ሲኦልን አስመለሰው
አፍ የተባለ (
መቃብር) ሁልጊዜ ይበላል ። በአፉ ያላምጥ በጨጓራውም (
የሲኦል እሳት) ይፈጭ ነበር (
በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ሲኦል) ። ከዕለታት አንድ ቀን አፍ የተባለ (
መቃብር) ከዚህ ቀደም ሲመገብ እንደ ነበራቸው ጥሬ ሥጋዎች (
ሙታን) መስሎት የሕይወት ምግብ የተባለ (
ክርስቶስን) ባየ ጊዜ ሊበላው ጎመጀ ። አገኘው ብሎ ተሰገብግቦሞ በላው ፤ ነገር ግን ሥጋው እንደዚህ ቀደሞቹ ሥጋ አልነበረም ። ሥጋው ኢመዋቲ ከሚባል የሥጋ ቅመም (
መለኮት) ጋር ተዋሕዶ ተሰርቶ ነበርና ለአፉ (
ለመቃብር) አልጣፈጠውም ። ሆድ የተባለም (
ሲኦል) ውጦት የነበረው የሥጋ ማባያ (
ነፍስም) ኢመዋቲ ከሚባል ቅመም (
መለኮት) ጋር ተዋሕዶ ነበርና ለሆድ(
ሲኦል) አልተስማማውም ። ስለዚህም ሆድ (
ሲኦል) ተረበሸ ፣ ተጨነቀ ፣ ወደ ላይ ወደ ላይ ይለውም ጀመር ፤ አልቻለምና አስመለሰው ፤ ያን ጊዜ አስቀድሞ የበላቸው ምግቦች (
ነፍሳት) ግልብጥ ብለው ወጡ ። ዛሬ! ሞት በእውነት ክርስቲያን ሲሞት ያስፈራዋል ። አሁንም ያስመልሰዋልና ።
መልካም በዓል ወዳጄ
+++++++++++
ዲ/ን ዘአማን
16/08/2014
አዲስ አበባ