Get Mystery Box with random crypto!

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

የቴሌግራም ቻናል አርማ uznesswzchristjesus — " ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"
የቴሌግራም ቻናል አርማ uznesswzchristjesus — " ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"
የሰርጥ አድራሻ: @uznesswzchristjesus
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.36K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ መንፈሳዊ ህይወትዎን የምያሳድጉ መንፈሳዊ ምክርን ያገኙበታል፡፡

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 19:00:37 "መጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠን ዕውቀት እንድጨምርልን ሳይሆን ህይወታችን እንድለወጥ ነው፡፡" ዲ ኤል ሙዲ፡፡

ሁል ግዜ ይህንን አስብ
መጽሐፍ ቅዱስን ካነበብክ፣ ካጠናክ፣ እና ካሰላሰልክ በኃላ አንድ ነገር ማድረግን እንዳትረሳ፤ እሱም፦ ጌታ በቃሉ ምን እንደተናገረህና በህይወትህ እንዴት በተግባር ላይ ማዋል እንደምትችል አስብ፤ ብቻልህ በማስታወሻ ለመጻፍ እና መንፈስ ቅዱስ በምሰጥህ ምሪት መሠረት ተግባራዊ አድርግ፡፡

መንፈሳዊ ዕድገት የምመጣው፣ የጋለና የተቀጣጠሌ መንፈሳዊ ህይወትን መኖር የምትችለው ባነበብከው፣ ባጠናሄው እንድሁም ባሰላሰልከው መጠን ሰይሆን ያነበብከውን ያጠናሄውን እና ያሰላሰልከውን ሁሉ በህይወትህ ላይ ተግባራዊ ባደረከው መጠን መሆኑን ልብ በል፡፡

በነገራችን ላይ ተግባራዊ እስካላደረግነው ድረስ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበባችን ማጥናታችንና ማሰላሰላችን ሰይጣንን አያስጨንቀውም፡፡

ቆሚ ብለህ አስብ!

ተግባራዊ ያልሆኔ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀትን ማወቅና መጽሐፍ ቅዱስን ምንም አለማወቅ ሁለቱም ዕኩል ናቸው፤ አንድ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱንም በተግባር ስመዘን ውጤቱ ይሆናል ከመቶ ዜሮ፡፡( 0/100)፡፡

ይህንን ዕርምጃ ወስደን እንድሁም ተግብረን በህይወታችን ፍሬ እንድናፈራ ( 30,60,100) የጌታ ጸጋና ሠላም ምህረቱም ይብዛልን፡፡ ተባርካቿል፡፡



https://t.me/UznesswzChristJesus
1.0K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 15:40:06 ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለን ቦታ ለኢየሱስ ያለንን ቦታ ያሳያል፥ ሰው መጽሐፍ ቅዱሱን ከሚወደው በላይ ኢየሱስን መውደድ አይችልም።

ጥንት በአለማችን ታላላቅ ሰዎች
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ
የተናገሩት አስገራሚ
ምስክርነቶች፡፡

1. “ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ መማር እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ፣ ነገር ግን ዩኒቨርስቲም ባይገቡ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ የሚገኘው ዕውቀት ዩኒቨርሲቲ ገብቶ መጽሐፍ ቅዱስን ሳያውቁ ከሚመረቁበት ዕውቀት እጅግ በጣም የተሻለ ነው፡፡”
"ፕሮፈሰር ዊሊያም ሊዮነን"

2. “ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበቤ ብዙ አትርፌያለሁ፡፡ እስቲ አንተም በመንፈስና በእምነት ተሞልተህ አንብበው፡፡ ያለጥርጥር በህይወት ዘመንህ ሁሉ የተሻለ ሰው ሆነህ ትኖራለህ… እንደተከበርክም ታልፋለህ፡፡”
"አብረሃም ሊንከን"

3. “እውነቴነው እመኑኝ! በምንም አይነት የብርታትም ሆነ የድካም ስሜት ውስጥ ቢሆን መጽሐፍ ቅዱሴን ሳላነብ ወደ መኝታዬ አልሄድም፡፡”
"ዳግላስ ማክአርተር"

