Get Mystery Box with random crypto!

Tesfaab Teshome

የቴሌግራም ቻናል አርማ tfanos — Tesfaab Teshome T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tfanos — Tesfaab Teshome
የሰርጥ አድራሻ: @tfanos
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.03K
የሰርጥ መግለጫ

ለአስተያየት @jtesfaab ላይ ይፃፋልኝ
ለመቀላቀል @tfanos ይጫኑ።
ቤተሰብ ስለሆንን አመሰግናለሁ ❤❤😍

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-25 22:30:03 ዳግም ጦርነት?

ዳግማዊው ጦርነት እየመጣ ነው። ምን ይዞ ይመጣ ይሆን? ይህ የእኛው ጦርነት የትልቁ ጦርነት አካል ይመስላል። የምን ይመስላል ነው፣ ነው እንጂ! ደግሞ የቱ ጦርነት አልክ እንዴ?

አዎ ዳግማዊው ጦርነት።

ቀዝቃዛው ጦርነት 2.0

የኃያላኑ ጦርነት የቀዘቀዘም ይሁን የፈላ እኛን ስቦና ጠልፎ ሊከተን መሻቱ ሳይታለም የተፈታ ነው።

ያለንበት አካባቢ ከባድ ነው። በዚያ ላይ ብዙ ህዝብ አለን። ደግሞ እጅ አንሰጥም ባይና ለአንዳንዶች ምሳሌ ነን። እናም ሁሉም "ና ወደኔ ና ወደኔ" እያሉ እየጎበኙን ነው።

ልብ በል ከዚህ ቀደም በነበረው የ2ተኛው የዓለም ጦርነት የኃያላኑ ፍትጊያ ለኛም ደርሶን አሽቶናል፤ የእኛም ሰዎች በጀግንነት ተፋልመዋል።

ከዚያም በኋላ በአሜሪካ ካምፕ እና በሶቭየት ህብረት ካምፕ ተከፍሎ ለ40 ዓመታት በዘለቀው ቀዝቃዛው ጦርነት 1.0 ገፈቱ ለእኛም ደርሶ ከሶማሊያ ጋር ተቆራቁሰናል።

ይህ የመጀመሪያው ቀዝቃዛው ጦርነት ጀርመንን መጀመሪያ 4 ቦታ ከፍሏት ነበር። በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በአሜሪካና በሶቭየት ምድብ ከፍሏት በኋላ ሦስቱ በአንድ ምድብ ገብተው ሶቭየት የያዘችውን ይዛ ለ40 ዓመታት ያህል ቆይተዋል።

ዛሬም ጅቡቲ ላይ ራሱ ያሉት የጦር ሰፈሮች ለእኛ አሳሳቢዎች ናቸው። ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ጃፓን እና ሌሎችም አሉ። በራችንን እንደማይጠረቅሙት ዋስትና የለንም።

አሁን ቀዝቃዛው ጦርነት 2.0 እየተቦካና እየተጋገረ ነው። የእኛም ምድብ እየለየለየት ይመስላል።

ከቀድሞው በባሰ ሁኔታ ምግብ የቀዝቃዛው ጦርነት አጀንዳ እየሆነ ይመስላል። ከስድስቱ የምግብ ቋቶች አንዱ የሆነው የሩስያና ኡክሬን የምግብ ቀጠና በጦርነት ላይ ነው። ሁለተኛውና የቻይና የምግብ ቀጠናም በአሜሪካ ግፊት ወደጦርነት እንዳይገባ ያሰጋል። ያ ከሆነ ዓለም በከፍተኛ የምግብ ችግር ውስጥ መውደቋ የማይቀር ነው።

የጸጥታው ምክር ቤት ምግብን መከልከል የጦር ወንጀል አድርጎ ቢያስቀምጥም ብዙዎች ድሮም ዛሬም እየተጠቀሙበት ነውና ይህ እንዳይደገም አሳሳቢ ነው።

እና ምን ይሻላል?

