Get Mystery Box with random crypto!

የግጥም ምሽት በቴሌግራም

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegetem32 — የግጥም ምሽት በቴሌግራም
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegetem32 — የግጥም ምሽት በቴሌግራም
የሰርጥ አድራሻ: @yegetem32
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.74K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ከተለያዩ መጽሐፍት የተቀነጨቡ ግጥሞች የሚቀርቡበት እንዲሁም ወርሃዊ የግጥም ውድድሮች የሚካሄዱበት ነው
ግጥም ለምትወዱ ሁሉ...የራሳችሁን ሙከራም የምታቀርቡበት ነው
ለማንኛውም አስታየት @Nirvana134 እንዲሁም @simba23 ላይ አለን

@yegetem32

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-17 23:41:53 join this poetic channel and read the poem then send any feed back or comment to poet Abrham fikre(ye kedas lij)
join
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
5.1K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-03 22:44:53
እምነት
""'''''''''''
የዓለም እሾህ ወግቶኝ
ከቤተ'ስቲያን ቅፅር፥መሬት ተንበርክኬ፤
ለጨነቀኝ ጭንቀት
ዕንባን አጎርፋለሁ፥መቅደሱን ታክኬ...

ፀልዬ ስነሳ
ያንኑ ጭንቀቴን አብሰለስላለሁ፤
አጉተመትማለሁ፤
አንስቼ ጥላለሁ፤
ድጋሚ ፈራለሁ፤
መቼም ሰው አይደለሁ!

ስሜትና ሀሳቤ፥አደብና ቀልቤ፤
ስክነቴን ሸክፈው
ሰቀቀን ሰዷቸው፥እርቀው ከበሬ፤
መልሶ ይወጋኛል
ለእምነቴ አለቅም፥የጭንቀቴን ፍሬ፤
የሞኝነት ነገር
"ባይችለውስ" ብዬ፥ፈጣሪን ጠርጥሬ...

አወይ ሰው መሆኔ!

አይ ፍርሃት፥
አይ ሸክም፥
አይ ጥረት፥
የህሊና ኡደት፥የመልፈስፈስ ዕዳ፤
ባይገባኝ ነው እንጂ
እምነቴ ቢጀግን
ግመል ጭንቄ ይሾልካል፥በመርፌ ቀዳዳ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
join
@HAKiKA1
@HAKiKA1
5.9K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 22:07:05 የልብህን ቁስል ትቶ የደረትከን ንቅሳት ያደንቃል፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያህ ብራንድ ይተመንልሃል፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩትን ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማል። — እያዩ ፈንገስ

@HAKiKA1
@HAKiKA1
Join us
5.3K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 14:51:38 # የተራዘመ_ውልደት


ጌታ ሆይ
ከአባትህ ቤት ወተህ ፥ ለኛ ስትቀጣ
ከሀጢአት ነፃነት ፥ ነፃ ስታወጣ
እንደ ድሮ መስሎ
ዳግም ለመወለድ ፥ ዘንድሮ ብትመጣ
አይ
አይ
አይ
እኚያ በትንፋሽ ፥ የሚያሞቁ ከብቶች
ግማሾቹ ታርደው ፥ ግማሾቹ በጥይት ተገለው
እስትንፋሳቸው ቆሟል ፥ ከሜዳ ላይ ወድቀው
አይ
አይ
አይ
ደሞ አህዮቹን
ያሞቁኛል ብለህ ፥ ብታስብ አሁንም
ብትፈልግ ብትፈልግ ፥ አይኖሩም ከግርግም
ካ..ገ..ኘ..ሃ..ቸ..ው..ም
ሲላላኩ ነው ሚውሉ ፥ በጦርነት ግድም
አይ
አይ
አይ
ሁሉ..ሁሉ..ሁሉ..ቀርቶ
ወገብ ማሳረፊያ ምናል ፥ ቢፈለግ ተገኝቶ
ሲታሰስ ሲታሰስ
ደጋግሞ ሲታሰስ
በእሳት ተበልቷል
አለ የተባለበት ፥ ምጣዱ ጋር ሳደርስ
ወዲያ ማዶ ከጋራው ላይ
አንዲት ጎጆ ዘንበል ያለች
እኔን ለመውለድ ከቶ ትበቃለች
ብለህ
ከቦታው ጋር ስደርስ ፥ ብታገኝም በረት
እሱም ተይዞ ፥ ጥይት ሆኗል፥ የሚከማችበት
እሱም ተይዞ ፥ ልጃገረድ አዛውንት ፥ ሆኗል የሚደፈርበት
ለዛ
ለዛ
ለዛ
ይኼን ሁሉ በደል
ይኼን ሁሉ ስቃይ
ይኼን ሁሉ ጭካኔ
ገና ሳትወለድ ፥ ከባሰ ከዛኔ
በቃ እንደውም እንደውም
በድሮ ውልደት ፥ እኛ ስንፃናና
ጊዜውን አራዝመኸ
አንተ አትወለድ ፥ በዘንድሮ ገ'ና
ይቅርብህ
ይቅርብህ
።።።።።።።።።።።።።።።።
ሳሙኤል አለሙ

