Get Mystery Box with random crypto!

TALIA MEDIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ taliamedia — TALIA MEDIA T
የቴሌግራም ቻናል አርማ taliamedia — TALIA MEDIA
የሰርጥ አድራሻ: @taliamedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 222
የሰርጥ መግለጫ

በ ዚህ ቻናል ላይ ለጉርሻ እማይከብዱ😁 ቀለል ቀለል ያሉ ትኩስ ዜና ፣አስተማሪ ፁሁፎች ይቀርብበታል።
አስተያየትና መረጃ ለመስጠት 👉 @TaliaMediaCobot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 13:16:44
ሶስት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ገለፀ።

የቡርጂ ልዩ ወረዳ በተለያዩ ጊዜያት በገላና ሸጥ እና ከምዕራብ ጉጂ ጋር በሚያዋስኑን አከባቢዎች የአከባቢውን ሠላም የማይፈልጉ ሀይሎች የንፁሐንን ሕይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ ብሏል።

" ምንም እንኳን የፀጥታ ሥጋት ብኖርም መተዳደሪያቸው የሆነውን የእርሻ ሥራ በማካሄድና ጤፍ በማጨድ ላይ የነበሩ ንፁሐን አርሶ አደሮች በገዛ መሬታቸው እና አከባቢያቸው ሲገደሉ ቁጥራቸው በርከት እያለ ያለ ነው " ብሏል።

ትላንትና በተመሳሳይ መልኩ #በዋሌያ ቀበሌ የዕለት ተግባራቸውን ለመከወን የወጡ ሶስት አርሶ አደረሮች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀጥፏል ሲል አሳውቋል።

ልዩ ወረዳው የቡርጂ ማሕበረሰብ እና የሟች ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ሀዘኑን ገልጾ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ አንዳሳዘነውና ቁጭት እንደፈጠረበት ገልጿል።

" ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የእጃቸውን እንዲያገኙ በጥብቅ እየሠራን ነው " ያለው የቡርጂ ልዩ ወረዳ " " የክልል መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገልን እንዳለ ለማረጋገጥ እንወዳለን " ሲል አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@taliamedia
191 viewsامير محمد, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:49:14
ሰበር ዜና
================
የሀምሌ 11 የሸራተን ስብሰባን ለማደናቀፍ የአህባሽ ቡድን ለሱፊያ ኡለሞቻችን እየደወሉ እንገላችኃለን እዳትሳተፉ ፣ ወደ አዲስ አበባ ብትመጡ ዋ በማለት እያስፈራሩ በመዛት ላይ እንደሚገኙ ተሳታፊዎች አሳውቀውናል። ከዚህም ባለፈ እንደለመዱት ሀምሌ 11 መውሊድ አለብን በማለት ጊዜ ለመግዛት አእየተጋጋጡ እንደሆነ ደርሰንበታል። ህዝበ ሙስሊሙ ይህን ሴራ የማክሸፍ ስራ እንዲሰራ ጥሪ እናቀርባለን። በአሁን ሰአት ዑመር ኢድሪስ ቤት መሽገው እያሴሩ ነው።

እንደ አዲስ አበባ መጅሊስ ሸራተንን ሰብረው በጉልበት ለመቆጣጠር ሊሞክሩ ይሆን ?

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
164 viewsامير محمد, edited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:46:14
#የጋራመኖሪያ

እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው!!

ከ14ኛ ዙር የ20/80 እንዲሁም ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ሰራተኞች ስም ዝርዝር!!