የሚሻለው ከምንግዜውም በበለጠ እርሻ ላይ ማተኮር ነው። ከመኪና፣ ውስኪና ፓርክ ይልቅ ግብርና ላይ የምናተኩርበት ጊዜ ላይ ነን። እህል ማከማቻዎቻችንንም ከጥቃት ክልል ራቅ ራቅ አድርጎ ማዘጋጀት ነው። እንቁላሎችህን አንድ ቅርጫት ውስጥ አታስቀምጥ ነው ነገሩ።

በአድዋ ድል ስንኩራራ ሳንዘጋጅ ቀርተን ጣልያን 40 ዓመት ቆይቶ ሲመጣ ለመትረየስና መድፍ እንጂ ለአውሮፕላን ውጊያ ስላልተዘጋጀን ብዙ ዋጋ አስከፈለን። አሁንም በካራማራ ድል እየተኩራራን 40 ዓመት ሞልቶናል። እኛ ለታንክና ጄት ውጊያ ስንዘጋጅ በረሃብ እንዳናልቅ ዝግጅት ያስፈልገናል።

መሬት ጦም እንዳያድር በልና እረስ!

ሁለተኛው ዙር ቀዝቃዛው ጦርነት እየመጣ ይመስላል። ሩስያ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ ሰሜን ኮርያ በአንድ ወገን ተሰልፈዋል። አሜሪካም ታሪካዊ አጋሮቿን ይዛ ተጨማሪ ድጋፍ እያሰባሰበች ነው።

እኛም ቁርጥ ያለ አቋማችንን ባናስታውቅም ወዴት እንደምናዘነብል ምልክት ሰጪ ሁኔታዎች የታዩ ይመስላል።

በዚህም አለ በዚያ የእህል ምርት ላይ ማትኮር ላይ እንዳንዘናጋ።

በበጋ ለማፈስ በክረምት እረስ ብቻ ሳይሆን በበጋ ላለመደቆስ በክረምት እረስ!

ይኸው ነው።

Cold War 2.0 might be loading >>>>

Duce luce paca

@Tfanos
206 views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:02:06 ለሰው ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊም ጠቃሚም መሆኑ ቢታወቅም ሁሌም እና ሁሉምን ሰው መደገፍን ጠቃሚም አስፈላጊም አድርጎ ማሰብ በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ልክ ሊሆን አይችልም!


#መስጠት_እወዳለሁ! የሚለውን ንግግር ውስጥ ምን ያህል?፤ ለማን?፤ ለምን? የሚለውን መመለስ በተጨማሪም እርግጠኝነት ለሚጎለው ነገ ምን አቅደሃል? የሚለውንም ጥያቄ መመለስ መቻል ግድ ነው፡፡


የሚቀጥለው ወር አስቤዛ ሳያስቀምጡ፤ ልጆች ድንገት ቢታመሙ ማሳከም የሚችል ጥቂት ብር ሳይዙ፤ ከቤት ኪራይ ቢባረር እቃ ማጓጓዣ ብር ሳያስቀምጥ፤ የመብራት አንፖል ቢቃጠል መቀየራ ብር ሳይኖረው፤ ወዘተ "እጄ ላይ ብር ካለ ለሰው መስጠት ያስደስተኛል!" ቢል ምክንያታዊ ነው?


ከሃይማኖት አስተምሮት አንጻር የተለያየ ምልከታ እና መልስ ሊኖር እንደሚችል እረዳለሁ! ነገር ግን እኔ የውይይቱን ሃሳብ ያመጣሁት ከሃይማኖት አስተምሮት ውጪ እንድንወያይበት ነው!


