Get Mystery Box with random crypto!

አፄዎቹ የኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ atsewechu_yegna — አፄዎቹ የኛ
የቴሌግራም ቻናል አርማ atsewechu_yegna — አፄዎቹ የኛ
የሰርጥ አድራሻ: @atsewechu_yegna
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 853
የሰርጥ መግለጫ

🔴⚪🔴 አፄዎቹ የኛ 🔴⚪🔴
💯% የቻናሉ አላማወች
👉 የቀጥታ ስርጭት
👉 የክለባችን የሆኑ ፎቶዎችን
👉 ቪዲዬዎችን
👉 የተጫዋቾችን ፎቶወች
👉 የክለቡን መዝሙር
👉 የደጋፊዎች ፎቶ
👉 የዝውውር ዜናወችን ያገኛሉ
🇦🇹 ፋሲል ከነማ ከክለብም በላይ ነው!!! 🇦🇹

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 13:40:16 የፋሲል ከነማ ዋና አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ (ቲጋና) ከፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ገጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

*ፋሲል ከነማ፦ ጤና ይስጥልኝ ኃይሉ ነጋሽ የፋሲል ከነማ ዋና አሰልጣኝ ሆነህ በመሾምህ እንኳን ደስ አለህ እያልኩ ቡድኑን በሀላፊነት በመረከብህ ምን ተሰማህ? ፊርማህ ለአንድ አመት መሆኑ የእግር ኳስ ሀሳብን ለመተግበር የሚፈጥረው አሉታዊ ተፅዕኖ አለ??

*አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ፦ እንኳን አብሮ ደስ አለን!
ቡድኑን በሀላፊነት በመረከቤ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። ምክንያቱም ፋሲል ከነማ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጠንካራነቱን በዋንጫ ክብሮች ያጀበ ለተከታታይ አመት በአፍሪካ መድረክ ሀገር የወከለ ከምስርታው ጀምሮ ትልቅ በሆነ ክለብ እና ክለቡን የህይወታቸው አካል አድርገው በሚደግፉ ደጋፊዎች ባሉበት ሁኔታ ሀላፊነት ወስዶ መሰራት ያስደስታል።
ሲቀጥል ከልጅነት እስከ እውቀት ላሳደገኝ ክለቤ ከተጫዋችነት ጀምሮ አሁን ደግሞ በአሰልጣኝነት መስራት ክብርም ኩራትም ነው እያልኩ የፊርማ አመት መብዛትና ማጠር ሳይሆን በምታስመዘግበው የስኬት ስራህ ነው ቀጣይነትህ የሚረጋገጠው እኔ ደግሞ ለክለቡ አዲስ ሰው ስላልሆንኩ ተፅዕኖ የለብኝም።

*ፋሲል ከነማ፦ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት በስምምነት ከተረከብክ በኋላ ለ2015 የውድድር አመት ዝግጅት ጀምራችኋል ከጀመራችሁ ስንት ጊዜ ሆናችሁ?? ዝግጅታችሁስ በምን አይነት ሁኔታ እየሄደ ይገኛል።

*አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ፦ ለ2015 ውድድር ዝግጅት ከጀመርን 23 ቀን አስቆጥረናል። የቡድናችን ስኳድ ተሟልቶ ልምምድ ለመጀመር ያልቻልንባቸው ሁኔታዎች የተጫዋቾች ጉዳት እና ለብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት ለመስጠት በሄዱ ልጆች እንዲሁም በሀገር ውስጥ የአጥቂ ቦታ ተጫዋች ለማስፈረም ያደረግነው ጥረት ባለመሳካቱ የውጭ ሀገር ተጫዋች ለማስፈረም ሂደቱ ጊዜ በመውሰዱ ልጆችን አሟልቶ ዝግጅት ለመስራት ብንቸገርም ባሉት ልጆች ዝግጅታችን በተገቢው መንገድ እየሰራን መጠናል አሁንም ጉዳት የተመለሱትን አዲስ ክለባችን የሚቀላቀሉትን እየጨመርን ልምምዳችን በቀን ሁለት ጊዜ በሜዳ ላይ እና በጅምናዚየም እየሰራን እንገኛለን።

*ፋሲል ከነማ፦ የአፄዎቹን ቡድን በ2015 የውድድር አመት በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እና በፕሪሚየር ሊጉ በአሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ ስር በምን አይነት የእግር ኳስ ሀሳብ እና አቀራረብ እንጠብቀው??

*አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ፦ በእርግጥ ፋሲል ከነማ ከ 2011 ዓ.ም ጀምሮ የራሱ የሆነ ቅርፅ የጨዋታ መንገድ ያለው ቡድን ነው። ሆኖም አሁንም ቢሆን የያዝናቸውን ተጫዋቾች ጥራት መሰረት አድርገን ኳስን ተቆጣጥሮ የሚጫወትና ቶሎ ቶሎ ወደ ተጋጣሚ የጎል ክልል የሚደርስ ቡድን ለመሰራት ጥረት እያደረግን ነው።

*ፋሲል ከነማ፦ በተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለባችን ለዋንጫ ክብር ሲበቃ ወሳኝ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች ጋር ተለያቶ አዳዲስ ልጆች አስፈርመናል ይሄ የቡድን ግንባታ እንዴት ይገለፃል??
ለእግር ኳስ ሀሳብህ መተግበሪያ የሚሆኑ ተጫዋቾችን አሟልተናል ብለህ ታምናለህ?? ከዚህ በኋላስ የተጫዋች ግዥ ይሆረናል??

*አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ፦ በእርግጥ ለ2015 እቅዳችን ይህ አልነበረም አብዛኛው የክለባችን ተጫዋቾች ውላቸውን የጨረሱ ስለነበሩ መቆየት ያለባቸውን በማቆየት ክፍተት አለብን ብለን ባሰብናቸው ቦታዎች ብቻ ጨምረን መጓዝ ነበር እቅዳችን...አስፈራሚ ኮሚቴዎች ውላቸውን ጨርሰው የምንፈልጋቸውን ልጆች ማቆየት እንዲቻል ከፍኛ ጥረት ቢያደርጉም በተለያዩ ምክኒያቶች አልተሳካም ሆኖም ተጫዋቾች ክለቡን ጠቅመዋል እነሱም ተጠቅመዋል ነገር ግን ማንንም ተጫዋች ያለፍላጎቱ ማቆየት አንፈልግም አዲስ የተቀላቀሉን ተጫዋቾች ክለባችንን የሚመጥኑ ስለሆኑ የተሻለ ነገር እንሰራለን ብለን እናምናለን። የተጫዋች ግዥን በተመለከተ አሁን ባለን ስኳድ ደስተኞች ነን ነገር ግን ፋሲልን ሊመጥን ይችላል ብለን ያመንበት የአጥቂ ቦታ ተጫዋች ካለ ወደፊት የምናየው ይሆናል።

*ፋሲል ከነማ፦ ከታዳጊ ቡድኑ ያደጉ አዲስ ተጫዋቾች አሉ? ከዚህ በፊት ያደጉትን ወጣቶች እድል መስጠት ላይ ምን ታስቧል?? የቡድናችን ስኳድ ጥልቀት እንዴት ነው??

*አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ፦ ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ያስፈልጉናል ብለን ያመንባቸውን ልጆች ብቻ ነው ወደ ዝግጅት ይዘን የገባነው ነገር ግን ዘንድሮም ልክ እንደሁልጊዜው ከታዳጊ ቡድኑ የሚመጡ ተጫዋቾች ይኖራሉ ያንንም የምናደርገው የዚህን የደርሶ መልስ ጨዋታ ካደረግን በኋላ ወደ ቡድኑ ተቀላቀለው አብረው ይሰራሉ። የቡድናችን ስኳድ ከአምናው የተሻለ ይሆናል ብለን እናምናለን በሁሉም ቦታዎች ላይ አማራጮች አሉ በዛላይ ከታዳጊዎቻችን ትልቅ ጥረት እና መሻሻል እንጠብቃለን እድሉን ለማግኘት ጠንክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል።

*ፋሲል ከነማ፦ የአሰልጣኝ አባላቶችህ እገዛ እንዴት ነው? የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ እየደረሰ ነው የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ እና ዝግጁ ለመሆን ምን እየተሰራ ነው??

*አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ፦ በእውነት ነው የምልህ የፋሲል ጥንካሬ ዋናው ስታፉ ነው። ሁሉም ክለብ እንዲኖረው የሚመኘው ሊኖረውም የሚገባ በጣም ጠንካራና ቀና የሆነ ስራህን በሙሉ የሚያቀልልህ ይቻላል እንጂ የማይቻል ነገር የለም ብሎ የሚያሰብ ትልቅ የሆነ የቡድን መሪ ይዘህ ካዛም አለፍ ስትል ይሄ የአንተሰራ ነው ይሄ የእኔ ሰራ ነው የማይባባል ሰታፍ ይዘህ እንዴት ውጤታማ አትሆንም ይሄ ነው የእኛ ትልቁ የውጤታችን ሚስጢር!! ይሄ መተሳሰብና የስራ ፍላጎት ተጫዋቾች ላይ በመወረዱ ውጤታማ እንድንሆን አድርጎናል፡፡

የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ጨዋታችን እየደረሰነው ቢያንስ ከዚህ በኋላ 10 ቀናቶች ይቀራሉ ሥራችንን በአግባቡ እየሰራን ነው ነገር ግን ትልቁ ችግራችን የወዳጅነት ጨዋታዎችን አለማድረጋችን ነው። ቀደም ብለው ዝግጅት ከጀመሩ ክለቦች ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ለማድረግ ጥረት እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን እዚሁ ባህር ዳር ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ለመጫወት ሞክረናል ወደፊትም ለማድረግ ፕሮግራም ይዘናል ይሄ በቂ ነው ብለን አናስብም ባሉት ቀሪ ቀናቶች ውስጥ አንድም ጨዋታ ቢሆን ከተሻለ ቡድን ጋር ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን።

*ፋሲል ከነማ፦ ከፋሲል ከነማ ቦርድ አመራሮች እና ደጋፊዎቻችን ምን አይነት እገዛ ትጠብቃለህ??

*አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ፦ የክለቡ ቦርድ አመራሮች አቅማቸው በፈቀደ መጠን መስራት ያለባቸውን እያደረጉ ነው ያለው ከዚህ በላይ ክለባችን ለማጠናከር ትልቅ ስራ እንደሚጠብቃቸው እያመንኩ ቡድኑን ለመገንባት በሰሩት ስራ ላቅያለ ምስጋና አለኝ።
ስለ ደጋፊው ምን እንደምልህ አላቅም የውጤታቸን ትልቁ እና ዋናው ተመስጋኝ ደጋፊዎቻችን ናቸው!! ክለባችን እንዲጠናከር ከመፈለግ አንፃር በዝውውር ወቅት ምን ያህል ጭንቀት እንደነበር ሁላችንም ተረድተነዋል አሁንም ቢሆን ቡድኑን የሚያውቁ አብዛኛውን ነባር ተጫዋቾችን ይዘን በመቀጠላችን ከአምናው የተሻለ ቡድን እንዳለን ተረድተው የተሻለ ነገር እንድንሰራ እንደተለመደው የማያራቋርጥ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪየን አስተላልፋለሁ።

ፋሲል ከነማ፦ ለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን!!

*አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ (ቲጋና)እኔም ከልብ አመሰግናለሁ።


#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
450 viewsedited  10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:27:36
#ፋሲል_ከነማ ጋምቢያዊ ዜግነት ያለውን አጥቂ አስፈርሟል!!

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ክለባችን ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክል ሲሆን ለቀጣይ የ2015 አመት የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ቡድኑን ለማጠናከር አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም በቃል ደረጃ ከስምምነት ደርሶ የነበረውን ጋምቢያዊ ዜግነት ያለውን አጥቂ በዛሬው ዕለት የግሉ አድርጓል፡፡

