አቡሻህር(አቡሻክር) ምንድን ነው?
በአለም ላይ እጂግ ርቂቅ እና ምጡቅ ስለሆነው ከእውቀቶች ሁሉ ስለ ላቀው እውቀት፣ ከጥበባትም ጥቡዕ ስለሆነው ሚስጥራዊ ጥብብን ስለያዘው ብዙም ስላልተነገረለት አቡሻህር በትቂጡ ልነግራችሁ ወደድኩ።
ይህ አቡሻሕር የሚባለው የቁጥር መጻህፍ ጭምር የያዘ ሲሆን ይህንን ማወቅ እጂግ የረቀቁ ጥበቦች ባለቤት ያደርጋል።
ብዙ ግዜ በሚዲያም ሆነ በቤተክርስትያን አውደ ምህርት የአቡሻህር ሊቁ እከሌ እየተባለ ሲጠሩ ሰምተናል ነገር ግን ይህ ስህተት ነው።
ምክኒያቱም የዘመን አቆጣጠር አዋቂ ወይም የባህረ ሀሳብ ሊቅ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የአቡሻሕር ሊቅ ወይም አዋቂ አይደሉም።
የዘመን አቆጣጠር ወይም ደግሞ የ ባህር ሀሳብ እውቀት አለምን በኬክሮስና በኬንትሮስ ከፍሎ አውድ እና አበቅቴ እንዲሁም አጾማትን ማውጣት የመሬትና የጨረቃ የፀሐይን እንዲሁም የከዋክብትን ምህዋር መለየትና ዘመንን የማራቀቅ እውቀት ነው።
ይህ ባህረ ሀሳብ ከ አቡሻህር ቅንጣቢ እውቀት የወጣ እንጂ አቡሻሕር አዋቂ አያሰኝም።
ይህንን ያልኩበት ዋና ምክኒያቴ ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ የአቡሻሕር አዋቂወች እጂግ ጥቂቶች በመሆናቸው ነው። 5 ሰወች ብቻም እንደሆኑ ይነገራል።.......
ለምን በትቂት ሰወች ተወሰነ ከተባለ የአቡሻሕር እወቀት በመማር በመደከም ብቻ የሚመጣ አይደለም እውቀቱ በመንፈስ ቅዲስ ገላጭነት ነው የሚማሩት።
የሚገርማችሁ ነገር እኒህ የአቡሻህር እዋቂወች ሰማያትን አይተው ከዋክብትን ተመልክተው የነፋሳትን አነፋፈስ እና የእጽዋቱን ሁኔታ ተመልከተዉ አለም ላይ እየሆነ ያለውን ወደ ፊትም የሚሆነው ነገር ያውቃሉ።
ይህም ብቻ አይደለም አቡሻህር ትምህርት መንፈስ ቅዱስ ለፈቀደላቸው ለበቁ አባቶች ብቻ ነው ትምህርቱ የሚገባው።
ስለሆነም አዋቂወች ለተንኮል የመጣን ሰውን ፊት አይተው ልቦናን እስከ ማንበብ ድረስ የሚያበቃ ጥበብ ነው።
ሰማይን አይተው የዝናባትን ሁኔታ የመዘወር ብቃትም ጥበብም አላቸው።
የነፋሳቱ ሀይል የመቆጣጠር ሀይል ታላቅ ጥበብንም ያውቃሉ።
እኒህ ሰወች ራሳቸውን የማደስ እና ከሰው የመሰውር ድንቅ ጥበብ ባለቤቶችም ናቸው። ራዕይን የማየትም ጸጋ አላቸው....
