Get Mystery Box with random crypto!

Tesfaab Teshome

የቴሌግራም ቻናል አርማ tfanos — Tesfaab Teshome T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tfanos — Tesfaab Teshome
የሰርጥ አድራሻ: @tfanos
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.03K
የሰርጥ መግለጫ

ለአስተያየት @jtesfaab ላይ ይፃፋልኝ
ለመቀላቀል @tfanos ይጫኑ።
ቤተሰብ ስለሆንን አመሰግናለሁ ❤❤😍

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-20 12:34:11 Book Review: Why Nations fail.

This is a very interesting question. Who wouldn’t want to know the answer? For this reason, I bought this book back in 2017 & wanted to know why. Since then it was on my bookshelf until some days ago I picked it up to read. This book is co-authored by Daron Acemoglu professor of economics at MIT & James Robinson British Economist.

So why do nations fail? Why Western Europe, North America & Japan are rich & more prosperous than Sub- Saharan African countries, South American, and South Asian countries? Do nations fail because of their geography? Culture? Ignorance? Or because European people are more intelligent than other people in poor countries? Not at all. Daron Acemoglu doesn’t believe in these theories. If you have read the popular book Guns, Germs & Steel by Jared Diamond that book was premised on geography thesis as the reason for prosperity & poverty of nations. Writers of this book debunked that geography theory as well as mentioned above.

Daron Acemoglu says If Geography, culture, or climate should have played a role in the poverty & prosperity of nations then there shouldn’t have been any differences between South Korea & North Korea. Both countries are so close, separated by a just border, yet so different. South Korea is rich, prosperous, with better living standards, education & health care. In contrast, North Korea is the opposite of it suffering in poverty & dictatorship.

So if not geography, culture & ignorance then what is it that leads countries to prosperity or poverty? Or why nations fail then.

Here comes the core of the book: Inclusive economic & political institutions & Extractive economic & political institutions. Rich, democratic, economically sound & stable countries have inclusive institutions while poor, unstable, absolute, or dictatorial have extractive institutions in place.

Inclusive institutions involve pluralism, broader political participation & economic opportunities in society for everybody, it allows innovation, entrepreneurship, property rights, rule of law, competition & accountability of leaders. Examples are Western democracies.

On the other hand, extractive institutions maintain the power of the narrow elite at the expense of society. Absolutist & repressive regimes thrive under this model. The narrow elite maintains economic monopolies to enrich themselves, ordinary people have no private property rights, political participation & economic opportunities. Controlling elite doesn’t like change because their power would be threatened by creative destruction so they resist inclusive institutions to take root & lead to democracy. Examples are European absolute monarchies of the time & Ottoman monarchies, sub-Saharan countries, and south Asian countries of today. European monarchies didn’t become prosperous until they gave up on extractive economic & political institutions in the 18th & 19th centuries & gradually marched towards inclusive institutions & democracy.

Countries with extractive institutions don’t encourage innovation & change because the narrow elite prefers the status quo it would always resist change. Ottoman empire banned printing press, Austro- Hungarian empire & Russian monarchy resisted railways & industrial Revolution in the fear of lest their power goes away if innovation & industrial Revolution is to be adopted. Because innovation & change overhaul the whole society & brings creative destruction. That’s why they remained behind those who adopted the Industrial Revolution & innovation.

Writers have researched for 15 years writing this book. Starting from the neolithic revolution about 10 thousand years ago to the 21st century. They found that inclusive economic & political institutions were the key that led to the prosperity of nations not the geography, culture, or ignorance instead institutions that made the difference. As North & South Korea example illustrates. While extractive economic & political institutions led to the absolutism, poverty & collapse of the countries.
345 views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 23:23:14 በቡራዩ በጅብ ተበልቶ እግሮቹን ያጣው ወጣት

