Get Mystery Box with random crypto!

TESTIMONY ☑

የቴሌግራም ቻናል አርማ testimonytube — TESTIMONY ☑ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ testimonytube — TESTIMONY ☑
የሰርጥ አድራሻ: @testimonytube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በየቀኑ የእግዚአብሄርን በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን በምስክርነት የሚቀርብበት ቻናል ነው ከሀገር ውስጥ የአገልጋዮች ዘማሪያን ሰባኪዎች እንዲሁም ከአለም ዙርያ የተገኙ ምስክርነቶች በየቀኑ ይቀርባሉ።
Contact Us☞ @TliveBot
ዋናው ገፃችን @KALTUBE
●Subscribe Us On YouTube👇
https://www.youtube.com/c/TestimonyTube

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-20 21:19:30 .ቆይታ ከዘማሪት አስቴር አበበ ጋር
ዘማሪት አስቴር በህይወቷ ፤ በቤተሰቧ ፤ በስደት ስላሳለፈችው ህይወት አሁን ስለምትኖርበት ሀገር እና ከነዛ ህይወቷ ስለወጡት ዝማሬዎቿ ያደረገችውን እጅግ አስተማሪ እና ቆይታና ውይይት እንድትከታተሉ እና ለሌሎች እንድታደርሱ እንጋብዛለን።
t.me/KALTUBE
Source - Talking Mezmur
Share Share Share
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
473 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-07 15:58:16 https://t.me/KALTUBE?livestream=61a4980801520117cf
753 views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 21:57:04
ስለ ኢየሱስ
( ለፕሮፋይላችሁ እና ለወዳጆቻችሁ ለመላክ )
HD
#QouteVerse #Kaltube #Jesus
#Jesusislove #jesusishealer
#JesusisCompassionate
#JesusisShepherd . . .

Share
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
910 views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-25 21:45:19 . ለውጠኝ ለውጠኝ ጌታዬ
Birhane Wengel Choir
Amazing Gospel Song
Share Share Share
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
757 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-16 16:22:48 ናይት ክለብ አድሬ በማግስቱ መድረክ ላይ እቆማለሁ!!

LIFE EX. 
ይህ በቃልቲዩብ የሚዘጋጅ ፕሮግራም ክርስቲያኖች በተለያየ አለማዊ ህይወት እና የህይወት ተፅእኖ ውስጥ የሚያልፉበትን የህይወት ገጠመኝ በልቦለድ መልክ የሚያስቃኝ ዝግጅት ነው። በሳምንቱ በተመረጡ ቀናት ጠዋት 3:00 ይቀርባል። ሶስተኛውን ታሪክ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

........

ለራሴ ያለኝ እይታ ሲበዛ የተጋነነ ነው። ራሴን በጣም ቆንጆ ፣ የፈለገችውን ነገር በፈለገችው ጊዜ ማግኘት የምትችል እና አሁን የተረዳሁት አዲሱ ማንነቴ ድንቅ የማስመሰል ወይም የትወና ሰው ነኝ።  ቤተሰቦቼ ገና ድሮ የአሁኑን ዘመን ውጥንቅጥ የሌለበት ክርስትና የኖሩ የቀደሙ አገልጋዮች ነበሩ። ከአያቶቼ ጀምሮ የወንጌል አገልጋዮች ምናልባትም ስማቸውን ብጠቅስላችሁ የምታውቋቸውን ታላላቅ አገልጋዮች በቅርበት የሚያውቁ ነበሩ። እኔም የጥሩ አገልጋይ ባልና ሚስት ልጅ ነኝ። ጌታን በዚ ጊዜ እንደዚ ሁኔታ ላይ ተቀበልኩ የምልበት ወቅት አልነበረም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስላደግኩ እዚም እዚያም ስል ቆይቼ መጨረሻ ላይ ወደ ወጣቶች ህብረት ተቀላቀልኩ። በዚያን ጊዜ ያን ያህል በህይወቴ አስከፊ ነገር ላይ አልነበርኩም የቤተሰብም ቁጥጥር ስላለ ማለት ነው።

