Get Mystery Box with random crypto!

TESFA_ETHIO ©™ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ tesfa_ethio — TESFA_ETHIO ©™ 🇪🇹 T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tesfa_ethio — TESFA_ETHIO ©™ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @tesfa_ethio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 940
የሰርጥ መግለጫ

ጥቂቶች ያሰቡልንን ነው እየኖርን ያለነው

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-23 12:21:12 ማስመሰሉ ይቁም::
አለማችን መታከም አለባት::እናንተ ስቃይ ላይ ሆናችሁ የውሸት መሳቁን ተውቱ::

የሰዎችንም ህመም ተረዱ።የአእምሮ ሰላም ይቅደም::ለልባችን ትኩረት እንስጠው::
ማን ያዘዋል እሼቱ
1.3K views☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´ Tesfa☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 12:18:13 "ሁሉን ነገር መፈለግ፣ ሁሉን መሻት፣ ያለገደብ ለመኖር ማሰብ የዚህ ዓለም ጣጣ፣ የድካም ምንጭ ነው። የምትጠቀምበትን ያክል ብቻ እወቅ።

ዛሬ በመኖርህ አመስግን ፣ አሁንህን አጣጥም።
351 views☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´ Tesfa☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´, 09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 12:11:49 በጥንታዊ መሳርያ እያጨድን፤በዘመናዊ መሳርያ እንጫረሳለን።
339 views☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´ Tesfa☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´, 09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 14:10:36 "በዙሪያህ ያለው ሁሉ ጨለማ ከመሰለህ ወደ ቀልብህ ተመለስና እንደገና ተመልከት፤ምናልባት ብርሃን መሆን ያለብህ አንተ ልትሆን ትችላለህ"!!!
ሩሚ
339 views☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´ Tesfa☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´, 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 14:09:45 "ችሎታህ የማይዋጥላቸዉ ጓደኞችህ በዉሃ ላይ ስትራመድ ቢያዩህ ዋና ስላማይችል ነዉ ይሉሃል።" አንተ ጉዞህም ቀጥል።
ኦሾ
298 views☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´ Tesfa☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 14:03:31 እንደ ንስር መብረር ከፈለክ ከዳክዬ ጋር መዋኘት አቁም !!
275 views☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´ Tesfa☆:*´¨`*:.☆(¯`*•.¸,¤°´, 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 21:20:09
በጫጫታ የተደበቀ ማንነት!

ጠዋት እንደነቃሁ ከአልጋዬ ሳልወጣ የመጀመሪያ ስራዬ ሶሻል ሚዲያ በመክፈት ምን እንደተለጠፈና ምን እንደተባለ ማየትና ማድመጥ ነው፡፡ ከአልጋዬ ወጥቼ ለመውጣት ስዘጋጅ የጆሮ ማድመጫ (Earphone) በጆሮዎቼ ላይ ሰክቼ ከሰዎች ጋር እያወራሁ መዘገጃጀት አዘውትራለሁ፡፡

ከቤቴ ስወጣም አሁንም የጆሮ ማድመጫ (Earphone) በጆሮዎቼ ላይ ሰክቼ ጠዋት የጀመርኩትን የሚዲያ ጉብኝት መቀጠል ወይም የሞቀ ሙዚቃ እያደመጡ መሄድ የየእለት ልምምዴ ነው፡፡

ስራዬ ቦታ ግር-ግር ነው፡፡ በሻይ ጊዜ ካፌው ጫጫታ ነው፡፡ ምሳ የምንሄደው በቡድን ሲሆን እዚያም ካለው ጫጫታ ጋር እኛም እንደመርና እየተንጫጫን እንመገባለን፡፡

ከስራ በኋላ ወደቤቴ ከመሄዴ በፊት ከጓደኞቼ ጋር ስንንጫጫ አምሽተን እቤት እገባለሁ፡፡ ማታም እቤት ስገባ ቴሌቭዥኑ ካልጮኸ ቅር ይለኛል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ቲቪው እንደበራና እንዳወራ ሲያድር ደስ ይለኛል፡፡

ለማሰብ፣ ለማሰላሰል፣ ለማቀድ፣ ራስን ለማየት . . . ጊዜ እስከማጣ ደረስ በጫጫታ ተደብቄ ይሆን?

ማናልባት ትኩረት የማጣው፣ አንድን ነገር የማልጀምረው፣ የጀመርኩትን ነገር የማልቀጥለውና የማልጨርሰው፣ ሕይወቴ ከእለት እለት እድገት የማይታይበት ለዚያ ይሆን?
https://t.me/tesfa_ethio
808 viewsTESFA_ETHIO, edited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 21:18:50 “ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች”

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በOctober 22, 1925 ጋንዲ (Mohandas Gandhi) በየሳምንቱ በሚያሳትመው Young India በተሰኘው የዜና መጽሔቱ ላይ “ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች” (The Seven Social Sins) የተሰኘን ጽሑፍ አስፍሮ ነበር፡፡
እነዚህ ዘመን-ዘለል እውነታዎች የግላችንንና የሕብረተሰባችንን ወቅታዊ ልምምድ በመገምገም ለማስተካከል ድጋፍ እንደሚያደርጉልን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

1. ስራ የሌለው ብልጽግና (Wealth without work)
2. ሕሊና የሌለው ደስታ (Pleasure without conscience)
3. ባህሪይ የሌለው እውቀት (Knowledge without character)
4. ግብረ-ገብ የሌለው ንግድ (Commerce without morality)
5. ሰብዓዊ ርህራሄ የሌለው ሳይንስ (Science without humanity)
6. መስዋእትነት የሌለው ኃይማኖት (Religion without sacrifice)
7. መርህ የሌለው ፖለቲካ (Politics without principles)
https://t.me/tesfa_ethio
546 viewsTESFA_ETHIO, edited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-18 22:49:31
በማይደገም ዛሬ ትላንትናን እየደገምን አንኑር
ቪዲዮውን አይታችሁ ስትጨርሱ ከተመቻችሁ share ማድረግ እንዳትረሱ።
Comment ካለችሁ ደግሞ በ @tesfa_1 ላይ ፃፉልኝ
428 viewsTESFA_ETHIO, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-17 18:42:56 ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
≈ዶ/ር ምህረት ደበበ

1. ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም "... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።

6. አታቋርጥ ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ።ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው።ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመስግን ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመስግን።

9. ያለስስት አድንቅ ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን
ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ-ስርዓት ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው
ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።

16. ተቆጠብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው።ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ።
https://t.me/tesfa_ethio
443 viewsTESFA_ETHIO, 15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