Get Mystery Box with random crypto!

Yasin Muhammed - Official Channel✔

የቴሌግራም ቻናል አርማ yasinmuhammed1 — Yasin Muhammed - Official Channel✔ Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yasinmuhammed1 — Yasin Muhammed - Official Channel✔
የሰርጥ አድራሻ: @yasinmuhammed1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.99K
የሰርጥ መግለጫ

❶) ሐዲስና ቁርኣናዊ ፁሁፎች፣
❷) ወቅታዊ ኢስላማዊ ጉዳዩች፣
➌) አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች፣
እንዲሁም ስህተት ካያችሁ አርሙኝ።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ inbox
👇
@AbuHiba

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-26 14:10:03
457 viewsYasin Mohammed, 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:21:58 የውሼት ሶላት ሰግጄ እንዲህ ካደረክልኝ የእውነት ብሰግድ ምን ልታደርግልኝ ነው

(ሼር በማድረግ አስተላልፉት!)
አንድ ንጉስ ሁሌ በዙፋኑ ቁጭ ብሎ ብቸኛ ሴት ልጁን ለማን መዳር እንዳለበት ያስባል።

ከእለታ አንድ ቀን በማታ ሰዓት እላፊ ንጉሱ ይነሳና አማካሪውን እና ወታደሮችን አስከትሎ ወደ መስጅድ ያቀናል።
በዛ ሰዐት እንቅልፉን አሸንፎ ለይል የሚሰግድ ወጣት ካለ ልጁን ሊድረው ቃል ይገባል።
በጣም የሚገርመው ደሞ በዛ ሰዐት አንድ ጉደኛ ሌባ መስጅድ ሚዘረፍ ነገር ካለ ብሎ ግቢ ሲገባ በሩን ዝግ ያገኘውና ከላይ መስኮቷን መታ አድርጎ ይገባል።
ልክ ገብቶ በጭለማ ይዞ ሚወጣውን ሲያስስ ድንገት የመስጅዱ በር ተበረገደ።

ጀለስ በቃ እሚሆነውን ሲያጣ እዛው ባለበት ቆሞ ሰላት አረመ /ውዱእ የለ ኒያ የለ. በቃ ከነዚ ሰዎች ቢቻ ለመትረፍ ሰላቱን ጀመረው።

ንጉሱም፦"ሱብሀን አላህ ለሰላት ካለው ጉጉት የተነሳ በሩ ሲዘጋበት ከላይ ገብቷል!!! አጂብ" አለ።
ከዚያም ለወታደሮቹ ሰላቱን እስኪያጠናቅቅ እዛው ጠብቀው ቤተ መንግስት ድረስ እንዲያመጡት ትዕዛዝ ሰጥቶ ንጉሱ ተመለሰ። ጀለስ ግን በቃ የፍራቻ ብዛት ልክ እንዳሰላመተ ወዲያው ሌላ ረክዓ ያርማል።

ይህን ሁኔታውን ያዩ ወታደሮች በግርምት ይመለከቱታል።
ከሰላቱ መርዘም የተነሳ መጠበቅ የሰለቻቸው ወታደሮችም ልጁ የጀመረውን ረክዓ እንዳጠናቀቀ ሊያስቆሙት ይወስኑና ልክ እንዳጠናቀቀ እጁን ይይዙታል። ከዚያም ይዘውት ወደ ቤተ መንግስት ወሰዱት።

ወታደሮችም ለንጉሱ፦ "የዒባዳው ጥንካሬ በጣም ይገርማል የሰላቱ ርዝመት አይወራም"
ብለው ሲነግሩት። ንጉሱም ወደ ሌባው ዞሮ፦"አንተ በዚህ ኢማንህ ለዘመናት እፈልግህ የነበርክ ሰው ነህ ስለዚህ እንዲት ብቸኛ ልጄን እድርሀለሁ ስልጣንም እሰጥሀለሁ" አለው።

