Get Mystery Box with random crypto!

Tesfaab Teshome

የቴሌግራም ቻናል አርማ tfanos — Tesfaab Teshome T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tfanos — Tesfaab Teshome
የሰርጥ አድራሻ: @tfanos
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.03K
የሰርጥ መግለጫ

ለአስተያየት @jtesfaab ላይ ይፃፋልኝ
ለመቀላቀል @tfanos ይጫኑ።
ቤተሰብ ስለሆንን አመሰግናለሁ ❤❤😍

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 22:15:44 የ20ኛው ክፍለ-ዘመን ዋና አብዮተኛ

ሄንሪ ፎርድ የ20ኛው ክፍለዘመን ዋና አብዮተኛ ነው።

20ኛው ክፍለ-ዘመን የጎምቱ አብዮተኞች ጊዜ ነበር።
አብዮተኞች በሰው ልጅ አኗኗር ላይ ስር-ነቀል ማሻሻያ ለማምጣት የሚታገሉ ናቸው።

በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ከተነሱት አብዮተኞች ውስጥ ሄንሪ ፎርድን የሚያክል ለውጥ ያመጣ አብዮተኛ ግን የለም። አዎ! በትክክል አንብበሃል፤ ፓትሪክ ሄንሪ ሳይሆን ሄንሪ ፎርድ ነው ያልኩት። ሄንሪ ፎርድ ባለ መኪና ኩባንያው፣ ኢንዱስትሪያሊስቱ!

ሄንሪ ፎርድ በሰው ልጅ ህይወት ላይ ከዘርፍ ዘርፍ ተዛማች ለውጥ ማምጣት ያስቻሉ ብዙ ስር-ነቀል የማኔጅመንት ስትራተጂካዊ ውሳኔዎችን የወሰደ የኢንዱስትሪ አብዮተኛ ነው።

ፎርድ ጠብመንጃ ሳያነሳ፣ ሰራዊት ሳያሰልፍ የብዙ ሰዎችን ህይወት ከነበረበት ከታችኛው መደብ ወደ መካከለኛው መደብ ያሸጋገረ ኢንዱስትሪያሊስት ነው።

ካርል ማርክስ በንድፈ-ሃሳብ ቀርጾት፣ ቭላድሚር ኢልዪች ኡልያኖቭ (ሌኒን) መሬት አውርዶት ጓዶቹ ቦልሼቪኮች ያላመጡትን የሰው ልጅ የኑሮ ማሻሻያ በሰለጠነ እሳቤ ማሻሻል የቻለው ሄንሪ ፎርድ ነው።

ሄንሪ ፎርድ የአውቶሞቢል ኢንዱስትሪ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣ ኢንተርፕሪነር፣ ካፒታሊስት፣ ማኔጀር፣ ኢኖቬተር፣ ኢንዱስትሪያሊስትና ሥራ-መሪ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው።

እ.አ.አ. በ1908 ፎርድ በመጀመሪያ ያወጣት ሞዴል ቲ (Model T) አውቶሞቢል ዋጋዋ 850 ዶላር ብቻ ነበር። ይህ በጊዜው ከነበሩት መኪኖች ዋጋ እጅግ ቅናሽ ነበር። ፎርድ ግን በዚህ ብቻ ሳይረካ በቀጣይ የአመራረት ስርዓቱ ላይ ትልቅ ኢኖቬሽን በማድረግ በ1916 የመኪናውን ዋጋ ወደ 350 ዶላር ዝቅ አደረገው። ቀጥሎም በ1927 ዋጋውን ወደ 290 ዶላር አወረደው። Unbelievable!

ለዚህ ዋና ምክንያቱ ደግሞ፣ የአንድ መኪና ማምረቻ ጊዜን ከ80% በላይ መቀነስ በመቻሉ ነው።

ፎርድ በዚህ ብቻ ሳይቆም ሠራተኞቹ መኪና መግዛት እንዲችሉ የሰዓት ደመወዛቸውን ከእጥፍ በላይ አሳድጓል። በዚህም ደሞዛቸውን ከ2.35 ዶላር ወደ 5.00 ዶላር የሰዓት ክፍያ አሳደገው። የተለየ እሳቤ!

ሠራተኞቹ የእረፍት ጊዜ እና የመዝናኛ ጊዜ እንዲያገኙ የሥራ ሰዓታቸውን በቀን ከነበረበት 9:00 ሰዓት ወደ 8:00 ሰዓት ዝቅ አደረገው። የሥራ ቀናቸውንም በመቀነስ ቅዳሜ እና እሁድ የእረፍት ቀን አደረገው።

ፎርድ የዊክ-ኤንድ ሃሳብን ያመጣ ነው። ከዚያ በፊት በሳምንት 40:00 የሥራ ሰዓት አልነበረም፣ ከፍ ያለ ነበር።

ሞዴል ቲ መኪና በ290 ዶላር፣ ዊክ-ኤንድና፣ 40:00 ሰዓት የሳምንት የሥራ ሰዓት፣ 5.00 ዶላር የሰዓት ክፍያ በማምጣት ፎርድ የአዲሱን ዘመን አኗኗር ለውጦታል። Wow!