ፋሲል ከነማ ያስፈረመው አጥቂ ጋራይ ጆፋን ዜግነቱ ጋምቢያዊ ሲሆን እድሜው 24 ቁመቱ 1-82 ሲሆን በሀገሩ ጋምቢያ የጀመረው የእግር ኳስ ህይወቱ በእስራኤል እና ጆርጂያ ክለቦች ቀጥሎ በጥሩ አቋም ላይ እንዳሳለፈ መረጃዎች የሚገልፁ ሲሆን #ጆፋን ወጣት ፣ ፈጣን እና ባለክህሎት ተጫዋች በመሆኑ በክለባችን ውስጥ ትልቅ ግልጋሎት እንደሚሰጥ ታምኖበት ለአንድ አመት በሚያቆይ ውል ፈርሟል።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
538 views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:42:35
ፋሲል ከነማ ጋምቢያዊ አጥቂ አስፈርሟል !

በዝውውር መስኮቱ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል ችለዉ የነበሩት ፋሲል ከነማዎች በተቃራኒው ከፊት መስመር አጥቂዎቻቸዉ ኦኪኪ አፎላቢ እና ሙጅብ ቃሲም ጋር ከተለያዩ በኋላ ግን እስከ ትላንት ድረስ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ሳያስፈርሙ መቆየታቸው ይታወሳል።

አማራ ስፖርት ከደቂቃዎች በፊት ባረጋገጠው መረጃ መሰረት አፄዎቹ ጋይራ ዮፍ የተባለዉን ጋምቢያዊ አጥቂ ማስፈረማቸዉ ታውቋል። ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ለእስራኤሎቹ ለአል ፋሀም ኤፍሲ ፣ ራማት ሀስሻሮን እና ቢን ይሁዳ ለመሳሰሉት ክለቦች እንዲሁም ለጋምቢያዉ ዋሊዳን ክለብ መጫወት የቻለ ሲሆን በአፄዎቹ ቤትም ለአንድ አመት ለመቆየት ፊርማዉን አኑሯል።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
520 viewsedited  10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:38:09
አሠልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ በዋና አሠልጣኝነት ሚና ከፋሲል ከነማ ጋር በቀጣዩ ዓመት ለመቆየት ውላቸውን አድሰዋል።
በተጠናቀቀው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ ከቀድሞ አሠልጣኙ ሥዩም ከበደ ጋር ተለያይቶ ዓመቱን በምክትል አሠልጣኙ ኃይሉ ነጋሽ እየተመራ ማገባደዱ ይታወቃል። በቀጣዩ ዓመት በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ሀገራችንን የሚወክለው ቡድኑም ዝግጅቱን ባህር ዳር ከተማ ላይ መቀመጫውን በማድረግ እየሰራ ይገኛል።

ክለቡን በጊዜያዊነት እያሰለጠኑ የነበሩት አሠልጣኝ ኃይሉ ነጋሽም ከደቂቃዎች በፊት በዋና አሠልጣኝነት መንበር የአንድ ዓመት ውል መፈረማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች የነበሩት አሠልጣኝ ኃይሉ ከ2010 ጀምሮ ክለቡን በምክትል አሠልጣኝነት ሲያገለግሉ እንደነበር አይዘነጋም። ከላይ እንደገለፅነውም ዘንድሮ ከአሠልጣኝ ሥዩም ስንብት በኋላ ክለቡን በጊዜያዊነት መርተው 2ኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ረድተው ነበር። አሁን ደግሞ ለከርሞ በዋና አሠልጣኝነት ለመዝለቅ የአንድ ዓመት ፊርማቸውን አኑረዋል።

በምክትል አሠልጣኝነት ሚና ሙሉቀን አቡሀይ እንደሚቀጥሉ ሲገለፅ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ የአሠልጣኝ ዘማርያም ምክትል የነበሩት እና ዋናው አሠልጣኝ ከቦታቸው ሲነሱ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በመንበሩ የቆዩት አሠልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ ደግሞ የአካል ብቃት አሠልጣኝ ሆነው የአሠልጣኝ ቡድኑን ተቀላቅለዋል።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
720 viewsedited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 15:18:37
#ፋሲል ከነማን ለመደገፍ ቀላል መንገድ ተዘጋጅቷል!!