ሌባውም የሚሰማውን ነገር ጆሮዎቹን ማመን አቃተው ግራ በመጋባት አቀረቀረ። አንገቱን በሀፍረት ደፋ'ና እንዲህ አለ፦ "ያ! አላህ! ከሰዎቹ ለማምለጥ ዝም ብዬ አስመስዬ በሰገድኩት ሰላት እንዲህ አይነት ከሆነ ስጦታህ አንተን በመፍራት ከልቤ ብስግድ ምን ይሆን ስጦህ "
ብሎ ተውበት በማድረግ ወደ አላህም ተመለሰ!

منقول
||
t.me/YasinMuhammed1
580 viewsYasin Mohammed, edited  17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 06:21:45 «የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው፣ እርሱ በአላህ ጥበቃ ስር ነው»።

ረሱል (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)
662 viewsYasin Mohammed, 03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:40:42 «የነገው እጣፈንታህ በአላህ እጅ ላይ መሆኑን ካወቅክ በእርሱ ላይ ሙሉ እምነትና ተስፋ ይኑርህ ዱዓ እያደረግክ ከርሱ ብቻ መልካም ነገርን ጠብቅ፣ አላህ ተስፋ ያደረጉበትን ባሮቹን የሚያሳፍር አምላክ አይደለም።
:
ዱዓ አድርግ የሆነ ነገር ፈልገህ ዱዓ ታደርግና ያ የፈለከው ነገር ከብዙ አመታትና ከረሳሀው ቡሀላ እውን ይሆንልሀል አንተ ብትረሳውም አላህ ግን አይረሳም ብቻ ዱዓ አድርግ እሱ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቆ እውን ያደርግልሃል»።
592 viewsYasin Mohammed, edited  18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:23:14 ዱኒያ
▬ ▬ ▬
«ዱኒያ ማለት ፈተና የበዛበት የውሸት አለም ነች፣ በአጭሩ ይች ዱንያ ማለት ወደ አኼራ የምንሸጋገርባት አጭር ድልድይ ነች»!!
||
አንድ ኡስታዝ ዱኒያን ሲገልፅ የማረሳውን አገላለፅ ላካፍላችሁ እንዲህ አሉ:-

ዱንያን ሲመስላት «ዱኒያ ማለት አደባባይ ላይ የቆመች ቆንጆ ሴት ነች! አንዱ መጥቶ በቁንጅናዋ ተማርኮ "ላግባሽ ይላታል" እርሷም እሺ! ትለዋለች። ቆንጆይቱ የቆመችው አደባባይ ላይ ነው ሁሉም ያያታል! በመቀጠልም ሌላኛው መጣ፤ እርሱም "ላግባሽ" ይላታል። እርሷም እሺ! አግባኝ የሚል መልስ ለሁሉቱም ትሰጣለች። በዚህ ግዜ ሁለቱ ሰዎች አደባባይ ላይ ባለችው ቆንጆ ይጣላሉ።
*
ይህንንም ተከትሎ ወደ ፍርድ ቤት ያቀናሉ። ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዳኛውም በምን ተጣልታችሁ ነው እዚህ የመጣችሁት ይላቸዋል። መጀመሪያ ላይ ላግባሽ ያላት እንዲህ አለ "እኔን እንደምታገባኝ ከእኔ ጋር ቃል ገብታ ነገር ግን ይኸኛው በእኔ ላይ ጣልቃ ገብቶብኝ ነው የተጣላነው" የሚል ክሱን አቀረበ። ዳኛውም እስኪ አንድ ግዜ ሁለታችሁም ውጭ ቆዩ እርሷንም በምን እንደተጣላችሁ ልጠይቃት ይላቸዋል።
እነርሱም ተያይዘው ወጡ።
*
ዳኛው በቁንጅናዋ ተማርኮ፤ ቆንጆዋን "ለምን ከዚህ ሁሉ እኔ አላገባሽም" ይላታል። እርሷም እሺ! ትለዋለች።

