2023-05-04 14:40:20
አደጋው በሁሉም ላይ በመሆኑ አጸፋ ምላሹንም ሁሉም ሊሰጥ ይገባል ....
ማጀቴ፣ ደብረሲና፣ ሸዋሮቢት የሆነው ሁሉ የሆነበት ምክንያት ህዝቡ ስላመረረ ነው። የምሬቱ መነሻም ለተከታታይ ጊዜያት ያለ ጥበቃ እና ከለላ መጠቃቱ ነው። ይልቁኑ አጥቂው የፌዴራል መንግስት ከለላ ሲያገኝ፣ የታሰሩ አጥቂዎች ያለ ፍርድ ሲፈቱ ታዝቧል። ይህ ህዝብ ከጥቃት የሚከላከል የሌለው፣ ለጥቃቱ እውቅና የሚሰጥ የሌለው እንዲሁም ፍትህ ያላገኘ ህዝብ ነው።
የአብይ አስተዳደርም ሆነ መከላከያ ጥቃቱን ግጭት በሚል የዳቦ ስም በማለባሰስ ወንጀሉን ባለቤት አልባ በማድረግ ተጠምደው ከርመዋል። ይህ በደል ህዝቡን አስመርሯል። ይህ የህልውና አደጋ እና ፍትህ አልቦ ሁነት ህዝቡ በአመጽ መብቱን እንዲያስከብር አስገድዶታል። ስዚህም አሁን ለመብቱ፣ ለህልውናው፣ ለነጻነቱ፣ ለከለላው እየታገለ ይገኛል።
በሰሜን ወሎ እና በሰሜን ጎንደር ከበባዎች እና መለስተኛ ተኩሶች እንዳሉ ይሰማል። እነዚህ አካባቢዎች እና በዚያ የሚገኙ ፋኖዎች በልዩ ሁኔታ ጠላት በባድማቸው ሊያጠቃቸው ሰራዊት በመላኩ ይህ መከራ ተሸከሙ እንጂ አደጋው የጋራ ነው።
የማጀቴ ፋኖ እና ገበሬ እየተዋጋ ያለው የአማራን ጦርነት እንጂ የሸዋን ጦርነት አይደለም። ምሬ የሚዋጋው ስለ አማራ እንጂ ስለሌላ አይደለም። የአንዳችን ጥቃት የሁሉም መሆኑ በደንብ ሊታመን ይገባል።
የሸዋን ምሬት የአማራ ምሬት አድርጎ መውሰድ ያስፈልጋል
በየትኛውም አካባቢ ያለ አማራ የደብረ ሲና፣ ማጀቴ እና አጣዬ ወጣቶችን ምሬት፣ ቁጣ፣ ጥቃት ከእነሱ እኩል ሊሰማን ይገባል። ምክንያቱም አማራ በመሆናቸው ተጠቁ እንጂ ሸዋነት አላስጠቃቸውም።
ባለፉት ጊዜያት በተናጠል የመዳን፣ ተነጥሎ የመታዬት እና ነጥሎ በማጥቃት ሂደት የታዩ ዝንጉነቶች መታረም አለባቸው። የጎንደር ችግር ከሸዋ አይለይም፣ የወሎም ከጎጃም አይለይም። መሠረታዊ ችግሩ እና አደጋ አስገኚው አንድ እና ያው ነው፤ ፋሽዝም ነው። ፋሽስቶች ናቸው። አደጋው የህልውና አደጋ ነው። ስለዚህም በጋራ ተመሳሳይ የግምገማ ይዘት ላይ ቆመን ቀጣዩን የትግል አቅጣጫ መተለም ይኖርብናል።
ድል ለአማራ !
#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
1.1K views11:40