Get Mystery Box with random crypto!

ማኅሌት ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ topazyon888 — ማኅሌት ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ topazyon888 — ማኅሌት ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @topazyon888
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.62K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ማኅሌት ሚዲያ እንኳን በሰላም መጡ፡፡ በዚህ ቻናል የተለያዩ መንፈሳዊ ስብከቶች እና ተከታታይ ትምህርቶች እንዲሁም የመንፈሳዊ መጻሕፍት ዳሰሳዎች ፣ አጫጭር የቤተ-ክርስቲያን አስተምሮዎች እና ዝማሬዎች ይቀርቡበታል፡፡የቻናሉን ይዘቶች ለሌሎች በማጋራትበማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ፡፡

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-25 17:54:32 ወንድማችን ዲ/ን Tsega Silase " እምዕቶነ እሳት " የተሰኘ አዲስ የዝማሬ ሥራ እነኋችሁ እያለን ነው ። ለወንድማችን እንኳን ደስ አለህ እያልን ዝማሬውን እናድምጥለት ።



790 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:10:01
1.2K views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 22:35:07
#ግንቦት_1_challenge

ግንቦት_1 የእናታችን ፣ የአማላጃችን ፣ የአዛኚቷ የእመ ብርሃን ልደቷ ነው ። የእርሷ ልደት የእኛም ልደታችን ነው ። ሁላችንም ይህንን ምስል profile picture። በማድረግ ከአሁን ሰአት ጀምሮ ልደቷን መዘከር እንጀምራለን ። ሁላችንም ኦርቶዶክስ ለሆኑ ጓደኞቻችን share በማድረግ ልደቷ ልደታችንን እናከብራለን ።
1.8K views19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 06:55:40
ሲኦልን አስመለሰው

አፍ የተባለ (መቃብር) ሁልጊዜ ይበላል ። በአፉ ያላምጥ በጨጓራውም (የሲኦል እሳት) ይፈጭ ነበር (በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ሲኦል) ። ከዕለታት አንድ ቀን አፍ የተባለ (መቃብር) ከዚህ ቀደም ሲመገብ እንደ ነበራቸው ጥሬ ሥጋዎች (ሙታን) መስሎት የሕይወት ምግብ የተባለ (ክርስቶስን) ባየ ጊዜ ሊበላው ጎመጀ ። አገኘው ብሎ ተሰገብግቦሞ በላው ፤ ነገር ግን ሥጋው እንደዚህ ቀደሞቹ ሥጋ አልነበረም ። ሥጋው ኢመዋቲ ከሚባል የሥጋ ቅመም (መለኮት) ጋር ተዋሕዶ ተሰርቶ ነበርና ለአፉ (ለመቃብር) አልጣፈጠውም ። ሆድ የተባለም (ሲኦል) ውጦት የነበረው የሥጋ ማባያ (ነፍስም) ኢመዋቲ ከሚባል ቅመም (መለኮት) ጋር ተዋሕዶ ነበርና ለሆድ( ሲኦል) አልተስማማውም ። ስለዚህም ሆድ (ሲኦል) ተረበሸ ፣ ተጨነቀ ፣ ወደ ላይ ወደ ላይ ይለውም ጀመር ፤ አልቻለምና አስመለሰው ፤ ያን ጊዜ አስቀድሞ የበላቸው ምግቦች (ነፍሳት) ግልብጥ ብለው ወጡ ። ዛሬ! ሞት በእውነት ክርስቲያን ሲሞት ያስፈራዋል ። አሁንም ያስመልሰዋልና ።

መልካም በዓል ወዳጄ
+++++++++++
ዲ/ን ዘአማን
16/08/2014
አዲስ አበባ
1.7K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 06:39:51
"እናቴ ማርያምን ባሰብኳት ጊዜ አለቀስኩ"