ብርሃኑ ዳባ ቤተሰቦቹ የሚኖሩት ቡራዩ ለኩ ከታ መንደር ነው።

ባላፈው ሳምት ነሐሴ 04/2014 ዓ.ም. ረቡዕ ዕለት ከሚኖርበት ሞጆ ወደ ቤተሰቦቹ ዘንድ የሄደው ጉዳይ ለማስፈፀም ነበር።

ነገር ግን አልተሳካለትም፤ በማግስቱ ሞጆ ተመልሶ የሥራ ገበታው ላይ መገኘት ያሰበው ብርሃኑ ወደ ጓደኛው ዘንድ ደወለ።

“ሌሊቱን ወደ ሞጆ የሚሄዱ መኪኖች አሉ። ስለዚህ ወደ ዊንጌት ሄጄ እነርሱን ለመያዝ ነበር ያሰብኩት” ሲል ያክላል።

“የዚያን ዕለት ቡራዩ ቤተሰቦቼ ጋር ሄጄ ነበር። ያሰብኩት ጉዳይ አልተሳካልኝም። የሥራዬ ቦታ ደግሞ ሞጆ ስለሆነ አንድ የማውቀው ሰው ጋር ደወልኩኝ። እና ዛሬ ማታ ስለምወጣ አብረን ተጉዘን ነገ ሥራ መግባት ትችላለህ አለኝ” ይላል አደጋው ከመድረሱ በፊት የተፈጠረውን ሲያስታውስ።

ብርሃኑ የደወለለት ወዳጁ ‘ዊንጌት እጠብቅሃለሁ’ ስላለው ከቡራዩ ከታ ወደ አስኮ እየተጓዘ እያለ በተለምዶ በግ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ጅብ ማየቱን ያስታውሳል።

ነገር ግን ብርሃኑ ያሰበበት ቦታ ከመድረሱ በፊት መንገድ ላይ ጅቦች ተተናኮሉት። በዚያም የተነሳ ሁለት እግሮቹን አጣ።

“በግ ተራ አካባቢ ቁልቁለቱን እየወረድኩ፣ አንድ ጅብ ሲመጣ አይቻለሁ። ከዚያ በኋላ የሆንኩትን ነገር አላስታውስም። በማግስቱ አምስት ሰዓት ላይ ራሴን ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁት፝።”

ብርሃኑ የተለያዩ የአካል ክፍሎቹ በጅብ ተነክሷል።

ጀርባው እጁ እንዲሁም እግሮቹ ላይ ከንክሻው የተነሳ ጉዳት ደርሶበታል።

ከሁሉም ግን እግሮቹ ላይ የደረሰው ጉዳት የከፋ ነበር።

“ስነቃ ሆስፒታል ውስጥ ተኝቻለሁ። ከጉልበቴ በታች ያለው አካሌ የለም። ቤተሰቦቼ የተኛሁበትን አልጋ ከብበው ቆመዋል።”

ከገባበት ሰመመን ሲነቃ ራሱን ሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ያገኘው ብርሃኑ ስለገጠመው ነገር በቅጡ የሚያስታውሰው የለም።
“ወደ ሆስፒታል ያመጣህ የፖሊስ አምቡላንስ ነው ይሉኛል እንጂ በትክክል ማን እንዳመጣኝ አላውቅም። ስነቃ ራሴን ሆስፒታል ውስጥ ተኝቼ ነው ያገኘሁት” ይላል ብርሃኑ።

“ከጉልበቴ በታች ተጎድቷል። አንደኛው እግሬ ከቁርጭምጭሚቴ በታች የለም። የቀኝ እግሬ ደግሞ ተንጠልጥሎ ነበር። ከዚህ በላይ ደም ከፈሰሰህ ትሞታለህ ስላሉኝ ተቆረጠ” ሲል ያክላል።

ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው አቤት ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ ይገኛል።

