Get Mystery Box with random crypto!

አፈምዑዝ🗣

የቴሌግራም ቻናል አርማ yabsramikiyas — አፈምዑዝ🗣
የቴሌግራም ቻናል አርማ yabsramikiyas — አፈምዑዝ🗣
የሰርጥ አድራሻ: @yabsramikiyas
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ትምህርታዊ፣ ሐገራዊ ፣ ፍልስፍናዊ ሃሳቦችን እናነሳለን።
ለአስተያየታችሁ T.me/Medlotetsedk

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-02 20:16:35 የበረሃው ሰይፍ፡ አክራሪ እስልምና ምንጭና ዥረቱ

በዓለም እና በኢትዮጵያ

[በኑረዲን ኢብን አል-መሲህ]

ታሪክን ማጥናት ብልህነት ነውና እችን መጽሐፍ ታነቧት ዘንድ ጋበዝኳችሁ
24 viewsYabsra, 17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 16:50:35 አንድ ፕሮፌሰር ነው አሉ።  ራሱን ሊያዝናና ወድዶ በአንዲት ታንኳ ጉዞውን ይጀምራል። ታንኳዋ ላይ ኾኖ ሰማዩን ይቃኛል። ባሕሩን ይቃኛል። ከዚያም ዐዋቂነቱን ሊያሳይ ሽቶ ቀዛፊው ላይ አንዳንድ ጥያቄዎችን ጣል ጣል ማድረግ ይጀምራል። “አስትሮኖሚ ታውቃለኽ?” የመጀመሪያ ጥያቄው ነበር። ቀዛፊው መልሶ “ምን አሉኝ ጌታዬ?” ሲል ይመልሳል። “አስትሮኖሚ ታውቃለኽ ወይ?” ሲል ደግሞ ይጠይቀዋል። “ምንድን ነው ደግሞ እርሱ? ዛሬ ገና ከእርሶ መስማቴ ነው። ምንም የማውቀው ነገር የለም” ሲል ቀዛፊው ይመልሳል። “ይኽን ካላወቅኽ የሕይወትኽን አንድ አራተኛ አጥተኻል!” ሲል ፕሮፌሰሩ ሸንቆጥ ያደርገዋል። ሌላ ጥያቄ ይ‘ነሣል ፦ “’ቦታኒ’ ወይም ‘ዞሎጂ’ ታውቃለኽ?” ቀዛፊው በልቡ “ዛሬ ምንድን ነው የሚለኝ ይኼ ሰውዬ?” ሲል ያጉረመርማል። ቀጠል አድርጎም “አላውቅም ጌታዬ!” ሲል መልስ ይሰጣል።

ከደቂቃዎች በኋላ ከየት መጣ የማይሉት ማዕበል ተነሥቶ ታንኳዋን ወዲያና ወዲህ ያማታት ጀመር። ቀዛፊው ጉዟቸውን የተቃና አድርጎ በሠላም ይደርሱ ዘንድ የሚቻለውን እየሞከረ ነው። ነገር ግን አልኾነም። ያለው ብቸኛ አማራጭ ዋኝቶ መትረፍ እንደኾነ ውስጡን እያሳመነው ነው። ታዲያ ዘወር ብሎ ፕሮፌሰሩን “ጌታዬ! ዋና ያውቃሉ?” ሲል ይጠይቃቸዋል። እርሳቸውም “ኧረ አላውቅም!” ሲሉ ይመልሳሉ። “ጌታዬ! ሙሉ ሕይዎትዎን አጥተዋል!” ሲል መለሰላቸው ይባላል።

ከቅዱስ ቍርባን ሕይወት መራቅም እንዲኹ ሙሉ ሕይወትን ማጣት ነው። ጤና ባይኖርኽ ፣ ሠላም ባይኖርኽ ፣ ዕውቀት ባይኖርኽ ፣. . . የሕይወትኽን የኾነ ክፍል አጥተኻል ሊባል ይችላል። ከቅዱስ ቍርባን ከራቅኽ ግን እግዚአብሔርን አጥተኻል። ይኽ ማለት ደግሞ ሙሉ ሕይወትኽን አጥተኻል ማለት ነው። ስለዚኽ ፥ ይኽ እንዳይኾን ዘወትር በቅዱስ ቍርባን ሕይወት መመላለስ ይገባል! ይቆየን!
39 viewsYabsra, 13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 06:05:31 በለቅሶ የተዋጠው መንደር...

