Get Mystery Box with random crypto!

Orthodox

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeemariyaam21 — Orthodox O
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeemariyaam21 — Orthodox
የሰርጥ አድራሻ: @yeemariyaam21
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8
የሰርጥ መግለጫ

በገጠር ኢትዮጽያ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ መረጃ እና የአገልግሎት ማነቃቂያ ለመስጠት የተከፈተ መንፈሳዊ የዘገባ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቻናል ነው

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-07 12:01:01 ሰላም ከሀገር ወጣ ብሄ ነበር አሁን መጥቼአለሁ እግዚአብሔር ይመስገን

እንኳን አደረሰን
499 views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 16:35:34 ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃሜውንም

ብታውቅ ትሸሸዋለህ
1.5K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 16:35:34 ከእርሱ ጋር ኀብረት ፍጠሩ!

@BiniGirmachew

እግዚአብሔርን ለማወቅ ለመውደድ ከእርሱ ጋር መተባበር አለባችሁ።

ንባብ ብቻውን በቂ አይደለም። ንባብ የሚከፍትላችሁ መዝጊያውን ብቻ ነው።

ከዚህ በኋላ እናንተ ትገቡና ከእግዚአብሔር ጋር ትኖራላችሁ ከዚያም ከእርሱ ጋር መኖር ጣፋጭ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።


ስለሆነም ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ትሞክሩታላችሁ እርሱ በሁሉም ነገር ውስጥ ተካፋይ እንዲሆንም ትፈቅዳላችሁ።


እንደ ባልጀራችሁ አድርጋችሁ ልትወዱት ሞክሩ አሳቦቻችሁንና ሚስጥሮቻችሁን ለእርሱ ንገሩት።

ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ጠብቁና እርሱ ምን ያህል ከእናንተና ለእናንተ እንደሚሰራ ታያላችሁ።

ከዚህ በተጨማሪ በአሳቦቻችሁና በተሰጥኦዎቻችሁ ከመተማመን የበለጠ በእርሱ ላይ መተማመንን ታውቃላችሁ።

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
1.5K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:40:20 ድነኀል ወይስ አልዳንክም?

@BiniGirmachew

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በአንድ መጽሐፋቸዉ እንዲህ ይላሉ። አንድ ወጣት ልጅ እንዲህ ብሎ ጠይቆኛል “አንድ ሰው ድነኀል ወይስ አልዳንኽም?” ብሎ

ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድ ነው?

መጀመሪያ ይሄ ሰዉ እዉነተኛ ኦርቶዶክስ እንዳልሆነ ማወቅ አለብህ።

በእርግጠኝነት ይሄ ሰዉ ፕሮቴስታንት ነዉ ወይንም ቢያንስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ውስጥ ነዉ የሚኖረዉ፣ ባህሉም የፕሮቴስታንት ነው። ከዚህ በፊት የተቀበልካቸዉን ምስጢራትንና ጥምቀትን እንደ ምንም ቆጥሮ፣ በሃይማኖትህ ላይ ጥርጥር ለመሙላት በመሞከር፣ ባለፈዉ የሕይወት ዘመንህ ሁሉ አሕዛብ እንደነበርክ አድርጎ እንደ ገና እመንና ዳን ሊልህ ነው።

ይሄ ሰዉ በፍጹም ኦርቶዶክስ ሊሆን አይችልም አነጋገሩም ይገልጠዋል።

ለማንኛዉም እንዲህ ብለህ ልትመልስለት ትችላለህ “በጥምቀት ከአዳም የውርስ ኀጢአት ድኜያለሁ፤

ይሄ ድኅነት የሚገኛዉ በደመ ክርስቶስ የቤዛነትንና የድኅነት ኀይል ነው። ነገር ግን የመጨረሻዉ ድኅነት በስጋ ስንለይ የሚገኝ ነው። አሁንም በውጊያ ላይ ነን “መጋዳላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፣ ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር እንጂ።” (ኤፌ. 6፥12)። ይሄንን ውጊያ ድል ስናደርግና ስናሸንፍ ድኅነትን እናገኛለን…”

በስጋ እስካለን ድረስ “ድል ነስተናል፤ ድኅነትን አግኝተናል” ልንል አንችልም።

ስለዚህ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት አታከብርም ወይም የተጠመቁበትን ዕለት፤ ይልቁንም ከዚህ ዓለም የተለዩበትን ወይንም መስዋዕት የሆኑበትን ቀን ታከብራለች እንጂ።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና “ዋነኞቻችሁን አስቡ፣ የኑሮአቸዉንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸዉ ምሰሉአቸዉ።” (ዕብ. 13፥7)።