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማህበር የአፄዎቹ ደጋፊዎች ክለባችን በተግባር ለመደገፍ የሚያገለግል የአባልነት መታወቂያ በቀላል መንገድ እንዲኖራቸው የሚያደርግ አሰራርን ይዞ የቀረበ ሲሆን ደጋፊዎቻችን በቋሚነት የክለባቸው አባል ሆነው መታወቂያ በማውጣትና በማደስ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ሆኔታዎች ተመቻችተዋል።

ይህንን ሊንክ በመጫን አባልነት ቅፁን ሞልተው ይላኩ!
ለሌሎች ደጋፊዎች ያጋሩ!!

https://forms.gle/ksqsPeiGbBgwpmSaA

ፋሲል ከነማን በተግባር ይደግፉ!!

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
970 viewsedited  12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 09:06:31
ነብሮ ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ ሆኗል
አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸው ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ ሆኗል !!

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የቻን ውድድር ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን አቻውን በደርሶ መልስ ውጤት ረቶ በመጨረሻው ዙር ከሩዋንዳ ጋር ለመፋለም ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ቡድኑ በዛሬው ዕለት ተሰባስቦ የጂምናዚየም ልምምድ ማድረግ የጀመረ ሲሆን ወሳኝ አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸውን ግን በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጪ አድርጓል። በምትኩም የሀዋሳ ከተማው ወንድማገኝ ኃይሉ ጥሪ እንደተደረገለት ተገልጿል።

Via Soccer Ethiopia

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
1.1K viewsedited  06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 20:06:37
ቅዱስ ጊዮርጊስ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚውን አውቋል።

ቡድኑ ይህን ዙር የሚያልፍ ከሆነ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ከዛለን (ደቡብ ሱዳን) እና ያንግ አፍሪካ (ታንዛኒያ) አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
923 viewsedited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 20:06:37
ፋሲል ከነማ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚውን አውቋል።

ቡድኑ ይህንን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ከሴፋክሲን (ቱኒዚያ) ጋር የሚፋለም ይሆናል።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
842 viewsedited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 11:54:34
#አፄዎቹ የኮንፌዴሬሽን ካፕ ተጋጣሚያቸውን #በነገዉ ዕለት አመሻሽ የሚያዎቁም ይሆና

ሀገራችንን በወከል በትልቁ የአፍሪካ የውድድር መድረክ የሚሳተፉት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን በነገው ዕለት የሚያውቁ ይሆናል ።

በቅድመ ማጣርያው ተሳታፊ የሆኑት ክለቦቻችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድሮች ላይ የሚካፈሉ ይሆናል ።

የቅድመ ማጠርያ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱ በነገው ዕለት በግብፅ ካይሮ አመሻሹን ይፋ እንደሚሆን ተገልጿል ።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
834 viewsedited  08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 19:16:03
#ፋሲል_ከነማ የ2015 ውድድር አመት ቅድመ ዝግጅት በባህርዳር ከተማ ያደርጋል!!

በተጠናቀቀው የ2014 ኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በከፍተኛ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ በማሳለፍ የ2ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት አፄዎቹ ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታ እና ለ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የቅድመ ዝግጅት ልምምዳቸውን ለመጀመር የፊታችን ሰኞ ነሐሴ 2/12/14 በውቢቷ ባህርዳር ከተማ ማረፊያቸውን በማድረግ ዝግጅታቸውን በቀን ሁለት ጊዜ በሜዳ እና በጅምናዚየም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ይጀምራሉ።

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ቡድኑን በአዲስ መልክ ለማጠናከር በአሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ (ቲጋና) መሪነት የበርካታ ተጫዋቾችን ውል በማደስና አዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኝ ሲሆን ውላቸውን ካጠናቀቁ ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

አፄዎቹ በባህርዳር መሰብሰቢያቸውን ካደረጉ በኋላ የህክምና ምርመራ ፣ የአመጋገብ ስርዓት እና የአሸናፊነት ስነልቦና ግንባታ ትምህርት በመውሰድ ቅድመ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ።

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የ2015 አመት የቡድን ስብስብን የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት እናሳውቃለን።

መልካም የዝግጅት ጊዜ!!

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


     #join #ተቀላቀሉ #share
          @Atsewechu_yegna
          @Atsewechu_yegna
760 viewsedited  16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