#ለምሳሌ፡- "ገንዘቡን ለማንም ሲበትን ኖሮ ልጆቹን በቤት ኪራይ ያሰቃያል!" የሚባል አባት ቤት መስራት የሚችልበትን የወጣትነት ዘመኑን ገንዘብ ለሰዎች ምክንያታዊም ሆነ ኢ-ምክንያታዊ በሆነ ምክንያት ሲያድል ከነበረ ከነባራዊው የኑሮ ትግል ቤተሰቡንም እራሱንም መጣሉ አይቀርም! ሰው መርዳት መልካም ሆኖ ሳለ እኔ የቆረቆዝኩት ለመስጠት ቅድሚያ በመስጠቴ ነው! የሚለው አባባል ትክክለኛ ሊሆን አይችልም!


#ለምሳሌ፡- በትጉነት ዘመን እየሰሩ ትጋታቸው ወደሚታይ ሃብትነት እስካልተለወጠ ድረስ "ሃብቴ የሰው ፍቅር ነው! የኢትዮጲያ ህዝብ ነው ሃብቴ" የሚሉ አባባሎችን የሚጠቀሙ ሰዎች በአብዛኛው የሰነፍ መልሶች እንደሆኑ ይሰማኛል፡፡ ለአስቤዛም ሆነ ለህክምና አዋጡልኝ ብሎ ህዝብን ማስቸገር ሰርቶ ከመታከም እና ከመሸመት እኩል ሊሆኑ አይችሉም!


ተፈጥሯቸው ሆኖ ለሰው ሲሉ ዓለማቸውን የሰጡ ሰዎች ከዚህ በፊት ነበሩም አሁንም  አሉ! ነገር ግን እነዚህ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች የነባራዊው ዓለም የኑሮ ተዋናዮች መገለጫ ሊሆኑ አይችሉም!


ማህበረሰባችን ውስጥ "ያለኝን ለሰዎች ባላካፍል ኖሮ ዛሬ የት ነበርኩ!?" የሚሉትም "ያለውን ለሰዎች ሲበትን ኖሮ እንጂ ቢያውቅበት ኖሮ ዛሬ የት ይደርስ ነበር" የሚሉትም አሉ፡፡


በማህበራዊ ኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ ሊኖራችሁ የሚገባው ግንኙነት ዋጋ ያለው እንዲሆን ይመከራል፡፡ በማህበራዊ የሰዎች እድገት ደረጃ ውስጥ ከሰዎች በምትክ የሚገኝ ምንም ምላሽ ሳይኖር መርዳት የመጨረሻው ደረጃ በመሆኑ ብዙዎቻችን ባለንበት ደረጃ በመደጋገፍ ውስጥ ምላሽ ተጠባቂ ነው፡፡


በየሰፈሩ ለታመመ፤ ለወለደ፤ ላዘነ እና ለተደሰተ የሚደረግ መዋጮ ስም ዝርዝር ይጻፍበትም አይጻፍበትም በሆነ ጊዜ ሰዎች በምትኩ ምንም አይጠብቁም? በገንዘብ ባይሆን እንኳ በድርጊት መልስ ይጠብቃሉ "ሃዘኔ/ደስታዬ ላይ ሳይገኝ!" የሚሉ መልሶች ትርጉም አላቸው፡፡


ከወዳጆቻችሁ ወይም ጓደኞቻችሁ መካከል ስንቶቹ ናቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትገቡ ዋስትና የመሆን ፍላጎትም ሆነ አቅም ያላቸው?


#ለምሳሌ፡- የ100ሺ ብር ዋስትና ብትጠየቁ ዋስ መሆን የሚችሉም የሚፈቅዱም ምን ያህል ጓደኞች ፈጥራችኋል? እንድትለወጡ የእውነት ከልባቸው የሚጥሩ ወይም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትገቡ በምክርም በጉልበትም ስንቶቹ በጽናት ከናንተ ጋር ይቆማሉ?