አንድ ወቅት ላይ ነበር ይህን ከላይ የምትመለከቱትን ምስል በfacebook ገጽ ላይ ያገኘሁት ። ይህች እናት የልጇን መርፌ እርሷ የተወጋች እስኪ መስል ድረስ መሸማቀቋን ፊቷ ያሳብቃል ። ይህን ስሜት ለመረዳት ሞኮርኩ ግን አልቻልኩም እናት መሆን ካልቻሉ አይረዱትምና። ምስሉ ሳላስበው ልቦናዬን ወደ ቀራንዮ ወሰደውና የልጇን መከራ በአይኗ ትመለከት ስለነበር ስለ አንዲት እናት አሰብኩ ።

ያቺስ እናት በዚያን ጊዜ እንዴት ሆና ይሆን!?


ልጇ..ሥጋን ከአጥንት በሚለይ ጅራፍ እየተገረፈ ስታይ የነበረችው ይህች እናት ልቧ ምን ያህል በሀዘን ጅራፍ ተገርፎ ይሆን!?

ልጇ...ጭንቅላትን የሚሰነጥቅ የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ተደርጎበት ስታይ የነበረችው ይህች እናት ምን ያህል ነፍሷ በሀዘን ተሰንጥቃ ይሆን!?

ልጇ...እጅና እግሩ በሚስማር ሲቸነከር የምታየው ይህች እናት ሚስማሩ ሲመታ ሰውነቷ እንዴት ተሸማቅቆ ይሆን! ?

ልጇ...በቀራንዮ አደባባይ ዕራቃኑን ሲሰቀል የምታየው ይህች እናት ኅሊናዋ በለቅሶ እንዴት ተሰቅሎ ይሆን?!

ልጇ...በመስቀል ላይ ተጠማሁ እያለ ሲጮህ የምታየው ይህች እናት አንጀቷ እንዴት ተንሰፍስፎ ይሆን?!

ህጻን ሳለ ልጇን ሄሮድስ እንዳይገልባት በግብጽ በረሀ ተንከራታ አስመልጣ ፣ እንዲህ የተቸገረችለት ልጇ እንደወንጀለኛ ሲሰቀል ያየችውን ፣ ስትወልድ ያላገኛት ምጥ ፣ ልጇ ሲሰቀል ግን የተሰቃየችው እናት ወደ ኋላ ተመልሼ አስተዋልኳትና

" እናቴ ማርያምን ባሰብኳት ጊዜ አለቀስኩ"

ዲ/ን ዘአማኑኤል ገዛኸኝ
2013 ዓ. ም
ሐዋሳ
911 views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 22:33:41 “ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።” እንዲል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ 2ኛ ተሰሎንቄ 3፥6 ክርስቲያናዊ ሕይወት ማዕከል ሊያደርግ የሚገባው አንዱ ሥርዐት ነውና አጿማትን (ዓቢይ ጾም ጾመ ነቢያትን) ፣ በዓላንት ምንነትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነና በሊቃውንት ትርጓሜና ሐተታ አስውቦ ያቀርብልናል ። የሐዲስ ኪዳን ምሥጋና ምን መምሰል አለበት በሚል የመዝሙር ንዋያተ ቅድሳትን አጠቃቀምም በተመለከተ ጎራ የያዙ ሊቃውንትን በሚያስታርቅና < ልዑል ኦርቶዶክሳዊ አእምሮን > በሚሰጥ አቀራረብ አስገራሚ ሀሳቦችን አንስቷል ። እንዲህም ብሎ ሀሳቡን ይጠቀልለዋል ፦
“ እናስተውል፡ “በሐዲስ ኪዳን መዝሙር እንኳን ያለ መሣሪያ መቅረብ አለበት የሚሉ ቅዱሳን አበው መኖራቸውን ከተመለከትን ዘፈን መስማት ይቻላል አይቻልም እንዴት ይባላል? የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ተጠቅመን የመዝሙር ግጥም ጽፈን ያለ መሣሪያ መጠቀም ወይም መሣሪያዎችን ራስን ከመግዛት ጋር ክርስቶሳዊ አድርገን መጠቀም እንዳለብን ቀደምት ሊቃውንት ከነገሩን ዘፈንን ለመዝፈንና በውስጣችን ያለውን ክፉ ፍትወት ለማርካት እንዴት እንደፍራለን? ዘፈን የተወገዘ ስለ መኾኑ ይህ ቃል በግሪኩ እንዲህ ነው በዕብራይስጡ እንዲያ የሚል ክርክር ውስጥ ከመግባት ይልቅ ሰውነታችንን ሕያው የኾነ መሣሪያ አድርገን ሕያው ምስጋና እናቅርብ፡ ይህ ለድኅነት የሚያበቃ ነውና! ” ገጽ 57-58


