Get Mystery Box with random crypto!

MEREJA TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ tv_mereja — MEREJA TV M
የቴሌግራም ቻናል አርማ tv_mereja — MEREJA TV
የሰርጥ አድራሻ: @tv_mereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.86K
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_ቲቪ | #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
ለማንኛውም መረጃ
➥ @User_bini
PROMOTION
➥ @user_bini
🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-08-29 08:41:08
ለ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ምዝገባ ከነሐሴ 23-ፃጉሜ 4/2014ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ይካሄዳል የአማራ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ልጆችን ማስተማር የዜግነት ግዴታን መወጣት መሆኑን በመረዳት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ልከው ዛሬውኑ ያስመዝግቡ ይላል ትምህርት ቢሮው።

መረጃው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ነው
3.4K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:30:16
Woldia University

በጦርነቱ ምክንያት የወልዲያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆኑን ከቤተቦቻችን የደረሰን መረጃ ያሳያል ።

"የወልደያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ውጡ ተብለው ግቢውን ለቀው በእግራቸው እየሄዱ ነው።
ሮቢት እና ገንደመዩ ላይ ውጊያው እንደቀጠለ ነው።"
4.0K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:26:32
የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

ለወንዶች 41፣
ለሴቶች 40 እና
ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

ለወንዶች 39፣
ለሴቶች 38 እና
ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።
 
4.8K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 10:40:03
አስደንጋጭ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች እያበረሩ እያለ እንቅልፍ ይዟቸው እንደነበር ታወቀ


ነገሩ እንዲህ ነው፣ August 15 ET343 ,Boing 737-800 የተባለ የኢትዮጵያ አውሮፕላን ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ በ37,000 ጫማ ከፍታ ላይ እየበረረ እያለ አዲስ አበባ ሊገባ ትንሽ ሲቀረው በወቅቱ አውሮፕላኑን ሲያበሩ የነበሩ ሁለቱም ፓይለቶች እንቅልፍ ይዟቸው የበረራ አቬሽን ሰራተኞች ፓይለቶቹን ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም አለመሳካቱን ተገልጿል። በኋላም ፓይለቶቹ እና የአቬሽን ሰራተኞች የሚገናኙበት ሲስተም ሲቋረጥ አውሮፕላኑ በሚያሰማው Automatic alarm ፓይለቶቹ ከእንቅልፋቸው ነቅተው አውሮፕላኑ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት አዲስ አበባ በሰላም አርፏል።
6.3K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 15:29:40 የ2015 የትምህርት ዘመን መስከረም 9 ይጀምራል

የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሀገር አቀፍ ሆኖ ይሰጣል

የ2015 ዓመት መደበኛ የትምህርት ዘመን መስከረም 9 ቀን እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።በ2015 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ላይ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ በ2014 የትምህርት ዘመን ላይ የተከናወነ ሲሆን አዲሱ ስረዓተ ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ በሁሉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ተግበራዊ ይሆናል።በሌላ በኩል በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም በከፊል በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 የትምህርት ዘመን የሙከራ ትግበራ ከተከናወነ በኃላ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ ይደረገል።

በ2015 ዓመት የትምህርት ዘመን 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፣የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ እንዲሁም 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ የማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል ፡፡በ2015 የትምህርት ዘመን ላይ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲተገበር በተለይ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ እና ከዚህ ቀደም በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረም በጋራ መሰራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የመጽሀፍ ስርጭትን በተመለከተ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በተማሪዎች እጅ እንዲደርስ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ አበበ ቸርነት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

Bisrat fm
5.4K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 15:53:00
ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ተማሪዎች እንዳይገኙ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ከመስከረም 30 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የሚሰጠውን የ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተከትሎ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መመሪያ ማውጣቱን አስታውቋል። በመመሪያው መሰረትም ተቋማቱ የትምህርት ዘመኑን የጊዜ ሰሌዳ በፈተና መርሃ ግብሩ መሰረት እንዲያዘጋጁ፣ በተጠቀሱት ቀናት መደበኛ ተማሪዎች በግቢዎቹ እንዳይገኙ፣ ለፈተና ማቆያ ስፍራ እንዲያዘጋጁ እና የምግብ አቅርቦት ዝግጅትም እንዲያደርጉ አሳስቧል።
5.1K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 09:44:57
በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ትምህርት ነፃ እና አስገዳጅ ይሆናል፡- የትምህርት ሚኒስቴር
****

በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት እና ጥናት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ከፍል የሚሰጥ ትምህርት ነፃ እና አስገዳጅ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአዲሱ የትምህርት ፍኖታ ካርታ ግኝት መሰረት ዜጎች ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በግዴታ እንዲማሩ ለማስቻልና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ እንደሚደረግ በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋረገድ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ገልጸዋል።

ፍኖተ ካርታውን ለማዘጋጀት ሲሞከር የትምህርት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ሊያሳይ የሚያስችል ጥናት መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው፤ መንግስት ለትምህርት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአዲስ መልክ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን ገልፀዋል።
4.5K views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 21:05:01
ትምህርት ሚኒስቴር ከ ኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እስከ መስከረም 5 ድረስ የሚቆይ በየቀኑ የሚጠቀሙት ያልተገደበ የኢንተርኔት ፓኬጅ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አላማውም በዚህ ክረምት በሁሉም ደረጃዎች የሚገኙ ተማሪዎች እንዲውም ማህበረሰቡ ለካርድ የሚያወጡትን ገንዘብ በመቀነስ በኦንላይን አጋዥ መማሪዎችን በመጠቀም ንቃተ ህሊናውን እንዲያሻሽል የታለመ ነው::

የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ከስር ያለውን ቦት በማስጀመር ለ 30 እና ከዚያ በላይ ለሚሆኑ ወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከ 15GB እስከ Unlimited Premium Package መጠቀም ይችላሉ ቦቱን ለማስጀመር ከስር ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ

https://t.me/MoE_OfficialBot?start=r07369204864
https://t.me/MoE_OfficialBot?start=r07369204864
2.1K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 11:40:54
"የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል"

ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች በተላከውን እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትክክለኛነቱን ባረጋገጠው ደብዳቤ መመልከት ችለናል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።
4.0K views08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 10:41:05 " አዲሱ ስርዓተ ትምህርት "

የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ክልሎች አስፈላጊ መፅሀፍትና ቋንቋ የመተርጎም ስራ እየሰሩ ሲሆን በፍጥነት ወደ መፅሀፍ የማሳተም ስራ እንዲገባ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዚህም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት (ኤለመንተሪ) ካሪኩለም ስራ ላይ ይውላል።

በተመሳሳይ በቀጣይ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ካሪኩለም የሙከራ ስራ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሞከር ሲሆን 2016 ዓ/ም ላይ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
3.5K views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