ቀደም ሲል የመኪና ባለቤትነት የሀብታሞች ጥጋብ ማሳያ ተደርጎ ይቆጠር የነበረው፣ በ1927 ከግማሽ በላይ የሚሆነው የአሜሪካ ቤተሰብ ባለመኪና መሆን ቻለ።

የአውቶሞቢል አጠቃቀም ማደግ ደግሞ ለጎማ፣ ለአስፋልት፣ ለመስታወት፣ ለብረት፣ ለነዳጅና ለሌሎች ብዙ ኩባንያዎች ማበብ ምክንያት መሆን ቻለ።

በዚህም ፎርድ ለመካከለኛ ገቢ ማህበረሰብ (Middle-Class) ለሚባለው የህብረተሰብ ክፍል መስፋፋት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። ለራሱም ከፍ ያለ ሀብት አግኝቶበታል። ባለበት ይመቸው!

ለዚህ ነው ሶሻሊዝም ድህነትን ሲያሰራጭ፣ ካፒታሊዝም ግን ሀብትን ያራባል የሚባለው።

ኢኖቬሽን ሁሌም ይለምልም!

የፎርድ ኩባንያ ወኪሎች ግን ልታናግሩኝ ይገባል።

Duce luce paca

@Tfanos
108 views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:42:55 የማስታወቂያ ሰኣት

ለሬዲዮ ፣ ለቲቪ ፣ ለመኪና ቅስቀሳ ወዘተ የሚሆን የድምፅ ማስታወቂያ /ፕሮዳክሽን/ የምትፈልጉ @Jtesfaab ላይ ፃፉልኝ። በቤተሰብ ዋጋ በጥሩ ጥራት እሰራለሁ!
210 views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:00:26 #ፀሐይ_ላይ_ተሰጥተው_ከበረዶ_አገር_ስንዴ_ልመና!


ኢትዮጵያ ብቻዋን በመጠን ከዮክሬን ሁለት እጥፍ የምትበልጥ አገር ናት! በህዝብ ብዛትም እንደዛው! በወጣት ቁጥርማ ኢትዮጵያ አጠገብ አትደርስም! ዪክሬን ከዓመት እስከአመት በከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ቅዝቃዜና በከፍተኛ ሙቀት የምትጨነቅ አገር ስትሆን ኢትዮጵያ ከዓመት እስከዓመት ለኑሮም ይሁን ለእርሻ እጅግ ምቹ የአየር ንብረት አላት! ይሁንና ዩክሬን ከዓለማችን ከፍተኛ የእህልና ወዘተ ምርት አምራች አገራት አንዷ ዋናዋም ናት!

እንግዲህ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ድፍን የአፍሪካ ባለስልጣን አንገቱን በከረቫት አንቆ እንደዝንጀሮ ፀሐይ ሲሞቅ ስለኒዩክሌርና ምናምን ሲዘባርቅ ይከርምና ከዚች ከአፍሪካ ጋር ስትነፃፀር በአጉሊ መነፅር እንኳ ከማትታይ አገር ስንዴና ዘይት ይማፀናል! ሰሞኑን ከሩሲያ ጋር በተፈጠረው ጦርነት አፍሪካ ከዳር እዳር በኑሮ ውድነት የሚናጥበት አንዱ ምክንያትም ይሄ ነው! ወጉን ሲያሳምሩት ታዲያ "ምዕራባዊያኑ ራሳችንን እንዳንችል የሸረቡብን ሴራ" ይሉሀል! ድህነት ምርጫ ነው! መሰልጠን ወይም ሞት ብሎ የተነሳ አገር በማንም ሴራ ተገቶ አያውቅም! የአስራ ሶስት ወር ፀሀይ ላይ ተሰጥተን በድህነት ሙቀጫ የምንወቀጥ ስጦች ነን?ምንድነን?