ወደ ሆስፒታል ሊጠይቁት የመጡ ሰዎች በቅድሚያ ቡራዩ ጤና ጣቢያ የመጀመርያ እርዳታ ከተሰጠው በኋላ፣ ለተጨማሪ ሕክምና ወደ አቤት ሆስፒታል መምጣቱን እንደነገሩት ለቢቢሲ ገልጿል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖሊስ ባልደረቦች ብርሃኑን ጉዳት ከደረሰበት ስፍራ አንስተው ወደ ሕክምና ተቋም የወሰዱት የአካባቢው የፀጥታ አባላት መሆናቸውን ይናገራሉ።

ኢንስፔክተር መልካሙ አሰፋ፣ በቡራዩ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ናቸው።

በዕለቱ እኩለ ሌሊት ላይ የፀጥታ አካላት ብርሃኑ የወደቀበት ስፍራ እንዳገኙት ለቢቢሲ ገልፀዋል።

“ስንደርስ አንድ እግሩ ሙሉ በሙሉ ተበልቷል። ሁለተኛው እግሩ ደግሞ ከቁርጭምጭሚቱ በታች ተበልቷል። ግራ ጎኑ ደግሞ ተቦጭቋል።”

የፀጥታ አባላቱ በስፍራው ሲደርሱ የጅብ ጩኽት ይሰማ እንደነበር የሚናገሩት ኢንስፔክተሩ፣ ብርሃኑን አንስተው በፖሊሰ መኪና በቅርብ ወደ ሚገኘው የቡራዩ ጤና ጣቢያ መውሰዳቸውን እና ከዚያ በኋላ ወደ ሆስፒታል እንዲሄድ ድጋፍ ማድረጋቸውን ይናገራሉ።

ወደ ቡራዩ ፖሊስ ከተመደቡ ቅርብ ጊዜያቸው መሆኑን የሚናገሩት ኢንስፔክተር መልካሙ በከተማው እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች አልፎ አልፎ ሲከሰቱ እንደቆዩ መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል።
BBC

የቴሌግራም ቻናልችንን ይቀላቀሉ

@Tfanos
430 views20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 10:53:00 በድብልቅልቁ አምላክ!
(በእውቀቱ ስዩም)

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የሰማሁዋቸው መልካም ዜናዎች ብዙ ናቸው ፤ ከጥቂቶች መሀል፤ የዶክተር አብይ አህመድ በህይወት መኖር፥ የህዳሴ ግድብ ሶሰተኛ ዙር ሙሌት፤ እና በመንግስት እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የድርድር አዝማሚያ መታየት -ተጠቃሽ ናቸው!

በተረፈ መአት ነገር ያሳስበኛል፤ ለምሳሌ የፍትህ እና የገበያው ነገር ያሳስበኛል! የፍትህ እና የገበያ ሰርአቱ ከሾቀ አገር በጤና እና በስርአት ሊያድር አይችልም፤

ወጭ ገቢውን ከአደጋ እንዲጠብቁ በየኬላው የተመደቡ ሰዎች ፥ መንገደኛ እንደጠላት ቆጥረው እሚከለክሉበት ዘመን ላይ ደርሰናል፤ ወደ አዲስአበባ እንዳትገቡ ተብለው ጎዳና ላይ ያደሩ ከሰሜን ሸዋ ከወሎ የመጡ ዜጎችን በደል ሰምተናል! ጣልያን እንኳን” ከዚህ እስኪዚህ ያለው የኔ ሰፈር ነው ከዚህ ወድያ ያለው የናንተነው “ ይል ነበር እንጂ አዲስአበባ እንዳትገቡብኝ የሚል ክልከላ አልነበረውም! ሸዋ ወደ ሸዋ እንዳይገባ ተከለከለ ቢባል ማን ያምናል?

