Get Mystery Box with random crypto!

#AAU ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አ | TALIA MEDIA

#AAU

ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ደነቀ በተማሪ ቢንያም ኢሳያስ ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ላይም ይህን ብለዋል (ከኢፕድ የተወሰደ) ፦

- ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ 4ኛ አመት ተማሪ እያለ ነው የአካል ጉዳት እንዳለበት የታወቀው ፤ ዩኒቨርሲቲው ላለፉት 8 ወራት ጉዳዩን ይዞ ሲመረምር ቆይቷል።

- ባዋቀረው ኮሚቴ በቀረበለት ምክረ ሀሳብ መሰረት ተማሪ ቢንያም ከጤና ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ትምህርቶችን እንዲማር ተወስኗል።
• በህክምና ፋርማሲ
• በህክምና ላብራቶሪ ሳይንስ
• በህክምና ላቦራቶሪ በመረጠው ዘርፍ እንዲማርና ባችለር ኦፍ ባዮሜዲካል ሳይንስ እንዲሰጠው ተወስኗል።

- ተማሪው የአካል ጉዳት እያለበት ለህክምና ትምህርት ዘርፍ መመደቡና ለደረሰው ችግር ዋንኛ ምክንያት የህክምና ኮሌጁ ተማሪዎችን ራሱ መመልመል ያለመቻሉ ነው።

- የህክምና ኮሌጁ እና የትምህርት ክፍሉ አስቀድሞ ማድረግ የሚገባውን ነገር ማድረግ ባለመቻሉ በተማሪ ቢንያም ላይ ለተከሰተው ችግር #ሀላፊነት እንወስዳለን።

ዛሬ የተወሰነውን ውሳኔ በተመለከተ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስና ቤተሰቦቹን በመጠየቅ ምላሻቸው ምን እንደሆነ እንልክላችኃለን።

ከዚህ ቀደም ተማሪ ቢንያም ያቋረጠውን የሜዲስን ትምህርት ቀጥሎ ሁለት እጅ የማይጠይቁ ስፔሻላይዜሽኖች ላይ መግባት እንደሚችል (ሳይካትሪ፣ ፐብሊክ ሄልዝ ሌሎችም) ገልፆ ነበር።

ከልጅነቱ ጀምሮ " ሜዲስን " የመማር ህልሙን ለማሳካት የለፋው ተማሪ ቢንያም 5ኛ ዓመት ደርሶ በዩኒቨርሲቲው አሰራር ችግር ከሚወደው ትምህርቱ እንዲወጣ መደረጉ ተማሪውን ጨምሮ መላ ቤተሰቡን ያሳዘነ ድርጊት ነው።

┄┄┄┉» ታሊያ_ሚድያ ┉┄┄┄┄
Telegram || @Taliamedia
እውነትን ለእውነተኞች