Get Mystery Box with random crypto!

Yasin Muhammed - Official Channel✔

የቴሌግራም ቻናል አርማ yasinmuhammed1 — Yasin Muhammed - Official Channel✔ Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yasinmuhammed1 — Yasin Muhammed - Official Channel✔
የሰርጥ አድራሻ: @yasinmuhammed1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.99K
የሰርጥ መግለጫ

❶) ሐዲስና ቁርኣናዊ ፁሁፎች፣
❷) ወቅታዊ ኢስላማዊ ጉዳዩች፣
➌) አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች፣
እንዲሁም ስህተት ካያችሁ አርሙኝ።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ inbox
👇
@AbuHiba

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-28 13:35:13
515 viewsYasin Mohammed, 10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:09:56 ቅደም ተከተላቸው ይህን ይመስላል

ሙስሊም የቡኻሪ ተማሪ ነው፣

ቡኻሪ የኢማሙ አህመድ ተማሪ ነው፣

ኢማሙ አህመድ የሻፊዒ ተማሪ ነው፣

ሻፊዒ የማሊክ ተማሪ ነው፣

ማሊክ የናፊዕ ተማሪ ነው፣

ናፊዕ የአዕረጅ ተማሪ ነው፣

አዕረጅ የአቡ ሁረይራ ተማሪ ነው፣

አቡ ሁረይራ የረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተማሪ ነው።

በሉ እየሸመደዳችሁ፣ የሆነ ቀን እጠይቃችኋለሁ።
||
t.me/YasinMuhammed1
175 viewsYasin Mohammed, edited  18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:04:48 ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (ረሂመሁላህ) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦
"ያ አባ ኢስሐቅ! አላህ ለምኑኝ እቀበላችሁለሁ አለ ነገር ግን ዱዓ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣን" የሚል ጥያቄ ጠየቋቸው...

እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "ቀልባችሁ በአስር ነገሮች ሞታለች" አሏቸው።
እነሱም፦ "ምን ምንድን ናቸው?" የሚል ጥያቄ አነሱ። እሳቸውም፦
❶ኛ) አላህን አውቃቹት ሐቁን አልተወጣችሁም።
➋ኛ) ቁርኣንን አነበባችሁት፣ አልሰራችበትም።
➌ኛ) ነቢዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፣ ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።
➍ኛ) የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።
➎ኛ) ሸይጣን ጠላታችን ነው ብላችሁ ከሱ ጋር ገጠማቹ።
➏ኛ) ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ ሚሆን ስራ አልሰራችሁም።
➐ኛ) የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።
➑ኛ) ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።
➒ኛ) ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፣ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።
➓ኛ) ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።
ታዲያ እንዴት ይቀበላችሁ
ﻓﻜﻴﻒ ﻳﺴﺘﺠﺎﺏ ﻟﻜم؟
ምንጭ:- ጃሚዑል በያን አልዒልሚ ወፈድሊሂ (2/12)

አላህ ዱዓ አድርገው ዱዓቸውን ከሚቀበላቸው ባሮቹ ያድርገን
181 viewsYasin Mohammed, edited  18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:51:26 ለነገሩ—ምንዳ ከፋይ አላህ ነው እውቅና ሠጡ አልሠጡ
297 viewsYasin Mohammed, 12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:11:45 فليست هذه الدنيا بشيء ... تسوئك حقبة وتسر وقتا

وغايتها إذا فكرت فيها ... كفيئك أو كحلمك إن حلمتا

سجنت بها وأنت لها محب... فكيف تحب ما فيه سجنتا



ምንም አየደለችም የዱንያዋ ህይወት
ዘመን አስደስታህ ታዝናለህ ሌላ ወቅት

ድካዋ'ኮ የሧ ስታስተነትናት
ወይ እንዳንተ ጥላ ወይ እንደ ህልምህ ናት

ታሥረሃል በውስጧ የሷ ወዳጅ ሆነህ
የታሰርክበትን እንዴት ትወዳለህ?!


ከታኢየቱል ኢልቢሪ የተወሰደ

ሙሐመድሲራጅ
299 viewsYasin Mohammed, 12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:45:20
ትዝብተ—ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
(ሁሌም ከሀይማኖት ጎጠኝነት የማይፀዱ!)
እንደሚታወቀው ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ አስመርቋል።
በምረቃ ስርኣቱም ላይ ዩኒቨርሲቲው ለቄስ አቡነ ኤርሚያስ እና ለአትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬትንም ሰጥቷል።
||
በነገራችን ላይ እነዚህ ቄስ—አቡነ ኤርሚያስ የወልድያ ከተማ ባለውለታ የሀይማኖት አባት ናቸው። የህወሃት ኃይሎች ከህዝቡ ጋር እሰጣ ገባ ገብተው ለመጨፍጨፍ ሲንቀሳቀሱ የማግባባት ሥራ ሰርተው ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ዶክትሬቱም ሲያንስባቸው እንጅ አይበዛባቸውም። ይገባቸዋል።

ነገር ግን አብረዋቸው ሲሰሩ የነበሩት ሐጂ ያሲን ኢድሪስ፤ የሙስሊሙ መሪ ለወልድያ ህዝብ እኩል ሲሰሩ የነበሩት ሙስሊም ክሪስቲያን ሳይሉ አብረው የሰሩት ለምን ለእነርሱስ አልተሰጣቸውም

