Get Mystery Box with random crypto!

Orthodox

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeemariyaam21 — Orthodox O
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeemariyaam21 — Orthodox
የሰርጥ አድራሻ: @yeemariyaam21
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8
የሰርጥ መግለጫ

በገጠር ኢትዮጽያ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ መረጃ እና የአገልግሎት ማነቃቂያ ለመስጠት የተከፈተ መንፈሳዊ የዘገባ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቻናል ነው

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-14 12:13:09
"ሥላሴ ትትነከር ወትትረመም፤"
***
የእግዚአብሔር ልዩ የአንድነት እና ሦስትነት ምስጢርን ያደንቁታል፤ ለፍጥረት የሚቻለውን ያህል ብቻ ይናገሩታል።

በተገለጠው በእውነት እና በመንፈስ ያመልኩታል፤ ጠቅልዬ ካላወቅሁት እና ሁሉን አከናውኜ ካልተናገርኩት ግን አይባልም፤ ይህ ከፍጥረት ውስንነት በላይ ከፍ ያለ አምላካዊ ሕላዌ ነውና።

በኦሪትና በነቢያት ቀድሞ የተነገረውን፣ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ሰው ሆኖ የገለጠውን

የቅድስት ሥላሴ ትምህርት ማወቅ ይህ የሰው ልጅ አምላኩን የማወቅ የማያልቅ ፍላጎቱ ለዘላለም በመንግሥተ ሰማያት የሚረካበት የደስታ ሕይወት ምንጭ ነው።

(ዮሐ. 17፥3) የቅድስና ሁሉ ፍጻሜ "ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ - ቅድስት ሥላሴን ማየት" ነውና! ይህ ቅድስት ሥላሴን "ማየት" ምን ይደንቅ!

በእግዚአብሔር ጸጋ ለዚህ የበቃችሁ ቅዱሳን ሆይ! ብፁዓን ናችሁ! እኛንም ያድለን ዘንድ ለምኑልን፤ አሜን።

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
1.7K viewsedited  09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:35:13 አትዋሹ ሀብታም ናችሁ

@BiniGirmachew

አንድ ድሀ ወደ አንድ ገዳም ሄዶ በዚያ ያገኛቸውን መነኩሴ አባት፡- “አባቴ ለምን በጣም ደሀ ሆንኩ ?” ብሎ ጠየቃቸው ። እርሳቸውም፡- “የምትሰጠው ብዙ አለህ እኮ ግን አላወቅከውምን ?” ብለው በጥያቄ መለሱለት ። ድሀውም፡- “የምሰጠው ምንም ነገር የለኝም” አላቸው ። እኒህ አባትም እንዲህ አሉት፡- ከማንም የማያንስ የምትሰጠው ብዙ ነገር አለህ ተመልከት፦

• ፊትህ፦ ይስቃል ፥ ይደሰታል ፣ ለኀዘነተኞች ፈገግታህን ያካፍላል !

• አንደበትህ፦ ውብ የሆኑ ቃላትን ትናገርበታለህ ፥ ታመሰግንበታለህ ፥ ሰዎችን ታበረታታበታለህ ፥ ትመክርበታለህ ፥ ታጽናናበታለህ !!

• ልብህ፦ ለመልካምነት ፥ ለእውነትና ለትሕትናን ክፍት ነው !

• ዓይንህ፦ ጎስቋሎችንና ችግረኞችን በፍቅርና በደግነት ትመለከታለች !! በኀዘን ለተዋጠው እንባን ትሰጣለች !

• እጆችህ፦ አቅመ ደካሞችን ያግዛሉ ።

ተመልከት ይህን ሁሉ መስጠት ከቻልህ አንተ ደሀ አይደለህም !!