ስለዚህ በቅዳሴ ላይ የቅዱሳንን መታሰቢያ እናደርጋለን፤ በእምነት ፍጹማን የሆኑትንና ሕይወታቸውን በእምነት የፈጸሙትን፣ በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ እናስባለን።

ይሄም የታላቁ አባ መቃርስን ከዚህ ዓለም መለየት እንዳስታውስ ያደርገኛል። ነፍሱ ከስጋው ተለይታ ስትሄድ “መቃርስ አንተ ድነኸል” እያሉ አጋንንት ነፍሱን አሳደዷት፤

ነገር ግን ገነት እስከሚገባ ድረስ “በጌታ ጸጋ ድኜያለኹ” አላላቸዉም ነበር…!

አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ነገረ ድኅነትን አስመልክቶ

ለፕሮቴስታንቶች መልስ ከሰጡበት “Salvation in the Orthodox Concept” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ ነዉ።

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
2.9K viewsedited  13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:03:58 በሕማም፣ በመከራና መሥዋዕት በመሆን ፍቅራችን ይፈተናል

@BiniGirmachew

ፍቅርን የሚያውቅ ሰው ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ሰው በመጀመሪያ መሥዋዕት ለማድረግ መልመድ ያለበት ከእርሱ ውጪ በሆኑ ነገሮች ማለትም ገንዘቡን፣ ጊዜውን እና ሀብቱን በመለገስ ነው፤ መስጠት ከማግኘት አንድ ነውና፡፡ ለሰዎች ደስታ እንደራሱ የሚጨነቅ እርሱ ፍቅርን ያውቃል፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ይኖራል፡፡ መሥዋዕትነት መክፈል ካልቻልን ግን ፍቅር አልገባንም ማለት ነው፤ አምላካችን እግዚአብሔርን ማፍቀር ካልቻልን ደግሞ ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ማግኘት አንችልም፡፡


ፍቅር የሚፈተነው በሕማም በመከራና መሥዋዕት በመሆን ነው፤ መሥዋዕት መሆን የማይችል ሰው የማይወድ ወይም የማያፈቅር ሰው ነው፡፡ የሚወድ ሰው ከሆነ ግን ለመውደድ ማንኛውም ነገር መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፡፡


የአባቶች ሁሉ አባት የተባለው አብርሃም ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር የተነሣ ወገኖቹንና የአባቱን ቤት ትቶ በመውጣት በአንድነት በድንኳን ውስጥ ኖሯል፤ ይሁን እንጂ አብርሃም ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር ያሳየው አንድ ልጁን በመሠዊያው ላይ ባስተኛው ጊዜ ነበር፡፡ እርሱ በልጁ ዙሪያ እንጨቶች ሰብስቦ ካቀጣጠለ በኋላ መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርበው ቢላዋ የያዘ እጁን ቃጥቶ ነበር፡፡


ነቢዩ ዳንኤል እግዚአብሔርን በወደደ ጊዜ ወደ ተራቡ አናብስት ይወረወር ዘንድ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ አቅርቧል፡፡ ሦስቱ ወጣቶች እንዲሁ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ያረጋገጡት በእቶኔ እሳት ውስጥ በመወርወር የከፈሉት መሥዋዕትነት ነው፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ፍቅር የገለጠው እንዲህ በማለት ነው፤ ‹‹አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ፤….›› (ፊል. ፫፥፰-፱)

አባታችን ያዕቆብ ከራሔል ጋር በፍቅር በወደቀ ጊዜ ስለ እርሷ ብዙ መሥዋዕትነት ከፍሏል፡፡ እርሱ ራሔልን ለማግኘት ለሃያ ዓመታት ያህል በቀን ሀሩንና በሌሊት ቁር መድከም ነበረበት፡፡ ይሁን እንጂ ለእርሷ ከፍተኛ ፍቅር ስለ ነበረው እነዚህ ዓመታት ለእርሱ እንደ ጥቂት ቀናት ነበር ያለፈለት፡፡ እኛም ለሰው ዘር በሙሉ ሲል በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ ለቀረበው ለኢየሱስ ክርስቶስ የምናቀርበው መሥዋዕት በዚህ ምድር የሚገጥመን ችግር በወጣት፤ የሚደርስብንን መከራ እና ሥቃይ በትዕግስት በማለፍ ነው፡፡