Sagi

@Tfanos
187 views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:48:53 # Development_እና_Happiness
በኢኮኖሚ ማደግ እና የዜጎች ደስተኝነት ምን ያገናኛቸዋል?
*********
ለምሳሌ፡- ከፍተኛ የገቢ ደረጃ ላይ የደረሰ አንድ ሰው
የሚኖርበት አካባቢ ንጹ ካልሆነ፤ ልጆቹን የሚያስተምርበት ጥሩ
ትምህርት ቤት ከሌለ፤ ከፍሎ የሚታከምበት ጥሩ ሃኪም ቤት
ከሌለ፤ ሰው በመሆኑ ብቻ የማይከበር ከሆነ፤ ወንጀል በመብዛቱ
አደጋ ይደርስብኛል ብሎ የሚሰጋ ከሆነ፤ የፈለገውን ሃይማኖት
የመከተል መብት ከሌለው፤ በሃይማኖት፤ በፖለቲካ ወይም በዘር
ሁኔታው መሸማቀቅ የሚደርስበት ከሆነ፤ በየመንገዱ የተቸገሩ
ሰዎችን የሚመለከት ከሆነ፤ የመንግስት ባለስልጣናት ተጽኖ
የሚያደርጉበት ከሆነ፤ ወዘተ ይህ ሰው ሃብታም ነው ወይስ ድሃ?
በ21ኛው ክፍለ ዘመን የዜጎችን የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ በነፍስ
ወከፍ ገቢ ብቻ መለካት ግዜ ያለፈበት ነው፤ ለዚህም ሲባል
በኢኮኖሚ መበልጸግ (Economic Development) መታየት
ያለበት ዜጎች ባላቸው የደስተኝነት ልክ ነው የሚሉ
ኢኮኖሚስቶች መብዛት ጀምረዋል በዋናነት Amartya Sen’s
እና Richard Layard ደስተኝነት የሰዎችን ጠቅላላ የኑሮ
ሁኔታን ከሚወስኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው ይላሉ
(Happiness is part of human well-being)፤ ብዙ
የጥናት ግኝቶች እንዳረጋገጡት የዜጎች ጠቅላላ ገቢ ሲጨምር
ዜጎች ደስተኝነታቸው አና እርካታቸው በተመሳሳይ መልኩ
እንደሚጨምር ነው፡፡
Richard Layard፡- የዜጎች የደስተኝነት ሁኔታ በ7 ምክንያቶች
ተጽኖ ይደርስበታል ይላል እነሱም የቤተሰብ ሁኔታ፤ የገቢ ሁኔታ፤
የስራ ሁኔታ፤ የማህበረሰብ እና የጓደኞች ሁኔታ፤ የጤና ሁኔታ፤
ነጻነት እንዲሁም ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- 4 ጓደኛማቾች ቢኖሩ እና ከመካከላቸው ብቸና ገቢ
ያለው አንድ ሰው ብቻ ሆኖ በተዝናኑ ቁጥር ምን ያህል ግዜ እሱ
ብቻ ሂሳብ እየከፈለ ይቆያል? ይሄ ጉዳይ በማህበራዊ ግንኙኘቱ
ደስተኛ እንዳይሆን ያደርገዋል፤ ስለዚህ ብቻውን ዘወትር ወጪ
ላለማውጣት የጋራ ግንኙነቱን ሊቀንስ ይችላል፤ ነገር ግን ሁሉም
በቂ ገቢ ያላቸው ቢሆን ቶሎ ቶሎ እና ረጅም የመዝናኛ ግዜ
እንዲኖራቸው ያስችላል Richard Layard የሚለው ይህንን
ነው የጓደኞች ሁኔታ የሰዎችን የደስተኝነት ደረጃ ይወስናል፡፡
በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ሀገራት መሪዎችም ሆኑ ህዝቦች
በምድር ላይ የተሰጣቸው ሃላፊነት የሚከተሉትን የዜጎች የእድገት
ዓላማዎች ማሳካት ነው፤ ጥቂት የስካንድንቪያ(Scandinavia)
ሀገራት ሲያሳኩት አሜሪካንን ጨምሮ እጅግ በጣም ብዙ ሀገራት
እስካሁን ማሳካት አልቻሉም! ዓላማዎቹ…..
በቀዳሚነት ዜጎች ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን
እንዲሟሉላቸው ያስፈልጋል ማለትም ምግብ፤ ውሃ፤ ልብስ፤
ቤት፤ የጤና ሽፋን፤ ጥበቃ ወዘተ፤ ከዚህ ሲያልፍ ብዙ የስራ
እድል፤ የተሻለ ትምህርት፤ ባህላቸውን የመጠበቅ መብት፤
በራሳቸው ነገሮችን የማድረግ ነጻነት (Not being used as a
tool by others for their own ends) ፤ የመከበር፤
እውቅና የማግኘት፤ በራስ የመተማመን ሁኔታ፤ እንዲሁም
በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች የፈለጉትን አማርጦ
የመጠቀም እድል እና ከጥገኝነት የመላቀቅ አቅም እንዲኖራቸው
ማድረግ ነው፡፡

@Tfanos
194 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:36:18 የምትኖሩት ኑሮ #ዋናውን ነው?


ልጅ እያለሁ እናቴ የነበረንን ጥሩ #ብርድ_ልብስ ለሙቀትም ሆነ ለምቾት እናውጣው ስላት ለክፉ ቀን ነው የተቀመጠው ትለኝ ነበር!