በዚህ ዓለም ላይ ከሌላቸው ሰዎች ይልቅ ያላቸውን ያላወቁ ሰዎች ይበዛሉ ። ያለንን ካላወቅነው ያው ድሀ ነን ። ድህነት ያለው እጅ ላይ ሳይሆን አእምሮ ላይ ነው ። ሁሉም ነገር ያላቸውና ምንም ነገር የሌላቸው ሰዎች በዓለም ላይ የሉም ። ጉድለቱን ያው ባለቤቱ ብቻ ያውቀዋል ፣ ሙላቱንም ሰዎች ብቻ ያውቁታል ። የጎደልንን እኛ ስናውቀው ፣ ያለንን ግን ሌሎች ያውቁታል ። ላወቀበት ፈገግታም ሀብት ነው ። አንድ ትልቅ ባለጠጋ ናቸው ፣ ስማቸውን ብጠራ ታውቋቸዋላችሁ ። ግን ስም አይጠሬ ናቸው ። በጣም ደስተኛና ሳቂታ የሆነ ወጣት ሁልጊዜ ማኪያቶ ይሠራላቸዋል ። አንድ ቀንም ከመቀመጫቸው ተነሥተው ወደዚህ ወጣት ሄዱና፡- “ልጄ ሁልጊዜ ሳይህ ፈገግታ ሞልቶብሃል ። ያንተን ደስታ እኔ ለአንድ ቀን አግኝቼው አላውቅም ፤ እንደ ተደሰትክ ፣ እንደ ሳቅህ ኑር” ብለው ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ። አዎ ፈገግታ ሀብትና ከሀብትም በላይ መሆኑን እኒህ ቢሊየነር መስክረዋል ።

ዝነኛ የነበሩት ፖፕ ዮሐንስ ዳግማዊ፡-። “አንድ ሰው የመጨረሻ ድሀ ቢሆንም እንኳ ለሌላው ሊሰጥ የሚችለው ነገር አለው ፤ እንዲሁም ሌላውም በጣም የተረፈው ሀብታም ቢሆንም ከሌላ ሰው መቀበል የሚያስፈልገው ነገር አለ” ብለዋል ። ይህ ዓለም ሙሉ ድሀ ነኝ ፣ ሙሉ ባለጠጋ ነኝ የማይባልበት ዓለም ነው ። እንዳንሳቀቅ የምንሰጠው አለን ፣ እንዳንኮራ የምንቀበለው አለን ። እግዚአብሔር ቅዱስ ሙላትን ፣ እንዲሁም ቅዱስ ጉድለትን በእኛ ውስጥ በማስቀመጡ ሕይወትን ውብ አድርጓታል ።

በዓለም ላይ ፈግታን የመሰለ ሀብትና ምግብ የለም ። ፈገግ ያሉልን ሰዎች ፀሐይ እንዳበሩልን ናቸው ። ፀሐይ በርቶም የጨለመባቸው ፈገግታን ሲያዩ ይደሰታሉ ። ልባቸው ኀዘን አርግዞ የሚኖሩ ፈገግታ ሲያዩ ይፈወሳሉ ። ዋጋ የለኝም የሚሉ ፈገግታ ሲያዩ ለካ አስደሳች ሰው ነኝ ብለው በራሳቸው ይኮራሉ ። ፈገግታ ከማንኛውም ስጦታ በፊት ከቀደመ ስጦታውን አስደሳች ያደርገዋል ። እውነተኛ ፈገግታ ያሳዩን ሰዎች በዘመናችን ሁሉ አንረሳቸውም ። በፈገግታ እንኳን ሰው እንስሳትም ይፈነድቃሉ ። በፈገግታ ውኃና ዛፍ ሳይቀር ይስቃሉ ። ፈገግ ስንል ቤቱ ይበራል ። የሥራው ቦታ ተወዳጅ ይሆናል ። ፈገግ ስንል ሰዎች ፈገግ ይላሉ ። የዘራነውን ወዲያው የምናጭደው በፈገግታ ብቻ ነው ። በፈገግታ ጠላትን መማረክ ይቻላል ። ላለመደሰት የቆረጠውን ኪዳኑን እንዲያፈርስ ማድረግ ቀላል ነው ። ፈገግታ መንፈሳዊነትን የሚነካ አይደለም ። መኮማተርና መኮሳተር መንፈሳዊነት ከመሰለን ተሳስተናል ። አዎ ምንም ድሀ ብንሆን ፈገግታን መስጠት እንችላለን ። በፈገግታችን የምንቀጥለው ዕድሜ አለና አበርትተን እንያዘው


