Get Mystery Box with random crypto!

ሊቀ መዘምራን

የቴሌግራም ቻናል አርማ z_tewodros — ሊቀ መዘምራን
የቴሌግራም ቻናል አርማ z_tewodros — ሊቀ መዘምራን
የሰርጥ አድራሻ: @z_tewodros
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58
የሰርጥ መግለጫ

✞ በየጊዜው አዳዲስ መንፈሳዊ
➢ ፅሁፎች
➢ መዝሙሮች
➢ ኦርቶዶክሳዊ መልእክቶች
➢ መንፈሳዊ ነገሮችን
ሁሉንም ለማግኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞
ለአስተያየቶ @Channel_admin09 ይጠቀሙ
Youtube:
https://youtube.com/@shamo_guy
➢ ሁሉም እንዲያነበው SHARE ያርጉ ! እናመሰግናለን !

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 23

2023-02-21 15:30:22 Channel photo updated
12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 08:20:42 ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት )

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡
‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው #ጾመ_ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን #ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ?
በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡

«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት፣ ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3፥13፡፡

ሳምንቱ ሙሴኒ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ. 4፥1-4/፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.1K views◦•●Yaredo●•◦, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 08:19:42
ማስታወቂያ

መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
በሌሊት ለሚሸና
ለነገረ በትን
ለደም ግፊት
ለስኳር ህመም መቀነሻ
ለሁሉም ቁርጥማት
ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
ለፊት ማድያት
ለሳል በሽታ
ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
ለማህጸን እንፌክሽን
ለአእምሮ ጭንቀት
ለወገብ ህመም
ለነርብ
ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
የሚጥል በሽታ
ገንዘብ ለሚበተንበት
ስራ አልሳካለት ላለ
ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
ለመፍትሔ ስራይ
ለአስም (ለሳይነስ)

ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ

እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል

ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
ይደውሉ
0917040506
0912718883

ቻናሉን ይቀላቀሉ
https://t.me/mergatah

ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
806 views◦•●Yaredo●•◦, 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 07:41:40 ማየት ስለሚናፍቁት የሀገራችን ቦታዎች

እዛው እንዳሉ አድርጎ የሚያቀርብልዎ

ethioculturetips.com

ethioculturetips.com

ethioculturetips.com

ከላይ ባለው አፕሊኬሽን በስልኮ ይመዝገቡ
ወይም ወደ 9676 OK ብለው ይላኩ
1.1K viewsE D U , 04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 21:41:07 #ሕርቃል_ማን_ነው? ለምንስ የመጀመሪያው ሳምንት ጾም በስሙ ተሰየመ?

የዐቢይ ጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት (ከዘወረደ እስከ ቅድስት ያለው) የምንጾመው ጾም ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ለመሆኑ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ የመጀመሪያው 7 ቀን ጾም በስሙ ተሰየመ?

ታሪኩ እንዲህ ነው፦ በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡

በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
3.3K views◦•●Yaredo●•◦, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 15:20:24 የአብነት ትምህርቶችን ለመማር ፈልገው በአቅራቢያዎ መማርያ አጥተው ተቸግረዋል ?

እንግዲያስ በtelegram ብቻ ያለ ምንም ክፍያ በነጻ መጽሐፍትን በpdf & voice ያግኙ
ውዳሴ ማርያም
የግእዝ ትምህርት
ወንጌለ ዮሐንስ
መዝሙረ ዳዊት
መጽሐፈ ሰዓታት እና ሌሎችን ለመማር ይቀላቀሉን
1.4K views◦•●Yaredo●•◦, 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 09:09:23 ከምግብና ከመጠጥ ያልተቆጠበ ሰው ለክርስቶስ ሕይወቱን መስጠት እንደሚከብደው ግልጽ ነው። ድፍረት ያላት ነፍስ ቀጣይነት ባለው መንፈሳዊ ልምምድ ራስን መግዛት ለሥጋ ፈቃድ የሚያስፈልገውን ምግብና መጠጥ በመተው የሥጋ ፈቃድን ድል መንሳትንና የሥጋ ፈቃድ ለነፍስ ፈቃድ ማስገዛት ይቻላታል። ይህች ነፍስ የሚመጣባትን ከባድ ነገር ሁሉ እስራትም ቢሆን ግርፋትም ቢሆን መቋቋም ይቻላታል።