4. “ ሰይጣን ሰዎችን ሙሉ ለሙሉ አሸንፎ ከቁጥጥር በታች የሚያውለው መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያነቡና እውነትን ከውስጡ እንዳይፈልጉ ልባቸውን ከዘጋ በኋላ ነው፡፡”
"ዶ/ር ሃዋርድ ከሊ"

5. "ባለፍኩባቸው የህይወት ዓመታት ሁሉ በብዙ ሚሊዮን ዶላር በሚቆጠር ገንዘብ ዕቃዎችን እየገዛሁ ስሸጥም ኖሬያለሁ፣ ይህም ለንግዴ ብዙ ትርፍ አስገኝቶልኛል፡፡ ነገር ግን እስከ ዛሬ ከገዛኋቸው ነገሮች ሁሉ የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ በነበርኩ ጊዜ የገዛሁትን ያህል ትርፍ ሊያስገኝልኝ የቻለ የለም፡፡
ይህ ታላቅ ንብረት በሁለት ዶላር ከአምሳ ሳንቲም የገዛሁት መድሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ለዛሬው ማንነቴ ምክንያት የሆነኝ ይሄው መጽሐፍ ነው"፡፡
"ጆን ሜክር /ከአሜሪካ ታላላቅ
ነጋዴዎች አንዱ/"

6. "ይህ መጽሐፍ እስከ ዛሬ ከታተሙት መጽሐፍት ሁሉ የላቀ ክብርን የተጐናፀፈ መጽሐፍ ነው፡፡ እያዘንኩ ወደ መቃብር የምሄደው ወድጄ አይደለም፣ እንደገና ዕድል አግንቼ ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ ላነብ ባለመቻሌ ምንኛ እንደምጸጽት ባወቃችሁልኝ"፡፡
"ፓትሪክ ሄንሪ/ በሞት አፋፍ ላይ
እያለ የተናገረው የመጨረሻ ቃል፡፡"

7. “ መጽሐፍ ቅዱስ የዕውቀት ሁሉ መፍለቂያ በመሆኑ በርካታ የዓላማችን መጽሐፍት የተዋቀሩት በዚሁ መጽሐፍ ላይ ነው፡፡”
"ዳዊት ታልማግ"

8. "በሀሴት ስንሞላም ይሁን ስናዝን መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መቻል ይኖርብናል፡፡ ያለበለዚያ ህይወትን አቻችለን ለመምራትም ሆነ ለመቋቋም አቅም አይኖረንም"፡፡
"ዶ/ር ሄለን ኬለር"

9. “ ያለ እግ/ርና ያለመጽሐፍ ቅዱስ በትክክለኛ ፍትህ ዓለምን መምራትና ማስተዳደር በፍጹም አይቻልም፡፡”
"ጆርጅ ዋሽንግተን / የአሜሪካ
የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት"

10." … የታላቋ የእንግሊዝ የዕድገት ሚስጥር የሚገኘው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ነውና ደጋግመህ አንብበው"፡፡
"ንግስት ሺክቶሪያ /አንድ አፊሪካዊ
"ልዑል ላቀረበላቸው ጥያቄ
የሰጡት መልስ /"

11. "ለምን ይሆን ሰዎች በተሳሳተ አቅጣጫ ህይወታቸውን የሚመሩት የተባረከው ቅዱስ መጽሐፍ በቀና ጐዳና ሊመራቸው መቻሉን አልተረዱትም ይሆን?"
"ሳይንቲስት ሚካኤል ፋራዳይ"

12. "በዓለም ላይ ካሉ ሰዎች አንዱ ነኝና እኔም በተራዬ በዓለም ላይ እየኖሩ ላሉት ሰዎች ሁሉ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ትጉ፡፡ በየትኛውም የዕድሜ ክልልም ሆነ በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ይህ ቅዱስ መጽሐፍ ተነቦ የሚያበቃ አይደለምና አንብቡት"፡፡
"ፕሬዚዳንት ጆን ኩዊንስ አደምስ"