ስልኮቻችሁ ውስጥ የተደረደሩ ሰዎችን ዋጋ መዝኑ እና ጊዜዎቻችሁን/ገንዘባችሁን የምታጠፉላቸው ሰዎችን ዋጋ መዝኑ! የብዙ ሰዎች ጓደኛ መሆኑ ለአስቤዛ መተማመኛ ካልሆነ በግንኙነት መካከል በብዙ መለኪያ መስፈርት ማውጣት ግድ ነው፡፡


The Ethiopian Economist View

@Tfanos
228 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:23:31 https://www.facebook.com/100074121486426/posts/pfbid0bL822QYFF2D9mPZbH9cdLUEMHDrpVbYMY3BawLzdz3CnCrGp1GY6R1gPYCFSunwil/?app=fbl
280 views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 23:16:06 This too shall pass | ይህም ያልፋል

የማያልፍ ነገር የለም። ባለበት የሚቆም ነገር የለም። እንዳለ የሚቆይ ነገር የለም። ነገሮች ይቀየራሉ። ቋሚው ነገር ለውጥ ብቻ ነው።

ለአረንጓዴው ዘመቻ ለአረንጓዴው
በርቱ ጭቁኖች ድሉ የኛ ነው

ብለን ችግኝ ተከልን። የመስኖ ቦዮች ተሠሩ። መሬት ታረሰ። ይህ ሁሉ የህዝብ ሥራ ባለቤት አልነበረውም። ያኔ ዛፍ ለመቁረጥ ቀበሌ ማስፈቀድ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ድርቅና ረሃብ አልቀረልንም። ኋላ ላይ ዛፎቹ ተቆረጡ።

ድርቅን ለመሸሽ ሰዎችን ከቦታ ቦታ አዛውረን አሰፈርን፣ በቆሎ አመረትን፣ ለመሪው እሸት ላክን። ከችግሩ ግን አልወጣንም። ዓመታት ቆይተን እንደገና ተራብን።

አይኖሩም አይኖሩም የማያነቡ ዓይኖች
አይኖሩም የማይጽፉ ጣቶች

ብሉን መሃይምነትን ለማጥፋት መሠረተ-ትምህርት ለማስተማር ዘመትን፣ በየዓመቱ ጀማሪ፣ ማጠናከሪያ፣ ድህረ እያልን አስተማርን፣ መሃይምነት ግን አልጠፋም።

ታጋይ ጀግና ፈፋ ለፈፋ
በጦር ሜዳ ጠላት ሲደፋ
ኢትዮጵያ ኑሪ ሀገሬ
አትደፍርም ዳር ድንበሬ

ብለን ሀገር ለመጠበቅ ብሔራዊ ውትድርና ዘመትን፣ በቅጥርም ብዙ ሆነን ዘመትን፣ ግን ድንበርና ግዛት አልተከበረም፣ እንዲያውም ግዛት ተወሰደ፣ ድንበር ተቀየረ።

ከችግር መውጣት ውስብስብ አይደለም። It is simple. But, it is not simple. ነገሩ ውስብስብ አይደለም ግን ቀላል አይደለም፤ ሥራና ተከታታይነት ያለው ዲሲፕሊን ይጠይቃል።

ችግር በዘመቻ አይጠፋም። ይህንን እንድንል የመጣንበት መንገድና ልምድ ያስገድደናል።

"ነጋ ጠባ ዘመቻ ትላለች" ሮማን ኅለተወርቅ ምርር ብሏት በኦሮማይ ላይ በበዓሉ ግርማ አንደበት። እንደዘመቻችን ብዛት የት በደረስን ነበር።

እኛ እድገት በህብረት ብለን በዘመቻ ስንናጥ እነ ቢል ጌትስ እና ስቲቭ ጆብስ ኩባንያ እየመሠረቱ ነበር፤ እነ ኤሎን መስክ ደግሞ የኮምፕዩተር ፕሮግራም ይጽፉ ነበር።