‹‹ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የኃጢአት መታሰቢያ አለ፤ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና›› እንደተባለውም ጌታችን ኢየሱስ መሥዋዕት ሆኖ ካዳነን በኋላ እኛም የምናቀርበው ለእርሱ መባ እና ምጽዋዕት ኃጢአታችንን ያስተሰርይልናል፡፡ ይህም በቤተክርስቲያን ለመዘከርም ሆነ ወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓል ለማክበር ስንሄድ እግዚአብሔር የምናቀርበው ስጦታ ነው፤ ሆኖም ግን በእምነት እና በበጎ ምግባር ያልተደገፈ ማንኛውም ስጦታ በእርሱ ዘንድ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ሁሉን የሚያይ አምላካችን ልባችንን እና ኵላሊታችንን ይመረምራልና የውስጣችንን ክፋት ስለሚያውቅ የምናቀርበውን መሥዋዕት አይቀበለውም፤ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በድፍረት በመርገጣችንም በኋላኛው ዓለም ይቀጣናል፡፡ (ዕብ. ፲፥፫-፬)

አባቶቻችን ሰማዕታትን ካህናት ለእግዚአብሔር ካላቸው ፍቅር የተነሣ ደማቸውን፣ ሕይወታቸውን እና መደላደላቸውን መሥዋዕት አድርገው አቅርበዋል፡፡ እነርሱ ለእግዚአብሔር የተለየ ፍቅር ስለነበራቸውና ሥቃይን ስለተለማመዱት ፈጽሞ ፈርተው አያውቅም ነበር፡፡

እኛም እንደ አባቶቻችን ለእምነታችንም ሆነ ለሃይማኖታችን ሰማዕት መሆን ባንችል እንኳን በዚህ በምድራዊ ሕይወታችን ማንኛውም ዓይነት ችግር እና መከራ ሲገጥመን ባለመማረር ሥቃዩንም ተቋቁመን ፈተናችንን ማለፍ ይጠበቅብናል፤ ከራሳችን አልፎ ለሌሎች መዳን ምክንያትም ልንሆን እንችላለን፡፡ ያን ጊዜም በሰላም፣ በፍቀር እና በአንድነት እንኖራለን፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር በሰላም እና በፍቅር አንድንኖር ፍቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
3.5K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 10:43:28 ራስን መንቀፍ

@BiniGirmachew

ራሱን የማይነቅፍ ሰው እርሱ ትክክል እንደሆነና እንዳልተሳሳተ አድርጎ ስለሚያስብ ምንም አይነት ስህተች ቢሰራ እንኳ ይቅርታ አይጠይቅም። ከወንድሙ ጋር ሲጋጭ ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ራሱን አያነሣሣም። እርቁ እንዲመጣ የሚፈልገው ከሌላ ወገን ነውና። ግን ለምን? ይህን የሚያመጣው ማንነት ነው! ሌላው ቢቀር እኔነቱ ምንም አይነት ስህተት እንዳልሠራ አድር ስለሚያሳምነው ስህተቱንም በእግዚአብሔር ፊት እንኳ እይናዘዝም።

ራስን መንቀፍ የሚመጣው ከትሕትና ሲሆን ትሕትና ደግሞ ራስን ወደመካድ ይመራል። ትሑት ያልሆነ ሰው ራሱን አይነቅፋም አይኮንንም። ሁልጊዜ የሚነቅፈው ሆነ የሚኮንነው ሌሎችን ነው። እንዲህ ዓይነቱን ሰው ለምን ሌሎችን እንደሚነቅፍ ብትጠይቁት ይህን በማለታችሁ ብቻ እንኳ ይገሥጻችኋል።

አንድ ራሱን ምንጊዜም በዓለማዊ ዘዴዎች የማያጎላና የማያከብር ሰው ዋናውና ተቀዳሚው ዓላማው ራሱን ከስህተትና ከጥፋት ማንጻት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው ሁልጊዜ ራሱን ይወቅሳል፣ ስህተቶቹን ይመረምራል፣ ለስህተቶቹም ማስተካከያ ይወስዳል፡፡