በሰማይ 4 ዓበይት እና 12 ንዑሳን ከዋክብቶች አሉ።
እኒሂ አራቱ ከዋክብት አራቱ አዝማናትን ማለትም ዘመነ ማቴወስ ማርቆስ ሉቃስና ዮሐንስን ሲያመለክቱ፤ 12ቱ ደግሞ ከ መስከረም እስከ ነሐሴ ድረስ ያሉትን ወራት የሚያመለክቱ ከዋክብት ናቸው።
ታዲያ እኒህ ዐበይትና ንዑሳን ከዋክብቶች በሰማይ ላይ በሚወጡ ወቅት እኒህ የአቢሻህር ሊቃውነት በሰማይ ያለውን የከዋክብትን አቀማመጥ ያያሉ። የሚመጣ ዘመኑንም ይተነብያ፤ በአለም ላይ የሚሆኑ እያንዳንዷን ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት በከዋክብቶች መሪነት ማወቅ ይችላሉ።
ከዚህ ጋራ በተያያዘ በቅርቡ በአንድ ታላቅ ገዳም ላይ የገጠመኝ ታሪክ በአጭሩ ልንገራችሁ።
ከአመት በፊት ወደ ጣና ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ ለማድረግ አሰብን የተወሰኑ ልጆች ጋራ ወደ ክቡራን ገብረኤል አቀናን።
በትንሽየ ጀልባ ተሰባስብን የጣና ሐይቅን ደረት ደረቱን እየገመስን በስተ ግራ እንጦስ ገዳምን ታከን ወደ ክቡሩ ስፍራ ክቡራን ገብርኤል ደረስን።
ከደሴቱ መሀል በበቀለ ቋጥኝ የመሰለ ተራራን እየታከክን ወደ ከፍታው ደረስን፤ ከተደላደለው ቦታም እንደደረስን ፊት ለፊት በክብ የተሰራውን የገዳሙን ቤተክርስቲያን ተሳልመን ወደ ግራ ወደ ሚገኘው እቃ ቤት ለመጓብኝት በሰልፍ ገባን።
እንደደረስን የእንኳን ደህና መጣችሁ ሰላምታቸውን የሰጡን አንድ በእድሜ ወጣት የገዳሙ ንብረት ክፍል ስማቸውን አስተዋውቀውን ወደ ውስጥ ገባን....።
ክቡራን ገብርኤል በ14ኛው ክፍለ ዘመን እንደ ተመሰረተ ጥንታዊና ታሪካዊ ታላላቅ የቤተክርስቲያኒቱን ሀብት የያዘ ድንቅ ቦታም እንደሆን እስጓብኛችን በያዙት መቋሚያ እያመለከቱ ገለጹልን (ይህንን በሌላ ጊዜ በሰፊው የምገልጸው ይሆናል)።.....
በእድሜ ወጣቱ አስጓብኛችን ሳይንስን ጥንቀሸቅ አድረገው የተማሩ እንደሆነ ከአነጋገራቸው እና ከሚሰጡን ቁጭት አዘል ገለጻ ለመረዳት ችያለሁ። ከእቃ ቤቱ ብዙ የብራና መጻህፍት መስቀሎች እና ስዕላትን ካሳዩን በኋላ። እኔ አንዱ የሆነ አይኔ ያረፈበትን ታላቅ ቅርስ በማየቴ አስደንግጦኝ እስኪጨርሱና እስክ ጠይቃቸው ቸኩያለሁ....ጥያቄ ካላችሁ ሲሉን የተወሰኑ ልጆች ስለ ቅርሷች አንዳንድ ጥያቄወችን ጠይው እሳቸውም መለሱላቸው። እኔም ጥያቄ እንዳለኝ ነገሪያቸው እድሉን ሲሰጡኝ ጥያቄየን ጠየኩ..... መልሳቸው የሚያስደነግጥ ነበር በሹክታ ለጠየኳቸው ከፍታ ባለው ድምጽ'' ስለ ዚህ አንተ ምን አገባህ? እንዴት ይህንን የማይመለከትህን ጥያቄ ልትጠይቀኝ ቻልክ?''.. በማለት ተቆጡኝ።