ነገር ግን አንዱ የህይወቴ ምዕራፍ በእኔ ውስጥ የመሸገውን ክፉ ማንነት ገልጦ አወጣው። ከአራት አመታት በፊት ነበር የሀይስኩል ትምህርቴን አጠናቅቄ ወደ ዩኒቨርስቲ የገባሁበት ለኔም አዲስ የሆነ ህይወት። ዘመድ የሚባል የሌለበት ማንም የማያውቀኝ ስፍራ። ጊቢ የተመደብኩበት ዶርም ስገባ ሶስት ሴቶች ከኔ ቀድመው ገብተው አልጋቸውን አንጥፈው አገኘሁ። ስማቸውንም ሜሮን ፤ ማህሌት ፤ ማህደር እያሉ ተዋወቁኝ የኔም ስም ሜሮን ነበር። በስማችን ቅደም ተከተል ስለተመደብን።

አይቼው የማላውቀው ህይወት የተጀመረው አርብ ምሽት ላይ ነበር ሴቶቹ ከምሽቱ 1ሰአት ላይ መለባበስ ጀመሩ የት ልትሄዱ ነው ብዬ ስጠይቅ ኦቨር ልንወጣ ነው አሉኝ። በወቅቱ ምን ማለት እንደሆነ ስላላወቅኩ ጠየቅኳቸው ናይት ክለብ ከጓደኞቻቸው ጋር ሊዝናኑ መሆኑን ነገሩኝ። ክርስቲያን መሆኔን ስላልነገርኳቸው አንቺም ልበሺና አብረን እንሂድ አሉኝ።
ይሄን በመጫን ይቀጥሉ...


@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
884 views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-09 21:24:55 የእግዚአብሔርን ክብር ከልቡ የሚራብ ትውልድ እየጠፋ እንዳለ ይሰማኛል ልቤ በራሴም በሰዎችም ያዝናል

LIFE EX.
ይህ በቃልቲዩብ የሚዘጋጅ ፕሮግራም ክርስቲያኖች በተለያየ አለማዊ ህይወት እና የኑሮ ተፅእኖ ውስጥ የሚያልፉበትን የህይወት ገጠመኝ በልቦለድ መልክ የሚያስቃኝ ዝግጅት ነው። በሳምንቱ በተመረጡ ቀናት ጠዋት 3:00 ይቀርባል። ሁለተኛውን ታሪክ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።
.......

ጌታን ያገኘሁበትን 2ተኛ አመት ለብቻዬ በማስብባት ልዩ ቀኔ እንደሌላው ጊዜ ደስተኛ አልነበርኩም። ምክንያቱም በህይወቴ ከአመት አመት እጅግ ደክሜዬለሁ። ጌታን ስቀበል በእውነቱ ወንጌልን ተረድቼ አልነበረም በቅንነት ነበር። ኋላ ላይ ግን መፅሐፍቅዱን የበለጠ ሳነብ ከእግዚአብሔር ጋር በፀሎት ስጣበቅ ወንጌል ምን እንደሆነ። እግዚአብሔር ምን አይነት አምላክ እንደሆነ ለፈጠራቸው ህዝቦች ምን አይነት በጎ ሀሳብ እንዳለው የበለጠ እየተረዳሁ ስሄድ ህይወቴን ለሱ አብልጬ ሰጠሁ ጊዜዬን በፀሎትና በአገልግሎት ከመጣበቡ ብዛት ምግብ ሳልበላ የምውልባቸው ቀናት ብዙ ነበሩ። በህይወቴ ግን ፍፁም እርካታ ነበረኝ። የበለጠ መሻቴ የነበረው ፍጥረት ሁሉ ኢየሱስን እንዲያውቅ ከዘልአለም ሞት እንዲድን በመሆኑ ወንጌል በገባሁበት ቦታ ሁሉ ያልመሰከርኩበት የለም ላብ እስኪያጠምቀኝ ድረስ በአደባባዮች ቆሜ የጌታዬን ማዳን አወራ ነበር። ወደ ቤቴም ስመለስ ለሰአታት በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክኬ ትውልዱ እሱን እንዲያውቅ አይኖቹ እንዲበራለት የእግዚአብሔር ክብር እንዲገለጥ አጥብቄ በእንባ እፀለይ ነበር።

