Get Mystery Box with random crypto!

ሕያው ቃል/Living Word/

የቴሌግራም ቻናል አርማ living_word_of_god — ሕያው ቃል/Living Word/
የቴሌግራም ቻናል አርማ living_word_of_god — ሕያው ቃል/Living Word/
የሰርጥ አድራሻ: @living_word_of_god
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.05K
የሰርጥ መግለጫ

" ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 10:10)
" እንዲህም አላቸው። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።"
(የማርቆስ ወንጌል 16፥15)
በአገልግሎታችን ላይ ጥያቄ ወይም አስተያየት ካሎት፥ Contact Us፦ @Berhaneyesus or @LW_comment_Bot በመጫን ያድርሱን
https://telegram.me/Living_word_of_GOD

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-21 13:21:34 . በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስም!!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
መጽሐፍ ቅዱስ ስናገር ፦ " ...አንድ ጊዜ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ ቀረበና ተንበርክኮ፦ ጌታ ሆይ፥ ልጄን ማርልኝ፥ በጨረቃ እየተነሣበት ክፉኛ ይሣቀያልና፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ብዙ ጊዜም በውኃ ይወድቃልና። ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው አለው። ...ወደ ዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ። ኢየሱስም ገሠጸው ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፥ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ። ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ኢየሱስ ቀረቡና፦ እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምን ነው? አሉት። “ኢየሱስም፦ ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።” አላቸው።
— ማቴዎስ 17፥14-20


ብዙዎቻችን በችግር ውስጥ ያለነው፤ በማጣት ውስጥ ያለነው፣ በህመም ውስጥ ያለነው፤ በእምነታችን ማነስ ምክንያት ነው። ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስ ስናገር ለሚያምን ጥቅት ይቻላል አላለም !! ያለው ለሚያምን ሁሉ ይቻላል... ነው። ሁሉ ውስጥ ጤንነት አለ፣ ሁሉ ውስጥ ገንዘብ አለ፣ ሁሉ ውስጥ ሰላም አለ፣ ሁሉ ውስጥ ሁሉም አለ። የእግዚአብሔር ቃል እራሱ እግዚአብሔር ነው። ቃሉን ስናምን የተነገረውን እግዚአብሔርን እናምናለን። ስለዚህ እምነት ማለት ስንታመም፤ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ "በርሱ ቁስል ተፈወስኩ" ቢለን ፈዉሳችንን በእምነት መቀበል መቻል ነው።

ምንም አይነት በሽታ ቢመጣ በርሱ ቁስል ተፈወስን የሚለውን ቃል አይሽርም። ምክንያቱም በርሱ ቁስል እኛ ተፈውሰናልና ምድር ላይ አዲስ ሀጢያት መጣ ብለን አንሰጋም፥ በየሚዲያው የምንሰማው አዲስ በሽታም አያሰጋንም። ክርስቶስ አንድ ጊዜ ለሁላችንም በመስቀል ላይ ተሰቅሏል። አሁን ዳግም ወደ ምድር መቶ መሞት አይጠበቅበትም። እየሱስ የሞተው ድሮ ለነበረው ሀጢያት ብቻ ሳይሆን አሁን እኛ እየሰራን ላለነው ሀጢያትም ጭምር ነው። ይሄንን ማመን ያለብክ እኛ ነን።

የእምነታችን መሰረት እየሱስ ክርቶስ ነው።
መጽሀፍ ሲናገር “ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤” ይላልና። (--1ኛ ቆሮንቶስ 15፥1) የቆምነው በክርስቶስ ላይ ነው “በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ። ” (—1ኛ ቆሮንቶስ 15፥2)

መጽሀፍ ቅዱስ የሕይወት እንጂ የሀይማኖት መመሪያ አይደለምና። “እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና (—2ኛ ቆሮ 5፥6-7 )መከራ፣ ድልም፣ መውደቅም፣ መነሳትም፣ በሆነ ጊዜ የምንመላለሰው በእምነት መሆን አለበት። ውጤቱ ስላማረ ብቻ አይደለም። ማመን ያለብን ነገር ግን፤ ሁኔታችን የሚስተካከለው ባመነው መጤን ወይም በክርስቶስ ላይ ባለን እምነት ልክ ነው። ለምሳሌ መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር፦ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።” ቢሎ በፊልጵስዩስ 4፥13 ይነግረናል። ይሄ ማለት፦ ሁል ጊዜ ፈተና ውስጥ ብትገባ የምታልፍበት መንገድ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳን ቃሉን ስታምን በክርስቶስ ላይ ያለህ እምነትህ፣ አቋምህ ፈጽሞ አይቀየርም። መጽሐፍ ቅዱስ ስናገር፦ “ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤” (— 2ኛ ቆሮ 4፥13) የምናምነው ግን የምናየውን ሳይሆን የማይታየውን ነገር ግን በእምነት ዓለም ውስጥ ያለውን ነው።

የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ" የሚል የሁልጊዜም መልዕክተ ነው...!! (ወደ ቆላስይስ 3:16)' እወዳችኋለሁ። የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ዘራችሁን፣ ኑሮዋችሁን፣ ቤታችሁን፣ ዘመናችሁንና ትዳራችሁን ሁሉ ይባርክ።
#መልካምና_ያማረ_ቀን_ይሁንላችሁ

እግዚአብሔር ሀገራችን እትዮጵያን ሰላም ያድርግልን። ቸር ሰንብቱ።

join share follow & comment
ሕያው ቃል /Living Word/
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD join #በማድረግ
ይ ላ ሉን

እንዲሁም በአገልግሎታችን ላይ ጥያቄ ወይም ሀሳብ አስተያየት ካሎት፥ Contact Us፦
@Berhaneyesus or @LW_comment_Bot በመጫን ያድርሱን፡፡
1.2K viewsB𝕖𝕣𝕙𝕒𝕟𝕖 Y𝕖𝕤𝕦𝕤 (O𝕗𝕗𝕚𝕔𝕚𝕒𝕝), edited  10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:19:30 . “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው”
===============

መጽሐፍ እንደሚነግረን “እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።” ይለናል።
— ኤፌሶን 5፥15 (አዲሱ መ.ት)

በእርግጥም “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው” ነገር ግን እንደ ቃሉ ዘመኑን መዋጀት ግድ ነው። — ኤፌሶን 5፥16 ለምሳሌ አሁን ያላችሁበት ፈተና ትልቁ የሕይወታችሁ ምዕራፍ ልሆን ይችላል። ግን ደግሞ በድል ትወጣላችሁ!! ብዙ ጊዜ ወድቃችሁ ተውቁ ይሆናል። ነገር ግን ከምንም ጊዜ በላይ እንደምንም ጠንክራችሁ ተነስታችሁም ይሆናል። ነገር ግን የአሁኑ ትግላችሁ ከወደቃችሁበት ጠንክራችሁ ለመነሳት ሳይሆን፤ ፈጽሞ ላለመውደቅ ይሁን።


“ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ።” — ኤፌሶን 5፥17 (አዲሱ መ.ት) የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና ሀሳብ ለማወቅ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ግድ ነው። “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
— ሮሜ 12፥2

እንዲሁ ጌታ ሀሳቡም ግልጽ ነው። “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።” — ኤርምያስ 29፥11 ይላልና።፥

“ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ኑሮአችሁ ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? በማለት አትጨነቁ። ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን? እስቲ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?

ለመሆኑ ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንዲት ሰዓት መጨመር የሚችል አለን? “ደግሞስ ስለ ልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ? እስቲ የሜዳ አበቦችን ተመልከቱ፤ አይለፉም፤ ወይም አይፈትሉም። ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ያን ያህል ክብር የነበረው ንጉሥ ሰሎሞን እንኳ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዲቱ አልለበሰም። እናንተ እምነት የጐደላችሁ እግዚአብሔር ዛሬ ታይቶ በነጋታው እሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር ይህን ያህል ካለበሰ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁ? ስለዚህ፣ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤ ማቴዎስ 6፥25 - 31 (አዲሱ መ.ት)

የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ" የሚል የሁልጊዜም መልዕክተ ነው...!! (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:16)' እወዳችኋለሁ። የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ዘራችሁን፣ ኑሮዋችሁን፣ ቤታችሁን፣ ዘመናችሁንና ትዳራችሁን ሁሉ ይባርክ።
#መልካምና_ያማረ_ቀን_ይሁንላችሁ

እግዚአብሔር ሀገራችን እትዮጵያን ሰላም ያድርግልን። ቸር ሰንብቱ።

join share follow & comment
ሕያው ቃል /Living Word/
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD join #በማድረግ፤
ይ ላ ሉን

እንዲሁም በአገልግሎታችን ላይ ጥያቄ ወይም ሀሳብ አስተያየት ካሎት፥ Contact Us፦ @Berhaneyesus or @LW_comment_Bot በመጫን ያድርሱን፡፡
1.9K viewsB𝕖𝕣𝕙𝕒𝕟𝕖 Y𝕖𝕤𝕦𝕤 (O𝕗𝕗𝕚𝕔𝕚𝕒𝕝), edited  07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 09:23:45 ከላኛው ልጥፍ የቀጠለ

ከሥጋ መለየት የማይቀር ነው፤ የትንሣኤ አካል ለብሰን መነሳትም የማይቀር ነው!!