“ ታሪኬ ብዙ ተሰማ እሸቴ
ተደብቂያለሁ፤ በገዛ ቤቴ “ ያለው አዝማሪ ነው ትዝ ያለኝ፤

አንዳንዴ፥ ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቀውን ተጠርጣሪ ፖሊስ ወደ ቤቱ ሊሸኘው ሲገባ ወደ ዘብጥያ ያወርደዋል፤ የፌዴራል ፖሊስ እና የክልል ፖሊስ በየፊናው ርምጃ ይወስዳል፤ አውራ ተቋማት ተናበውና ተከባብረው በመስራት ፈንታ በሽምያ በፉክክር እና በመናናቅ የሚሰሩ ከሆነ ወዮልን! ስርአተ መንግስቱ ወደ ድብልቅልቅነት እንዳይመለስ ይታሰብበት!

በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ብዙ የክፍለሀገር ገዥዎች አምጸው አገር ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ነበር፤ እና በመንገድ ስትሄድ ሽፍታ ከያዘህ ሽፍታው የሚደገፈውን ያገር ገዥ ስም ጠርተህ ለመዳን ትፍጨረጨራለህ ፤ አንዱ ነጋዴ በአባይ ሸለቆ ሲወርድ ሽፍቶች አገኙትና ሸቀጡን ቀሙት፤ ይህ ስላልበቃቸው ከብበው በወይራ ሽመል ይከኩት ጀመር፤ ሰውየው “ በቴዎድሮስ አምላክ” ብሎ ነጠላ ጩኸት ለቀቀ! “ ዱላው ግን ተጠናክሮ ቀጠለ፤ “ በተድላጉዋሉ አምላከ “ ብሎ ጮኸ! አሁንም አልራሩለትም! ሰውየው “ በሀይለ መለኮት አምላክ” ብሎ ተማጸነ፤ አልተፋቱትም፤
በመጨረሻ ሰውየው ቢጨንቀው፥

“በድብልቅልቁ አምላክ ማሩኝ”

@Tfanos
562 views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 17:30:22 ምርጥ ቴአትር ለምርጧ ሀዋሳ ከሰባተኛ ፕሮሞሽን!
ኮከቦቹን በአካል ሲተውኑ ልንከልማቸው ሶስት ቀን ብቻ ቀረን "ላጤው ባለትዳር" ቴአትር እሁድ ነሃሴ 8 ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ በሲዳማ ባህል አዳራሽ ይታያል...በፍፁም አይቀርም!
513 views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 12:36:50 በትናንትናው ዕለት አልጀዚራ ስለ ህዳሴው ግድብ በሰራው ዘገባ ላይ አንድ የሱዳን ገበሬ "በፊት ውኃው እዚህ ይደርስ ነበር በዚህ ወቅት፣ አሁን ከፍታው ቀንሷል። በዛ ላይ ይዞ ይመጣ የነበረው ለም አፈር አሁን የለም" ሲሉ ተናገሩ።

ከዛሬው ዕለት ጀምሮ የውኃ ጥያቄያቸው መልስ ያገኛል። የለም አፈሩን ነገር ግን እንግዲህ እርማቸውን ያውጡ!

በ ኤሊመንተሪ የጂኦግራፊ ትምህርት "ዓባይ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ይዞ የሚወጣው አፈር በጭነት መኪኖች ቢጫን የገልባጭ መኪኖቹ ሰልፍ የምድር ወገብን ያካልላል" የሚል ምሳሌ እንደነበር ትዝ ይለኛል። [የአፈሩን ብዛት ለልጅ አዕምሮ እንዲገባ ሆኖ የቀረበ አሪፍ ምሳሌ ነው ]

ዛሬ ግን በግልጽ እንደሚታየው ውኃው በግድቡ አናት ሲሄድ ኩልል ያለ የምንጭ ውኃ እንጂ የወንዝ ፈጽሞ አይመስልም። ያ ማለት አፈራችን ድንበር አቋርጦ መሄዱ አበቃ ማለት ነው።

ይህ ደስታም ነው፤ ፈተናም ነው!