አንዳንድ ቤተሰቦች ቤት ጥሩ ሰሀን፤ ሲኒ፤ ብርጭቆ፤ መጥበሻ፤ ወዘተ በብፌ ውስጥ ተቆልፎበት በተጣመመ ሰሀን መመገብ፤  በተሸረፈ ሲኒ መጠጣት ልምድ ነው።


አንዳንዶች ጋር ልብስ ሳይቀር ቀን እየጠበቀ ቁም ሳጥን ውስጥ ተንጠልጥሎ በዓመት አንዴ ብቻ ሊለበስ ይችላል (በዓመት አንዴ ሲዘንጥ ለራሱም ለሌሎችም እንግዳ ይሆናል!)።


የተለያዩ የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶች ውስጥ የሰዎች ህይወት ወደ ፊት ባሉ ቀናት እንደሚመጣ ነው የሚመስሉት!


በኢኮኖሚክስ ቁጠባ መሰረታዊ ምክር ነው! ስለዚህ ከወጪ ቀንሶ መቆጠብ ግድ ነው #ለምሳሌ፦ ከጥሩ ምግብም ሆነ መጠጥ መቀነስ፤ ጥሩ ከመልበስ መቀነስ፤ ከመዝናናት መቀነስ፤ ወዘተ ማለት ነው።



አብዛኛው ኢኮኖሚያዊ ጥናቶች ገቢ ትዳር ከመያዝ እና ከልጆች ቁጥር ጋር ያለው ግንኙነት ቀጥተኛ ነው! #ለምሳሌ፦ ለመሰረታዊ ወጪዎች ገቢ ካልበቃ ትዳር ገቢው እስኪገኝ መቆየት አለበት የሚል ስሜት አለው! የልጆች ቁጥርም በተመሳሳይ።


#ለምሳል፦ ትዳር ለመያዝ፤ ልጅ ለመውለድ፤ ልጅ ለመድገም፤ ወዘተ መጀመሪያ ማሟላት ስለሚኖርባቸው ጉዳይ የሚያስቡ ሰዎችን የምትመለከቱት እድሚያቸው የደረሰ ቢሆንም #ወደፊት የሚል ቃል አለው!


#ለምሳሌ፦ ደሞዛቸው ዝቅተኛ ሆኖ ምንም ሳይኖራቸው ከሚበሉት ከሚጠጡት ቀንሰው ከ4 ዓመት በኋላ ትምህርቱ የተሻለ ገቢ አስገኝቶኝ #ወደፊት የምፈልገውን አደርጋለሁ የሚሉም አሉ።


#ለምሳሌ፦ ብዙዎች ለጡረታ ጊዜዬ በሚል ከመዝናናቱም ከሌሎቹም ቀንሰው #ወደፊት ለሚባለው Undefined ለሆነው ጊዜ ቅድሚያ ይሰጣሉ።


የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ሰዎች #ወደፊት እንዳሉ ማሰባቸውን ያሳያል! የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶችም ሰዎች እና ድርጅቶች #ዛሬ የሚያደርጉት ውሳኔ በሙሉ #ነገ እንዳለ በማመን ነው።


#ለምሳሌ፦ ገቢ ማሳደግ (Income Maximization)፤ ወጪ መቀነስ (Cost Minimization)፤ እርካታ መጨመር (Utility maximization) የሚሉ የኢኮኖሚክስ ሃሳቦች ከዛሬ በተሻለ ነገን እርግጠኝነት የጎደለው በመሆኑ ወደፊትን የሻለ ትኩረት ስለመስጠት ነው።


ይህንን አስተምሮት እየተከተሉ ከሆነ ግለሰባዊ ግብ እና ከተለመደው ማዕቀፍ የዘለለ ነገር ሊኖር እንደሚችልም ማሰብ ተገቢ ነው።



#ለምሳሌ፦ በሰፈራችሁ ወይም መስሪያቤታችሁ  "ያሰኘውን ሳይበላ!፤ እንደጓደኞቹ ደህና ልብስ ሳይለብስ እና በስራ ተወጥሮ አንድ ቀን ሳይዝናና ሞተ!" የተባለ ሰው አላጋጠማችሁም?


ጥያቄው ወደፊት መቼ ነው? ደግሞ ችግሩ ይህ ወደፊት መቼ እንደሆነ አለመታወቁ ነው!