3. ስብከት

አንባቢው ራሱን በንባብ ውስጥ ከቶ እንዲመለከት የሚያደርጉ ፣ የሚመክሩ፣ የሚገስጹ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርን በማስረጽ ኦርቶዶክሳዊ አእምሮን የሚያድሉ ትምህርቶች የተነሱ ሲሆን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅጽር አስገብቶን ከመጻጉዖ አልጋ አስቀምጦ መጻጉን የሚያሰተዋውቀን ፣ በኒቆዲሞስ ሌሊት እንድንታደም የሚጋብዘን ፣ ከፍሬ አልባ በለሷ ጋር ለተግሣጽ የሚየቆመን ፣ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆኖ ከቤ/ክ መንፈስ ውጪ ከሆነው ይሁዳ እንድንለይ የሚመክረን የጽሑፍ ዓምድ ነው ።

ባጠቃላይ ይህ " ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ " የተሰኘው መጽሐፍ ራስን መቀደስ እንደሚገባ በሚያሰረዳ ጽሑፍ ጀምሮ በኖኅ መርከብ በተመሰለችው ቤተ ክርስቲያን አስገብቶ ከበዓላቶቿ ከአጿማቶቿ ሥርዓቶች ያሳትፈናል ። በመርከቧ ውስጥ ሊኖረን ስለሚገባን ሕይወትም በመርከቧ ውስጥ ከተሳፈሩት መጻጉዕ ፣ ኒቆዲሞስ ፣ ይሁዳ ፣ ጥጦስ ፣ ባለ ሽቶዋ ማርያም...... ሕይወት እንድንማር ተጓዦቹን ያስተዋውቀናል ። ከመርከቡ ውጪ ሆነው ትችትና ኑፋቄ ከሚወረውሩትም ተጓዥ አንባቢውን ጠብቆ ፣ አጽንቶ ፣ ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ ሰጥቶ ለድኅነት ያበቃዋል

#የመጽሐፉ_ጠቀሜታ

በይዘቱ ዕቅበተ እምነታዊ እንደመሆኑ ከኑፋቄ ይጠብቃል ፣ ያጸናል ። ሥርዓተ ቤተክርስቲያናዊ እንደ መሆኑም ቤተ ክርስቲያን ይገልጣል ፣ ያርማል ። ስብከት እንደ መሆኑ በምግባር ያንጻል ። የብዙ ሊቃውንት እይታ የታከለበት እንደመሆኑም ሕሊና አበውን (mind of fathers) የሚሰጥና የድኅነትን መንገድ የሚያሳይ ነው ።

ለምናነብ ለኛም እግዚአብሔር በቸርነቱ ኦርቶዶክሳዊ አእምሮን ያድለን!!!!

ዲ/ን ዘአማኑኤል ገዛኸኝ
2014/07/18
ሐዋሳ
1.5K views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 22:33:41 ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