በዚህም ምክንያት ሊካሰሱ የመጡትና ዳኛው በልጅቱ ይጣላሉ።
ነገር ግን በዚህ መሀል እርሷ እንዲህ አለች:- "ከዚህ ሁሉ ሶስታችሁንም የሚያስታርቅ ሀሳብ አለኝ ከተስማማችሁ?" ትላቸዋለች።
*
" እኔ ወደፊት እሮጣለሁ እናንተ ከሗላ ተከተሉኝ፤ እኔን መጀመሪያ የያዘኝ ያገባኛል ነገር ግን በዚህም ውስጥ አንድ መስፈርት አለኝ፤ እርሱም ስትሮጡ እኔን ብቻ ተመልከቱ ወደ ጎን መዞር፣ እርስ በእርስ መተያየት አይቻልም ይህ ነው ሀሳቤ" ትላቸዋለች። በዚህ ሀሳቧም ይስማማሉ።
*
ሩጫውም ተጀመረ እርሷ ላይ ለመድረስ ሲሮጡ፤ ዳኛው ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ወድቆ ይሞታል፣ ሁለቱ አላዩትም! በመቀጠልም አንድኛው ይከተላል፣ ሌላኛውም ይቀጥላል።

በመጨረሻም ሶስቱም አግቢኝ ባዮች ቆንጆይቱን ሳይደርሱባት ሞቱ።

ይህቺ ናት ዱኒያ እኛ ዛሬ አንዱን ወንድማችንን ወደ አኼራ ሽኝተን በዱኒያ ቁንጅና ተማርከን መሮጣችንን ቀጥለናል፤ ከጎናችን ዱኒያን ትተዋት የሄዱትን አንመለከትም ነገ ከነገ ወዲያ እኔ፣ አንተ፣ አንቺም ተረኞች ነን።
*
በመጨረሻም ሽይኹ ይህንን ጨመሩ «ዱኒያ ማለት አደባባይ ላይ የቆመች የአሮጊት ቆንጆም ናት» አሉ። አባባሉን ሲያብራሩም እንዲህ ይላሉ:-
ዱኒያ አደባባይ ላይ የቆመች ናት ሲባል:- ዱኒያን ሁሉም ያያታል፣ ለመያዝም ይፈልጋታል፣
የአሮጊት ቆንጆ ነች ሲባል ደግሞ:- ዱኒያ ያኔ የእኛን ቅድመ አያቶች፣ አባቶች አድክማ ሳይዟት ትተዎት የሄዱ፣ እንዲሁም እኛም የምንይዛት እየመሰለንና ሁሌም ቆንጆና፣ አዲስ መስላ እየታየችን እርሷን ለመያዝ እንደክማለን ለዚያም ነው ዱኒያ የአሮጊት ቆንጆ ናት ያልኳችሁ» ብለው ዱኒያን ገለፁ።

ዱኒያ ላይ ዛሬ ተደስተህ፣ ነገ ታለቅሳለህ ዛሬ አግኝተህ፣ ነገ ታጣለህ ፈተናውን ሁሉ አልፌ ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ ብለህ ኡፎይ ስትልና የእረፍት ኑሮ መኖር ስትጀምር፤ ድንገት ሳታስበው የሰበሰብከው ሁሉ ይበተናል።
ለእኛ ለሙስሊሞች ዱኒያ እዚህ ምድር ምንም አይደለች፣ እንደውም እስር ቤት ናት።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
«ዱኒያ ለሙዕሚኖች እስር ቤት ናት ለካፊሮች ደግሞ ጀነት ነች»።
ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ:
«ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﺳﺠﻦ ﺍﻟﻤﺆﻣﻦ ﻭﺟﻨﺔ ﺍﻟﻜﺎﻓﺮ.»
ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ
አምላካችን አላህም እወቁ ዱንያ የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም ይለናል:-
اعْلَمُوا أَنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِي الْأَمْوَالِ وَالْأَوْلَادِ ۖ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ الْكُفَّارَ نَبَاتُهُ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَاهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَامًا ۖ وَفِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٌ ۚ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ۞
ቅርቢቱ ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቁ፡፡ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ብጤ ናት፣ በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አልለ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
ሱረቱል-ሐዲድ (20)