የጉብኝታችን ስአት እንዳለቀ ነግረውን የሆነ ጥግ ይዘው ከትልቅ ዋርካው ግንድ ተደግፈው ከዕቃ ቤቱ የሚወጣውን ተማሪ ይመለከታሉ። ወደ እርሳቸው ተጠግቸ ይቅርታ ቅድም የጠየኩወት እኔም ቤተ ክህነት አደግ ቢጤ ነኝ እና አንድ የማውቀው እና የሰማሁት እውነት ሳለለ እንጂ እንዲህ በደፈናው ለግብዘነት አይደለም አልኳቸው። እርሳቸው በጥርጣሬ አይን ይመለከቱኝ ጀመር... እንዳላመኑኝ ገብቶኛል።
ታዲያ በዚህ ጊዜ ወግ ወግን እየወለደ ስለ አቡሻሕር የሚያዉቁት ነገር ካለ ይንገሩኝ ብየ ጠየኳቸው። እርሳቸው ግን አሁንም ከጥርጣሬ መንፈስ ስላልወጡ አይ የማውቀዉ ነገር የለም አሉኝ።
ስለዚህ አቡሻህር ስለሚባለው ነገር የሚያውቅ ሰው አታገኝም ብታገኝ እንኳ አይነግሩህም አሉኝ።
በእርግጥ እኔም የማውቀዉ ነገር አለ አልኳቸው......ትኩር ብለው አይተው እየተቀመጡ እኔንም እንድቀመጥ እየጋበዙ ጀሮዋቸውን በጉጉት ሲሰጡኝ ሳይ ወሬየን ቀጠልኩ ..... የአቡሻሕር አዋቂወች 5 ናቸዉ ነገር ግን የት የት እንደሚገኙ ብዙም የሚየውቅ ሰው የለም....
አንዱ እዚህው ጣና ገዳማት ውስጥ ዳጋ እስጢፍኖስ ይገኛሉ፤ ስላቸው እሳቸው እንኳ... ብለው ዝም ሲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተሰውረው እንደ ጠፉ ሰምቻለሁ አልኳቸው በመገረም አንገታቸውን እየነቀነቁ አውንታውን ገለጹልኝ... መስማት ጀመሩ። ሌላው ሰው ኤርትራ ወደ ሰሜኑ ደንበር አካባቢ አሉ ሲባሉ ሰምቻለሁ(በእኔ ግምት እኒህ ሰው አባ ዘወንጌል ሳዮሆኑ አይቀሩም...)... ሶስተኛው ደምቢያ ከሚባል ልዩ ስሙ ሰቀልት አካባቢ የነበሩ መምህር ሲሆኑ ካረፉ ብዙ ጊዜያቸው እንደሆኑ ነገርኳቸው። አራተኛው የት እንዳሉ አላውቅም........
አምስተኛው ግን በ ሰሜን ጎንደር ዙሪያ አካባቢ ለዘመናት እራሳቸውን መቃብር ቤት ደብቀዉ የሚኖሩ እጂግ አዋቂ እና ጠቢብ ጎልማሳ የእግዚአብሔር ሰው ሲሆኑ ራሳቸውን ደብቀዉ የሚኖሩበትም ታላቅ ሚስጥር እንዳላቸው በዘመን ውስጥ የሚገለጡ እና የአቡሻህር የምስክር ማህተሙን በአይኔ እንዳየሁ ለቅርስ ጠባቂው ስነግራቸው በመገረም የእኒህን አባት ስም ጠየቁኝ.....።
እኒህ ጎልማሳ ሰው ጊዜና ዘመን ከሰጠን ለቤተክርስቲያን ሆነ ለሀገር አምድ ሁነው እንደሚገለጡ ተስፋ አለኝ።
ለጥበበኛ ሰው አንድ ቃል ትበቃለች..... የጥበብ ጭላንጭሏ መንገድ ይነገራል እንጂ በአፋ በአደባባይ አትገለጥም! ስለዚህ እናንተም ከዚህ ጽሁፍ አንድ ታላቅ እውነት እንዳለ ተረዱና እውነትና ጥበብን በቅን ልቦና ፈልጉ!
UTOPHIA ዩቶፕያ
Join us
@utophiainfo