የመኖሪያ እድሜ ጣሪያን ያለፈ ጎልማሳ ወደፊትን ማስቀደሙ አይቀርም! አዛውንቶችን ጠጋ ብላችሁ አውሯቸው ለወደፊት ሲሉ ዛሬ የሚተውት ብዙ ነገር አላቸው።


አንዳንድ ሰዎች በሰራሁት ገንዘብ የተሻለ ካልተመገብኩ፤ የተሻለ ቤት ውስጥ ካልኖርኩ፤ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ሰውነቴን እና አዕምሮዬ ዘና እንዲል ካላደረኩ፤ ጥሩ ስሜት የሚፈጥርልኝን ንፁህ እና አዲስ ልብስ ካለበስኩ፤ ወዘተ ህይወቴን መቼ እኖራለሁ ይላሉ።


አንዳንዶች እኔን ጨምሮ እየኖርኩ ያለሁት እና ይበልጥ ዋጋ የምሰጠው #ለዛሬ ነው ነገር ግን የዛሬ ምቾቴ በቀጣይ ጊዚያትም እንዳላጣው ስለወደፊት ማሰብም መዘጋጀትም ያስፈልጋል በሚል የሚኖሩ አሉ።


ዋናው ጉዳያቸው ወደፊት እንደሆነ በአመለካከትም ሆነ በተግባር የሚያምኑ ሰዎች ዛሬ እየኖሩ ያሉት ለመጪው ዋና ህይወታቸው ዝግጅት እንደሆነ ያስባሉ።



ወደፊት የሚለው ጊዜ ግብ ወይም መስፈርት ከሌለው ግልፅ ስለማይሆን ሰውየውን ህይወቱን ሙሉ እንደደካማ እየቆጠረ እንዲኖር ሊያደርግ ይችላል።


#ለምሳሌ፦ ትዳር የምመሰርተው ቤት እና መኪና ሲኖረኝ ነው ያለ ሰው በ40 ዓመቱ ቤትም መኪናም አግኝቶ በ45 ዓመቱ ቢያገባ እና ቢወልድ ልጁ 18 ዓመት ሲሞላው Already አዛውንት ሆኗል (63 ዓመት)!



በ30 ዓመቱ አባት ሆኖ ቢሆን የ48 ዓመት ጎልማሳ እና የ18 ዓመት ወጣት መዝናኛ ቦታ ቢሄዱ ጨዋታቸው ተቀራራቢ ይሆን ነበር! ዛሬውን እየኖረ ወደፊቱን ማሰቡን ባያቆም እንደማለት ነው!

Via The Ethiopian Economist View

@Tfanos
271 views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:23:47 የገንዘብ የመግዛት አቅም እጅግ በፍጥነት እየተሽመደመደ ነው። በዚህ ሁኔታ ሁለት እና ሶስት አመት የሚቆይ እቁብ መግባት አዋጭ ነው? (እጣው ዘግይቶ ለሚወጣላቸው)
257 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 16:01:17 እናየው ይሆን ይህን ቀን አልፈን?!

(በእውቀቱ ስዩም)

በጦር መርታት ነው፤ የሁሉም ተስፋው
የሰላም ዋጋ መቸ ታሰበ?
አብሮ ለመኖር መላው የጠፋው
አብሮ ለመሞት ተሰባሰበ::

እንዳውሬ መኖር ፤እንደ ሰው ለብሶ
እብዱን ስንፈራው ፤ ጭምቱ ብሶ
“ውረድ እንውረድ” የሁሉም ዘፈን
እናየው ይሆን ፤ ይሕን ቀን አልፈን ?


የሞት ፈረስ ነው፥ አንደኛው ላንዱ
የሁሉም ክንዱ-
-ለማነቅ ተግቶ ፤ ለማቀፍ ዛለ
“ አንተኛው ታገስ፤ አንተም ተመለስ “
የሚል የታለ?
እንደ ጥጥ ሸክም ፤ ሽበት ቀለለ
መስቀል ጨረቃው አልተከበረ
ማርጀት ነው እንጂ መሸምገል ቀረ : :


@Tfanos
193 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:33:41 በአንድ ወቅት አንድ የማውቀው ሰው የተከራየው የንግድ ቤት አከራዮች ኑሮ እየተወደደ ስለሆነ ትንሽ ብር እንዲጨምርላቸው ጠየቁት። እሱ ግን ውላችን አምስት አመት ስለሆነ አልጨምርም አለ።ሰዎቹ አምስት አመት ሲሞላ ጠብቀው ውጣ አሉት።ቤቱ ስራ ስለነበረው እጥፍ ልጨምር ቢልም ቤታችንን እንድትለቅ ነው የምንፈልገው አሉት።ቢለምን ቢያስለምን እምቢ አሉት። ቀጥሎ አይኑ እያየ እሱ ከሰጣቸው ዋጋ ባነሰ ብር ለሌላ ሰው አከራዩት።

እዚህ የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም የሚለውን የግለሰብን የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጥስ አዋጅ ደግፈህ ጮቤ የረገጥክ ከትንሽ ግዜ በኃላ ባለቤቱ ያገኝሀል። አንድ ሰው ጥሮ ግሮ የሰራውን ቤት ለማን ማከራየት እንዳለበት፣ በስንት ማከራየት እንዳለበት የሚወስነው እሱ እንጂ አዳነች አይደለችም። አዛኝ ከሆነች በራሷ ገንዘብ ቤት ሰርታ ማከራየት ነው።