ጭንቀትህ ለዱኒያ ሳይሆን ለአኼራ መሆን ሲጀምር የውስጥ ሠላምና መረጋጋት ታገኛለህ።
*
ጀሊሉ እንኳን ርካሿን ዱኒያን ውድና ውብ የሆነቺዋን ፊርደውሰል አዕላን ይሰጣል!
ብዙ አትጨነቁ ዱኒያ ለተጨነቀላትና ለጓጓላት አትሆንም።
ረሱላችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሀዲሳቸው «ጭንቀቱ ዱኒያ የሆነች፣ አላህ (ሱብሃንሁ ወተዓላ) ድህነትን በዓይኖቹ መሀከል ያደርግበታል፣ ነገሩን ሁሉ ይበትንበታል፣ ከዱኒያም የተወሰነለት እንጂ ወደሱ አይመጣም» ብለዋልና!

ራስን ሳያስጨንቁና ድንበር ያለፈ ጉጉት ሳይኖር የተከተበልንን በሀላሉ መፈለግ ነው።
እና ለዱኒያ ብዙ መጨነቅ አያስፈልግም
ለዱኒያ ኑሮ፣ ጣጣ፣ የምንጨነቅ ሳይሆን ለአኬራችን የምንጨነቅ አላህ ያድርገን።

ለዛሬ ይህችን ካልኩ ይበቃኛል በሉ ይመቻችሁ!
ወሰላሙዓለይኩም!

መልክቱን ለሌሎችም እንዲደርስ ሁላችሁም ሼር አድርጉት
--------------------
ነሀሴ 18, 2014 E.C
ሙሐረም 26,1443 H.C
August 24, 2022 G.C
||
t.me/YasinMuhammed1
615 viewsYasin Mohammed, edited  17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:24:29 አንዲት አባቷ የመስጅድ ኢማም የሆነች ልጅ ነበረች። ልጁ በቁንጅናዋ ተማርኮ ዚና እንዲሰሩ ይጠይቃታል፤ ቆንጆይቱም "እሺ ነገር ግን ሁለት መስፈርቶች አሉኝ እነርሱን ካሟላህ " ትለዋለች። መስፈርቷንም በዚህ መልኩ ትነግረዋለች።
1ኛ) ትንሽ ጊዜ ስጠኝ።
2ኛ) እንደምታቀው አባቴ የመስጅድ ኢማም ነው እና ስጠኝ እስካልኩህ ግዜ ድረስ መስጅድ እየሄድክ በጀመዐ ሶላትህን ስገድ" ትለዋለች።
:
ልጁም እሺ ብሎ ተስማማ።
ቃሉንና መስፈርቱን ለመጠበቅ ሲል መስጅድ መሄድን አዘወተረ።

በመጨረሻም የሰጣት ግዜም አለቀ።
"ያንን የሰሳጠሁህን መስፈርት ተገበርከው ቃልህንስ በትክክል እያከበርክ ነው" የሚል ጥያቄ አነሳችለት።
እርሱም "አወ! እየተገበርኩ ነው ነገር ግን ቃል ያስገባሁሽን ነገር አላህ ይቅር ይበለኝ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል። መስጅድ በምመላለስበት ሰዓት ወደ አላህ ተመልሻለሁ" አላት።

አርሷም "ማሻ አላህ! እኔም እሺ ያልኩህ ዝሙት ለመስራት ሳይሆን "ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች" በሚለው በዚህ በአላህ ቃል እርግጠኝነት ተሞልቼ ነው።

اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ ۖ إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ
ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡
ሱረቱል አንከቡት (45)
*
ጭብጥ
ሶላትን በትክክል ከሰገድነው ከወንጀል ይከለክለናል።
554 viewsYasin Mohammed, edited  16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 13:28:54 የሶላት ሰአት ቢያልፍብህ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
እንቅልፍ ተኝተህ ወይንም ረስተህ የሶላት ሰአት ቢያልፍብህ ምንድነው ማድረግ ያለብህ
||
አንዳንዶቻችን በእንቅልፍ ምክኒያት ወይንም በሆነ ምክኒያት የሶላት መስገጃ ሰአት ያልፍብንና ልክ እንዳልሰገድን ስናስታውስ "አይ አሁን ሰአቱ ካለፈ ቡሃላ ብሰግደው ምን ያደርጋል" ብለን በዛው ሳንሰግድ እንተዋዋለን! ይህ ስህተት ነው።
:
እንቅልፍ ተኝተህ ልክ ስትነቃ የሶላት ሰአት እንዳለፈብህ ካወቅክ ቶሎ ወዲያው ስገድ የሶላቱ ሰአት ስላለፈ አልሰግድም አትበል ፡
:
ልክ እንደዚያው በሆነ ስራ ወይንም በሌላ ምክኒያት የሶላቱን ሰአት ረስተኸው ቢያልፍብህና ከዛ እንዳልሰገድክ ብታስታውስ አይ ሰአቱ ስላለፈብኝ አልሰግድም አትበል እንዳልሰገድክ ባስታወስክበት ሰአት ቶሎ ወዲያው ስገድ።

ይሄን አስመልክቶ ነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:-
"እንቅልፍ ተኝቶ ወይም ረስቶ ሶላት ያለፈው ሰው ባስታወሰው ሰዓት ይስገደው"።
ምንጭ:- ሙስሊም (684)
558 viewsYasin Mohammed, edited  10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:01:19 «ከእናንተ መካከል በነፍሱ፣ በቤቱና በቤተሰቡ ስጋት ሳይኖርበት ሰላም የሆነ፤ አካሉ ከህመም ነፃ የሆነና የዕለት ጉርሻውን ያገኘ ዱንያ በተሟላ መልኩ ለርሱ ተሰብስባለች»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

ምንጭ:- ቲርሚዚ (2346)
558 viewsYasin Mohammed, 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 11:31:28 አስማእ ቢንት አቢበክር
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አስማእ ቢንት አቢበክር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) የታላቁ ሶሐባህ የዙበይር ኢብኑልዐዋም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ሚስት ነበረች፡፡ አባቷ ደግሞ ታላቁ ሲዲቅ አቡበክር ረዲየላሁ ዐንሁ ናቸው፡፡
*
ከእርሷ በተላለፈው እንዲህ ትላለች፡-

