረከረ ። ዘወር ብዬ የጉዶን ፊት አየት ባደርግ ቅናት በልቡ መጠንሰሱ በጉልህ ይታያል ። «ምነው ስሜትህም ጨዋታህም ድንገት እንደጨለመ ብርሀን ደብዘዝ አለብኝ ። ሴትየዋ እንዳልከው ተወዳዳሪ የሌለው ውበት ነው ያላት» አልኩት ። ይቀጥላል... ሀሳብ አስተያየት Any Comment @Zeget77 ╔═══❖• •❖═══╗ @Abusmovies ╚═══❖• •❖═══╝ 195 views 𝒜ℬ𝒟 , 19:26