ብዙ ኀዘን ፣ የልብም ስብራት ያለብን ፣ ቀንበር እንደ ተሸከመ የጎበጥነው ሰዎች ክፉ ተናገሩኝ ብለን ነው ። አንደበት ኃይል አለውና ይጎዳል ። ለመልካም ከተጠቀምንበት በአንደበታችን ማስደሰት ፣ መጠገንና ሰዎችን ነጻ ማውጣት እንችላለን ። በአንደበታችን እግዚአብሔርን ስናመሰግን አካባቢውን መለወጥ እንችላለን ። እኛ ስናመሰግን ሰዎች ራሳቸውን ማየት ይጀምራሉ ። ስናደንቃቸው ኃይልን ይሞላሉ ። ጥሩ ፣ ጥሩ ስንናገርላቸው በደስታ ይሰክራሉ ። በዓለም ላይ በበጎ ጎኑ ያልተጠቀምንበት ነገር ቢኖር አንደበት ነው ። አንደበት የኒውክለርን ያህል ጎጂ ነው ። አንደበት ከተጠቀሙበት ነቢይና ሐዋርያ ፣ ሰማዕት የሚያሰኝ ነው ። በአንደበታችን መልካም መናገር ተገቢ ነው ። ቀድሞ የሚዘጋው እርሱ ነውና ። ዘግይቶ ተከፍቶ ቀድሞ የሚዘጋ አንደበት ነውና መልካም ልንናገርበት ይገባል ። ምንም የምሰጠው የለኝም ማለት ስንፍና ነው ። መልካም ቃል የወርቅ ሳንቲም ነው ።

ምስኪኖችን በሙሉ ዓይናችን ስናያቸው ችግሬን አወቀልኝ ብለው ይደሰታሉ
። በአንድ የሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ስጎበኝ፡- “ሕፃናቱ ምን ያስፈልጋቸዋል?” ስል፡- “የሚፈልጉት የሚያያቸውና የሚያቅፋቸው ሰው ነው ። ምግብ እዚህ ይሟላል ፣ የእናት ፍቅር ግን ልንሰጣቸው አልቻልንም ። እባካችሁ መጥታችሁ እቀፏቸው” አሉኝ ። እስካሁን ይህ ድምፅ ውስጤን ያጠቀጥቀዋል ። ለማቀፍ ባለጠጋ መሆን አያስፈልግም ። ሰውን በፍቅር ዓይን ስናየው ይበረታታል ። ዓይንም ፍቅርን ያሳብቃል ። ዓይንም ይናገራል ። በዓለም ላይ በቃላት የሚገለጡ ነገሮች ጥቂት ናቸው ። ቃላት የማይችሉትን ዓይን ይገልጠዋል ። ዓይን ከተጎዱት ጋር አብራ ስታለቅስ የተጎዳው ሰው ኀዘኑን ይተዋል ። መቼም ላይረሳን በልቡ ይጽፈናል ። ከሚያዝኑት ጋር ማዘን ትልቅ ዋጋ አለው ። ለዚህ ባለጠጋ መሆን አያስፈልግም ።