ምክኒያቱም ድንበር አቋርጦ አለመሄዱ ብቻ ለኛ ጥቅም እንዲሰጠን አያደርገውም። እንዲያውም እንዲህ አስራ ምናምን ዓመት ሙሉ አቃስተን የገነባነውን ግድብ በደለል የመሙላት ፈተና ጋርጧል።

ግድቡ በደለል እንዳይሞላ መሰራት ያለበት ዋና ጉዳይ በቀበሌ ደረጃ የሚመነዘር የአፈር ጥበቃ ስራ ነው። ይህ ሥራ ከፍተኛ ትብብር፤ ሀገራዊ መግባባትና መረጋጋት፤ ዘላቂነቱ የተረጋገጠ የመሬት ባለቤትነት መብት፤ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት....ያካተተ ጠንካራ ሀገራዊ የፖሊሲ እርምጃዎች ይፈልጋል። ግድባችን ያለዕድሜው በደለል እንዳይሞላ፤ ከዛም በላይ ደግሞ 60% የሚሆነው የሀገራችን መልከአምድር የዓባይ ገባር እንደመሆኑ የእርሻ መሬቶቻችን እንዳይራቆቱ grass-root የአፈር ጥበቃ ሥራ ወሳኝ ነው።

የሱዳን ግድቦች የእስከአሁኑ ፈተና በደለል መሞላት ነበር። ሱዳን ግድቦቿን ከደለል ለማጽዳት በየዓመቱ ከፍተኛ ወጪ የምታወጣ ሲሆን ያንንም አድርጋ የ ውኃ መያዣዎቿ (reservoir) አቅም በጣም ቀንሶባታል። በዚህም ምክኒያት የኃይል ማመንጫዎቿ ከአቅማቸው በታች ነው የሚያመነጩት። እኛ ግን ያ possibility እንብዛም ያለን አይመስለኝም። ምክኒያቱም ግድባችን የሚገኘው በጣም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ በመሆኑ ደለል የማጽዳት ሥራ ቴክኒካዊና ኢኮኖሚያዊ አዋጪነቱ አጠያያቂ መሆኑ አይቀርም።

ከዚህ አኳያ በቀበሌ ደረጃ የሚሰራው የአፈር ጥበቃ ሥራ ምትክ የለሽ ቢሆንም በተጨማሪም በአንጻራዊነት ለማጽዳት ቀላል የሆኑ ሌሎች ግድቦችን ስለመገንባትም ማሰብ ሳያስፈልገን አይቀርም!

ቺርስ

@Tfanos
550 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 23:15:45 በአንድ መጽሐፍ ብቻ የገነነችው ደራሲ
------
አፈንዲ ሙተቂ
------
አዎን! ዝነኛዋ ደራሲ ማርጋሬት ሚሼል ናት። ማርጋሬት ማን ናት? በአጭሩ እንወቃት።
----
የተወለደችው በአትላንታ ከተማ (ጆርጂያ ግዛት) ነው። በትምሕርቷ በማሳቹሴትስ ግዛት ካለው "Smith College" የተመረቀች ብትሆንም ስራ የጀመረችው በአትላንታ ነው። በከተማዋ ወደ ጋዜጠኝነት ገብታ ብዙ ሰርታለች። በተለይም "The Atlanta Journal" የተሰኘው ዕድሜ-ጠገብ ጋዜጣ ከሚኮራባቸው አምደኞቹ አንዷ ነበረች።

በ1901 የተወለደችው ማርጋሬት ሚሼል በ1949 በመኪና አደጋ ተገጭታ የሞተችው በትውልድ ከተማዋ አትላንታ ውስጥ ነው። የተቀበረችውም በከተማዋ ባለው የካቶሊክ መካነ-መቃብር ነው።
----
ማርጋሬት ከልጅነቷ ጀምሮ የስነ-ጽሑፍና የኪነ-ጥበብ ፍቅር ነበራት። ነገር ግን ሁኔታዎች ተመቻችተውላት ለመጻፍ አልቻለችም። ዕድሜዋ ሰላሳ አምስት ዓመት ሲሆን ግን በዓለም ዙሪያ ስሟን ያስጠራውን ብቸኛ መጽሐፏን መጻፍ ጀመረች። መጽሐፉንም ከሁለት ዓመት በኋላ 1037 ገጾች አጠናቀቀችው።

