Get Mystery Box with random crypto!

የግጥም ምሽት በቴሌግራም

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegetem32 — የግጥም ምሽት በቴሌግራም
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegetem32 — የግጥም ምሽት በቴሌግራም
የሰርጥ አድራሻ: @yegetem32
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.74K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ከተለያዩ መጽሐፍት የተቀነጨቡ ግጥሞች የሚቀርቡበት እንዲሁም ወርሃዊ የግጥም ውድድሮች የሚካሄዱበት ነው
ግጥም ለምትወዱ ሁሉ...የራሳችሁን ሙከራም የምታቀርቡበት ነው
ለማንኛውም አስታየት @Nirvana134 እንዲሁም @simba23 ላይ አለን

@yegetem32

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-11-26 21:08:33
እፎይ
""""""
አይቆረቁርህም፥
አይጎረብጥህም፥ደግሞ ለመቀመጥ፤
በሀሳብ እሩቅ አትሂድ፥ከመሬት ተዘርፈጥ፤
ሶፋና በርጩማ፥ብለህ ከቶ አትምረጥ፤
ምቾት ሲበዛ ነው፥እሳቤ የሚቀብጥ...

እመን

አይቆረቁርህም፥
አይጎረብጥህም፥
መቀመጫ ገር ነው፥አያውቅም አማሮ፤
አመል ከተገራ፥ከታጠበ አዕምሮ...

ተቀመጥ፥
አትቅበጥ፥
አትናቅ፥
አታማርጥ፥
ለምቾትህ አደልድል
አፈር ተፀይፈህ፥ፈፅሞ አትገደር፤
ህሊና ካልፀዳ
አይገጣጠሙም፥እፎይታና ወንበር..!


አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Run_Viva_Run
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
4.2K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 13:32:25 ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
ሲራክ ወንድሙ @siraaq
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
https://t.me/yegetem32
3.8K viewsC-ራክ, 10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 19:59:36
ተጓዥ
"""""""
ሂዱ ከመከራው፥
ቢከብድም ተራራው፥
ሜዳ ብቻ አይደለም፥ህይወት ስንክሳሯ፤
ስኬት ጫፉ አይሆንም
ፈተና ነው ደስታው፥በልብ ለሚመራ...

ሂዱ በጭንቅ መንገድ
የጭቃ ማጥ ጥርጊያን፥መርገጡ ቢሰቅም፤
አልጋ በአልጋ ሆኖ
የሮጡበት ኮቴ፥ከአንጀት አያስቅም...

ሂዱ...ሂዱ...ሂዱ
ቢያስፈራም መንገዱ፥
አያል ሆኖ ጉዱ፥
ውጤት አልባ ሆኖ
የተጓዙት ዳና፥አፈር ደም ቢያቀምስም፤
ላደከመ እርምጃው
ብልህ እግሩን እንጂ፥መንገዱን አይወቅስም..!

#ይሄዳል

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
join

@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
3.9K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-24 09:28:55 ገላዬ....
ከመስኩ ላይ ቆሜ ፥ እምባን ባረገዘ
በናፍቆት ወይቦ ፥ በተድበዘበዘ
በዚያ መንታ አይኔ...
የመራቤን ጅራፍ ፥ የምኞቴን ጩኸት
ላንቀላፋው ጤዛ ፥ ለወፍ ጎጆው ምልዓት
ዘምሬ
ዘምሬ
ደስኩሬ
ደስኩሬ
ህቅ ባለው መንፈስ ፥ ምሬት ባየው ልሳን
ብናገር ለእነሱ ፥ የኔን እንዲህ መሆን
የአንቺ ወዲያ መቅረት ፥ የንጋት ሰቀቀን
በጉድ ወጣ እያሉ ፥ ለሰማይ ለምድሩ
ለሰው ላራዊቱ ፥ ለቀየው መንደሩ
መስቀሉ ናት ብለው ፥ ናፍቆት ወለፈንዴ
ተሸነፈ ብለው ፥ ያሙኝ ይሆን እንዴ?
.................. / / .....................
ሲራክ ወንድሙ
@yegetem32
@yegetem32
4.5K viewsC-ራክ, 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