#መቅድመ_ነገር

እንደ ዕድል ሆና ይህቺ መጽሐፍ ከአዘጋጁ ቀድማ እጄ የገባች መጽሐፍ ነበረች ። ( አዘጋጁ ሻሸመኔ ስለ ነበረ ነው! ) ። <ይደልዎ ለዘያነብብ ቅድመ ይዝክር ስሞ ለባዕለ መጽሐፍ> እንዲል ዲ/ን ዮሐንስ በተለያዩ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ ያለ ወንድማችን ሲሆን " ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ " በሚል ርዕስ ከቅዱሳን አበው ፣ ከቀደምት ሊቃውንት እና ከቅርብ መምህራን የተቀሰሙ ትምህርቶች ቀስሞ ያዘጋጀው 3ኛው መጽሐፉ ነው ። ከዚህ ቀደም ከእሁድ አንስቶ እስከ አርብ ድረስ የተፈጠሩ የፍጥረታት ወርቅ የሆኑ ምሥጢራት በአንጥረኞቹ ሊቃውንት እይታ የሚያስቃኝ " መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት " የተሰኘ መጽሐፍና በተአምረ ማርያምና በነገረ ክርስቶስ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ያዘጋጀው " ትምህርተ ጽድቅ " የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባብያን አድርሷል ።

#የመጽሐፉ_ርዕስ

ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ_orthodx mind
ኦርቶ፦ (የቀና ፣ ርቱዕ ፣ ትክክለኛ) ፣ ዶክስ (ትምህርት ፣ አረዳድ) የሚል ፍቺ ሲኖረው አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላቸው " አእምሮ " የሚለውን " መረዳት ፣ ዕውቀት " ብለው ይተረጉሙታል ። በመሆኑም መጽሐፉ ትክክለኛ ፣ ቀና ፣ ርቱዕ የሆነውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወደ መረዳት የሚመራ መጽሐፍ ነው ።

" ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ " ማዕከላዊ ሃሳብን ያየዘ ሲሆን ምክንያትና ውጤት ፣ መነሻና መድረሻ ያለው ስያሜ ነው ። መነሻው ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ (Orthodox teaching) ሲሆን መድረሻው የድኅነትን መንገድ ማሳየት ነው ። አንድ ሰው ኦርቶዶክሳዊ አእምሮን ለማግኘት በቅድሚያ በመጽሐፍ ቅዱስና በቀደምት የቤተ ክርሲቲያን አበው የትምህርት መሰረት ላይ መቆም አለበት ። በዚህም ኦርቶዶክሳዊ መረዳትን ያገኛል ። በመረዳትም ብቻም አያቆምም በድኅነት(Salvation) መንገድ ይጓዛል ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ St. Gregory Nazianzen "የጥበባችን (የስብከታችን) ዓላማ ለነፍስ ክንፎችን መስጠት፥ ከዓለም አደጋ አድኖ ለእግዚአብሔር መስጠት፤ ... በአደጋ ውስጥ ያሉትን ለመመለስ፤ በሕውከት ውስጥ ያሉትን ክርስቶስ በመንፈስ በልቡናቸው ውስጥ እንዲያድር ለማድረግ ነው።" እንዲል ።

#መጽሐፉ_ዓላማ

በመቅድሙ ላይ " ምክንያተ ጽሒፍ " የተሰኘውን የመጽሐፍ መሰረታውያን ባይገለጽም አንባቢው ግን መጽሐፉን አንብቦ ከጨረሰ በኋላ የመጽሐፉን ዓላማ በግልጥ መረዳት ይችላል ።
ጸሐፊው ዓላማና ግብ ብሎ ከተጠቀሳቸው የመጽሐፉ ጉዳዮች መካከል :-

1. ዕቅበተ እምነት

“ መናፍቃን ... በወደቁበት የአስተሳሰብ ውድቀት እኛንም ለመጣል በብዙ ስልታዊ መንገድ ሊመጡ የሚችሉ መኾናቸውን አስቀድሞ መረዳት ያስፈልጋል ። እነርሱ የሚያቀርቡልንን የተሳሳተ ሐሳብ እንደ እውነት አድርገን እንድንቀበል እኛ ከምናምነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ አንዳንድ ጥቅሶችን ይወረውራሉ። ከማር ይልቅ የሚጣፍጠውን ቃለ እግዚአብሔር አሳይተው ወደ ውስጥ ይከቱንና በተንኮላቸው መረብ ያጠምዱናል። ስለዚህ በእጅጉ ተጠንቅቀን የቤተ ክርስቲያንን የመረዳት አእምሮ (The Church Mind) ማግኘት አለብን። እውነት የሚቀዳው ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ኾነ ልንሰማም የሚገባው በእርሷ በኩል ነው። ” ገጽ 12

2. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ማሳወቅ

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት የሚመለከቱ ጉዳዮች ተዳስሰዋል። ይህም የኾነበት ምክንያት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ተረድተን በእርሷ ሥርዓት ከእርሷ ጋር በአንድነት ለመጓዝ ነው። ( ገጽ 12)

3. ማጽናትና ማንጻት

“ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ትምህርታዊ ስብከቶች ተካትተዋል። ትምህርታዊ ስብከት ዋና ዓላማው ማሳወቅ፣ ማጽናትና ማንጻት ነው። ለክርስቲያን በዋናነት የሚሰበከው ማጽናትና ማንጻትን ማዕከል ያደረገ ስብከት ነው። ወደ እውነተኛው የክርስትና ሕይወት እንድንገባ፣ ከኃጢአት መንገድ እንድንላቀቅ ያግዛል ማለት ነው ። ” ገጽ 13

#የመጽሐፉ_ይዘት

ይህ ከ70 በላይ ሀገርኛ ፣ ከ700 በላይ የባሕር ማዶ ማመሳከሪያ ዋቢ መጻሕፍት ፣ በ276 የኅዳግ ማስታወሻዎች(Foot notes) የተሰነደው " ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ" የተሰኘው መጽሐፍ በ 350 ገጽና ሃያ ስምንት አርዕስት የተከፋፈለ ነው ። የመጽሐፉ አዘጋጅ በመግቢያው ላይ ስለ መጽሐፉ ምንነት ለመግለጽ የሞከረ ሲሆን በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በቅድስና የማይታወቁ ሊቃውንትን (ኦሪገን ፣ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ ፣ አውግስጢኖስ) አስተምህሮ በመጽሐፉ ውስጥ በነገረ ሃይማኖታዊ ትምህርቶቻቸው ሳይሆን በጎ የሆኑ ሞራላዊ ፣ ሥነ ምግባራዊና የትርጓሜ ሐተታዎች (Selective በሆነ approach) ስለ መጠቀሙና ለምን እንደተጠቀም ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል ።

እንደ መደገፊያም ካነሳው ሀሳብ መካከል

“ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በቅድስና የማይታወቁ ሊቃውንትን ተጠቅሜያለሁ። ምክንያቱም በነገረ አበው ትምህርት እነዚህ ሊቃውንት ልዩ አባቶች ተብለው ይጠራሉና ነው ። ይሄን የመሰለ ነገር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትርጓሜያት ውስጥም አለ። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በእምነታቸው ባይመስሉንም ባዘጋጁት የመዝገበ ቃላት መጽሐፍ ይታወሳሉ። እርሳቸውን ሙሉ በሙሉ አልፈልግም የሚል መዝገበ ቃላቸውን ከመተው ነው መጀመር ያለበት። በትርጓሜያችን ደግሞ አውሳብዮስ ተወስቷል። አውሳብዮስ ዘቂሳርያ አርዮሳዊ መኾኑ ይታወቃል። ነገር ግን በወንጌል ትርጓሜ ላይ ያበረከተው አስተዋጽኦ በእኛ ትርጓሜ ተቀምጧል። የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ስንልም በዋናነት የሚጠቀሰው የእርሱ "የቤተ ክርስቲያን ታሪክ" የሚለው 10 ቅጽ ያለው ትልቅ መጽሐፍ መኾኑን ልብ ይሏል። እርሱን ስሕተቱን ትተን መልካም ሥራውን አንቀበልም ካልን የቤተ ክርስቲያንን የሦስት መቶ ዓመታት ታሪክ በአግባቡ ማወቅ አንችልም ። ” ገጽ 14