ወሩ ወርሓ ሰኔ ቀኑ የወሩ 17ኛ ቀን ነው ድንገት ከአንድ መንደር ተገኘሁ መንደሩ የመነኮሳት መንደር ነው...ብዙ መነኮሳት አንድ አረጋዊ መነኮስ ከበው ያለቅሳሉ እሱም በጣም እያለቀሰ ነው የነገሩን ሥርና ጫፍ ለማወቅ የሚሻ ጉጉቴ እግሮቼን ከስፍራው ቸከላቸውና ቆሜ ቀረሁ፡፡
❖ ❖ ❖

አለባበሱ እንደነገሩ የሆነ የሰውን ዐይን የማይስብ ድሪቶ ለባሽ ምስኪን ሰው በባዶ እግሩ እየተራመደ ወደሚያለቅሱት መነኮሳት ተጠጋ፤ ያ እያለቀሰ የነበረ አረጋዊ መነኮስ ይህንን ምስኪን መሳይ ሰው ሽቅብ ተመለከተውና ይቀርበው ዘንድ ምልክት ሰጠው ያወቀውም ይመስላል፡፡
❖ ❖ ❖

ምስኪኑና ባለ ባዶ እግሩ ሰው በቀስታ ወደ አረጋዊው መነኮስ ጎንበስ ብሎ "አባቴ ሆይ ምን ሆነህ ነው የምታለቅ ሰው? መነኮሳቱስ ስለምን ያለቅሳሉ?" ሲል ጠየቀው፡፡

እኔ ሁለት ነገር አልለይ ብለውኛል አንደኛው የዚህ የምስኪኑና የባለ ባዶ እግሩ ሰው ማንነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የአረጋዊው መነኮስ የለቅሶ ጉዳይ ናቸው፡፡ ቀስ እያልኩ ጉዳዩን ለማጣራት መጠጋት ጀመርኩ፡፡
❖ ❖ ❖

አረጋዊው ሰው ከበው የሚያለቅሱለትን መነኮሳት በዐይን ጥቅሻ ትተውት እንዲሄዱ አዘዛቸውና መነኮሳቱ በቅጽበት ተበተኑ፡፡
ጠጋ ብዬ ሳይ የአረጋዊው መነኮስ ማንነት አሁን መጣልኝ የማውቀው የአንድ ትልቅ ገዳም አስተዳዳሪ ናቸው የከበቧቸው መነኮሳትም የገዳሙ መናንያን ሲሆኑ የሚያለቅሱትም አስተዳዳሪያቸው ህመም ጠንቶባቸው በሞት ጣር ላይ በመሆናቸው ምክንያት ነበር፡፡
❖ ❖ ❖

አረጋዊው መነኮሳቱ መሄዳቸውን ዐይቶ ለዚያ ምስኪን ባለ ባዶ እግር ድሪቶ ለባሽ እንዲህ አለው...
"ወንድሜ ሆይ እኔ ከዚህ አስቀድሞ ማንም ሰው ያልሰራትን ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ አባቴ ሆይ ብቻ በጸሎትህ አትርሳኝ..." እያለ እንባውን ዘረገፈው

በአዩኝ አላዩኝ እግሮቼ እየተንቀጠቀጡም ቢሆን ጠጋ ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ
❖ ❖ ❖

አረጋዊው መነኮስ ኑዛዜውን ቀጠለ እንዲህም አለ...
"እኔ በምኖርበት ሥፍራ ቅስና መሾም ፈልጌ አባቶች ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ እሩቅና የማልታወቅበት ስፍራ ሔጄ ቅስና ተሹሜያለሁ ክህነት አለኝ ብዪ በድፍረት ቅዳሴ ቀደስኩ...፤የጠላሁትንም ብዙ ሰው በመርዝ ገደልኩ፤ ከእናቴ ጋር ዐሥር ጊዜ በተራክቦ ተኛሁ ከእኔ መፀነሰች ጊዜ መርዝ አጠጥቼያት ሕፃኑን ሳይወለድ በሆዷ ውስጥ እያለ ገደልኩት፤ ኃጢአቴ ብዙ ነው ተነግሮም አያልቅም፤ ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም፤ አባቴ ሆይ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና በጸሎትህ አትርሳኝ..." ብሎ እጅግ በበዛ ጣርና ጋር እየተሰቃየ ከብዙ ቆይታ በኀላ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡
ለካስ የመነኮሳቱ ለቅሶ ይኸው ጣርና ጋር ኖሯል አልኩ በልቤ...
❖ ❖ ❖

ያ ምስኪን ባለ ባዶ እግር የአረጋዊውን ሙት በድን መሬት ላይ ትቶ ዐይኖቹን ሽቅብ አነሳ ነፍሱ እየተከታተላት መሰለኝ ወዲያው መራራ ለቅሶን እያለቀሰ በባዶ እግሩ እየተቻኮለ ገሠገሠ...ሔደ ከዐይኔም ተሰወረ...
❖ ❖ ❖

በኀላ እንደሰማሁት ያ ምስኪን ባለ ባዶ እግር ባሕታዊ ለትጹን ይባላል ይህ ጻድቅ በወንጌል "ስለ ወዳጆቹ ነፍሱን አሳልፎ የሚሰጥ ያለ ከሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" የሚለውን የቅዱስ ወንጌል ቃል አብነት አድርጎ የአረጋዊው ነፍስ ትማር በጾም በጸሎት በስግደትና በልዩ ልዩ ተጋድሎ ጠምዶ አምስት ጊዜ ለመሞት ደርሶ እየተጋደለ እግዚአብሔርን ለመነው ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ "ተው ለዚህ ሰው አትለምንለት ራስህንም አትግደል እግዚአብሔር እውነተኛ ፈፈራጅ ስለሆነ የእሱ ኃጢአት ሥርየት የለውም" አለው፡፡
❖ ❖ ❖