በጉልበት የምናግዛቸው ብዙ ደካሞች አሉ ። መንገድ የምናሻግራቸው ዓይነ ሥውራን ፣ ገላቸውን የምናጥባቸው የአእምሮ ሕሙማን ፣ ቤታቸውን የምናጸዳላቸው ባልቴት አረጋውያን ብዙ ናቸው ። ገንዘብ መስጠት ባንችል ጉልበት ገንዘብ ነውና ያንን መስጠት እንችላለን ። ለመስጠት ፈቃዱ ካለን መስጠት እንችላለን ። እግዚአብሔር ተቀባይ ብቻ አድርጎ አልፈጠረንም ፣ መስጠት የምንችል አድርጎም ፈጥሮናል ። እባካችሁ ስጡ ።

ምሽቱን የሰላም ያድርግላችሁ

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
2.8K viewsedited  18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 08:55:12
እናዳመጠው

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
3.4K viewsedited  05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:19:43
3.2K views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 12:10:19
ኮልፌ
ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን

የትላንቱ ምሽት እንዴት ደስ ትል ነበር

በድጋሚ እንኳን አደረሰን
3.8K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 12:03:19
የዛሬው ቀን በተጨማሪ

የቅዱስ ጴጥሮስ እና የቅዱስ ጳውሎስ ያረፉበት ቀን ነው።


እንኳን አደረሰን

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
3.7K viewsedited  09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 10:15:47
" እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት ርሷንም እሻለሁ። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ። መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። " ➬ መዝ.፳፮ ፥ ፬.
4.6K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:47:02
##እልል በሉ በአንደነት ዘምሩ##

አመሰግኑ ለክብሩ ዘምሩለት

እንድ እግዚአብሔር ያለ ማንም
የለም በሉ

እንደ እኔ እናተም ዘምሩ#####

ከእግዚአብሔር ጋር የምኑልበት ቀን ያድርግልን።

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
5.5K viewsedited  04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 11:55:52 ሕይወትን በፍቅር


@BiniGirmachew

የፍቅርን ትክክለኛ ትርጉም ተማር፡፡ በሕይወትህ ውስጥም ዋናው ነገር ይህ ይሁን፡፡ እግዚአብሔርን አፍቅር፣ ራስህን ውደድ ሌሎችንም እንዲሁ፡፡ ይህንንም ግልጽ ባልሆነ መንገድ አታድርገው፡፡ ትህትና ይኑርህ፡፡ ከእያንዳንዱ ሕይወት ካለው ነገር የምትማረው የሆነ ነገር አለ፡፡ በሌሎች ሰዎች ደስተኛ ሁን፡፡ የሌሎችንም ሰሜት ተረዳ፡፡

ከሞከርክ ሁሉንም ሰው መውደድ ትችላለህ፡፡ ከምስጋና ጋር ቸር፣ ከትችት ጋር ጥንቁቅ፣ አገልግሎት ለመስጠትም የነቃህ ሁን፡፡ ብዙውን ድርሻ የሚወስደው እኛ ለሌሎች የምናደርገው ነው፡፡ ስለዚህ እንክብካቤህን ለሚሹ ከምትችለው ያነሰ አታድርግ፡፡ እውነተኛ ፍቅር ምድር ላይ ያለውን ሁሉ ቋንቋ ይናገራልና፡፡

ብርሃን ወረቀት ላይ በብርሃን እጅ የተጻፈ የብርሃን ቃል፣ ሥፍራን፣ ርቀትንና ጊዜን የሚደመስስ ኃይል ፍቅር ነው፡፡ ስለዚህ ትመሰገን ዘንድ አመስግን፣ ፍቅርን ትቀበል ዘንድ ፍቅርህን ስጥ፣ መልካም ስም የሚገዛው በፍቅር ነውና!

