2022-07-05 23:25:06
"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"#
በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን ►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
#የንዋያተ_ቅዱሳት_የአቀማመጥና_የአጠቃቀም_ሥርዓትየሥርዓት ባለቤት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለሁሉም ነገር ሥርዓት ያላት እንደመሆኑ መጠን ንዋያት ቅድሳቷንም እንዴት መጠቀም እንዳለባትና የት ማስቀመጥ እንዳለባት ሥርዓት ሠርታለች።
የንዋያተ ቅድሳት የቀጠቃቀም ሥርዓት●ከንዋያት ቅድሳት ውስጥ ካህኑ የሚጠቀምባቸው ዲያቆኑ ግን የማይጠቀምባቸው አሉ።
●ካህኑ የሚነካቸው/የሚዳስሳቸው ዲያቆኑ ግን ሊነካቸው የማይገባ አሉ።
የካህናት ልብሰ ተክህኖ እና አክሊል ከዲያቆናት የተለየ ነው።
●ልዑካኑ በመጠቀም የሚለያዩባቸው ንዋያተ ቅዱሳት ለምሳሌ፦
➺ማዕጠንቱን ካህናት ይጠቀሙበታል ዲያቆናት ግን አይጠቀሙበትም።
➺መንበሩን ካህናት ይነኩታል ዲያቆናት ግን አይነኩትም
➺ታቦተ ሕጉን ካህናት ይዳስሱታል ለዲያቆናት ግን አይፈቀድም።
➺እንዲሁም በአገልግሎት ጊዜ ለምሳሌ በቅዳሴ ልብሰ ተክህኖ በአንድ ላይ ሆኖ ከአበው ታላቅ የሆነ አባት ባርኮ ይሰጣል። ልዑካኑም መጠናቸውን ተመልክተው ይለብሳሉ። ከለበሱ በኋላ ረዘመብኝ አጠረብኝ ብሎ ማውለቅ አይፈቀድም። ልብሰ ተክህኖው እስከ ተረከዛቸው ሊሆን ይገባል። ልብሰ ተክህኖው ነጭ ሊሆን ይገባል።
እነዚህንና የመሳሰሉትን ሥርዓቶች ቤተክርስቲያን ሠርታለች።
የንዋያተ ቅዱሳት የአቀማመጥ ሥርዓትንዋያተ ቅዱሳት ተጸልዮባቸው ንዋያተ ቅዱሳት ሚለውን ስያሜ ካገኙ በኋላ፦
●በዕቃ ቤት ውስጥ ይቀመጣሉ።
●በዕጣን ይታጠናሉ።
●ብል እንዳያበላሻቸው በየጊዜው ይጎበኛሉ/ንፋስ ያገኛሉ።
●የሚታጠቡት ይታጠባሉ የማይታጠቡት ይወለወላሉ።
●ከቅጽረ ቤተክረስቲያን ውጪ ከማንኛውም ቤት አይቀመጡም።
●ለሥጋዊ ተግባር መገልገያ ማድረግ ተገቢ አይደለም። (ፍት አንቀጽ 12) እንደዚህ አይነት የአቀማመጥ ሥርዓት አላቸው።
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄
@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->በቤተክርስቲያን ዙሪያ የሚሠሩ ቤቶች
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!! ገፅ ❹❾
2.3K views20:25