ይህንን የሰማው ጻድቁ ለትጹን "እሱን የማትምረው ከሆነማ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ በማለት" ይሞት ዘንድ ራሱን ወደ ባሕር ወረወረና ሞተ፡፡
ወዲያው ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘውና አባ ለትጹንን አስነስቶ በፊቱ አቆመው እንዲህም አለው "ለትጹን ወዳጄ ሆይ ለዚህ ምሕረት ለማይገባው ሰው ስለምን ራስህን ታስጨንቃለህ ህይወትህንስ በከንቱ ታጣለህ?" ሲል ጠየቀው፡፡
አባ ለትጹንም መለሰ እንዲህ ሲል

"መሓሪና ይቅር ባይ ጌታዬና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዚህን ኃጢአተኛ ሰው ነፍስ ማርልኝ የማትምረው ከሆነ ግን የእኔንም ነፍስ ጨምረህ ከእሱ ጋራ ወደ ስቃይ ሥፍራ ጣላት" አለው፡፡
❖ ❖ ❖

ጌታችንም የአባ ለትጽኑንን ደግነት አድንቆ የዚያን ኃጢአተኛ ሰው ነፍስ ያመጣት ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም አመጣት ጌታችንም ያቺን ነፍስ ተቀብሎ በከበሩ እጆቹ ዳሰሳት እንዳልተፈጠረችም አደረጋት "ይህቺ ነፍስ አፈር ትሁን እንጂ ለስቃይም ለሕይወትም አትሁን" አለ፡፡ እንዳለውም ከ እም ኀበ አልቦ ኀበ ቦ ወደ እም ኀበ ቦ ኀበ አልቦ (ካለ መኖር ወደ መኖር እንዳመጣት ሁሉ ከመኖር ወደ አለመኖር መለሳት) አባ ለትጹንም የፈጣሪውን ፈጽሞ አመሰገነው፡፡

ይህ አባ ለትጹን ከብሕንሳ አገር የነበረ በጎልማሳነቱ በአባ ኤስድሮስ የመነኮሰ፤ ሰባት ሰባት ቀን እየጾመ መጋደል የጀመረ፤ መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ ከመድኃኔ ዓለም የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለ ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ በረከቱ በሁላችን ላይ አድሮ ይኑር፡፡
አርኬ
ሰላም ለአባ ለትጹን እስከ ፍጻሜ ዘክህለ፡፡ ከመ ያውጽእ እምደይን ብእሴ ህጉለ፡፡ ለለ መዋዕል ሰዱስ እንዘ ይበልዕ ቁጽለ፡፡ እም ብዝኀ ተጋደለ ገድለ፡፡ በአምሳለ ዖፍ ኮነ ሥጋሁ ቀሊለ፡፡
የሰኔ ፲፯ ቀን ስንክሳር
❖ ❖ ❖

ማስታወሻ
የዛሬ ዓመት አንብባው የጻድቁ ፍቅር ስቧት በዚህ ቀን ዳቦ ጋግራና ሻማ አብርታ እኔና ባለቤቴን ከትንሹ ወንድሟ ጋር ለጸሎት አቁማ ላዘከረችን የበኩር ልጄ ተማሪ ጽዮን (ፍቅርተ ቂርቆስ) ክብር ተጻፈ፡፡

ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም.
አራት ኪሎ
አዲስ አበባ
42 viewsYabsra, 03:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 07:46:40 (ሠ) ለቃሉዎች የተከለከሉ ተግባራት፡-[12]
በተሰበረ ወይም በተሰነጠቀ ወንበር ላይ አይቀመጡም፤
ጸጉራቸውን፣ ጺማቸውንም[13] አይላጩም፤
አያርሱም፣ አይቆፍሩም፤
ከሰው ጋር ዘወትር አይገናኙም፤
ከገዳ መሪዎች ጋር በመንገድ አይተላለፉም፤
በበዓላት ቀን ካልኾነ በስተቀር ከብት አያርዱም፤
ከቤታቸው ውጪ የተዘጋጀውን ምግብ አይበሉም፤
ከገብስ የተዘጋጀ ምግብ ውጭ አይበሉም፤
ብቻቸውን አይሔዱም፣ ወንዝም አይሻገሩም፡፡
(ረ) የእምነት መሪዎች የሥራ ድርሻ:- አባ ሙዳ (ቃሉ) የሃይማኖት አባት እንጂ የአስተዳደር መሪ አይደለምና በፖለቲካ ውስጥ እንዲገቡ ፈጽሞ አይፈቀድለትም፡፡[14] ይልቁንም የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት እንዲፈጽም ይጠበቃል፡-[15]
ምርጫ ላይ ለሚነሱት አለመግባባቶች መፍትሔ መስጠት፤
በአካባቢዎች ያሉት የሃይማኖት መሪዎችን መርዳትና መምራት፤
ሕግና ልማዶች እንዲከበሩ ማስተባበር፤
የተፈጥሮ ሕጎች (ሰፉ) እንዳይጣሱ መጠበቅ፤
በሐመቺሣ ዕለት ለሕጻናት ስም ማውጣት፣ መመረቅ፤
የፈውስ ጸሎት ማድረግ፤
የበደሉ ክሰው፣ የተበደሉ ተክሰው እንዲታረቁ ማድረግ፤
የፈጣሪን ሕግጋት ማስተማር፤
ለስምንት ዓመት ብቻ ሥልጣን ለሚረከቡት አባ ገዳዎች ሥርዓተ መንግሥት መፈጸም፤ 
ለእነዚህ የገዳ መሪዎች ሃይማኖታዊ ቡራኬ፣ ምርቃትና እውቅና መስጠት፤
አዲሱን የገዳ አመራር Qumbii (ቁምቢ) የሚባል መራራ ፍሬ (‹‹ቅዱስ ምግብ››) እንዲበላ አድርጎ እግዚአብሔርን እንዳያሳዝን፣ ፍርድ እንዳያዛባ፣ ሕዝብ እንዳይበድል ቃለ መሐላ ማስፈጸም፡፡ ሉባው ሥርዓተ መንግሥት የሚፈጽምበት ይህ ቁምቢ እንደ ‹‹ቅዱስ ቁርባን›› የሚታይ ነው፤ መሪዎቹን ‹‹እውነት ያናግራቸዋል›› ተብሎም ይታመናል፡፡[16]
~~~~~~~
31 viewsYabsra, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 07:46:40 የዋቄፈና እምነት መሪዎች:- ማንነት፣ የመምረጫ መሥፈርትና የሥራ ድርሻ!
==================================
(ሀ)አባ ሙዳ (Abbaa Muudaa) ወይም Qaalluu (ቃሉ)፡- ቃሉ የዋቄፈና እምነት መሪ (ከፍተኛው የክህነት ባለቤት) ሲኾን የመጀመሪያው ቃሉ ከሰማይ የወረደ ሰው እንደኾነ ይታመናል፡፡[1] እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር የሚገናኘው በቃሉ አማካይነት (ድልድይነት) እንደኾነም ይታሰባል፡፡[2] አባ ሙዳ፣ ቃሉ፣ እሬሳ ገዳ የሚባሉት ስሞች ለአንድ የዋቄፈና እምነት መሪ የተሰጡ ስያሜዎች (ተሿሚ ግለሰብ የሚያመለክቱ) ሲኾኑ መጠሪያው እንደየአካባቢው የሚለያይ ነው፡፡[3] አባ ሙዳነት አንዴ ከተሰጠ በኋላ ኃላፊነቱ እስከ ዕድሜ ልክ አይሻርም፤ [እንደ ብሉይ ኪዳኑ ክህነት] ከዘር ዘርም የሚተላለፍ ነው፡፡[4] በዋቄፈና እምነት ውስጥ የሴቷም ሢመት እንዲሁ ነው፡- ማንኛዋም ሴት ቃሊቲ (የሃይማኖት መሪ) ከኾነች እስከ ዕድሜ ልኳ ድረስ መሪ የመኾን መብት አላት፡፡[5] እናም፥ አባ ሙዳ ወይም ቃሉ ‹‹የኦሮሞ ሌዋውያን ናቸው›› ማለት ይቻላል (ሌዋውያኑ ወንዶች ብቻ ከመኾናቸው በቀር)፡፡