መጽሐፉ በ1936 "Gone with the Wind" በሚል ርእስ ታትሞ ወጣ። በጭብጡ፣ በሴራ ቀረጻው፣ በትረካው ፍሰትና በስነ-ጽሑፍ ውበቱ የተለየ ሆኖ በመገኘቱ የ1937 የNational Book Award እና የPultizer Award አሸናፊ ለመሆን በቃ። በ1939 በፊልም ተቀይሮ ተሰራ። ፊልሙም እንደ መጽሐፉ እጅግ ስኬታማ ሆነና አስር የኦስካር ሽልማቶችን አሸነፈ (ይህ ሪከርድ ለአስር ዓመት ሳይደፈር ቆይቶ በ1950 Ben Hur በተሰኘው ፊልም ተሰብሯል)።
-----
Gone with the wind በእንግሊዝኛ ተናጋሪው ዓለም ብቻ ሳይገደብ በሌሎች ቋንቋዎችም ተተርጉሞ ታትሟል። ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከቅዱስ ቁርአን ቀጥሎ በብዙ ቋንቋዎች በመተርጎም ሪከርድ የያዘውም እርሱ ነው። እስከ ዛሬ ድረስ በ82 ቋንቋዎች ተተርጉሟል። የእንግሊዝኛው መጽሐፍና በሌሎች ቋንቋዎች የተተረጎሙት ድርሰቶች በድምሩ 100 ሚሊዮን ኮፒ ያህል ተሽጠዋል።
------
ማርጋሬት ሚሼል ከዚህ መጽሐፍ በኋላ ሌላ ድርሰት አልጻፈችም። ለዚህ ምክንያቱ ሌላ ሳይሆን ከመጀመሪያ መጽሐፏ (ከፊልሙ ጭምር) ተጠቃሚ አለመሆኗ ነው። መጽሐፉ በህይወት ዘመኗ 10 ሚሊዮን ኮፒ ያህል የተሸጠ ሲሆን ለማርጋሬት የደረሳት ግን 100,000 ዶላር ብቻ ነው (ከፊልሙ ደግሞ "የደራሲው ክፍያ" ተብሎ 50,000 ተቀብላለች)።

ማርጋሬት ከመጽሐፉ ህትመት በኋላ ያለውን ሕይወቷን በጋዜጠኝነት እና ከአድናቂዎች ለሚደርሷት ብዙ ሺህ ደብዳቤዎች መልስ በመጻፍ ነበር ያሳለፈችው። በ1949 በመኪና ተገጭታ ከአምስት ቀናት በኋላ ስትሞት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ሃሪ ትሩማን ባወጡት የሐዘን መግለጫ "ጊዜ የማይሽረውን መጽሐፍ ለዓለም ህዝብ የሰጠች ታላቅ አርቲስት" በማለት አሞግሰዋታል።
----
ማርጋሬት በሕይወት ሳለች የታተመላት ድርሰት "Gone with the wind" ብቻ ነው። በ1996 ግን የአስራ አምስት ዓመት ጉብል ሆና የጻፈችው "ኖቬላ" ተገኝቶ በእርሷ ስም ታትሟል። እንደዚሁም በAtlanta Journal ላይ የጻፈቻቸው መጣጥፎች በአንድ ላይ ተሰብስበው በቅርቡ ታትመዋል።
------
ዛሬም ጥያቄ አለኝ!

የማርጋሬት ሚሼል ዝነኛ መጽሐፍ ግማሹ ያህል "ክፍል አንድ" ተብሎ በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉሟል። የተተረጎመበት ርእስ ምን ይላል? ተርጓሚው ማን ነው?
-----
@Jtesfaab ላይ መመለስ ይቻላል

@tfanos
619 views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