2022-08-18 21:25:25
"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን ►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#የቅብዐ_ሜሮን_አፈጻጸም ቅብዐ ሜሮን በዋነኛ ምሥጢራዊ አገልግሎቱ ከምሥጢረ ጥምቀት አፈጻጸም አይለይም።
በእኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ከላይ እንደገለጥነው የሜሮን አቀባብ ወዲያ ከጥምቀት አያይዞ ይፈጸማል።
ይህም ማለት ተጠማቂው ሰው ጥምቀት ከተፈጸመለት በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውኑ ጥምቀቱን እንደተቀበለ ሜሮን ይቀባል።
ሜሮን ሲቀባም በመንፈስ ቅዱስ መጠመቁን፣ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለዱንን፣ መንፈስ ቅዱስን እንዳደረበት ይረጋገጥለታል፤ ተጠማቂው ተጠምቆ ሜሮን መቀባቱ መንፈስ ቅዱስን መቀበሉን ያመለክታል፡፡
የአቀባቡም ሥርዓት የተጠመቀው ሕጻን እንደኾነ በክርስትና ዋሱ እቅፍ እንዳለ ይቀባል። አዋቂ እንደኾነ ከማጥመቂያው ወጥቶ እንደቆመ ቄሱ ሜሮኑን በአውራ ጣቱ እየጠለፈ “እቀብአከ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እያለ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በትዕምርተ መስቀለ ያትመዋል በመጀመሪያ ግንባሩን ያትመዋል አዕምሮው የተባረከ እንዲኾን ግራ ቀኝ አይኖቹን ያትመዋል ዓይኖቹ የእግዚአብሔርን እውነት እንዲያዩ፣ ግራ ቀኝ ጆሮቹን ያትመዋል ጆሮዎቹ የእዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ፣ አፉን ከናፍሩን ያትመዋል፣ እውነት እንዲናገር የእግዚአብሔርን ጥበብ እንዲማር፣ ደረቱን ያትመዋል፡፡ ልቡ ቅን እንዲያስብ፣ ግራ ቀኝ እጆቹን ይቀባዋል፡፡
እጆቹ ለመልካም ሥራ እንዲፋጠኑ፣
ግራ ቀኝ እግሮቹን ይቀባዋል እግሮቹ ወደ መልካም ሥራ እንዲፋጠኑ።
በአጠቃላይ መላ ሰውነቱን ይቀባዋል በኋላ ሰውነቱ የእግዚአብሔር ማደሪያ እንዲሆን።
በሜሮን የሚታተሙ በሜሮን የሚቀደሱ አዲስ ክርስቲያኖች ብቻ አይደሉም፡፡ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶ ካለቀ በኋላ አገልግሎት የሚጀመርበት በሜሮን ከተቀባ በኋላ ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ንዋያተ ታቦት፣ ጻህል፣ ጽዋ፣ ዕርፈ መስቀል፣ መሶበ ወርቅ፣ ማዕጠንት፣ ማህፈድ፣ መንበር፣ እነዚህና የመሳሰሉትም ለአገልግሎት ከመቅረባቸው በፊት በሜሮን ይታተማሉ ልዩ ጸሎትና ቡራኬም ይፈጸምባቸዋል ከዚያ በኋላ ተራ ሥራ አይሰራባቸውም፡፡
በግሪክና በሌሎች መለካውያን አቀባቡ ከእኛው ጋር ተመሳሳይነት አለው ከጥምቀት ጋር አያይዘው ይቀባሉ ሲቀቡ ግን “ማህተመ ፀጋ ዘመንፈስ ቅዱስ ዝውእቱ” እያሉ ነው። የሚቀባው ቄሱ ነው።
በዚህም መሠረት በእኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የተወሰኑትን የአቀባብ ሥርዓቶች ከዚህ በታች እንመልከት።
በዕለተ ጥምቀት ሜሮን በጳጳሳት ከተባረከ በኋላ ለአገልግሎት የተሰየመው ቄስ በእጁ ይዞ ይጸልይበታል።
መጽሐፈ ክርስትናንም ይደግማል (ያነባል)። የተጠማቂውን ፴፮ ሕዋሳት በታዘዘው መሠረት ክፍል ክፍሉን እየለየ ይቀባል።
ቅብዐ ሜሮኑን በአውራ ጣቱ እየጠቀሰ (እያስነካ) በትእምርተ መስቀል አምሳል
