2022-06-29 18:56:50
"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"#
በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን ►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#
በቅዳሴና_በሌሎች_የጸሎት_ጊዜያት_የሚያገለግሉ_ንዋየ_ቅዱሳት (ከትላንቱ የቀጠለ)...
፭. ዐውድ፦ በድርገት ጊዜ ጻሕሉ የሚቀመጥበት ሰፋ ያለ ትልቅ ሰሐን ነው። ሥጋው እንዳይነጥብ (እንዳይወድቅ) የሚያገለግል ሲሆን ከነሐስ፣ ከብረትና ከእንጨት ይሠራል።
ዐውድ ስሙ እንደሚያመለክተው አደባባይ ማለት ስለሆነ ጌታችን የተፈረደበት የጲላጦስ አደባባይ ምሳሌ ነው።
፮. አጎበር፦ አጎበር ማለት "ከፍ ያለ" ማለት ሲሆን በዐውዱ ላይ የሚደፋ አራት ማዕዘን ሦስት እግር ያለው እንጨት ወይም ብረት ሊሆን ይችላል። ይህም ሥጋውን ልብሱ እንዳይነካው ከፍ አድርጎ ልብሱን የሚይዝ ነው። እንዲሁም መጎናጸፊያውን ከፍ አድርጎ ክብሩን የሚገልጽ ነው።
፯. ጽንሐሕ፦ የዕጣን ማጠኛ ወይም ማሣረጊያ ማለት ነው። ከወርቅ፣ ከብር፣ ከብረትና ከነሐስ ሊሠራ ይችላል።
በኦሪት የወርቅ ማዕጠንት እንዲሠራ ለሙሴ እግዚአብሔር ያዘዘው ነው። (ዘጸ 30፥6-10) በዚህ ምሳሌ ዛሬ ድረስ ይሠራል።
የእመቤታችን ምሳሌ ነው። አጣኑ የትስብእት/የሥጋ፤ ፍሕሙ የመለኮት፣ የወርቅ ዘንጉ የመንፈስ ቅዱስ፤ ምሳሌ ነው።
የጽንሐሕ የተለያዩ ክፍሎችና ምሳሌያዊ ትርጉማቸው፦1, ሙዳይ የሚመስለው የጽንሐሕው ክፍል፦ እጣንና እሳቱ የሚዋህዱበት ክፍል ነው። ክዳን ከበላዩ አለው። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅጸን ምሳሌ ነው። እሳቱ በዚህ ክፍል ተቀምጦ ጽንሐሕውን እንደማያቃጥለው ሁሉ እመቤታችንም እሳተ መለኮቱን በማኅጸንዋ ተሸክማው አላቃጠላትም።
2, የሙዳዩ መክደኛ፦ በክዳኑ በላይ መስቀል አለበት ይህም የቀራኒዮ ምሳሌ ነው።
3, በመካከል የሚገኝ አንድ ዘንግ፦ በሦስቱ ዘንጎች መካከል የሚገኝ አንድ ዘንግ አለ። የቅድስት ሥላሴ አንድነታቸው ምሳሌ ነው።
4, ሽኩራዎችን የያዙ ሦስት ዘንግ፦ እግዚአብሔር በመለኮት፣ በሕልውና፣ በአገዛዝ አንድ ቢሆንም በስም፣ በግብርና በአካል ሦስት መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው።
የመካከለኛውን ዘንግ አይተን አንድነቱን ስናስብ በዳር ያሉትን ሦስት ዘንጎች ተመልክተን ሦስትነቱን እናስባለን።
5, በዘንጎቹ ላይ የሚገኙት ሽኩራዎች፦ በቁጥር 12 ወይም 24 መሆን አለባቸው። 12 ከሆኑ የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፤ 24 ከሆኑ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ምሳሌ ናቸው።
ጽንሐሕው ሲወዛወዝ የሚያወጣው ድምጽ የሐዋርያት ስብከት ምሳሌ ነው። ወይም የ24 ሰማያውያን ካህናት ምስጋና ምሳሌ ነው። (ራእ 4፥7)
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄
@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->በቅዳሴና በሌሎች የጸሎት ጊዜያት የሚያገለግሉ ንዋየ ቅዱሳት...
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!
ገፅ ❹❹
2.2K views15:56