ኦሮሞዎች የቃሉ መንፈስ ማደርያ እንዲኾን የተመረጠውን ሰው በሌላም አጠራር፥ ‹‹አያንቱ›› (በቁሙ ሲፈታ ዕድለኛ ማለት ነው) ወይም ‹‹ሉባ›› (ካህን) ብለው ይጠሩታል፡፡ እነዚህ ስለ መጻእያት ትንቢት በመናገር፣ እንደ ሐሳበ ዘመን ሊቃውንት በማገልገል፣ እንዲሁም በሕዝቡና በዋቃ መካከል ድልድይ በመኾን (መረጃ በማስተላለፍና በአማላጅነት) እንደሚያገለግሉ የሚታመኑ ናቸው፡፡ እንዲያውም፥ ‹‹ቃሉ በክርስትናው እምነት ውስጥ እንዳለው እንደ ‹ጳጳስ› እና በእስልምናው ውስጥ እንዳለው እንደ ‹ኢማም› ዓይነት ተመሳሳይ ደረጃ ያለው፣ የሃይማኖትና የመንፈሳዊ ክብረ በዓላት አዋቂ የኾነ፣ ከአያና ውስጥ ከአንዱ ጋር ልዩና የጠበቀ ግንኙነት ያለው፣ በተወሰነ ወቅትም ይኸው አያና የሚሠፍርበት (የሚነግሥበት) ሰው ነው›› በማለት የገለጹ አሉ፡፡[6]
በርካታ የማኅበረሰቡ ባህልና ሥርዓተ አምልኮዎች የሚተገበሩት፣ እስከ ዛሬም ድረስ ተጠብቀው የሚገኙት በቃሉ ተቋማት ዘንድ ነው፡፡ የሥርዓቱ ፈጻሚዎችም የቃሉ ማደርያዎች (አያንቱ) ናቸው፡፡ ስለዚህም ቃሉ ለኦሮሞ ብዙ ነገር ናቸው፡- እንደ ነቢያት ትንቢት ይናገሩላቸዋል፣ እንደ ሊቃውንት ዘመኑን ይቆጥሩላቸዋል (መቁጠር ብቻም ሳይኾን እንደ ጠንቋዮችም በጎና ክፉ ቀናትን ይለዩላቸዋል)፣ እንደ ካህናት መሥዋዕት ያቀርቡላቸዋል፣ እንደ ቅዱሳንም ከዋቃ ጋር ያስታርቋቸዋል (ያማልዷቸዋል)፡፡
(ለ) Caamsituu (ጫምሲቱ)፡- እነዚህ ደግሞ በማኅበረሰቡ ዘንድ እንደ ‹‹ልዩ ጸሎተኞች›› የሚታመኑ ሲሆን፥ በተለያዩ ምክንያቶች ዝናብ እንዳይዘንብ ሲፈለግ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸው (ዝናብ እንዳይዘንብ የሚያደርጉ) ሰዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- በመከር ወቅት እህል እንዳያበላሽ፣ በሠርግና ቀብር ቀናት ሕዝቡ እንዳይረበሽ ሲባል፣ ወዘተ ሊኾን ይችላል፡፡ እነዚህ caamsituu (ጫምሲቱ) ይባላሉ፤ በቁሙ ሲተረጎም ‹‹ዝናብ የሚያባራ›› እንደማለት ነው፡፡ በእርግጥ እነዚህ ጫምሲቱዎች ምን ዓይነት ‹‹ጸሎት›› እንደሚጸልዩና ምን ዓይነት ድርጊቶች እንደሚያከናውኑ ግልጽ ባይኾንም ድርጊቱ ግን በቅዱስ መጽሐፍ ላይ ከምናውቀው የነቢዩ ኤልያስ ተግባር ጋር ተመሳሳይነት ያለው እንደኾነ እንረዳለን (1ነገ.17፡1-7፤ ያዕ.5፡17-18)፡፡  
(ሐ) Ayyaana Abbaa (አያና አባ)፡- ኦሮሞዎች በዓይን የማይታዩ ክፉና ደግ መናፍስት እንዳሉ ያምናሉ፡- ክፉ መናፍስት የሚባሉት ቀሳፊዎች ሲኾኑ ስማቸው ''seexana'' (በየቦታው የሚዘዋወርና ከኹሉ የባሰ ኃይለኛ)፣ ''golfaa'' (በየመንደሩ የሚኖር)፣ እና ''dachee'' (በደንና በቆላ ቀመስ /አፋፍ/ የሚኖር) ነው፡፡ ደጋግ መናፍስት ጠባቂ መናፍስት (ውቃቢ) ሲኾኑ በዋናነት ''ayyaana abbaa'' (የአባት አምላክ) እና ''giiftii/aayyolee'' (እመቤት) ይባላሉ፡፡[7]
ማኅበረሰቡ ለሁለቱም መናፍስት መሥዋዕት ያቀርባል፡- ክፉዎቹ ተመግበው በያሉበት እንዲያርፉ (እንዳይተናኮሉ)፣ ደጋጎቹ ደግሞ ለማደርያነት በሚመርጧቸው ሰዎች አማካይነት በዋቃ ቶኪቻ እና በሰዎች መካከል እንዲያማልዱ ለመለማመን ሲባል፡፡ ‹‹በተለይ ተገቢው መሥዋዕት በተገቢው ጊዜ የቀረበ እንደኾነ›› ይላሉ የማኅበረሰቡ አዛውንት፥[8] ‹‹ወዲያ ወዲህ እየተክለፈለፉ አደጋ እንዳያደርሱብን አለቃቸው ይቆጣጠራቸዋል፤ አለበለዚያ ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠናል፡፡››
(መ) ለ ‹‹አያንቱነት›› (የእምነት መሪነት) የሚያበቁ ኹኔታዎች፡-