ዳዊት "በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ ... ክፉን አልፈራም"። እንዳይፈራ ያደረገው አብሮነቱ ነው "አንተ ከእኔ ጋር ነህና" እንኳን ጥላው ሞት ራሱ ሲመጣ ትቶን አይሄድም!! ከጌታ ጋር ወደ ጌታ ነው የምንሄደው!!

ከ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በፊት በክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት ምክንያት ብዙዎች ተገድለዋል!! አስደናቂው ነገር በሞት ፊት ሕይወትን ዘምረው ነው ያለፉት!! ፊታቸው ላይ የነበረው ደስታ ሊገደሉ ሳይሆን ሊሸለሙ የተሰለፉ ነበር ያስመሰላቸው!! ተገርፈው ሲወጡ ደስ እያላቸው ነበር!! ልዩነት ያመጣው፦ ውስጣቸው የነበረው የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ ነው!!

ለማለት የፈለኩት፦ እግዚአብሔር እስከ መጨረሻዋ ሰከንድ አይተወንም፤ ከሞትም በኋላ ከእርሱ ጋር ነን!! በአብሮነቱ ተማመኑ!!
#መልካምና_ያማረ_ቀን_ይሁንላችሁ

እግዚአብሔር ሀገራችን እትዮጵያን ሰላም ያድርግልን። ቸር ስንብቱ።

join share follow & comment
ሕያው ቃል /Living Word/
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD join #በማድረግ
ይ ላ ሉን
212 viewsB𝕖𝕣𝕙𝕒𝕟𝕖 Y𝕖𝕤𝕦𝕤 (O𝕗𝕗𝕚𝕔𝕚𝕒𝕝), edited  06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 09:18:52
በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።❞ —መዝሙር 23፥4

የምስራች!! በየትኛውም ሁኔታ ስታልፉ እግዚአብሔር አብሯችሁ ነው!! ራሳችንን ልንተወው እንኳን እንችላለን፤ እርሱ ግን ትቶን ሄዶ አያውቅም!!

በዚህኛው ኑሮ በብዙ ነገር ውስጥ አልፈናል፤ ማግኘት እና ማጣት፣ መወደድ እና መጠላት፣ መክበር እና መዋረድ፣ ... በእነዚህ የኑሮ ጠርዞች ሁሉ እግዚአብሔር አብሮን አለ!!

ማግኘትን experience ስናደርገው ... ያገኘነው እንደማያኖረን ስለሚያውቅ ለራሳችን አልተወንም!! ማጣት ደጅ ሲያንኳኳ ደግሞ "ተወጡት" ብሎ አጋፍጦን አልሄደም!!

ስንወደድ ... ወዳጆች ሲከቡን ... አክባሪ ሲበዛልን ... "አሁን አላስፈልጋቸውም" አላለም፤ ያለ እርሱ ፍቅር ሕይወታችን እንደማይደምቅ ያውቀዋል!! የእርሱ ክብር ጎድሎን ሰው እንደማንሆን ያውቃል!!

ስንጠላ፣ ሰዎች ፊታቸውን ሲያዞሩ፣ ሲጸየፉን፣ ሲያዋርዱን፣ ... እኛ ጋር ለመቆም አይፈራም!! ወዳጆች ጠላት ሆነዉ ሲነሱ አብሮ ሰይፍ አይመዝም!! አድማ ይበትናል እንጂ ከአድመኞች ጋር አያድምም!! እግዚአብሔር ለአንተ/ለአንቺ ነው!!

አንድ ነገር ቀረ፤ የሥጋ ሞትን Experience ማድረግ!! ለሰው ልጅ የመጨረሻው ጭንቅ ቀን ያኔ ነው!! የሰው መንፈስ ከሥጋ የሚለይበት ሰአት እጅግ በጣም ከባድ ጊዜ ነው!! ያኔ እንኳን እግዚአብሔር አብሮን ነው!!

ዳዊት ...በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም አለ!! ሰዎች የሞት ጥላ ሲመጣ፤ ደብቀዉት የኖሩትን ምስጢር፣ የካዱትን ብድር፣ ከሌላ የወለዱትን ልጅ፣ ... ሌላም ብዙ ነገር ይናዘዛሉ!! ምከንያቱም የሞት ጥላ እጅግ በጣም አስፈሪ ነው። ይቀጥላል...
231 viewsB𝕖𝕣𝕙𝕒𝕟𝕖 Y𝕖𝕤𝕦𝕤 (O𝕗𝕗𝕚𝕔𝕚𝕒𝕝), 06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 12:05:37 https://vm.tiktok.com/ZMNuAkkYw/
719 viewsB𝕖𝕣𝕙𝕒𝕟𝕖 Y𝕖𝕤𝕦𝕤 (O𝕗𝕗𝕚𝕔𝕚𝕒𝕝), 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 20:02:54
#የሰላም_𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 “እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥5

“በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።” — 1ኛ ጴጥሮስ 5፥14
#መልካም_ምሽት

እግዚአብሔር ሀገራችን እትዮጵያን ሰላም ያድርግልን። ቸር እንሰንብት።

join share follow & comment
ሕያው ቃል /Living Word/
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD join #በማድረግ
ይ ላ ሉን
924 viewsB𝕖𝕣𝕙𝕒𝕟𝕖 Y𝕖𝕤𝕦𝕤 (O𝕗𝕗𝕚𝕔𝕚𝕒𝕝), 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:59:44
#የሰላም_𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
— ሮሜ 12፥2

ሕያው ቃል /Living Word/
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD join #በማድረግ
ይ ላ ሉን
797 viewsB𝕖𝕣𝕙𝕒𝕟𝕖 Y𝕖𝕤𝕦𝕤 (O𝕗𝕗𝕚𝕔𝕚𝕒𝕝), edited  14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 17:59:58
ይሄ #በሕያው_ቃል_ሚዲያ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የተዘጋጀ #የሰላም_𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 ነው። ማንም ወዶና ፈቅዶ በልተወለደበት ማንነት መሞት ይብቃ

“በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤” — ሮሜ 12፥10

“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።”
— ራእይ 5፥9-10

በተጨማሪም የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 አካል ለመሆን የሚያስፈልገው መስፈርት፦
1ኛ, በሕያው ቃል ሚዲያ የተዘጋጀውን የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 picture profile ማድረግ፤
2ኛ, Facebook ላይ ከምትለጥፉት መጣጥፎች ጋር ወይም ከፎቶግራፋችሁ ጎን የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 pictureን መለጠፍ፤
3ኛ, ይሄንን የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 መልዕክት ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ማድረግ ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ሀገራችን እትዮጵያን ሰላም ያድርግልን። ቸር እንሰንብት።

join share follow & comment
ሕያው ቃል /Living Word/
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD join #በማድረግ
ይ ላ ሉን
1.2K viewsBerhane Yesus (Official), edited  14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 19:23:52
ይሄ #በሕያው_ቃል_ሚዲያ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የተዘጋጀ የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 ነው። እግሬ መንገዳችሁን ይሄንን መዝሙር እያዳመጣችሁ እና እየተገባበዛችሁ 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕘𝕦𝕟 እንቀጥላለን። ተባረኩልኝ፤

ብዙዎቻችሁ የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 እየተቀባበላችሁ ስለሆነ ከልብ አመሰግናለሁ። ኘሮግራሙ አየር ላይ ከዋለበት በሰዓት
አንስቶ እስከ አሁን ወደ 157 ሰው ፕሮፋይሉ የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 ሆኗል።

እናንተን እግዚአብሔር ያክብራችሁ። ሰላማችሁ ሞልቶ እና በዝቶ እንደ የወንዝ ጅረት ይፍሰስ። ሌሎቻችሁም ለሰዎች ሼር እያደረጋችሁ ቀጥሉ።
𝕗𝕒𝕔𝕖𝕓𝕠𝕠𝕜 ላይም እንዲሁ ተባብረንና አንድ ሆነን እናደርጋለን። የጻድቅ ሰው ሰላም በአንደበቱ ላይ ነው...!!
https://telegram.me/Living_word_of_GOD join #በማድረግ
ይ ላ ሉን
964 viewsBerhane Yesus (Official), edited  16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 18:31:19
ይሄ #በሕያው_ቃል_ሚዲያ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የተዘጋጀ የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 ነው። በእርግማን ውጤት በተገኘ ቋንቋ መገዳደል ይብቃን

እንዲሁም የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 አካል ለመሆን የሚያስፈልገው መስፈርት፦
1ኛ, በሕያው ቃል ሚዲያ የተዘጋጀውን የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 picture profile ማድረግ፤
2ኛ, Facebook ላይ ከምትለጥፉት መጣጥፎች ጋር ወይም ከፎቶግራፋችሁ ጎን የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 pictureን መለጠፍ፤
3ኛ, ይሄንን የሰላም 𝕔𝕙𝕒𝕝𝕝𝕖𝕟𝕘𝕖 መልዕክት ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ማድረግ ብቻ ነው።

“ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤”
— ሮሜ 12፥9

እግዚአብሔር ሀገራችን እትዮጵያን ሰላም ያድርግልን። ቸር ሰንብቱ።

join share follow & comment
ሕያው ቃል /Living Word/
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD
https://telegram.me/Living_word_of_GOD join #በማድረግ
ይ ላ ሉን
908 viewsBerhane Yesus (Official), edited  15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