ፍቅር በሚያስደምምና ባልተለመደ መንገድ ይሠራል፡፡ በሕይወትም ውስጥ ፍቅር ሊለውጠው የማይችለው ምንም ነገር የለም፡፡ በጣም የተለመደውን ቦታ እንኳን ሳይቀር ወደ ተዋበ፣ ወደ አሸበረቀና ግርማን ወደ ተላበሰ መንደር ይቀይረዋል፡፡

ፍቅር፡-

1. ራስ ወዳድ ብቻ አይደለም፡- ይረዳል፣ ይራራልም፡፡ ሁሉን በስሜት ሳይሆን በልቡ ያያል፡፡

2. እያንዳንዱ ሰው የሚፈልገው ምላሽ ነው ፡- ከጨቅላው ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ እንስሳትን ጨምሮ የሁሉም ሕይወት የሚናገረው ቋንቋ ነው፡፡

3. የሚገዛ አይደለም፡- የዋጋ ተመን የሌለው ነጻ ነው፡፡ ልክ እንደ ንጹሕ ተአምር የሕይወት ጣፋጭ ምስጢር ነው፡፡ ስለዚህ ፍቅርን እንደ ትልቅ ሀብት ቁጠረው፡፡ በጥልቀትና በፍጹም ልብ ውደድ፡፡ ይህንንም በደስታ አድርገው፡፡ ምናልባት በሂደቱ ውስጥ ትጐዳ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሕይወትን ሙሉ ለሙሉ ለመኖር ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ታላቅ ፍቅርና ታላቅ ስኬት ትልልቅ ፈተናዎች አሉበት፡፡ ስለዚህ ያለ ማቋረጥ ፍቅርን ለግስ፡፡ ወደ ሌሎች ያፈሰስከው ፍቅር መልሶ ወደ አንተ መፍሰሱ አይቀሬ ነው፡፡ ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበዛ በረከት ስለሆነ በዚህ ውስጥ በመኖር ልዩ ደስታን ማግኘት እንችላለን፡፡

የማያስተውል ዓይን ብቻ በሰው ውስጥ የሉትን መልካምነቶች ማየት አይችልም እንጂ ፍቅር እውር አይደለም፡፡ እውነተኛ ፍቅርና ርኅራኄ ሁልጊዜም ደስታዎቹን ያጠራል፡፡ በትክክል ለማየት ይረዳል፣ ይፈውሳል፡፡ ክፉ ስሜት እንዲደበዝዝ፣ መልካሙ መንፈስ ደግሞ እንዲነቃ ያስችላል፡፡ በሰው ውስጥ ያለውን መጥፎውን ሳይሆን መልካሙን ነገር ያፋጥናል፡፡ ከብርሃን ይልቅ የሚያድስ፣ ከአበቦች ይልቅ መዓዛ ያለው፣ ከብዙ ዜማዎችም ይልቅ ጥዑም ነው፡፡

አስታውስ! ሕይወት የምትለካው ሌሎችን ሰዎች በመሰጥንባቸው ጊዜያቶች ሳይሆን እኛ በሕይወት በተመሰጥንባቸው ቅጽበቶች ነው፡፡

ሰው ሃይማኖቱን ሲወድ በሃይማኖቱ ሥር ያሉትን ያፈቅራል፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ሲያፈቅር ግን የሰውን ዘር ሁሉ ይወዳል ፍቅር ኃይለኛ ልብን የማስታገስ፣ እንደ ድንጋይ የሆነውን ነገር የማለስለስ፣ ቋጠሮንም የመፍታት ለዛ አለው፡፡


@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
5.8K viewsedited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:25:42
አቤቱ እያንዳንዱን ልመናውን አስብ።

ሴቶቻቸውን ጠብቅ፤ ጎልማሶቻቸውን አቅና፤

ሽማግሌዎቻቸውን አጽና፤ በመከራ የተቀጠቀጡትን አድን፤ በስደት የተበተኑትን ሰብስብ፤ መንገድ ከሚሄዱት ጋራም በረድኤት ሂድ። በመከራም የሚጨነቁትን አድን።

በጸብ በክርክር በጽኑ አገዛዝ ያሉትን በረድኤትህ አስባቸው።

አቤቱ ዓለምን የያዝህ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ በረድኤትህ አስበን።


@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
4.3K viewsedited  05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