ዙበይር ሲያገባኝ ጊዜ ምድር ላይ ውሃ ከሚቀዳባት ግመልና ከአንድ ፈረስ ውጭ ምንም ገንዘብ አልነበረውም፡፡ ፈረሱን እመግባለሁ፤ ውሃ እቀዳለሁ፤ የሚታለብበትን ከቆዳ የሚዘጋጅ አንኮላ እሰፋለሁ፤ እንዲሁም አቦካለሁ፡፡ ማብሰሉን ግን በቅጡ አልችልበትም ነበር፡፡ እናም የአንሷር ልጃ-ገረዶች ነበሩ የሚያበስሉልኝ፡፡ የእውነት ሴቶች ነበሩ፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለዙበይር ቆርጠው ከሰጡት መሬት ተምር በእራሴ ተሸክሜ አመጣ ነበር፡፡ ሶስት ፈርሰኽ ያክል ከኔ ይርቅ ነበር፡፡
*
ታዲያ አንድ ቀን በእራሴ ተሸክሜ እየመጣሁ ሳለ የአላህ መልእክተኛን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አገኘኋቸው፡፡ ከእርሳቸው ጋር ከአንሷር የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ ጠሩኝና ግመሉን እያሳረፉት “ኢኽ ኢኽ” አሉ፡፡ እኔን ከኋላቸው ግመሉ ላይ ሊያስቀምጡኝ ግመሉን እያስተኙ መሆኑ ነው፡፡ ግን ከወንዶች ጋር ለመሄድ አፈርኩኝ፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ዙበይርንና ቅናቱን አስታወስኩኝ፡፡ እጅግ ቀናተኛ ሰው ነበር፡፡
የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳፈርኩኝ ስላወቁ ጥለውኝ ሄዱ፡፡
:
ከዚያም ዙበይር ዘንድ መጣሁና “በእራሴ ተምር ተሸክሜ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሶሐቦቻቸው ጋር ሆነው አግኝተውኝ ነበር፡፡ ግመላቸው ላይ ሊያስቀምጡኝ ግመሉን አስተኝተውልኝ ነበር፡፡ ግን አፈርኳቸው፤ ቅናትህንም አሰብኩኝና ተውኩት” አልኩት፡፡

ዙበይር ታዲያ ምን አለ? “ወላሂ! ተምር መሸከምሽ ከእርሳቸው ጋር ግመል ላይ ከመቀመጥሽ እኔ ዘንድ የከበደ ነው!” አለ፡፡
*
ቀጥላም እንዲህ አለች:- ከዚህ በኋላ (አባቴ) አቡበክር የፈረሱን የምትስብልኝና የምታወጣኝ አንዲት አገልጋይ ላከልኝ፡፡ ልክ ነፃ ያወጣኝ ያክል ነበር የተሰማኝ!”
ቡኻሪና ሙስሊም

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ብዙ ቁም-ነገሮችን መቅሰም እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ያክል

1) አስማእ ምን ያክል ለባሏ ታዛዥ እንደነበረች፡፡
2)  የአስማእን ሃላፊነት ብዛት፣
3) አስማእ የአንሷር ሴቶችን ማድነቋ ምን ያክል ከምቀኝነት የራቀች እንደነበረች ያስረዳል፡፡ ዛሬ ሌላው ቀርቶ ተመሳሳይ አቋም ባላቸው ሰዎች መካከል እንኳን የሚታየው ምቀኝነት እራሱ እጅግ አስቀያሚ ነው፡፡
4) የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሶሐቦቻቸው ያላቸው መቆርቆርና ትህትና፡፡
5) የአስማእን አይን አፋርነት
6) የአስማእን በሌለበት እንኳን የባሏን ስሜት መጠበቋ
7) የዙበይርን ቀናተኝነት፡፡ ይስተዋል! ቅጥ ያጣ እንዳይሆን እንጂ ሰው በሚስቱ ላይ መቅናቱ አግባብ ነው፡፡

ማንም እንዳይደርስባት፣ ማንም እንዳያይበት፣ ማንም… ማለቱ እርሷን ከመጥላትም ከማሰቃየትም የመጣ አይደለም፡፡ የእኔ ከማለት የመነጨ እንጂ!
659 viewsYasin Mohammed, edited  08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:49:18 በውስጥ ከደረሱኝ መልክቶች መካከል አንዱና ብዙው ነው ለወንድማችን ሼር አድርጉለት
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድ ሙስሊም  ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ  ﷺ ነግረውናል ።