እነዚህ ሰዎች እያንዳንዳቸው የመሠረቱት ኩባንያ እና የሚያስተዳድሩት ሀብት ከኢትዮጵያ በብዙ እጥፍ ይበልጣል። ተጽዕኗቸውም እንደዚያው እጅግ ከፍ ያለ ነው።

ትውልዱ እንዲማር የሚያስፈልገው ተመሳሳይ ነገርን በመድገም ያንኑ ውጤት መድገም እንጂ የተለየ ነገር መፍጠር እንደማይቻል ነው።

ንቃ! ከዲስኩር ማዳመጥ ውጣ።

በየቀኑ ባይቻል ቢያንስ በሳምንት አንድ ነገር አሻሽል።

ሁሉም ያልፋል፣ ጊዜም ጭምር። የሚያልፈው ጊዜ ላይ የማያልፍ ነገር ጫንበት።

ዘለቄታዊ ለውጥ ላይ አተኩር።

Duce luce peaca

@Tfanos
309 views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:47:08 ብራቮ ኬንያ !!!

ኬንያ በቅርቡ ዋና ከተማዋን ናይሮቢን እንደነ ኒዮርክ ጄኔቭ እና ብራስልስ አይነት ትልቁ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ እና ኮንፈረንስ ከተማ ለማድረግ እየሰራች ነው ።

በ2022/23 ዓ.ም ብቻ 94 ትልልቅ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን አዘጋጅታለች ወይንም ታዘጋጃለች ። ከነዚህ መካከል 63 (64) ያህሉ በጎረቤት አገር ይዘጋጅ የነበረ እድልን ነው የነጠቀችው ።
ይህም ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የተገኝ ትልቅ ድሏ ነው ።

ብዙ አለም አቀፍ እና አሁጉራዊ ተቋሟት ዋና መስሪያ ቤታቸውን በፊት ከነበሩበት የኬንያ ጎረቤት ከተማ ነቅለው ነው ወደ ኬንያ የሄዱት ።

ይህ ለኬንያውያን ከ ኮንፈረንስ ቱሪዝም እና ተቋሟቱ ከሚተዳደሩበት የውጭ ምንዛሬ በጀት ትልቅ ገቢን የሚያስገኝላቸው ሆኗል ።

ኬንያ ከምስራቅ አፍሪካ በኢኮኖሚም በፖለቲካም ሆነ በዲፕሎማሲም ከፍታውን በመያዝ አካባቢያዊ ተፅዕኖን መፍጠርን ታሳቢ ያደረገች ይመስላል ። የቀራት የአፍሪካ ህብረት መቀመጫን ወደ እርሷ ማምጣት ነው ። ያሉትን ሁኔታዎች ስናይ ደግሞ በሂደት ይህ አይሆንም ብሎ መገመት ያስቸግራል ።

ምክንያቱም አሁን የአፍሪካ ህብረት ያለበት ከተማ እድገት ለአህጉራዊ መቀመጫነት ያለው Grace ,Characterstics እና conformity ን ማየት ይቻላል ። character Assassination ተካሂዶበት ይሆን? የሚያሰኝ ነው ።

ለአገራዊ ዋና ከተማነትም እንኳን ብዙ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ኹነቶች እያተስተናገደበት መሆኑ ሊያደበዝዘው የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል ።

በ2014 ዓመት ምህረት በሚያዚያ እና ግንቦት ወር ብቻ በኬንያ ሪዞርት እና ሆቴሎች ውስጥ ጋብቻቸውን የፈፀሙ ኢትዮጵያዊያን ጥንዶች ቁጥር አስራ ስምንት ደርሶ ነበር ።

እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ኬንያ ውስጥ ነዋሪ ሆነው ሳይሆን ሁለቱም ሙሽሮች ወይንም አንዱ ከአዲስ አበባ ሌላው ከምዕራብያውያን ተነስተው በመሄድ ነበር የተሞሸሩት ።