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነቱ የተነሳ

በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-

1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ
2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን :_ዳይሬክተር
3ኛ. ሀብታሙ ከበደ :_ሶፍትዌር ባለሙያ
4ኛ. ዬሴፍ ሙላት :_ሶፍትዌር ባለሙያ
5ኛ. ጌታቸው በሪሁን :_ሶፍትዌር ባለሙያ
6ኛ. ቃሲም ከድር :_ሶፍትዌር ባለሙያ
7ኛ. ስጦታው ግዛቸው :_ሶፍትዌሩን ያለማ
8.ኛ. ባየልኝ ረታ ፡_ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ
9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፡_የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ
10ኛ .ኩምሳ ቶላ ፡_ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

በቀጣይም ሂደቱን እየተከታተልን ለህዝባችን ማድረሳችንን የምንቀጥል ይሆናል፡፡

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
291 viewsامير محمد, 19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:27:43
#NewsAlert

አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ። 

ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በፌደራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት፥ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኤልሻዳይ ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው። 

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በእንጅባራ በመሳሰሉ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ ማብራራታቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
351 viewsAmir, edited  09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 22:58:08
#መልካምዜና

የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና የመስመር አጥቂ አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካ ኢንባሲ በሀገር ውስጥ የስራ ፍቃድ ጋር በተያያዘ ገጥሞት የነበረው እክል ተስተካክሎ ከ24-48 ሰአት ውስጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያቀና የተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ሚድያዎች ዘግበውታል።

ነገር ግን በደቡብ አፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተደነገገው የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ገደብ ጋር በተያያዘ አቡበከር ናስር ከሰንዳውስ ክለብ ውጪ ለተጨማሪ 1 አመት በውሰት ለአንዱ የደቡብ አፍሪካ ክለብ ሊጫወት ይችላል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ክለቡ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ ክለቦች ጋር በመነጋገር ላይ ነው።


┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
346 viewsAmir, edited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 22:37:34
#AddisAbaba

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአዲስ አበባ ካቢኔ አባል የሆኑት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ አልታሰሩም።

ከ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ችግር የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የአ/አ አስተዳደር መግለፁ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ " ወ/ሮ ያስሚን ወሃቢረቢ በቁጥጥር ስር ዉለዋል " ተብሎ መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

ነገር ግን ፤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ያስሚን ወሃቢረቢ በቁጥጥር ስር ውለዋል ተከባሉት ግለሰቦች መካከል እንዳልሆኑ #ኢትዮጵያ_ቼክ መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ከራሳቸው ከወ/ሮ ያስሚን እንዲሁም ከከተማ አስተዳደሩ ማረጋገጡን አሳውቋል።

ወ/ሮ ያስሚን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባል እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሲሆኑ የምክር ቤቱ አባል መሆናቸው በግልፅ ሂደት ካልተነሳ በቀር ያለመከሰስ መብት አላቸው።

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
319 viewsAmir, edited  19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 22:35:48
#AAU

ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ደነቀ በተማሪ ቢንያም ኢሳያስ ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ላይም ይህን ብለዋል (ከኢፕድ የተወሰደ) ፦

- ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ 4ኛ አመት ተማሪ እያለ ነው የአካል ጉዳት እንዳለበት የታወቀው ፤ ዩኒቨርሲቲው ላለፉት 8 ወራት ጉዳዩን ይዞ ሲመረምር ቆይቷል።

- ባዋቀረው ኮሚቴ በቀረበለት ምክረ ሀሳብ መሰረት ተማሪ ቢንያም ከጤና ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ትምህርቶችን እንዲማር ተወስኗል።
• በህክምና ፋርማሲ
• በህክምና ላብራቶሪ ሳይንስ
• በህክምና ላቦራቶሪ በመረጠው ዘርፍ እንዲማርና ባችለር ኦፍ ባዮሜዲካል ሳይንስ እንዲሰጠው ተወስኗል።

- ተማሪው የአካል ጉዳት እያለበት ለህክምና ትምህርት ዘርፍ መመደቡና ለደረሰው ችግር ዋንኛ ምክንያት የህክምና ኮሌጁ ተማሪዎችን ራሱ መመልመል ያለመቻሉ ነው።

- የህክምና ኮሌጁ እና የትምህርት ክፍሉ አስቀድሞ ማድረግ የሚገባውን ነገር ማድረግ ባለመቻሉ በተማሪ ቢንያም ላይ ለተከሰተው ችግር #ሀላፊነት እንወስዳለን።