የሱና ወንድማችን አብዱ ሰይድ ይባላል። በልጅነቱ በሆነ አጋጣሚ በተፈጠረ አደጋ አንድ አይኑን አጥቶ ሲኖር የነበረና በችግርና በመከራ ውስጥም ቢሆን አግብቶ ሁለት ልጆችን ወልዷል።አላህ አግርቶሎት በቀረችው በአንድ አይኑ #ቁረአንም_ሀፍዟል  እስካሁን በቆየበትም ጊዜ ለሱና ባለው ጉጉትና ፍላጎት የተነሳ ከቤተሰቦቹ ተገሎና ርቆ ምንም እገዛ እንኳን የማያደርጉለትና ዘወር ብለው የማያዩት ሲሆን ስራም ትንሽም ቢሆን የቀን ስራ እየሰራ ቤተሰቦችን ያስተዳድር ነበር ። አሁን ግን መስጊድ ቁጭ ብሎ ቁረአን ሲቀራ ነው የሚውለው ።

ሆኖም አሁን ደግሞ የአሏህ ውሳኔ ሆነና በሚኖርበት ግቢ በተፈጠረ የእሳት አደጋ ምክንያት እሳቱን ለመከላከል ጥረት በሚያደርግበት ወቅት የኤሌክትሪክ መብራት ይዞት ጭንቅላቱን ክፉኛ የተመታ ሲሆን ይህ አደጋም የቀረችው አንድኛው አይኑ ላይም ተፅእኖ በመፍጠሩ ከፍተኛ ህመም ሲፈጥርበት ዶክተሮችም በፍጥነት አድስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመሄድ ህክምና ካልወሰድክ የአይንህ ነርቭ በመነካቱ ሁለተኛውንም አይንህን ልታጣው ትችላለህ ብለውታል።

ስለዚህ ይህ የሱና ወንድማችን የቀረችውን አንድ አይኑን ለማትረፍ  ህክምናውን ለመጀመር በትንሹ 70,000ሺ ብር( ሰባ ሺ ብር) እንደሚያስፈልገው በዶክተሮች ተነግሮታል ።ይሄንን ብር ደግሞ አይደለም በአንድ ጊዜ በአንድ አመትም ማገኘት ስለማይችል የኛ የወንድምና የእህቶቹ እገዛና እርዳታ ያስፈልገዋል

ያ አሏህ... ተመልኩቱ አንዷንም የተረፈችዋንም አይኑን ሊያጣት ነው ሲደመር ችግር ፣ ድህነት ፣ ልጆች ማሳደግ ፣ ስራ ማጣት ፣ ከቤተሰብ መገለል እያሰቃየው ነው።

እኛ ደግሞ ሁለቱም አይኖች አሉን። #አልሀምዱሊላህ ፣ አሏህም በቁረአኑ እንዲህ ብሎናል  (أَلَمْ نَجْعَل لَّهُۥ عَيْنَيْنِ) "ለእርሱ(ለሰው ልጅ) ሁለት አይኖችን አላደረግንለትምን?"( ሱረቱል በለድ ፣ 8) ይላል። ታዲያ አሏህ እንዲህ አይነት ፀጋ ሲውልልን ምስጋናችን ከምንገልፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ እንዲህ በአይናቸው የተፈተኑ ሰዎችን በማገዝና በመርዳት አሏህ የኛንም አይኖች እንዲጠብቅልን ዱዓ በማድረግ ነው።

ውድ ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች ፣  ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪውን በመሸፈን ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለድኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን  የአቅማቹህን እንድታበረክቱ  ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች  የእርዳታ ጥሪያችንን   እናስተላልፋለን።

በገንዘብ መርዳት ባትችሉ share በማድረግ ተባበሩት።

ወንድማችንን ለመርዳት የተቋቋመ  የባንክ አካውንት ቁጥር :- የኢትዮ ንግድ ባንክ
       #1000034096008    
#የአካውንቱ ስም :- አብዱ ሰይድ መሀመድ

ለበለጠ መረጃ የወንድማችን ስልክ
ስልክ:     #0914324157

"በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ  ﷺ ነግረውናል ።

ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች ግሩፖች ሸር እንዲታደርጉልን ።
613 viewsYasin Mohammed, edited  04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