ኬንያን ምርጫቸው ያደረጉበት ምክንያት ለጊዜው ባይታወቅም የበለጠ ምቾት ደስታ ፈልገው እንደሚሆን መገመት አይከብድም ። ኬንያውያን የሆቴል እና ሪዞርት ባለቤቶች ኢትዮጵያዊ ማርኬቲንግ ማኔጀርን መቅጠር ጀምረዋልም ይባላል።

ኬያውያኑ አገራቸውን የምስራቅ አፍሪካ ብሎም የአፍሪካ ልዕለ ኃያል ( African Gate ) አድርገው ለማቅረብ እየሰሩ ነው ።

ከነብዙ ችግሮቻቸው ጋር እንዲህ መስራታቸውን አለማድነቅ እንዴት ይቻላል ?


@Tfanos
428 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 12:49:15 #Cobra_Effect!


እንግሊዛውያን ህንድን በቅኝ ግዛት ያስተዳድሩ በነበረበት ጊዜ እንዲህ ሆነ።


በህንድ ሀገር በደልሂ ከተማ የመርዘኛ ኮብራ እባቦች መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ደረሰ። እንግሊዞችም የእባቦቹን ቁጥር ለመቀነስ መፍትሄ ያሉትን አስቀመጡ። ኮብራ እባብ ገሎ ይዞ ለሚመጣ ማንኛውም ግለሰብ ከመንግስት ሽልማት እንደሚበረከትለት አዋጅ አስነገሩ።


ይህን ተከትሎም የእባቦቹን ቁጥር ለጥቂት ጊዜ ለመቀነስ ተቻለ። ከጊዜ በኋላ ግን ህንዳውያኑ ሽልማት ለማገኘት ሲሉ በየጓሮቸው እባብ ያረቡ ጀመር።



ይህን የተረዳው የእንግሊዝ መንግስትም አዋጁን ሽሮ ሽልማት መስጠት አቆመ። በዚህ የተናደዱት ህንዳውያንም እያረቧቸው የነበሩትን እባቦች ለቀቋቸው። የመርዘኛ ኮብራ እባቦች ቁጥርም ከፊቱ የባሰ ሆነ።


ይህን ሁኔት የጀርመኑ ኢኮኖሚስት Horst Siebert "Cobra effect" ብሎ ይጠራዋል። #Cobra_Effect በቀላሉ ሲተረጎም፦ ለችግሩ የምንሰጠው መፍትሄና መፍትሄው ላስከተለው ችግር የምንሰነዝረው ምላሽ የከፋ ችግር ሲፈጥር ...እንደማለት ነው (ናትናኤል ሞላ)።


በእኛ ሀገር የኢኮኖሚ ጫናን ለመቋቋም እና ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ የተለያዩ የሞንተሪ እና የቪስካል ፖሊስ እርምጃዎች ሲወሰዱ እና ያልተገመቱ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ሲያስከትሉ የመመልከት ልምድ አለ!


ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ውሳኔዎችም ያመጣሉ የተባሉትን ሰላም እና የተረጋጋ ኑሮ ካለማምጣታቸው በተጨማሪ ለማስተካከል የዘገየ አልያም አባባሽ ተጨማሪ ውሳኔም ያስተናገዱ ብዙ ጉዳዮች መጥቀስ ይቻላል።


በፖሊሲ እና መመሪያዎች መውጣት ተመሳሳይ አሉታዋ ተፅዕኖዎችን እንዳያመጣ የሚወጡ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ለምን?፤ ለማን?፤ መቼ?፤ የት? እና እንዴት? የሚሉ ጥያቄዎችን መመለሳቸውን በአግባቡ እያረጋገጡ መሄድ ግድ ነው።


በእድሜ ዘመናችሁ የመንግስት  ውሳኔ ያስከተለው ተፅዕኖ! ተፅዕኖውን ለመቀነስ የተወሰደው ማስተካከያ የባሰ ተፅዕኖ ሲፈጥር የተመለከታችሁበትን አጋጣሚ በምሳሌ ብዙ እያነሳን ልንወያይበት እንችላለን!