ሲጀመር የቤት ኪራይ እየጨመረ ያለው አከራዩ አይደለም።እንደማንኛውም እቃ የቤት ኪራይ ዋጋ እና የወለድ ምጣኔም መንግስት አትሞ ከረጨው ብር ጋር እራሳቸውን adjust እያደረጉ ስለሆነ ነው። መንግስት የመብራት ታሪፍ በእጥፍ ልጨምር ነው ከሚለው ዜና ቀጥሎ ግለሰቦች የቤት ኪራይ መጨመር አይችሉም የሚባልባት ሀገር በጣም ታስቃለች።የቤት ኪራይን ጨምሮ የሁሉንም እቃ ዋጋ ጣርያ አስነክቶ የይስሙላ "የቤት ኪራይ አትጨምሩ" የሚል አዋጅ ያወጣውን መንግስት የምታመሰግኑ ሰዎች ደግሞ የበለጠ ታስቃላችሁ።

VIA Mekoya kebede

@Tfanos
214 views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 23:09:27 አሁን ግን ቦሩ ዶዮ ከጦርነት ተመልሶ፣ ወልዶ ከብዶ ጠብቆታል።

ዲማ በአሁኑ ሰዓት የ60 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ቤተሰቦቹ አግብቶ ዓይኑን በአይኑ እንዲያይ እያሰቡ መሆኑን ይናገራል።

እርሱም በሕይወት ካለሁ የበፊቱን ረስቼ ሕይወቴን እንደ አዲስ መቀጠል እፈልጋለሁ ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።

ምንጭ Bbc

@Tfanos
240 views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 23:09:27 በነገሌ ቦረና ሞቷል ተብሎ የተለቀሰለት ግለሰብ ከ32 ዓመት በኋላ በሕይወት ተገኘ
ይህ የሆነው በኢትዮጵያ፣ ነገሌ ቦረና፣ ጎብቻ ቀበሌ ውስጥ ነው።

ከ32 ዓመት በፊት ሞቷል ተብሎ ወዳጅ ዘመድ እርሙን ያወጣለት ሰው፣ 'አለሁ' ብሎ የቤተሰቦቹን ደጃፍ አንኳኳ።

ሞቷል ብለው በሐዘን እንባ የተራጩለት ልጃቸውን ያገኙ ቤተሰቦች፣ በደስታ አነቡ።

በሕይወት መኖሩን የሰሙ የጎብቻ ቀበሌ ነዋሪዎች ሁሉ የዜናውን እውነትነት ለማረጋገጥ ወደ ቤተሰቦቹ ቤት እየጎረፉ ነው።

ዲማ ዶዮ ቦሩ ይባላል። በነገሌ ቦረና ነው ነዋሪነቱ።

በ1982 ዓ.ም. በወቅቱ አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው መንግሥት ለብሔራዊ ውትድርና በግዳጅ ተወሰደ።

ዲማ በአካባቢው ታጣቂዎች ተይዞ ሲወሰድ ቤተሰቦቹ በሐዘን ክፉኛ ተሰበሩ።

ዲማ፣ በወቅቱ አብረውት ከ100 የማያንሱ ወጣቶች ለጦርነት መወሰዳቸውን ያስታውሳል።

ከዚያም ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ከዘመተ በኋላ ቤተሰቦቹ የሰሙት ወሬ በሐዘን ማቅ እንዲለብሱ አደረጋቸው።

ወላጆቹ በነበረው ጦርነት ላይ ከእርሱ ጋር አብረው የዘመቱ መሞታቸውን፣ ዲማ ደግሞ መቁሰሉን ነበር የሰሙት።

በእርግጥ ልጃቸው ስለመሞቱ ከማንም ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አላገኙም።

ዲማ በወታደርነት በግዳጅ እንዲዘምት ሲደረግ አላገባም፤ አልወለደም ነበር።

እናት የልጃቸውን ልጆች አለመሳማቸው ያንገበግባቸዋል።

ለዓመታት ድምፁ የጠፋው ዲማ ያፈራቸውን ንብረቶች፣ ከብቶች ቤተሰቡ ተከፋፈለ።

ይህ ሁሉ ከሆነ ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ ዲማ ቤተሰቦቹን ፈልጎ መጣ።

የእርሱ ወደ ቤተሰቡ መቀላቀል በብዙዎች ዘንድ እንደ ተዓምር ተቆጥሯል።

ወደ ዲማ ቤተሰቦች ዘንድ እየመጡ እንኳን ለቤትህ አበቃህ የሚሉ የቤተሰቡን ደስታ ከመጋራት ባሻገር ጥያቄም አላቸው።

ከ32 ዓመት በፊት አብረውት ዘምተው የነበሩ የአካባቢው ወጣቶች፣ ዛሬም በሕይወት ካሉ ለማረጋገጥ የሚፈልጉ መኖራቸውን የዲማ የወንድም ልጅ፣ ታሪ ካሀና ዶዮ ለቢቢሲ ተናግሯል።