አንዳንድ ግዜ የሚገርመዉ ነገር ሙስሊምን ለምን እደምትጠሉት ሳስበው ይደንቃል
ይህ ክልል ሁሌም ታጥቦ አይጠሬ ናቹህ።
እውነታውን ግን ታሪክ መዝግቦ አስቀምጦላችኋል።
:
ሁሌም ከሀይማኖት ጎጠኝነት የማይፀዱ፣ ታጥበው የማይጠሩ፤ ሁሉን ነገር ራሳቸው ከቆሙበት ሃይማኖት ብቻ እየሰፈሩ የቆሰለ ትርክት ለመፍጠር የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም።

እንደዚያ ባልሆነማ ኖሮ በደግነት መነፀር ከታሰበ በሀጅ ያሲንና በአባ ኤርሚያስ መካከል ልዩነት ባልተፈጠረ ነበር።
የሚሻለው ሁሉንም በልኩ መስፈር ነው።
:
የምንግዜም ኢስላሞፎቢያቸው ስለሚያናድድ እንጅ በመሰረቱ "ስለበጎ ስራ ምንዳ ከላይ ሲሆን ነው ጥሩው፤ የምድር ሰጥቶ መች ያጠግብና"
||
t.me/YasinMuhammed1
315 viewsYasin Mohammed, edited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:34:14 ምራቁን የዋጠ፣ አስተዋይ፣ ኮስተር ማለት ባለበት ጊዜና ቦታ ኮስታራ ብልህ፣ አስተሳሰበ—ምጡቅ፣ ረጋ ያለ ሰው ስወድ። እህእ!
428 viewsYasin Mohammed, edited  16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:40:16 ምክር:- አንድ
1) ለእዩልኝ አትስራ
ለእዩልኝ መስራት ትልቅ በሽታ ነው።
ይልቅ ስራህን ሁሉ ለአላህ ብለህ ስራ፣ እርሱ በእውቀቱ ሁልጊዜም ካንተ ጋር መሆኑን አት ዘንጋ።

ለእዩልኝ ሰሪዎች ሰላምን አያገኙም።

አንዳንዱ ወንድ ታክሲ ላይ ሲሳፈር ከአጠገቡ ሙስሊም ሴት ካዬና ደስ ካለችው፣ በቃ የሚሰራው ይጠፋበታል።
ሙስሊምነቱን እንዳላወቀች ካሰበ፣
ስልኩን ያወጣና፣ ወደ ማይፈልግበት ቦታ ደውሎ፣"ሄሎ! አስሰላሙ ዓለይኩም ወራሕመቱላህ ወበረካቱህ" ይላል።
ከዚያም የሆነ ወሬ ያወራና ስልኩን ዘግቶ ይቁነጠነጣል።
*
እርሷም ሙስሊም ወንድ ካየች አለባበሷን ለማስተካከል ነቃ ነቃ ትላለች።
በርግጥ ብዙ ጊዜ ሙስሊም ሴቶች ሙስሊምነታቸው በአለባበሳቸው ስለሚያስታውቅ፣ እርሷ እንደርሱ ስልክ መደወል ላይጠበቅባት ይችላል።
ኧረ! ስንት ጉድ አለ መሰለህ! ህእ!
*
አንዳንዱ ደግሞ ከአንተ ጋር መተዋወቅ ከፈለገ፣ በቃ ከአጠገብህ ከጓደኛው ጋር ወይም ከሌላ ሰው ጋር ይሆንና ድምፁን ከፍ አድርጎ አንተ እንድት ሰማው፣ አንተን ያማልለዋል፣ "ይሄ ልጅማ ጎበዝ ነው!" 'በቃ መተዋወቅ አለብኝ!' ብለህ እንድትል የተለያዩ ነገሮችን፣ ያለውን የሌለውን ይቀውጠዋል።

ከፈለገ በዓረብኛ አሊያም በእንግሊዝኛ ለማውራት ይፍጨረጨራል።
አንተ "ይህ ሰው አዋቂ ነው!" እንድትለው ነህው፣ ሶርፍ፣ ተፍሲሩን፣ ፊቅሁን፣ የሰፈር ህይወቱንና ተሞክሮውን ሁሉ ለማስተዋወቅ የህይዎት ዳገቱን ሁሉ ይቧጭራል።

የሚገርማችሁ እኔ ጥሎብኝ እንዲህ አይነት ሰው ሲያጋጥመኝ፣ ቅንጣትም ያክል ቦታ አልሰጠው፣ እንዲያውም እንዴት እንደምዘጋው።

ከሴቶች የምወድላችሁ ባህሪ ደግሞ ብዙ ግዜ መኪና ታክሲ ላይ ስትወጡ "ቢስሚላህ" ብላችሁ የምቀመጡት እና እኛን የረሳነውን የምታስታውሱንን ነገር እወድላችኋለሁ ቀጥሉበት።
464 viewsYasin Mohammed, edited  15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:51:11
439 viewsYasin Mohammed, 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:40:16 ጦርነት ውድ ነው! ዋጋውም ከባድ ነው፤ ብዙሐኑ ሲከስር ጥቂቶች ያተርፉበታል
433 viewsYasin Mohammed, 14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