The Ethiopian Economics viw

@Tfanos
394 views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:08:58 ከናንተ መሓል ልባም ማነው?

የግጥም ሲዲ ፕሮዲውስ የሚያደርግ? ከገጣሚውጋ አብሮ የሚሰራ

@Jtesfaab ብትፅፉልኝ ላይ መወያየት ይቻላል
386 viewsedited  19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 12:39:34 ቤት ሸጦ መኪና በመግዛት ራይድ የሚሰራ ሰው ለራሱ ስራ እንደፈጠረ ቢሰማው! ምክንያታዊ ነው?


አንድ ልጅ እያደረሰኝ ሲያወራኝ "ተመርቄ ቤተሰቦቼ ላይ ከምቀመጥ ብዬ! ቤተሰቦቼ የገዙልኝን እድሳት የሚቀረው ሁለት መኝታ ኮንደሚኒየም ቤት (የዛሬ ዓመት ከምናምን የገዙት 600ሺ ነበር ብሏል) ሸጨው መኪና በመግዛት ለራሴ የስራ እድል ፈጥሬ እየሰራሁ ነው!" አለኝ፡፡


በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ የቢሆን ስሌት (Assumption) ታዋቂ ነው! ስለዚህ ቢሆን ወይም let assume እያልኩ ነው የማቀርብላችሁ ስለዚህ አመክንዮው ላይ እንወያይበት (ሊሆንም ላይሆንም መቻል አለ ማለቴ ነው!)። ሃሳቡ የትችት ሳይሆን የውይይት መነሻ ብቻ ነው!


ቤቱን ስንት ሸጥከው? ስለው "2 ሚሊየን ብር!" መኪና ስንት ገዛህ ስለው "1.6 ሚሊየን ብር! የቀረውን ብር አንዳንድ ነገሮች ገዝቼበት የተረፈውን በባንክ አስቀመጥኩ" አለኝ፡፡


በመኪናው በቀን ስንት ትሰራለህ ብዬ ጠየኩት? "ወጪዬን ችዬ 1,500 ብር አለኝ!" እና ከቤት እራስህን ችለህ ወጣህ? ስለው "ቤተሰብ ላይ ነው አሁንም ያለሁት" አለኝ!


ስራ እንዴት ነው? አልኩት! "ከጠዋት እስከ ማታ ዘራፊ እንዳያጋጥም እየተመኘን እየታገልን ነው" አለኝ! እስከ አሁን በአካውንትህ ስንት አስቀመጥክ? ስለው "ማጠፋፋት አይቀርም....ብር" አለኝ።


Let assume!


አሁን የሰርቪስ እና ሌሎች ወጪዎች እንደሌሉ ብናስብ (ቤተሰቦቹ እየመገቡት! ከቤት ባያባርሩት ብንል!) ይህ ሰው በወር 45ሺ ብር ቢያስቀምጥ በዓመት 540ሺ ብር ይኖረዋል! በቀላል ስሌት የመኪናው ዋጋ በሶስት ዓመት ውስጥ ምንም ባይጨምር (1.6 ሚሊየን ብር እንደሆነ ቢቆይ) የመኪናውን ወጪ ለመሸፈን ሶስት ዓመት ያስፈልጋል፡፡


ምሳሌ 1፡- በቀን 1,500 ብር አስገብቶ በሶስት ዓመት ውስጥ በመኪናው የሰራውን 1.6 ሚሊየን ብር ይዞ ሲጠቀምባት የነበረችውን መኪናውን ከሶስት ዓመት በኋላ 1.5 ሚሊየን ብር ቢሸጣት ብንል ይህ ሰው ያካበተው ሃብት 3.1 ሚሊየን ብር ይሆናል! ዘንድሮ 2 ሚሊየን የሸጠውን ቤት ከሶስት ዓመት በኋላ 3.1 ሚሊየን ብር መልሶ ሊገዛው ይችላል?


