Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ timihert_minister — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ timihert_minister — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @timihert_minister
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.06K
የሰርጥ መግለጫ

ተጨማሪ መረጃዎችን
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም-https://t.me/timihert_minister
ይከታተሉ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-13 19:04:56
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀ፡፡
------------------------
መጋቢት 4 /2015ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ዓመት መጨረሻ በሚሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ደያ ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን በስነ-ልቦና የማዘጋጀት ስራ እየሰራ እንዳለም ም/ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ 62 የትምህርት ክፍሎች የማሰልጠኛ ማኑዋሎችን አዘጋጅተው ለተማሪዎቻቸው ስልጠና በመስጠት ላይም እንደሆነም ዶ/ር ሙላቱ አክለዋል።

ለተማሪዎችም በትምህርት መስኩ ማወቅ የሚገባቸውን አበይት ነጥቦች ተዘጋጅተው ዝግጅት እንዲያደርጉባቸው ተደራሽ መደረጉንም ተናግረዋል።

ተማሪዎቹም ፈተናውን እንዲለማመዱና የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው የተለያዩ ሞዴል ፈተናዎች ተዘጋጅተው እየተሰጡ እንዳሉም ም/ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

በፈተናው ወቅት ኩረጃ እንዳይኖር ከማድረግ አንፃር ፈተናዎችን በኮምፒዩተር የታገዘ ለማድረግ ሶፍት ዌር የማልማትና ግብዓቶችን የሟሟላት ስራ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና በሀገራችን አዲስ አይደለም ያሉት ም/ፕሬዚዳንቱ የህግና ጤና ተማሪዎችን ከዚህ በፊት አስፈትነው መልካም ውጤት ያስመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው እሱን እንደ ልምድ በመውሰድ በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሀግብሮች በግልና በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።
2.4K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 19:37:40
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለጋሞ ባይራ አዳሪ ትምህርት ቤት ግብዓት ለማሟላት እየሰራ ነው።
-----------------------------------------------

የካቲት 27/2015ዓም .(የትምህርት ሚኒስቴር ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለጋሞ ባይራ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ግብዓቶችን የሟሟላት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የጋሞ ባይራ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጋሞ ልማት ማህበር ተነሳሽነት ተጀምሮ ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ ስራ ገብቷል፡

በዚህም 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዎቹን 214 የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ከሁሉም ትምህርት ቤቶች በ8ኛ ክፍል ውጤታቸው መሰረት በመመልመል የመማር ማስተማር ስራ ጀምሯል።

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር ተክሉ ወጋየሁ( ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ቤተ-መጽሐፍት፣ ቤተ-ሙከራዎችን እና አይ ሲቲ ክፍሎችን የማደራጀትና አስፈላጊ ግብዓቶችን የሟሟላት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ቤቱ መምህራንን ብቃትን መሰረት በማድረግ ከመመልመል ጀምሮ አስፈላጊውን የሙያ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፀዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02k6vw3joqHTVytv5KRyXVMouxpvedgNMGLk88yUi2W1GhNWAJcMeV4Ls5MvjESzQ8l&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
2.0K views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 21:38:28
ትምህርት ቤቶች ባልተስፋፉበት የደቡብ ኦሞ ዞን የአርሶና አርብቶ አደር አካባቢ ዳሰነች ወረዳ ህጻናት "መማር ያስከብራል" የሚለውን መዝሙር እንዲህ ባማረ አንድነት እየዘመሩልን ነው

ትምህርት ቤቶች ባልተስፋፉበት በረሃማ አካባቢ ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥ የሚማሩ እነኚህ ህጻናት ተምረው እንደዝማሬያቸው ሀገርን እንዲያኮሩ የሁሉንም አካል ትብብር ይሻሉ።

የተሻሉ ት/ቤቶች ለነገይቱ የኢትዮጵያ ልጆች!!

መማር ያስከብራል፤
ሀገርን ያኮራል።
2.6K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 16:40:17
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ
..............................................................................
የካቲት 24/2015 (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው የኦሞራቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድጋይ አስቀመጡ ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲና ሌሎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 20 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን ወጪው በደቡብ ክልል መንግስትና ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ-ሠናይ ድርጅት በጋራ እንደሚሸፈን ተገልጿል ።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ ከ1 ዓመት እስከ 2 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደምጠበቅም በመርሃ ግብሩ ተጠቅሷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
2.6K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 18:49:13
እንኳን ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል
በሰላም አደረሳችሁ።

ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ኩራት!

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር!
2.4K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 18:49:13
2.2K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 18:49:13
"የአድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሣይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነ የድል በዓል ነው" ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚንስትር
....................................................
የካቲት 22/2015 (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞችና  127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ  ዝግጅቶች አክብረዋል።

"የአድዋ ድል በዓል ለአገራዊ አንድነት፣ጀግንነት እና ጽናት መልህቅ" በሚል መሪ ቃል በተከበረው የድል በዓል ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሣይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነ የድል በዓል ነው ብለዋል።

ሚንስትሩ በመልዕክታቸው አያይዘው እንደተናገሩት የአድዋ ድል በአል የሁሉም ብሄር ብሄረሠቦችና ህዝቦች የድል በዓል በመሆኑ  ልዩነትና የጠብ መነሻ አድርጎ ለማሳየት የሚሞክሩ ሀይሎችን  እምቢ ማለት ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሣሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የአድዋ ድል በጋራ ቆሞ፣በቁርጠኝነት ሠርቶ ፣በጽናት ታግሎ በመቆም የበለፀገች ሀገር በመገንባት እንዴት  ለትውልድ ማስረከብ እንደሚቻል ታላቅ ትምህርት የምንቀስምበት የድል በአል ነው ብለዋል።

ሙሉ ዜናው

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02NKutruxocXAFzdtrAE5HitUkiyUowUJ2QRRqR84RKyXFW2oDmYQoQSddc8ciGUoPl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
2.0K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