Get Mystery Box with random crypto!

ዘ ተዋህዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewhodox — ዘ ተዋህዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewhodox — ዘ ተዋህዶ
የሰርጥ አድራሻ: @tewhodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.44K
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ናቹሁ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየንና በዚህ ቻናል የተዋህዶ ፎቶችን ስለ ሚያገኙበ ተቀላቀሉበትበየቀኑ አዳዲስ ፎቶ ያገኙበታል

ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካለ
👉 @DagiN19
ሼር በማድረግ የቤተክርስቲያን እና የቅዱሳን ምስእል ያስፋፉ!
@tewhodox
@tewhodox
@tewhodox

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 05:00:00
የመስቀል መዝሙሮችን ከነግጥሞቻቸው ቀድመው ለሚያጠኑ ሰንበት ትምህርት ቤት ያቀረበውን ቻናል በመቀላቀል ከታች ያሉትን መዝሙሮች ያጥኑ።


@Orthodox_addis_mezmur
@Orthodox_addis_mezmur
@Orthodox_addis_mezmur


መስቀል አበባ.mp3
መስቀል ተመሬኩዘን.mp3
ደስ ይበለን.mp3
እሰይ እልል በሉ.mp3
ዮም መስቀል.mp3
ቤተከርስቲያን ርእየቶ.mp3
በመስቀሉ ቤዘወነ.mp3
መስቀሉሰ.mp3
መስቀል ብርሃን.mp3
አለው ሞገስ.mp3
መስቀል አብርሃ.mp3
ርዕዩ ዕበዩ.mp3
በኃይለ መስቀሉ.mp3
ተሰኢነነ.mp3
ትቤሎ ዕሌኒ.mp3
ወይቤሎ መስቀል.mp3
ኧኸ በመስቀልከ.mp3
ወበእንተዝ አዘዙነ.mp3
ዝንቱ መስቀል ረድኤት.mp3
ደስ ይበለን.mp3
መስቀል አበራ.mp3


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘
@Orthodox_addis_mezmur
@Eotc_Books_By_Pdf
@orthodox_spiritual_poems
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
1 view02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 23:56:28
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥቷል ለመቀላቀል ከስር ያለውን ሊንክ ንኩት።




https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI




.
16 views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 08:12:58 ደብረ-ታቦር /ቡሄ/

ቡሄ ፣ ጅራፍ ማስጮ ፣ ችቦ ማብራትና ሙልሙል ዳቦ ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነ
በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ነሐሴ ውስጥ እጅግ በርካታ በዓላት ይከበራሉ፡ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ በጾመ ማርያም/
ፍልሰታ/ መገባደጃ ላይ የምናከብረው ከጌታችንንና ከአምላካችን ከመድሐኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኝ አበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የደብረ_ታቦር }በዓል ትልቁና ዋነኛው ነው፡፡
ደብረ-ታቦር ጌታችን ያዕቆብ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ካወጣቸው በኃላ በዛ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን
አምላክነቱን ያሳየበት ዕለት ነው ።ታዲያ ይህን እለትበሀገራችንና ቤተ-ክርስቲያናችን በቀላሉ አክብራው የምታልፍ በዓል አይደለም፡፡ ይልቁንም የተለያዩ ሥርዓቶችን በመፈፀም አስባው አክብራው ታልፋለች፡፡ ስለዚህም ዛሬ የበዓሉ ዋዜማ ላይ እንገኛለንና እንደ እግዚአብሔር አምላካችን መልካም ፈቃድ በበዓሉ ላይ ትርጉማቸውን
አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ለበርካታ ጊዜያት የምንፈፅማቸውን ትውፊታዊ የሃይማኖት ሥርዓቶች ምስጢራቸው ምን እንደሆነ
እናያለን፡፡ ከስሙ ለመጀመር ያህል የደብረ-ታቦር በዓል በሀገራችን ቡሄ እየተባለ ነው የሚጠራው ቡሄ ምን ማለት ነው?