(መ-1) በዋቃ መመረጥ፡- በማኅበረሰቡ እምነት እነዚህ ሰዎች አያንቱ (ዕድለኛ) መባላቸው ተገቢ ነው፤ ይህ ያለ ዋቃ (እግዚአብሔር) ምርጫ የሚገኝ አይደለምና፡፡ በመሠረቱ ይህ ሁኔታ ለክህነት ከመመረጥ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ክህነት መመረጥን (መታደልን) እንደሚጠይቅ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናልና፡- ‹‹እናንተ...የተመረጠ ትውልድ፣ የመንግሥትና የክህነት ወገን፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ ለርስቱም የተለየ ወገን ናችሁ›› እንዲል (1ጴጥ.2፡9)፡፡ ‹‹ዕድለኛ›› መሰኘትም ለሁሉም ያልተሰጠውን የመመረጥ ክብር ማግኘት መቻል ነው፤ ‹‹በውኑ ሁሉ ሐዋርያት ይሆናሉን?...›› እንደተባለ (1ቆሮ.12፡29)፡፡ ሁሉም ካህናት መሆን ቢችሉማ ኖሮ ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ በምን ቅድመ ሁኔታ መመረጥ እንዳለባቸው ባልተናገረ ነበር (1ጢሞ.3:2-13፤ ቲቶ.1:5-9)፡፡
(መ-2) ከሕዝቡ የብቃት ምስክርነት፡- ከሰማያዊው ዋቃ በተጨማሪ ቃሉ (አያንቱ) ለመኾን የሕዝብ ምስክርነት ያስፈልጋል፡- ‹‹ቃሉ…በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ንጹህና ምስጉን፣ ባህላዊውን ነውር እግድ (taboos) የሚጠነቀቅ፣ ‹‹safuu›› (ሳፉ) የሚሰኙ የሥነ ምግባር እሴቶችን (values) የሚጠብቅ፣ በየወቅቱ ያሉትን የእምነት ክብረ በዓላት የሚያከብር (የሚያስከብር)፣ በሚያደርጋቸውም ክንዋኔዎች ኹሉ እውነትን የሚከተል፣ ከኀጥአትም የራቀ መኾን አለበት›› እንዲል፡፡[9] የኦሪት ካህናትም ‹‹ነውር ያለባቸው›› እንዳይኾኑ የሚመረጡበትን ቅድመ ሁኔታ እግዚአብሔር በዝርዝር ለሙሴ ነግሮታል (ዘሌዋ.21፡16-23)፡፡
(መ-3) ግርዛት፡- ኦሮሞም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ኹሉ የግርዛት ባህል አለው፡፡ እዚህ ላይ ለማንሳት የተፈለገው ግን በማኅበረሰቡ ዘንድ ብቻ የሚታወቀውን የግዝረት አፈጻጸም ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በማኅበረሰቡ የገዳ ሥርዓት ውስጥ በሃይማኖታዊ መሪነት የሚሾሙት ሰዎች የተለያዩ ደረጃዎች ያላቸው ሲኾን ከመጀመርያው ደረጃ (ገዳ አያና) ወደ ሉባ ለመሸጋገር በ40 ዓመታቸው መገረዝ ዋናው ቅድመ ሁኔታ ነበር፡፡[10] ስለዚህም ሉባ ለመኾን በዕድሜ 40 ዓመት መሙላት የግድ ከመኾኑም በላይ በጠባይ፣ በዕውቀትና ስለ ትጋቱ (ችሎታው) በሕዝቡ ዘንድ የተመሰከረለት ሊኾን ይገባዋል፡፡ ተገርዘው ‹‹ሉባ›› የተባሉት ኹሉ በእጩነት ለመቅረብ መብት ቢኖራቸውም በአንድ ሉባ አስተዳደር ሥልጣን የሚይዙት ግን ከእነርሱ መካከል የሚመረጡት 12 ብቻ ናቸው፡፡[11]
29 viewsYabsra, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 07:32:10 ደራሲ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ፀሀፊው በታዘባቸው ነገሮች ላይ የሰላ ትችቱን ፅፎታል ።

join and share
@filsifina000
@filsifina000
29 viewsYabsra, 04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 09:00:38
"አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ"

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያልን በዓለ ዕርገትን በማስመልከት ልዩ መርሃ ግብር ስላዘጋጀን ሁላችሁም በዕለቱ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ በአክብሮት ጠርተናችኋል።

በዕለቱ
የበገና ዝማሬ

ትምህርት በተጋባዥ መምህር

የልምድ ልውውጥ

መዝሙር በማኅበረ ቅዱሳን ሐዋሳ ማዕከል መዘምራን የሚቀርብ ይሆናል