አንድ ወቅት ላይ ቤተሰቤ ከተማ ልንቀይር መሆኑን አሳወቁኝ። ወደ አዕምሮዬ የመጣው ግን ያቺ ቀኑን ሙሉ የምውልባት የቤተክርስቲያን ክፍል ፤ እነዛ ለእግዚአብሔር ፈቃድና ሀሳብ የተሰጡ ንፁህ እና ታታሪ ወንድሞቼ እና እህቶቼን መለየቱ ነበር። በቤተሰቤ ስር ኑሮዬ ግዴታ በመሆኑ አማራጭ አልነበረኝም ሞቅ ወዳለው ግርግርና ትርምስ ወደ ሞላው ከተማ አዲስአበባ ከቤተሰቤ ጋር መጣን። ሰፈራችን አካባቢ በግዝፈታቸው ተለቅ ያሉ ብዙ ሰው የሚታደምባቸው ቤተክርስቲያኖች ነበሩ። ከነርሱም በታች አነስተኛ ቁጥር ያለው ሰው የሚይዙ ቤተክርስቲያኖችም ነበሩ። ቤተሰቤ አባል ሆነን እንድንካፈል የመረጡት ትልቅ ወይም Mega Church የሚባለውን ነበር። መጀመርያ አካባቢ ላይ በህይወቴ በፀሎቴ ላይ የህይወት ልዩነት አልነበረኝም በትጋት እፀልይ አገለግል ነበር። ኋላ ላይ ግን የቤተክርስቲያኑን የተለያዩ ህብረቶች መቀላቀል ጀመርኩ በገባሁበት ህብረት ያለነው ወጣቶች እጅግ ብዙ ስንሆን እኛን ለመከታተል ከኛ በእድሜ ከፍ ያለ ሰው ህብረቱን ይመራ ነበር። ህብረቱ ውስጥ ከልቡ አጠገቡ ላለው ሰዉ የሚጨነቅ ፤ ፊቱ ከመፀለይና በእግዚአብሔር ፊት ከመሆን ብዛት የወዛ ሰው ማግኘት ይከብድ ነበር። ሁሉም በሳምንት አንድ ቀን መርሀግብር የሚያደርግበት ስፍራ እንጂ ምንም ለህይወት የሚተርፍ ነገር እንደሌለበት በተደጋጋሚ አየሁ። በህብረታችን የነበሩት እህቶች የሚያስጨንቃቸው አለባበስና ውበት እንጂ ከልብ ለእግዚአብሔር መኖር መላ ህይወትን ለርሱ መስዋዕት አድርጎ መስጠት አልነበረም። በወንድሞች በኩል በመፅሐፍቅዱስ ጥናታችን ሰአት የማይሰማው ድምፃቸው የኳስ ወሬዎችን እና አዲስ የወጣ መዝሙር ቪዲዩ ለማውራት ሲሆን መደማመጥ ያቅታቸዋል። የሆነ ነገር ጎድሏል ብዬ ብዙ ጊዜ አስባለሁ። በነርሱ እይታ ከገጠር የመጣሁ በአለባበሴም ደካማ ስለነበርኩ ብዙዎቹ አይቀርቡኝም ነበር። ልቤ ላይ ያለውን ሸክም የሚጋራኝ ለፀሎት ልቡ ክፍት የሆነ ስለ እግዚአብሔር ስለ ኢየሱስ ሲሰማ ሀሴት የሚያደርግ ሰው ማግኘት ከበደኝ። ተንበርክኮ ከመፀለይ ይልቅ እለት እለት የህብረታችንን ጉድለት ማሰላሰል ብቻ አበዛሁ። ቀድሞ ከነበረኝ ህብረት ጋር ነገሮችን በማነፃፀር ራሴን ወደማይገባ ድብርት ከተትኩት። አዎ እዚህ ያለሁበት ስፍራ እልም ያለ ደረቅ ምድረበዳ ነው። መንፈስ የሌለበት የደቂቃዎች ፀሎት ፤ የድምፅ ውበት መፈተኛ እና ጩኸት ብቻ የሆነ አምልኮ።.....አስጨነቀኝ።.... የራሴን ባላንስ ላለማጣት እየተንገዳገድኩም ለመቆም ሞከርኩ ግን አቃተኝ። የክርስትና ህይወቴ ከእግዚአብሔር ፤ ከቃሉ ፤ ከፀሎት በራቀ ቁጥር በፊት የተረዳኋቸው መገለጦች የነበረኝ መሻትና ረሀብ ሁሉ ከልቤ ጠፉ። ይበልጥ ደግሞ ከቤተክርስቲያን ውጪ ወጣት ክርስቲያኖች በህይወታቸው የሚያደርጉትን ያልተገባ ሀጥያት በአይኖቼ ማየት ስጀምር ፤ ሳምንቱን ሙሉ በሀጥያት ተመላልሰው በሳምንት አንድ ቀን በልበ ሙሉነት ያለ ወቀሳና ኩነኔ ህብረት ፕሮግራም አለኝ ብለው ሲመጡ ሳይ ከበደኝ። በነርሱ ላይ አልፈርድም ነበር በእርግጥም የሚከታተለን እረኛ አልነበረንም። በትንሽ ከተግባባኋቸው ጋር ስለ እግዚአብሔር ጥቂት ሳወራ ፊታቸው ላይ መሰላቸት ይታየኝ ነበር። አፍ አውጥተው ባያወሩትም በእግዚአብሔር ቤት እያሉ የሉም ነበረ። ለመፀለይ አንገታችንን ስንደፋ ቤቱ በዝምታ ተውጦ ያስጨንቀኝ ነበር። እንደኔ ሁሉም በራሱ ሀሳብ የሚመላለስ እንጂ የሚፀልይ ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ።