በእግዚአብሔርና በተጋድሎ የፀኑ ሰዎች ሥጋቸውን እስከሞት ድረስ አሳልፈው በመስጠት ሰማዕትነትን መቀበል ይቻላቸዋል። በአካላዊ ስሜት ብቻ ሳይሆን ከመጾም በሚገኘው መንፈሳዊ ጥቅም ሰማዕታት ጾምን የስልጠና ትምህርት ቤት አድርገውታል። የጾም ቀናት የሚጠቅሙን ለመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በኃጢአታችን እንድንፀፀት እና ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ብቻ ሳይሆን ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ያለንን ፍቅር ለመግለጽም ይጠቅሙናል። ሰማዕታት የጾምን፣የፀሎትን እና የብሕትውናን ሕይወት የኖሩ ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው በዚህችም ዓለም የሚጠቅሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ የዚህች ዓለም መልክ አላፊ ነው"1ኛ ቆሮ 7፥34

እውነተኛ ጾም አንድን ሰው ራሱን እንዴት መቆጣጠር እንዳለበት ያሰለጥነዋል። ቀሪ ሕይወቱን እንዴት መኖር እንዳለበት እንዲያውቅ ያደርገዋል። ራስን መቆጣጠር ለቅድስና ሕይወት መሠረት ነው። ጾም ቅጣት ሳይሆን ደስታ ነው።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ (የሕይወት መዓዛ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
3.7K views◦•●Yaredo●•◦, 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 09:07:12
ማስታወቂያ

መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
በሌሊት ለሚሸና
ለነገረ በትን
ለደም ግፊት
ለስኳር ህመም መቀነሻ
ለሁሉም ቁርጥማት
ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
ለፊት ማድያት
ለሳል በሽታ
ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
ለማህጸን እንፌክሽን
ለአእምሮ ጭንቀት
ለወገብ ህመም
ለነርብ
ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
የሚጥል በሽታ
ገንዘብ ለሚበተንበት
ስራ አልሳካለት ላለ
ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
ለመፍትሔ ስራይ
ለአስም (ለሳይነስ)

ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ

እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል

ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
ይደውሉ
0917040506
0912718883

ቻናሉን ይቀላቀሉ
https://t.me/mergatah

ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
3.1K views◦•●Yaredo●•◦, 06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 08:26:20 ማየት ስለሚናፍቁት የሀገራችን ቦታዎች

እዛው እንዳሉ አድርጎ የሚያቀርብልዎ

ethioculturetips.com

ethioculturetips.com

ethioculturetips.com

ከላይ ባለው አፕሊኬሽን በስልኮ ይመዝገቡ
ወይም ወደ 9676 OK ብለው ይላኩ
3.0K viewsE D U , 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 20:51:27 ✞ እንዲህ በአራት ነጥብ ✞

እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዘጋ ምዕራፉ
እግዚአብሔር ሊያሸንፍ የእርሱ ሆኖ ሰልፉ
መልካም ለመናገር አፉ ባይታደል
ይህን እስኪያይ ጠላት ምን አለ ዝም ቢል(፪)

መልካሙን ደብቆ ክፉን እያሳየ
ይለኝ ነበር ጠላት እግዚአብሔር ዘገየ
ግን ሁሉን በጊዜው ውብ አርጎ ሲሰራ
አፍሯል ለዘላለም ደንቆት የእርሱ ስራ(፪)
አዝ= = = = =
በቃ ልጅ የለህም አትወልድም ሳራ
ላይሰማህ እግዚአብሔር ቆመህ ብትጣራ
እያለ ጠላቴ መስሎት ያሸነፈ
ይስሐቅ ተወለደ ያ ቀንም አለፈ(፪)
አዝ= = = = =
ፍፃሜዬን ሳያይ ገና ከጅምሩ
ጠላት በእርሱ ግምት ብዙ መናገሩ
አስብሎታል ቴቄል ተቀይሮ ስሙ
የዘገየ መስሎ ጌታ በመቅደሙ(፪)
አዝ= = = = =
ድንጋይ ያሸከመን ውሃ ተሸከመ
ለኛ ቀን ወጣልን ለእርሱ ግን ጨለመ
ገዳይ ቢዘገይም ሟች በመገስገሱ
ፈረሰኛው ሞተ እስከነፈረሱ(፪)
አዝ= = = = =
ቢመስለንም ሌቱ ፍፁም የማይነጋ
ተቆልፎ ሚቀር በሩ እንደተዘጋ
እርሱን ተስፋ አድርገው በአመንክበት ፅና
ቀን አለው እግዚአብሔር ያደርግሃል ቀና(፪)


መዝሙር በ
ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
2.6K views◦•●Yaredo●•◦, 17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