ቦታ ደብረ ታቦር ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን

ዕለተ ሐሙስ

#Share
66 viewsYabsra, 06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 11:38:09
"ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን"

ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
56 viewsYabsra, 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 13:58:08 + የሰጠኸኝ ሴት +

እግዚአብሔር አዳምን "አትብላ ካልሁህ ዛፍ በላህን?" ብሎ ጠየቀው:: አዳምም :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ አለ::

የሰጠኸኝ ሴት! በጣም ይገርማል:: ሚስቴ አላለም::
አዳምና ሔዋን የተገናኙ ቀን አዳም ያለውን አስታውሱ
"ይህች አጥንት ከአጥንቴ
ይህች ሥጋ ከሥጋዬ" ብሎአት ነበር::
ምንም እንክዋን አዳም ወላጆች ባይኖሩትም ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ብሎም ነበር::
ራቁታቸውን ቢሆኑም አይተፋፈሩም ነበር::

አሁን በራቁቱ ብቻ ሳይሆን በሔዋንም አፈረባት::
እናትና አባቱን ይተዋል እንዳላለ ሔዋንን ራስዋን ተዋት::
ከሚስቱ ጋር መተባበር ቀርቶ ክስ ጀመረ::

አካሌ አጥንቴ ሥጋዬ ማለቱ ቀረና የሠጠኸኝ ሴት አለ::
የጫጉላው ጊዜ አለፈና ከሚስትነትዋ ሴትነትዋ ብቻ ታየው::

በጋብቻ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሠጠንን ነገር
ሁሉ ቀድመን የራሳችን እናደርጋለን ነገሮች ሲበላሹ ግን ባለቤትነቱን ወደ እርሱ እንመልሰዋለን::

የሠጠኸኝ ሥራ
የሠጠኸኝ ወላጆች
የሠጠኸኝ ሰፈር
የሠጠኸኝ ሀገር
የሠጠኸኝ መሪ
የሠጠኸኝ ጉዋደኞች
የሠጠኸኝ ደካማ ሥጋ
የሠጠኸኝ ዓይን

ትናንት ሲሠጠን ዘምረን የተቀበልነውን ሥጦታ ዛሬ ለምሬት እንጠቅሰዋለን:: የሠጠኸኝ የሠጠኸኝ .... ሠጠኝና በላሁ ብለን ቀርጥፈን ለበላነው ዕፀ በለስ ፈጣሪን እንከስሰዋለን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 17 2012
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
61 viewsYabsra, 10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 13:58:07 ሀመቺሣ/Hammachiisaa- እንደ ጥምቀተ ክርስትና
==================================
‹‹ሀመቺሣ›› በአፋን ኦሮሞ ‹‹ማሳቀፍ›› ማለት ነው፡፡ ይህ ባህል የተወለዱ ሕጻናት በ‹‹መንፈሳውያን የሃይማኖት አባቶች›› (አባ ሙዳ፣ ሉባ፣ ቃሉ፣ ወዘተ) ታቅፈው የሚባረኩበት ሥርዓት ነው፡፡ በዕለቱም አዲስ ስም ይሰጣቸዋልና፥ አመቺሳ፡- ‹‹የሕጻናት/ልጆች ስም ማውጫ ቀን›› በመባልም ይታወቃል፡፡[1] ብዙውን ጊዜ በተወለዱ በመንፈቅ ዕድሜ እንደሚከናወን ቢገመትም ትክክለኛ ቀኑን ለመወሰን አስቀድመው ሙሉ ቀን መቁጠር ወደሚችሉት አዋቂዎች ዘንድ በመሄድ ጨረቃ የምትታይበትን ቀን አስበው ‹‹ጨጊኖ›› (ጎደሎ/መጥፎ ቀን እንደማለት ነው) በማይውልበት ዕለት ስለሚወሰን አመቺሣው ሊዘገይ ይችላል፡፡[2] በእርግጥ፥ የማኅበረሰቡ አዛውንት የወንድና የሴት ሕጻን አመቺሣ በቀናት እንደሚለያዩ (የወንዱ እንደሚቀድም) ቢናገሩም ትክክለኛውን ግን ለመግለጽ ይቸገራሉ፡፡