በዚህ መጽሐፍ የተካተቱ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ኦርቶዶክሳዊ ዕውቀትን የሚሰጡ ሲሆኑ በ3 አይነት የጽሑፍ ምድቦች የሚመደቡ ናችው :: እነዚህም

1. ዕቅበተ እምነት(apology )

መናፍቃን ዛሬም ቅርጻቸውን እየለዋወጡ በዛው ልክ የትምህርቶቻቸውና የጥያቄዎቻቸውንም ቅርጽ በመለዋወጥ የሚያነሷቸውን ሀሰተኛ ትምህርቶች ምን እንደሆነ ይገልጣል ። ስህተቶቻቸው ከምን የመነጨ እንደሆነ ለመግለጥ ይሞክራል ። በመቀጠልም በአበውና በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ለቤተ ክርስትያን ጥብቅና ይቆማል( defensive) ። ጥብቅና በመቆም ብቻ አያቆምም ገፍቶ " ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል " እያለ ተግዳሮታዊ የሆኑ ጥያቄዎችን (Challengeable question) በመጠየቅ ይሞግታል ።

ቅዱስ ሄሬኔዎስ “ መናፍቃን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሊጠቅሱ ይችላሉ፥ ኾኖም አተረጓጎማቸው በሐዋርያዊ ትውፊት ከተቀበለችውና ከጠበቀችው ከቤተ ክርስቲያን የእውነት መርሕ ጋር የማይስማማ በመኾኑ ትምህርታቸው ስሕተት ነው። " እንዲል ባለ ማወቅና ሆን ብለው በነገረ መላእክት ፣ በነገረ ድኅነት ፣ በህጻናት ጥምቀት ፣ ታቦት ፣ ቅዱሳን ሥዕላት...ዙርያ ለሚያነሷቸው የተሳሳተ ትምህርታቸው መልስ ይሰጣል ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪም በገድለ ተክለ ሐይማኖት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ይሰጣል ።

2. ሥርዓት ቤተ ክርስቲያን
1.1K views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 22:33:41
882 views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 10:59:09 ማስያስ

#መቅድመ_ነገር

መጽሐፏን ያገኘኋት ከፌስ ቡክ ጥያቄና መልስ ፡ በሽልማት መልክ ነበር ። እንደ አጋጣሚ ሀዋሳ ነበርኩና በአንዲት በጓደኛዬ በኩል መጽሐፉን ተቀብዬ ለመጽሐፉ አዘጋጅ ልባዊ ምስጋናን በማቅረብ መጽሐፉን አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ አጠር ያለች ይዘታዊ ዳሰሳ (content review) ለማዘጋጀት ቃል ገብቼ ነበር ። ብዘገይም በቃሌ ተገኝቻለሁ ። ይኸው እነኋችሁ!!!

#የመጽሐፉ_ርዕስና_ዓላማ

ማስያስ ፦ በአረማይክ መሲሕ ፣ በዐረብኛው አልመሲሕ በግሪኩ ደግሞ ማስያስ እያልን የምንጠራውን ሥግው ቃል መድኃኔዓለምን ጥዑመ ስም የያዘ ነው ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት " ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ " ያለው ግዘፍ አካል ነስቶ ለአፍ የሚጥም ፣ ለጆሮ ደስ የሚያሰኝ ፣ ለአጋገር የሚመች ፣ ለዓይን የሚስብ ፣ ለንባብ በሚጋብዝ ምጥን ቃል " ማስያስ " በሚለው ስያሜ አግኝቼዋለሁ ።

በመጽሐፉ ሽፋን ገጽ ላይ ጸሐፊው ስለ መጽሐፉ ጠቅላይ ዓላማ (General Objective) " የኦርቶዶክሳዊው ነገረ መለኮት መቅድማዊ ነጥቦች " በማለት መሠረታዊ የሆኑ የነገረ መለኮት ጽንሠ ሃሳቦችን (Conceptual framework of Theology) ሊያስውቅ የሚችል መጽሐፍ እንደሆነ ለመግለጽ ሞክሯል ።