ቤቱ ከሶስት ዓመት በኋላ 10 ሚሊየን ብር ሊደርስ ይችላል (አዲስ አበባ ውስጥ የቤት/ቦታ ዋጋ እራሱን እጥፍ ለማድረግ ዓመት እየፈጀበት አይደለም!) ቤቱን እንደዘጋ ለሶስት ዓመት ቢያስቀምጠው 10 ሚሊየን ብር ያገኝ ነበር (10 ሚሊየን ብር #አንፃራዊ መኪናም ቤትም ሊገዛለት ይችላል!)፡፡


ምሳሌ 2፡- የተወሰነ ተበድሮም ይሁን ቤተሰብ አስቸግሮ ቤቱን አድሶ በወር 10ሺ ብር አከራይቶ ቢሆን በዓመት 120ሺ ብር አለው (የቤት ኪራይ ዋጋ በዓመት በ30 ከመቶ እያደገ ቢሄድ እና የቤቱ ዋጋ በዓመት 100-150% ቢያድግ) በሶስት ዓመት በኋላ ቤት ኪራዩ በወር 20ሺ (በዓመት 240ሺ ብር) የቤቱ የሽያጭ ዋጋ 10 ሚሊየን ብር ሊደርስ ይችላል፡፡


ስራ መፍጠር ማለት የሚውሉበት ምክንያት ማዘጋጀት ማለት አይደለም! እቤት ያለምንም አይነት ስራ መቀመጥ ከብዙ ጉዳዮች አንጻር መጥፎ እንደሆነ እረዳለሁ! ነገር ግን ትርፍ እና ኪሳራ ከመጪው ጊዜ ሁኔታ ጋር መሰላት አለበት! ሶስት ዓመት መኪና ገዝቶ እየሰሩ እንደሆነ ከሚሰማቸው ሶስት ዓመት የወደዱትን ተጨማሪ ትምህርት እየተማሩ ዛሬ ላይ 2 ሚሊየን ብር የሚሸጥ ቤታቸው 10 ሚሊየን ብር እስኪደርስ የዋጋውን መጨመር መጠበቅ አይሻልም?


አንዳንድ ወላጆች ስራ እንዳይፈታ ለልጄ መሬቴን/ቤቴን ሸጬ መኪና/ባጃጅ ገዝቼለት! ሱቅ ከፍቼለት፤ ወዘተ ይሉ እና ግን ልጆዎት ምን ለወጠ ሲባል መልስ ይጠፋል (መሬቴን ሸጬ አስመርቄው ወይም ሰርግ ደግሼለት የሚሉም አሉ!)፡፡


ስለዚህ አሁን ላይ ወላጆችም ሆኑ ወጣቶች በገቢ፤ በወጪ እና በአዋዋላቸው ላይ በሚያደርጉት ውሳኔ ከሁለቴ በላይ በማሰብ የቀደሙ፤ የአሁን እና የመጪው ጊዜ ሁኔታዎችን ከግምት የከተተ ውሳኔ ለመወሰን ቢሞክሩ መጥፎ አይደለም!


The Ethiopian Economist Viw

@Tfanos
501 views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 12:35:03
353 views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 12:34:11 As of Today’s Sierra Leone a western African country illustrates.

This book is premised on the institutional history of the world from a political economy’s perspective.

I found this book very compelling. This is a heavy read in terms of pages but easy & entertaining to read. It is very coherent with compelling arguments. It doesn’t leave any part of the world or history untouched generally. Writers discuss the Roman empire, Maya city-states, Ottoman Empire, African Empires, European Empires & down to the nation-states to prove their point. Highly recommended.


@Tfanos
337 views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