ቡሄ
,
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል
ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት በዓሉ የሚውልበት ወቅት የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት የሚመጣበት ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት
የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋግሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
እስኪ የሙልሙል ዳቦን ነገር ካነሳን እርሱስ ሃይማኖታዊ ትርጉም ይኖረው እንደሆነ የታሪኩንም አመጣጥ በዛው እንመልከት

ሙልሙል ዳቦ
,
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን
አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች
በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን
በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሊነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን ነው። ታዳጊዎች በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" ሲሉን ይበሉት ዘንድ ሙልሙል ይሰጣቸዋል። ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ
መዛሙርቱን በደረሳችሁበት ሁሉ ሰላምታን ስጡ /ማቴ 10፣12/ብሏልና ሕፃናቱም የሐዋርያት ምሳሌ ስለሆኑ የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን መጽሐፋዊ ነው ማለት ነው። መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ
አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆቹም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና ህፃናቱ በሐዋሪያት ይመሰላሉ፡፡ ሌላው ሕፃናትና እረኞችን ስናነሳ ጅራፋቸውንም
ማንሳታችን አይቀሬ ነው፡፡ በሀገራችንም ከበዓሉ ቀን መድረስ አንስቶ ለበርካታ ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ጅራፍ ይጮሃል ይሄም በዚህ ታላቅ በዓል ሌላው ምሳሌያዊ ምስጢር ነው።

የጅራፍ ማጮህ ምሳሌነት
,
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን የሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና
ሕማም እናስብበታለን፣ ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ
የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ
ለማስተላለፍ ከመኖሪያ ቤት ርቆና በሜዳ በተራራማ አካባቢ ብናረገው ጠቃሚ ነው፡፡ አሁን አሁን ግን ጅራፍን በርችት መቀየሩ
የሚያመጣውም የምስጢር ተፋልሶ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
የደብረ ታቦር በዓል በዚህ አይነት ምሳሌያት እየተከበረ ሰንብቶ መጠናቀቂያ የሚሆነው በሌላ ምሳሌያዊ ምስጢር ችቦ በማብራት ነው።

ችቦ ማብራት
,
በዚህ በዓል ምዕመናን በቤተ ክርስቲያንና በየቤታቸው ችቦ ለኩሰው የማብራታቸው ምስጢር ስለሁለት ነገር ነው። የመጀመሪያው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ተራራ ላይ የገለጠውን ብርሃናዊ መለኮት ለማሳየት የሚያመለክት ሲሆን ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በተራራው ላይ የነበሩትን እረኞች ፍለጋ የወጡ ቤተሰቦቻቸው መሽቶ ስለነበር ይታያቸው ዘንድ እሳት ለኩሰው መብራት የመያዛቸውን ታሪክ ለመዘከር ነው።


በአጠቃላይ እንግዲህ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያት ጋር ይከበራል። እንግዲህ ይህ ታላቅ በዓል ከነሥርዓቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ
ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጦሞች ስድብ ፌዝና ሳቅ ያዘሉ ሆነው ይታያሉ። ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት
ያስተላልፋሉ።የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን
ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

ዘተዋህዶ
@tewhodox
@tewhodox
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ
686 views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 11:10:10
ዘተዋህዶ
@tewhodox
@tewhodox
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ
487 views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 21:52:03 ​​​​ፍልሰታ ምን ማለት ነው?

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"

‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››

ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ 

‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡

ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› 

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡

ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ 

ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው
ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡
ዘተዋህዶ
@tewhodox
@tewhodox
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ
461 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 21:31:57 ፆመ ፍልሰታ
(ጾመ ፍልሰታ) ፍልሰታ ፆም(ጾመ ለማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር የፍልሰታ ፆም ከነሀሴ 1እስከ15 ነው ቤተ ክርስትያናችን እደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌቴሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል በ8ወር በነሀሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል በዚህ የቀብር ስነስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር አላቸው ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ"እመቤታችን ተነስታ አርጋለች ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው

ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታትነዋል በዓመቱ ትንሳዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሀሴ 1 ጀምሮ ሱባዬ ገቡ በነሀሴ14ቀንም ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ከቀበሯትም በጟላ በነሀሴ16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህች ጊዜ ትፆማለች

የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን
ዘተዋህዶ
@tewhodox
@tewhodox
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ
526 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:37:12
ዘተዋህዶ
@tewhodox
@tewhodox
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ
432 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:20:38 ""ሚስጥረ ስላሴ "

ምስጢረ ሥላሴ፦ስለ ስላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው።
<= >የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል፦ እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው።
<= >እግዚአብሔር በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦
አብ ወልድ

መንፈስ ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍጥረት1፡ 2 " "ምሳሌ30፡4" ።

>እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው፦ ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦
መውለድና ፤ማስረጽ የአብ
መወለድ፡ የወልድ
መስረጽ፡ የመንፈስ ቅዱስ ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝሙር2፡7"
<=>እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።
ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።

ለመንፈስቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው። <=>የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞችትርጉም

አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸነው።

ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝሙር2፡7"

#መንፈስቅዱስ፦ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው።

{{"ኢዮብ26፡13"}}
የቅድስት ስላሴ እረድኤት
በረከታቸው አይለየን አሜን
አሜን አሜን አሜን

ሀገራችን ኢትዮጵያ የቀራንዮ ንጉስ ሰላሙን ያውርድልን
አሜን አሜን አሜን

ዘተዋህዶ
@tewhodox
@tewhodox
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ
466 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 15:18:23 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ስማኝ ልጄ!!!!!!!

1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!

2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትልበስ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!
ዘተዋህዶ
@tewhodox
@tewhodox
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩመ
558 views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 13:27:21
ገዳማትን እወዳለሁ የጥበብ ምንጭ ናቸው የምህረት መፍለቂያ ናቸው ችዬ ባግዛቸው በአፍ ብቻ መሆን የለበትም ወገኔ ዛሬ ላይ ገዳማት በአረም እየተሸፈኑ ነው ከዚህም ውስጥ አንዱ
መካነ ሕይወት ጮቢ በዓታ ለማርያም ገዳም ነው በትናንትናው ዕለት የወጣው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል ወገኔ ለገዳማት ለአድባራት እንድረስ ካሁን በፊት እርዳታም ሆነ በሌላ ነገር ገዳሙን ማገዝ ያልቻን ጊዜው አሁን ነው ያላችሁ በገንዘብ የሌላችሁ ደሞ ይህን መልእክት ቢያንስ ለአንድ የተዋሕዶ ልጅ ብትልኩለት እሱ መርዳት ይችል ይሆናል እና በገንዘብ መርዳት ካልቻላችሁ አሁንኑ ሼር አድርጉ

የእናንተን እረዳታ ይፈልጋል ከላይ ደብዳቤው እንደተገለጸው የስንዴ ፣ የአተር፣ ባቄላ፣ በተጨማሪ የጤፈ ማስ ጀምረን እራሳችንን ለመቻል እያደረግነው ጥረት በአረም ምክንያት ችግር ወስጥ ልንወድቅ ነው እናም ሰለበዓታ ስትሉ የምትችሉትን እርዱን።

የሚያስፈልገው

36 ፖላስ አረም።

ማጥፊያ የሰንዴና የጤፍ
24ዲ ፎር ዲ የባቄላና አተር አረም ማጥፊያ

ገዝቶ ለማቀበል ለሚፈልግ 0927707000 መጠቀም ይቻላል ወይም @BeGood16 በመጠቀም ሊያወራኝ ይችላሉ
በገንዘብ ለመርዳት ከታች ያለውን account ተጠቀሙ
ንግድ ባንክ
መካነ ሕይወት ጮቢ በዓታ ለማርያም አንድነት ገዳም
1000075836116

አደራ በፍጥነት ለተዋህዶ ልጆች ሼር በማድረግ ለእግዚአብሔር አበድሩ እርሱ ብድርን የማይመልስ አይደለምና

የግእዝ ትምህርት በyoutube
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
842 views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