እቀብዐከ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እያለ ተጠማቂውን ይቀባዋል፡፡
በሥርዓተ ጥምቀት እንደገለጽነው ንዑሰ ክርስቲያን ሴት ከሆነች ልብስ ለብሳ
ከአንገቷ በላይ ኤጲስ ቆጶሱ (ቄሱ) ይቀባታል፡፡ በኋላም ከአንገት በታች ያሉትን ቀሪ ሕዋሳት ጳጳሱ ወይም ቄሱ ተጋርዶ (ተሸፍኖ) ዲያቆናዊት የቄሱን እጅ ይዛ እየመራች ይቀባታል፡፡
የተጠማቂው ፴፮ቱ ሕዋሳት በሜሮን ሲከብሩ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን
የአቀባባቸው ቅደም ተከተል የታወቀ ነው፡፡
ከላይ እንደገለጽነው ሁሉም በትእምርተ መስቀል አምሳል የሚታተሙ (የሚቀቡ) ናቸው። ግንባሩን ግራና ቀኝ ሁለት ቦታ ይቀባና በፊቱ ላይ እፍ ይገልበታል..........1
ሁለቱን የአፍንጫ በሮች፣ …........2
ሁለቱን ከናፍር፣ ……………………...2
ሁለቱን ጆሮዎች፣ ……………....2
ሁለቱን ዓይኖች፣ ……………….2
ደረቱን፣.………………………….....1
ልቡን፣ ……………..………………….1
ከመሐል አናት እስከ ወገብ ያለውን አካል፣ ………….1
መሐል ጀርባውን፣……………….1
እንብርቱን፣ ……………………….1
ሁለቱን እጆች፣ ……………….….2
የእጆቹን መገናኛዎች፣………....2
ትከሻዎቹን፣……………………….2
ማጅራቱን፣…..…………………….1
አንገቱን፣ …………………...……1
ክርኖቹን፣ …………..….….….2
የእጆቹን ውጪያዊ ክፍሎች (መዳፎች)፣ ……………....………2
የእጆቹን ውስጣዊ ክፍሎች (መዳፎች)፣ ………………...2
የእግር መገናኛዎቹን (መዳፎች)፣ …………..…2
ጉልበቶቹን፣ …………...………….2
የእግሮቹን ውጪያዊ ክፍሎች (ጣቶች)፣ ………….…….….2
የእግሮቹን ውስጣዊ ክፍሎች (ጣቶች)፣ ………....……...…2
በድምሩ 36 ሕዋሳት ይሆናሉ፡፡ እነዚህን ሕዋሳት በቅደም ተከተል ከቀባ በኋላ በተጠማቂው ላይ እጁን ጭኖ “በሰማያውያን በረከት የተባረክህ ሁን” እያለ ይባርከዋል፡፡
ሠላሳ ስድስቱ የተጠማቂው ሕዋሳት በዚህ መልክ በቅብዐ ማሮን ታትመው የእግዚአብሔር ገንዘቦች (ማደሪያዎች) ይሆናሉ፡፡ ከተጠማቂዎች ሌላ ቅብዐ ሜሮን ለሁለት ምሥጢራት ማክበሪያነት (ማተሚያነት) ያገለግላል። እነዚህም ምሥጢረ ክህነትና ምሥጢረ ተክሊል ናቸው።
በምሥጢረ ክህነት ካህናት ከቄሱ ጀምሮ ወደ ላይ ያሉት ማለትም ጳጳስና ቄስ በቅብዐ ሜሮን ከብረው ካህናተ እግዚአብሔር ይሆናሉ።
ይህም በብሉይ ኪዳን “እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግላቸው ነገር ይህ ነው፤ የቅብዐትንም ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈሰዋለህ፤ ትቀባውማለህ፡፡
ልጆቹንም ታቆርባቸዋለህ፤ ቀሚሶችንም ታለብሳቸዋለህ፤ በመታጠቂያም ታስታጥቃቸዋለህ፤ ቆብንም ታደርግላቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዓትም ክህነት ይሆንላቸዋል፡፡ እንዲሁም የአሮንና የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ፡፡
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄
@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->ቅብዐ ሜሮን የሚያስገኘው ጸጋ
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!
ገፅ ❽❽
1.9K viewsedited 18:25