"በየዕለቱ ሰዎች እየመጡ ስለቤተሰቦቻቸው ይጠይቁታል። አንዳንዱ 'ከአንተ ጋር ታፍሶ የተወሰደው ወንድሜን አይተኸዋል?' ይላል ሌላው ደግሞ ስለልጁ ይጠይቃል። በርካታ ሰው ነው በየዕለቱ የሚጎበኘው።"

ታሪ ዲማ ወደ ውትድርና ሲወሰድ ገና አልተወለደም ነበር።

"አባቴ የስምንት ዓመት ልጅ እያለ ነው እርሱ ወደ ጦር ሜዳ የዘመተው። አሁን እኔ 18 ዓመቴ ነው። ልክ እንደ ሁለተኛ አባቴ የማየው አጎቴን ስላገኘሁ ደስተኛ ነኝ። ይህ ተዓምር ነው። ለእኔም ለቤተሰቡም ተዓምር ነው።"

የዲማ እናት ሞቶ አፈር ያላለበሱትን ልጅ ሞቷል ብለው እርማቸውን ለማውጣት ተቸግረው ነበር።

"ሁሉም በቃ ሞቷል የእርሱን ነገር እርሺው ሲሉኝ እሺ አላልኩም ነበር። እንደ ሞተ አይሰማኝም ነበር፤ ይመጣል ብዬ አስብ ነበር" ይላሉ የዲማ ዶዮ እናት።

የዲማ እናት እርጅና ተጭኗቸዋል። ነገር ግን ልጃቸው ወደ ጦርነት የተወሰደ ዕለት የነበረውን ሁኔታ በትክክል ያስታውሳሉ።

"ስንት ዓመቱ እንደነበር አላስታውስም። ነገር ግን እድሜው ለሥራ ደርሶ ነበር። አብረን እየሄድን እያለ ነው መጥተው በጉልበት ነጥቀውኝ የወሰዱት።"

ከዚያ በኋላ ግን ከልጃቸው ቃል አልሰሙም። ይኸው ከ32 ዓመት በኋላ በራቸውን አንኳኩቶ መጣ።

"በጣም ደስተኞች ነን፤ እርሱ የመጣ ዕለት በደስታ ራሴን ስቼ ነበር። እንደ ዐይናችን ብሌን የምንሳሳለት ልጅ ነበር።"

ዲማ ለ32 ዓመታት የት ነበር?
ዲማ በአካባቢው ታጣቂዎች በ1982 ዓ.ም. ታፍሶ ከተወሰደ በኋላ ወደ ባሕር ዳር መላኩን ይናገራል።

ባሕር ዳር የተወሰደው ከተያዘ ከ18 ቀናት በኋላ እንደነበርም አይዘነጋም።

በተመደበበት ጦርነት ላይ በርካቶች ከፊቱ ሲረግፉ ተመልክቷል። ሌሎች ደግሞ እግራቸው በመራቸው ሸሽተዋል።

በጦርነቱ ላይ ዓመት ያህል ከተሳተፈ በኋላ፣ በመቁሰሉ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወሰደ።

"ሕክምና ተደርጎልኝ ከሆስፒታል ስወጣ ማንንም አላውቅም ነበር። እዚያ የነበሩ ሰዎች ከየት እንደመጣሁ ጠየቁኝ። ከነገርኳቸው በኋላ፣ በእረኝነት እንዳገለግል ወሰዱኝ" ይላል።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ሌላ ሰው ወደ ቤንች ማጂ ወስዶት በቤቱ እንዲያገለግል እንዳደረገው ያስረዳል።

ወደ ቤንች ማጂ በቤቱ አንዲያገለግል የወሰደው ግለሰብ፣ ቤተሰቦቹ የሉም በሚል ከማንም ጋር እንዳይገናኝ እንዳደረገው ይገልጻል።

"ደጋግመው 'ቤተሰቦችህ እዚያ የሉም። ተመልሰህ የምትገባበት የለም። ስለዚህ ወዴት ትሄዳለህ?' ይሉኝ ነበር።"

"እኔም ደጋግሜ 'ምንም እንኳ የምገባበት ቤተሰብ ባይኖረኝ የተወለድኩበት ስፍራ ሄጄ እዚያ ልኑር እላቸው ነበር" ሲል ለቢቢሲ አስረድቷል።

የዲማ ጩኸት ግን ሰሚ ጆሮ ሳያገኝ ቆየ።

"ማንም የተረዳኝ አልነበረም፤ ብቻ 'የሚሄድበት የለውም፤ ተኝቶ የእኛን ገንዘብ መብላት ብቻ' ይሉኝ ነበር።"