መምህር ብርሃኑ አድማስም ስለ በመጽሐፉ ኆኅት በተገብቶ ዲ/ን ሚኪያስ መጽሐፉን ማስያስ ያለበትን ምክንያት " ክርስቶስ የትንቢት ሁሉ ፍጻሜ ፣ የንባብ ሁሉ ትርጓሜ ፣ የምሳሌያትና የጥላዎች ሁሉ ጥላ አካል ፣ የስብከትና የትምህርት ሁሉ መዳረሻ የአገልግሎት ሁሉ ዓላማ ፣ የጉባኤያት ሁሉ ጉዳይ ፣ የምሥጢራት ሁሉ ማኅተም ፣ የሕይወት ሁሉ እስትንፋስ መሆኑን የሚያምኑ አገልጋዮች ተግባራቸው ሁልጊዜም ይህንኑ እርሱን በምእመናን ልቡና ለማሰደር የሚረዱ ትምህርቶችን ፣ ጽሑፎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ ነው ። ዲያቆን ሚኪያስም መጽሐፉን " ማስያስ " ያለበት ምክንያት ይኸው የአገልግሎታችን ሁሉ ማዕከል እና የቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ምሥጢር እርሱ መሆኑን ለማሳየት ይመስለኛል ። " በማለት የመጽሐፉን ወሳኝ ዓለማ (Critical Objective) ያብራራል ።

#የመጽሐፉ_ይዘት

ይህ በ327 ገጽ ፣ ከ40 በላይ ሀገርኛ ፣ ከ50 በላይ የባሕር ማዶ ማመሳከሪያ ዋቢ መጻሕፍት ፣ በ300 የኅዳግ ማስታወሻዎች(Foot notes) የተሰነደው " ማስያስ " የተሰኘው መጽሐፍ በሰባት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን

#ምዕራፍ_1 = ኦርቶዶክሳዊ ፍኖተ አእምሮ

- ሃይማኖትን (ክርስትና) የአእምሮ ሕመም (Mental Illness) አድርገው እምነት (Faith) እና አመክንዮ (Reason) በጽንፍ ተቃርኖ ውስጥ ያሉ አድርገው በስህተት ለሚጓዙት የስህተታቸውን ምንነትና የስህተቶቻቸውን መንስኤ ይገልጻል ። ውግንናውን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በማድረግ በማስረጃ ይሞግታል ።

- በነገረ መለኮት ትምህርትም ሰፊ ቦታ የሚሰጣቸውን ዕውቀት ፣ አእምሮ ጠባዐይ ፣ አእምሮ መንፈሳዊና ምስጢረ ሥላሴ የተሰኙ ወሳኝ ጉዳዮች ሲያብራራ በተጨማሪም የባሕርየ እግዚአብሔር (Essence of God) አይመረመሬነት በኢ- አውንታዊ ነገረ መለኮት (Negative Theology) የተቃኘውን የአበውና ሊቃውንት ትምህርት ያቀርባል ። እንደ ማጣፈጫ ጨው ከተጠቀሳቸውም መካካል
" በነገረ መለኮት ዕውቀታቸው የተመሰገኑ ሕንዳዊው ሊቀ ጳጳስ ጳውሎስ ማር ጎርጎርዮስ ስለ ልዑል እግዚአብሔር መጻፍ ሲጀምሩ እንዲህ ይላሉ " ስለ እግዚአብሔር ማንነት እንዳስተምር ብጠየቅ ፡ የማስታወሻ ወረቀቶቼን ይዤ ወጥቼ የትምህርቴን ርእስ ተናግሬ ለረዥም ሰዓት ዝም ብዬ ከቆየሁ በኋላ ስላዳመጣችሁኝ አመሠግናለሁ " ብዬ ከመናገርያ ቦታዬ እወርዳለሁ " በማለት ጥልቅ ነገርን ተናግረው ነበር ። " ገጽ 29