በአንድ ወቅት ጳጳሱ ቴዎፊለስ መነኮሳት አባቶች የሚኖቱበትን በአት ሲጎበኙ የዚያ ቦታ አስጎብኚ ለሆኑት መነኩሴ በዚህ ሳሉ ስለገኟቸው ቅዱስናዎች ሲጠይቋቸው “እመኑኝ አባቴ! ከሁሉም ነገር በላይ ራስን ከመውቀስ የሚበልጥ ቅድስና የለም!” በማለት መልሰውላቸዋል፡፡ ይህ አንድ ሰው ራሱን ብቻ እንጂ ሌሎች ሰዎችን፣ አካባቢውንና እግዚአብሔርን የማይወቅስበት መንፈሳዊ መንገድ ነው፡፡

ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የወቀሰ ሰው በወዲያኛው ዐለም ከመወቀስ ይድናል። ሰው ራሱን የሚወቅስበት ምክንያት ወደ ንሰሐ ለመቅረብ ነው። ንሰሐ ከገባ ደግሞ እግዚአብሔር ሐጢያቱን ይቅር ይለዋል። ራሱን ከማክበር አንጻር ራሱን የማይወቅስ ሰው ግን ሳይሻሻል በሐጢያት ውስጥ በመወቀስ ይኖራል።

ቅዱስ እንጦንስ “እኛ ራሳችን ከወቀስን ዳኛው በእኛ ይደሰታል።” ብሎ የተናገረው ምንኛ እውነት ነው! ከዚህ በመቀጠልም “እኛ ሐጢያቶቻችንን የምናስታውሳቸው ከሆነ እግዚአብሔር በንሰሐ ይረሳልናል፤ እኛ ሐጢያቶቻችንን የምንዘነጋቸው ከሆነ ግን እግዚአብሔር ያስታውሰናል፡፡” በማለት ተናግሯል።

ራስን መውቀስ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ ይረዳናል፡፡ ሰውን “አንተ ትክክል ነው፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቼ የተሳሳትሁት እኔ ነኝ . . . ” በማለት ይቅርታ መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ ቃላት የወንድምህን ቁጣ ሰለሚገቱት ይታረቅሃል፡፡ ይህን ሳታደርግ ራስህን ነጻ ለማውጣት የምትከራከር ከሆነ ግን ጠላት ስህተትህን ለማጋለጥ ማንም አይደርስበትም፡፡

ይህን አስመልክቶ ቅዱስ መቃርስ የተናገረው አባባል ምነኛ ድንቅ ነው! “ወንድሜ ሆይ! ሌሎች ሳይወቅሱህ አንተ ራስህን ውቀስ!”

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
6.3K viewsedited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 20:11:46
ዘበዓለ ደብረ ታቦር ሥርዓተ ማኅሌት

ምንጭ - የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
6.3K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:44:14 የአዕምሮ ጭንቀት ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር ያለው ግንኙነት

ሙሉውን ለማንበብ

https://t.me/BiniGirmachew
https://t.me/BiniGirmachew
6.1K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:59:48 የድንግል ማርያም ልጆች (ሐራዊ) ORTHODOX TEWAHIDO pinned «ልጆቿ እረኛ እንደሌለው መንጋ በየጊዜው ወደ ሌላው ሐይማኖት የሚጎርፉት ለምንድነው? ለምንድነው ሐይማኖታቸውን የሚቀይሩት? እስኪ ስረዓት በዓለው መልኩ እንወያይ እናንተ ችግር ነው የምትሉትን በተጨማሪ ከመፍቴ ሃሳብ ጋር አስተያየት ያስቀምጡው ስለመልካም ሃሳብ እግዚአብሔር ይስጥልኝ አስተያየት ለመስጠት ከፈለጉ ይጫኑ https://t.me/+MwUzq8Wcro82OTg8 …»
17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:56:55 ልጆቿ እረኛ እንደሌለው መንጋ በየጊዜው ወደ ሌላው ሐይማኖት የሚጎርፉት ለምንድነው?

ለምንድነው ሐይማኖታቸውን የሚቀይሩት?

እስኪ ስረዓት በዓለው መልኩ እንወያይ

እናንተ ችግር ነው የምትሉትን በተጨማሪ ከመፍቴ ሃሳብ ጋር አስተያየት ያስቀምጡው

ስለመልካም ሃሳብ እግዚአብሔር ይስጥልኝ


አስተያየት ለመስጠት ከፈለጉ ይጫኑ


https://t.me/+MwUzq8Wcro82OTg8
https://t.me/+MwUzq8Wcro82OTg8
https://t.me/+MwUzq8Wcro82OTg8

ማንም ሰው ምንም አይነት ማስታወቂያ መለጠፍ አይቻልም
6.7K viewsedited  17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