ከቤታችን ራቅ ወዳለ ሰዎች ወደማይመጡበት ቦታ ተቀምጬ ትውልዱ ለእግዚአብሔር ፍቅር አለኝ የሚለው ውሸቱን ነው እንድል አደረገኝ። ተቀባይ ከሌለ እግዚአብሔር ክብሩን በማን ይገልጣል። ኑሮአችን ለእግዚአብሔር መንፈስ መስራት የሚመች አለመሆኑን ደጋግሜ አሰብኩ ፤ እንደ ድሮው ግን ውስጤ የነበረው እሳት በርዶ ዝምታና ፤ መተያየት ከውስጤና ከውጪው አለም ጋር ሙግት መግጠም ላይ ብቻ ነበርኩ። ወጣቶች ጊዜያዊ ደስታቸውን አስበልጠው ጌታን ያሉ እየመሰሉ ሊሸውዱት ይሞክራሉ። ግን ያውቃል የሉም..... በመንፈስ የተሞሉ መስለው ለስላሳ ዝማሬዎችን ሲዘምሩ ይታያል ህይወታቸው ግን ውስጡ ባዶ ነው። ለእግዚአብሔር ራሳቸውን አሳልፈው መስጠት የማይወጡት ግብግብ ሆኖባቸዋል። በትልቁ በትንሹ መረበሽ ፤ ብቸኝነት ፣ ፍርሀት ፤ ግራ መጋባት እና ጭንቀት ቤታቸውን አማኝ ነኝ በሚሉ ላይ ሰርተው ሳይ ለሌላ ትውልድ ቀርቶ ይሄ ትውልድ ለራሱ ይሆናል ወይ ብሎ አስጨነቀኝ። አገልጋዮች አገልግሎትን ገበያ አድርገው በገንዘብ ሲተምኑ ፤ ነቢያት ነን ባዮች በአባቶች ተከብሮ የመጣውን የጌታን ስም እየጠሩ አደባባይ ላይ ሲቀልዱ ፤ በአህዛብ ዘንድ እምነታችን የቀልድና የፌዝ ምንጭ ሲሆን የሚከላከል ንፁህ እምነት ያለው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ቁጥር ትንሽ ሲሆን ሳይ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ገባሁ።