የሀመቺሣ ዋና ዓላማ የተወለዱ ሕጻናት በሃይማኖት አባቶች አማካይነት ከፈጣሪያቸው ፀጋና ረድኤት እንዲያገኙበት ሲኾን የሕፃኑ እናት የታቀፈችውን ልጇን ስታስታቅፍ፥ ‹‹ከዚህ በኋላ ለአንተ ሰጠሁህ›› በሚል ለፈጣሪ አደራ ማስረከቧ ነው፡- ልጁ ካልታቀፈ አያድግም (ይቀሰፋል)፣ ቢያድግም አይፋፋም፣ እንከን አያጣውም ተብሎ ይታመናልና፡፡ ምንም እንኳ እናቲቱ በወለደች በአምስተኛ ቀኗ (ሸነኒ በሚባል ሥርዓት) በተለያዩ ቅጠላ ቅጠሎች ገላዋን ታጥባ ‹‹የነጻች›› ብትኾንም የአራስነቷን ጊዜ ጨርሳ ወደ ሥርዓተ አምልኮው የምትሔደው ግን በዚህ ዕለት ነው፤ እርሷም አስፈላጊውን ‹‹መባ›› (አሞሌ ጨው፣ አረቂ፣ ዳቦ፣ በኑግ የታሸ ቆሎ፣ ማር፣ ወዘተ) ለልጁና ለራሷ ይዛ ሄዳ ''garaa jiidhaa ta'i, ilma lammiif ta'u da'i'' (‹‹ማኅፀነ ርጥብ /ወላድ/ ኹኚ፤ ለወገን የሚተርፍ ወንድ ልጅ ውለጂ››) ተብላ ትመረቃለች፡፡
ሥርዓቱ፡- በትክክለኛው ቀን የሕጻኑ ቤተሰቦች ወደ ሥፍራው ይወስዱትና በእርጥብ ሣር ተጎዝጉዞ፣ በገል እሳት አማካይነት በሚሸቱ እጽዋት ጢስ በታወደው ማምለኪያ ቤት ይገኛሉ፡፡ እናት ልጇን ታቅፋ ከፊት፣ አባት ከኋላ፣ ሌሎችም እንደየማዕርጋቸው ኾነው ከታቃፊው ፊት ይቀርቡና ሁለት አሞሌ ጨው አበርክተው ልጁን ይሰጡታል፡፡ የሃይማኖት አባትም ልጁን ታቅፎ ወደ ‹‹ዋቃ ቶኪቻ›› እንዲህ ሲል ይጸልያል፡-[3]
‹‹ኹሉን የፈጠርክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከአባት ጀርባ ደም አንስተህ፣ በእናት ማኅፀን ቋጥረህ፣ እስትንፋስ ያለው አድርገህ፣ መውለድና ምጥ ረድተህ ገላግለህ በዓይናችን ስላሳየኸን ከፍ ባለ እምነት እናመሰግንሃለን፡፡ እንደዚሁም፥ ይኽንን ልጅ በአንተ ስጦታ በእነዚህ በሁለቱ መካከል የተገኘውን ወገኑን የሚረዳና የሚያስተዳድር፣ እናት አባቱን የሚጦር፣ የሽማግሌዎችን ምክር የሚሰማ፣ የጎሣውን ባህል የሚጠብቅ፣ አንተን ፈርቶ አንተን አምኖ ባንተ የሚያድር እንድታደርግልን ከልብ እንለምንሃለን፡፡ ረጅም ዕድሜ ስጠው፣ እናትና አባቱ እርሱ ከተወለደ ደላን ብለው እንዲያመሰግኑህ[4] መልካም ገድ አድርግላቸው፤ የእነዚህን አማኞች ሕዝቦችህን ልመና እህ ብለህ ስማ፣ የምህረት መልስም መልስላቸው!››
ከዚህ በኋላ ለልጁ ስም ያወጣለታል (እናትና አባቱ ካወጡለት ሌላ)፡፡ እንትፍ ብሎ እንዲያድግ መርቆት መልሶ ይሰጣቸዋል፡፡
በመሠረቱ ይህ ሥርዓት በዘሌዋ.12፥1-8 ላይ ከተቀመጠውና ዛሬም በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ሥፍራ ከሚሰጠው የ፵ እና ፹ ልጅነት ጥምቀት (ክርስትና ማስነሣት) ጋር የሚመሳሰል ኾኖ እናገኘዋለን፡፡[5] በኦሪቱ ሴቷ የግዳጅዋ ጊዜ ሲፈጸም ከእነ ሕጻኗ ወደ ቤተመቅደስ ገብታ ከሕርስ የምትነጻበት ሥርዓት ሲኾን ቀናቱም አዳምና ሔዋን ተፈጥረው በልጅነት ክብር ወደ ገነት የገቡባቸውን ጊዜያት እንደሚጠቁሙ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡ አሁንም በዚሁ መሠረት ታቅፈው የሚመጡትን ሕጻናት መርቃ፣ የሥላሴን ልጅነት ሰጥታ (አጥምቃ)፣ ሥጋ ወደሙን ታቀብላለች፤ የክርስትና አባትና እናትም ኃላፊነታቸውን ይውጡ ዘንድ ታስረክባለች፡፡ ደግሞም፥ ለሕጻናቱ አዲስ ስም መሰጠቱም ሀመቺሣንና ክርስትና ማንሣትን ያመሳስላቸዋል፡፡
እዚህ ላይ የሚገርመው ነገር ቢኖር ሀመቺሣ የግድ ከክርስትና በፊት መፈጸሙ ነው፡፡ አንድ ሕጻን አስቀድሞ ክርስትና ከተነሣ በምንም ተአምር አይታቀፍም፤ ይህን ያደረገ ቤተሰብም ‹‹እስከ መወገዝ›› ይደርሳል፡፡ ይኽ ምናልባትም፥ ‹‹የሁለቱን መናፍስት ተቃራኒነት›› በግልጽ ቢያሳይም አዛውንቱ ግን ቁርጥ ያለ መልስ አይሰጡም፤ በቃ ''qooda isaati'' (ሥርዓቱ ነው) በሚል ይቋጫሉ፡፡ 
~~~~~~~
43 viewsYabsra, 10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