13. "ብዙ ጊዜ ደጋግሜ የተናገርኩት ወደ ፊትም የምናገረው መልዕክት አለኝ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዜጐችን በሙሉ ቀና ያደርጋል፣ ባሎችን የተሻሉ፣ጨዋና ከሁሉም በላይ ደግም ደግ አባት እንዲሆኑ ይረዳቸዋል"፡፡
"ፕሬዝዳንት ቶማስ ጃፈርሰን"

14." … ዛሬ ለደረስኩበት የህይወትና የኑሮ ደረጃ ቀዳሚ ተመስጋኞቹ በልጅነት አእምሮዬ መጽሐፍ ቅዱስን እያስተማሩ ያሳደጉኝ ወላጆቼ ናቸው"፡፡
"ዳንኤል ዊብስተር"

15. "መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ አዕምሮንና መንፈስን ወደሚያድስ ለምለም ስፍራ እንደመጓዝ ነው"፡፡
"አይዘን ሀወር"

16. "እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ስጦታዎች ሁሉ የከበረ ስጦታ መጽሐፍ ቅዱስ ነው"፡፡
"አበርሃም ሊንከን"

17. "መጽሐፍ ቅዱስ የድሆችና የጥቂቶች ተስፋ ነው"፡፡
"ቶማስ አክስ"

18. ለአንድ ሰው ትልቁ ውድቀት ለእ/ግር ቃል አለመታዘዝ ነው፡፡
"ቤንታ ሲና"

የተከበሩት ለከበረው መጽሐፍ ቅዱስ የሰጡት ምስክነት፡፡
2.3K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 07:52:41 እግዝአብሔርን በፍጹም ማመን ማለት፤ ለህይወትህ ከሁሉ የምሻለውን መልካም ነገር ሁሉ እርሱ ያውቃል በምል ዕምነት መኖር ማለት ነው፡፡
846 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 12:03:25 ወዳጄ አሁን ዓላማ ከሌለህ ተኝተህ አትዋል፣ ከአንዱ ማህበራዊ ድረገጽ ወደሌላው ስትገባና ስትወጣም አትዋል፣ ጌም ስትጫወት ወይም ፊልም ስታይም አትዋል! ዓላማህን እስክታገኝ ድረስ ዓላማህን ማግኘትን እራሱን ዓላማህ አድርገው።

መጸለይ ጀምር፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ጀምር፣ ሌሎች ጠቃሚ መጽሐፍት ማንበብ ጀምር፣ ማሰብ እና ማሰላሰል ጀምር፣ መጻፍ ጀምር! ዓላማህን ማግኘትን ዓላማህ አድርገው ያኔ ሕይወት ይጀምራል!
1.6K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 20:22:51 የወንጌል አርበኛ ቢሊ_ግርሃምን አንዲት የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ለጠየቀቻቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ በጣም ትልቅ ትምህርት አለው። እንዲህ አለቻቸው፦
“አሁን ሁሉን ነገሮችን እንደ አዲስ የመሥራት ዕድል ቢሰጥዎ ምን የሚለውጡት ነገር አለ?”
“ከብዙ ጉዞና አገልግሎት ይልቅ ከጌታ ጋር በጸሎትና በጽሞና አሳልፍ ነበር።"
“ለወጣት ሰባክያን ምን ይመክራሉ?”
“ብዙ ጸልዩ፤ ብዙ አንብቡ ጥቂት አገልግሉ ነው የምላቸው”።
ጸሎት ከጌታ ጋር ህብረት የማድረጊያ ትልቁ መንገድ ነው። ብዙ የሚጸልይ በጣም ብዙን ፍሬ ያፈራል።
1.5K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:01:34 “አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው።” ዘጸአት 33፥13
373 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 00:04:51 በሕይወት በምድር ሳላችሁ አንድ ነገር አስተውሉ ሁሌም ቢሆን በእግዚአብሔር እይታ ውስጥ እንደሆናችሁ።
458 views21:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 16:59:14 .
711 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:56:28 እግዚአብሔርን መፈለግ እና እግዚአብሔርን ማገልገል ዕድል ነው።

ከዝህ የምበልጥ ዕድል ከሰማይ በታች የለም፡፡ እነዝህንም ተግባራዊ ካደረጌ ክርስትያን በላይ በምድር ላይ ዕድለኛ የለም፡፡
1.1K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