በተስፋመቁረጥ የጀመረው ውድቀቴ .....
ይሄን በመጫን ይቀጥሉ
780 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-07 21:06:05 . አልችልበትም ያላንተ መኖር
Singer Zerfe Kebede
Amazing Worship Song
Share Share Share
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
678 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-20 21:04:46 #ተለቀቀ
ቃልኛ መንፈሳዊ መፅሔት
ስምንተኛ እትም
በቃልቲዩብ የተዘጋጀ
9ሜ.ባ PDF ያውርዱት

●18 ጥያቄዎች
ለተወዳጇ ዘማሪት አዜብ ሐይሉ
አማኝ በአጋንንት ሊያዝ ይችላልን?
(በነቢይ መሳይ አለማየሁ)
ትኩረትና ቴክኖሎጂ
(በሳሙኤል ከበደ)
ክርስቲያናዊ የቤት ውስጥ ሰራተኛ አያያዝ ምን መምሰል አለበት
(በቢንያም አዲሱ)
የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት እንዴት ሆነ
(በአቤኔዘር አለማየሁ)
እና ሌሎች . . .

... ለወዳጆቻችሁ ለአማኞች ፣ ለማያምኑ ሼር
ለበፊት እትሞችን | ይሄን ይጫኑ |

@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
740 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-15 20:35:11
ቃልኛ መንፈሳዊ መፅሔታችን 8ተኛ እትም በዚህ ሳምንት ቅዳሜ በነፃ ወደናንተ ይደርሳል።

በዚህ እትም
●18 ጥያቄዎች
ለተወዳጇ ዘማሪት አዜብ ሐይሉ
አማኝ በአጋንንት ሊያዝ ይችላልን?
(በነቢይ መሳይ አለማየሁ)
ትኩረትና ቴክኖሎጂ
(በሳሙኤል ከበደ)
ክርስቲያናዊ የቤት ውስጥ ሰራተኛ አያያዝ ምን መምሰል አለበት
(በቢንያም አዲሱ)
የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት እንዴት ሆነ
(በአቤኔዘር አለማየሁ)
ነፃ ምርጫ
(በፓስተር ቶማስ)

እና ሌሎች መንፈሳዊ ፁህፎች ፤ ወጎች ፤ የተለያዩ ነገሮች ይኖራሉ።
|| ቅዳሜ ይጠብቁን ||
በቃልቲዩብ ቴሌግራም በነፃ ይለቀቃል

@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE

| የበፊት እትሞችን ለማግኘት ይሄን ይጫኑ |
706 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-08 21:33:54
የተለያዩ መንፈሳዊና መፅሐፍቅዱሳዊ ጥያቄዎቾን መልስና ማብራሪያ የያዘውን በነቢይ መሳይ እና በቻናላችን የተዘጋጀውን 124መልሶች ያላነበባችሁ እንድታነቡ እንጋብዛለን።
በተጨማሪም አማኝ ላልሆኑ ወዳጆቻችሁ ሼር አድርጓቸው።
ማውጫ
124 ANSWERS BY Prophet Mesay Alemayehu & KALTUBE

https://t.me/KALTUBE/7474
https://t.me/KALTUBE/7474
https://t.me/KALTUBE/7474
697 views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