@Samuelalemuu
5.9K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-02 23:09:59
አልቀርም
""""""""""
ከሩቅ ተቀምጠሽ
ኮቴዬን ጠብቀሽ
በናፍቆት አለንጋ፥ልቦናሽ ተገርፎ፤
እያገላበጠ
ጉጉት ምን ቢያነድሽ
ውስጥሽ አይከፋ፥አይቀየም ደርሶ...
እኔ እየመጣሁ ነው
ስችል አፈትልኬ፥
ቢያቅት በእንብርክኬ፥
ብወድቅ ተንፏቅቄ፥አልቀርብሽ ከቶ፤
ቢዘገይ ነው እንጂ
ፍቅር እየገፋው፥ሰው አይቀርም ታክቶ!

#አልቀርም_መጣለሁ


አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
join

@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
5.3K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 22:16:05
እ.ን.ደ.ራ.ጅ?
""""""""""""""
አሳማና ዶሮ ቡና ተጠራሩ፤
በቡና ቁርስ ወሬ
የባጡን የቆጡን ሁሉንም አወሩ...
አውርተው፥
አውርተው፥
ለህይወታቸው ለውጥ፥ለመድረስ ለስኬት፤
ዶሮ "እንክፈት" አለች
"አለ የተባለ ታዋቂ ምግብ ቤት"

"እሺ" ተባባሉ፤
በሀሳብም አልቀሩ፤

በአንድ ተደራጅተው ምግብ ቤት አቆሙ፤
ታ.ት.ረ.ው ለመስራት በአንድ ልብ ተስማሙ፤
አውጥተው አውርደው
ለሬስቱራንቷ ስም ለመስጠት አጤኑ፤
በሀሳባቸው ማምሻ
"ያ'ሳማ ስጋና እንቁላል ምግብ ቤት"በሚለው አፀኑ

ከዛማ

ከዕለት ወደዕለት
ከዓመት ወደ ዓመት ደንበኛቸው በዛ፤
እጅ ያስቆረጥማል
የአሳማ ስጋ አልሆነም የዋዛ...
በዝና ተሰምቶ
የሩቅ እንግዳዎች
ምግቡን ለመቅመስ ይመጡ ጀመረ፤
የዶሮ እንቁላልም
እንደአሳማ ስጋ ይጣፍጥ ነበረ።

እንዲህ ነው እንግዲህ
የአንዳንድ ምክክሮች የተግባር መቋጮ፤
የህብረት ተብሎ
ለአንዱ መሰዋት ነው ለአንደኛው መዋጮ..!


አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
join
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
4.4K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-08 11:38:11
ሁለት ገፅ
"""""""""""
የደሀ የህልሙን ቅቤ
ሀብታም በእውን ቀመሰው፤
ደም ግባቱን አ.ሻ.ቅ.ቦ
መልኩን ወዝ አለበሰው፤
የደሀ የሰማዩን ላም
ቱጃር አልቦ ጨረሰው፤
ምስኪን ተስፋው ነጠፈ
ደሀ ጠኔ ወረሰው..!

አዬዬ.. ሰው........አዬዬ..ሰው

የክፋት ዓለም ንውዘት
የክፋት ህይወት መንጠቆ፤
እውነት ወዲያ ተሽቀንጥራ
ሁሉም ውሸትን ታጥቆ፤
የሰው ላብ ከማር ጣፍጦ
የስርቆሽ ሀሳብ ሰንቆ፤
በግ በአንድ ብር ይስቃል
በፍየል መቶው ተነጥቆ..!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
join and share
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
4.6K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-07 05:58:54
ጦቢያዊቷ

ሳቋ የፀሀይ ልክ
ልብ የሚያሞቅ ጥርሷ፤
ቁጣዋ የነብር
ግርማዋ የአንበሳ፤
ግልምጫዋ ይገድላል
እንኳንስ ተኩሳ
..!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
join
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
4.2K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-03 06:28:06
ትሁኔ....ይሁኔ
""""""""""""""""
ትሁኔ

በአንድ ሰሞን ቀን አንግሶ፤
ደም ግባቷን አሞግሶ፤
በውበት ልክ የምትቃኝ፤
ሁሌ የምትል መልኬ በቃኝ...

በፊት ልቧን ያኮፈሰች
ሁሉ ሲላት ቆንጆ ብቻ፤
አሁን ስጋት ያናወዛት
የምትመኝ ሶስት ጉልቻ..!

ስትኮራ
ስትቆነን ውብነቷ የነጠፈ፤
የዕድሜ አለሟ
እንደ ድንገት በሆይ ሆይታ የከነፈ፤
ድንቅ ገፅዋ የረገፈ...



ኔ...

ይሁኔ

መሸታ ቤት ዘውትር ቤቱ፤
ወጣት መሳይ ዕድሜው የአንቱ...
ከዛች ከዚች ሲነካካ፤
ያልሰከነ ልቡ ያ'ረጋ...
በእድሜው ዘመን ወደ አመሻሽ፤
ብሎ የሚጮህ "የሚስት ያለሽ''...



ኔ...

ይህን ያየ መንደርተኛ፤
ለሰው ኑሮ የማይተኛ...
ትሁኔንም አማከረ፤
ይሁኔንም መረመረ...
ቀረፃቸው በአንድ ጠርዝ
በራሱ ሀሳብ አድበልብሎ፤
ጊዜ ሄዷል ተፋቀሩ
"ይሁን" እና "ትሁን" ብሎ...
.
.
አንድ ጥያቄ አለኝ
በውስጤ ግር ያለኝ...
.
.
በዘመን ውርጅብኝ ታሪክ ሲለጣጠፍ፤
በውሸት የዳበረ የዘመኑን ጉድፍ...
በሁለት ፆታ ፍቅር
ህዝብ ተቅጠልጥሎ እያለ ሰለሜ፤
ዓላማና ፍቅር
በምን ተገናኙ እላለሁኝ ቆሜ..?
***
ያረፈደ ሁሉ
ካረፈደ ኃላ ዘመን ከጠገገ፤
መሰሉን መሰሉን
የረፈደበትን ሰርክ እየፈለገ...
መንደርተኛው ሁሉ
"ጊዜ ሄደባቸው" እያለ እያወጋ፤
በቡና ቁርስ ወሬ
"እከሌን ለእከሊት" ብሎ እያጋባ፤
ለዓላማ ሲደገስ
በሽሙጥ ጭብጫቦ በሽሙጥ ሀይሎጋ፤
ስሜት ሆነ ሞቱ
ፍቅር ገደል ገባ፤
ሰዉ ታቅፎ አደረ
ነፍስ የሌለው ስጋ..!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
join
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
4.2K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