#ምዕራፍ_2 = ፍጥረት

- ከላይ በአሚነ እግዚአብሔር የተወጠነው ትምህርት በዚህ ምዕራፍ በአእምሮ ፍጥረተ ዓለም ይጸናል ። በትልቁ ዓለም የሚኖረው ትንሹ ዓለም (Microcosm)፣ ግሩምና ድንቅ የሆነው የሰው ልጅን የፍጥረት ሁሉ ዘውድ የሆነበትን ምክንያት ይዳስሳል ።

- በመቀጠልም በእግዚአብሔር አርአያና መልክ የተፈጠረው የሰው ልጅን ድቀትና ድኅነት በሰፊው ያስቃኛል ።

#ምዕራፍ_3 = የመገለጡ ጥላዎች በብሉይ ኪዳን

- "ሐዲስ ኪዳን ማለት የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ ነው " እንዲሉ ወንጌል ሳትሰራ ወንጌልን በጻፉ በብሉይ ኪዳን ወንጌላውያንና በዘመነ አበው ፣ በዘመነ መሣፍንት ፣ በዘመነ ነቢያት ፣ በዘመነ ነገስት " ታሪኮች " ማስያስ "ን እያሳየ ያስደንቀናል ።

- የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መካከለኞች ፣ የሰማያዊ ሙሽራ እናትና ጓደኛ ያስተዋውቀናል ። በተለይን እናቱ በነገረ ድኅነት (Soteriology) ለሰው ልጆች መዳን ስለ አላት ድርሻ ያሳውቀናል ።


#ምዕራፍ_4 = ሥጋዌ

- ቀደም ሲል የሙሽሮቹን እናትና ጓደኛ ያስተዋወቀን ፤ አሁን ደግሞ ሰማያዊው ሙሽራ ማስያስን ያስተዋውቀናል ። የሰርጉ ባለቤት(ማስያስ) ፣ የሰርጉን ዓይነት (ተዋሕዶ) ፣ የሰርጉን ዕለት፣ ሰዓትና ቦታ የሚገልጽ........የሰማያዊ የሰርግ ጥሪ ካርድ ይሰጠናል ።

#ምዕራፍ_5 = ነገረ ቤተ ክርስቲያን

- የሰርጉን የጥሪ ካርድ ይዘን ወደ ሰርግ ቤቱ(ቤተ ክርስቲያን) ይወስደናል ።

#ምዕራፍ_6 = ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓተ አምልኮ

- የሰርጎች ሁሉ ሰርግ በሆነው(ቅዳሴ) ድግስ ያሳትፈናል ።

#ምዕራፍ_7 = ሱታፌ አምላክ
-ከሰርጉ ማዕድ አሳትፎ ከሙሽራው ጋር ያዛምደናል ።


#የመጽሐፉ_ጠቀሜታ

" እስመ ረኪበ ቀጢናት በቀጢናት ፣ ወረኪበ ገዚፋት በገዚፋት ፤ ቀጢን ውእቱ ነገረ መለኮት ወየኀሥሥ ኅሊና ቀጢነ " እንዲሉ አበው ፣ መጽሐፉ ነገረ መለኮታዊ እንደመሆኑ የረቀቀና የመጠቀ ኅሊናን ይሻል። ነገር ግን የመጽሐፉ አዘጋጅ የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን የነገረ መለኮት ሐሳቦች አጉልቶ የታሪክና የሀሳብ ፍሰቱን በጠበቀ አጻጻፍ ውብና ሁሉም አንባቢ ሊረዳው በሚችልና ቀጢነ ኅሊናን በሚሰጥ መልኩ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው ።

ሚከዋ ብዕርህ ትለምልም!!!

መቅድሙ እንዲህ ከሆነ ውስጡ እንዴት ይሆን?

ዲ/ን ዘአማኑኤል ገዛኸኝ
2017/07/11
ሐዋሳ
1.2K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 10:59:09
997 views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