ዛሬ የተወሰነውን ውሳኔ በተመለከተ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስና ቤተሰቦቹን በመጠየቅ ምላሻቸው ምን እንደሆነ እንልክላችኃለን።

ከዚህ ቀደም ተማሪ ቢንያም ያቋረጠውን የሜዲስን ትምህርት ቀጥሎ ሁለት እጅ የማይጠይቁ ስፔሻላይዜሽኖች ላይ መግባት እንደሚችል (ሳይካትሪ፣ ፐብሊክ ሄልዝ ሌሎችም) ገልፆ ነበር።

ከልጅነቱ ጀምሮ " ሜዲስን " የመማር ህልሙን ለማሳካት የለፋው ተማሪ ቢንያም 5ኛ ዓመት ደርሶ በዩኒቨርሲቲው አሰራር ችግር ከሚወደው ትምህርቱ እንዲወጣ መደረጉ ተማሪውን ጨምሮ መላ ቤተሰቡን ያሳዘነ ድርጊት ነው።

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
336 viewsAmir, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 22:16:49
#ማብራሪያ የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦

" ... ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል።

በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡

ከዚህ በመነሳትም የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር #በቁጥጥር_ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

ለተፈጠረው ስህተት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ይጠይቃል። "

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
421 viewsAmir ibnuZeyneb, 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 22:14:16
#ሰበር ዜና፦ በወሎ ኦሮሞና በሸዋ አካባቢ ዳግም ጦርነት ተቀስቅሷል!!
………………
ጦርነቱ የተነሳው ትናንት ሀምሌ 03/2014 በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሲሆን ይህን እድል በመጠቀም በእነ ሀብታሙ አያሌውና ሌሎች ፅንፈኛ የአማራ አክቲቪስቶች የሚዘወረው ቡድን በዛሬው ውሎ በወሎ ኦሮሞወች ላይ በከባድ መሳሪያ ሳይቀር ጦርነት በመክፈት ብዙ አልቋል።

ከስፍራው ምንጮቻችን እንደገለፁት ፅንፈኛው ቡድን ጦርነቱን ሆም ብሎ እብደጀመረውና የሀገር ሽማግሌወች ሳይቀር ለማብረድ ቢሞክሩም ሳይሳካ ቀርቶ ተባብሶ ቀጥሏል።

መንግስት በአስቸኳይ ጉዳዩን ቶሎ ገብቶ እንዲፈታ እናሳስባለን!!

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
341 viewsAmir ibnuZeyneb, edited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:14:02 #ዜና_ስፖርት

የቅጣት ውሳኔ

ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊዎች ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለቦች የሥነ ምግባር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ በተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ውደድሮች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የሥነ ምግባር ሪፖርት በመመርመር የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በዚህ መሰረትም ድሬዳዋ ከተማ ከባህርዳር ጋር በነበረው የ28ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል፡፡

የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች በዕለቱ ባጠፉት ጥፋትና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥፋት ከተላለፈባቸው ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መመሪያ መሰረት 75 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል በሊግ ኩባንያው ዲስፕሊን ኮሚቴ ተወስኖበታል፡፡

በተመሳሳይ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የ30ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ከ68ኛው ደቂቃ ጀምሮ ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልተከተለ ድጋፍ ስለመስጠቱ ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በተጨማሪም ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የጥበቃ ሃይሎች ሊቆጣጠሩት ባልቻለ ሁኔታ የክለቡ ደጋፊዎች ወደ መጫወቻ ሜዳ ጥሰው ስለመግባታቸውና ስለማወካቸው እንዲሁም ለሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት አፈጻጸም እንቅፋት ስለመሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በዚህም የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ ባጠፉት ጥፋትና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥፋት ከተላለፈባቸው ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መመሪያ መሰረት 100 ሺ ብር እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ፋሲል ከነማ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች ያለ ደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲያካሂድ መወሰኑን ከሊግ ኩባንያው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች
366 viewsAmir, edited  16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