ዲማ በቤንች ማጂ ያሳለፈውን የብቸኝነት፣ ፍቅር ማጣት እና በሐዘን ያሳለፈውን ጊዜ ያስታውሳል።

"ቤተሰብ አልመሰረትኩም። እዚያ ትዳር መመስረት በባህሉ ምክንያት ለእኔ ከባድ ነበር" ይላል።

ዲማ በዘመድ አዝማድ ረሃብ፣ በወገን እጦት በተቆራመደባት ቤንች ማጂ በአንድ ፋብሪካ በጥበቃነት ተቀጥሮ መሥራት ቢጀምርም ወርሃዊ ደመወዝ እንደማይከፈለው ይናገራል።

"ምንም ክፍያ አላገኝም። እንዳልሞት ብቻ የዕለት ምግቤን ይሰጡኛል" ይላል።
ወደ ቤተሰቦቹ እንዴት ሊመጣ ቻለ?
ዲማ በፋብሪካ ዘበኝነት እየሰራ ያገኘው ጓደኛው ጋር የነበረው ንግግር ዛሬ ቤተሰቦቹን ለማግኘት እንዳበቃው ይመሰክራል።

ጓደኛው ሹፌር ሲሆን በተደጋጋሚም ወደ ቦረና ያቤሎ ለስራ ይንቀሳቀሳል።

"አንድ ቀን ዲማ የትውልድ ስፍራህ የት ነው? ብሎ ጠየቀኝ። የትውልድ ስፍራዬን እና የቤተሰቦቼን መኖርያ አካባቢ ስነግረው 'ያቤሎ ጓደኛ ስላለኝ እጠይቅልሃለሁ' አለኝ" ይላል።

ከዚያ በኋላ የሆነው ሁሉ ለዲማም ለቤተሰቦቹም ተዓምር ነው።

ያቤሎ ካለው የሹፌር ጓደኛው ወዳጅ፣ በስልክ ሁለት ሶስቴ ካወራ በኋላ፣ በነገሌ ቦረና የሚገኙ ቤተሰቦቹን አፈላልጎ አገናኘው።

"በፈጣሪ እርዳታ የቤተሰቦቼን ስልክ ቁጥር አገኘሁ" የሚለው ዲማ ተወልዶ ካደገበት ቀዬ ሲወጣ ወንድሙ ዲድ ዶዮ ሕጻን እንደነበር ያስታውሳል።

ዲድ እና ቀሪው ቤተሰብ ወንድማችሁ በሕይወት አለ የሚለውን ወሬ ሲሰሙ የደስታ ማእበል አጥለቀለቃቸው።

ነገር ግን ሽራፊ ጥርጣሬም ቢሆን አላጣቸውም

ስለዚህ የቤተሰቦቹን ስም እንዲሁም ሌሎች የሚያስታውሳቸውን ነገሮች እንዲዘረዝር ጠየቁት።

ዲማም የቤተሰቡን እና የጎሳውን ስም እንዲሁም ሌሎች የጋራ ትዝታዎቻቸውን ዘረዘረ።

ቤተሰቦቹ ካፈሯቸው ሰባት ልጆች መካከል ሶስተኛ የሆነው ዲማ በሕይወት መኖሩ በዚህ መልኩ ተረጋገጠ።

ከዚያ በኋላም ሹፌር ጓደኛው ይዞት አዲስ አበባ፣ ከዚያም ወደ ነገሌ ቦረና ወስዶ ከቤተሰቦቹ ጋር ቀላቀለው።

ዲድ ወንድሙ ዲማ በመንደራቸው የደረሰ እለት የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳል።

ሁሉም ፊቱ በእንባ ታጥቦ ነበር የሚለው ዲድ፣ ወላጆቹ ብቻ ሳይሆኑ ልጆቻቸው በደርግ ታፍሰው የተወሰዱባቸው እና እርማቸውን ያላወጡ ተሰባስበው ሊያዩት መጥተው ነበር ይላል።

ዲማ ደግሞ ተወልዶ ጥርስ የነቀለባት መንደር ተቀይራ ጠብቃዋለች።

"ያኔ ወደ ጦር ሜዳ ስሄድ ከብቶቻችን ብዙ ነበሩ። ከቤተሰቦቼ እና ዘመዶቼ ውጪ ልጅ ሆነን አብረን እንጫወት ከነበሩ መካከል አንዳቸውንም አላገኘሁም" ይላል።

ዲማ ወደ ጦር ሜዳ ሲሄድ አባቱ በሕይወት ነበሩ። ታላቅ ወንድሙ ቦሩ ዶዮም ወደ አስመራ ለጦርነት ተወስዶ ሞቷል መባሉን ያስታውሳል።
229 views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