Get Mystery Box with random crypto!

Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ

የቴሌግራም ቻናል አርማ suleimanabdellanews14 — Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ S
የቴሌግራም ቻናል አርማ suleimanabdellanews14 — Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ
የሰርጥ አድራሻ: @suleimanabdellanews14
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.64K
የሰርጥ መግለጫ

ጥቆማ‼️
በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ፣ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይባርክ
ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ
በውስጥ መስመር ከፈለጉን 👉 @Sulamen14

Ratings & Reviews

1.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

3


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 21:55:42
በጦርነት መሀል ብዙ ክስተት አለ። መሸነፍ መዋጋት መሞት መሰደድ መራብ መጠማት መቆመጥ አለበት። ይህ የጦርነቱ ስርአተ ስሪት ነው። ዋናው ነገር ግን እንደ አለት የጠነከረ አቋምና ስነልቦና መገንባት ነው። መንግስታችንም ይሁን ወታደራዊ መሪዎቻችን ከአምናው ድክመታችንና ከጥንካሪያችን ወስደው ራሳቸውን የበለጠ ማጠናከር አለባቸው። ህዝባችን ከበፊቱ ስህተት ተምሮ የተሻለ ስነልቦና መገንባት አለበት። ከዛውጭ ትኩረታችን መሉ በመሉ ህወሓትን ታርጌት ማድረግ አለበት። ሳይበራችንም ይሁን
የህዝባችን ወቅታዊ ትኩረት በሙሉ ወደ ህወሓት ማተኮር አለበት።

ልላው ቆቦም ይሁን ሌሎች ከተሞቻችን በጥላት እጅ መግባት የለባቸውም። ቆቦስ ሆነ ከዚህ ሌላ አንዲት ከተማ ላይ ከበበ ሲደረግ ሁሉም ፊት ላይ ሄዶ የመሀሉን ከተማ መቆጣጠር አለብን። መንግስትም ይሁን ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ የገጠመው ተስፋ የቆየረጠ ቡድን ጋር ነው። እኛም በዛው ልክ መጠንከር አለብን። ተስፋ አስቆራጭ እና መሰል የብሽሽቅ ሀሰቦችን በሰራዊቱ በህዝባችን ላይ አጉል ነገር የሚጭሩ ሀሳቦችን ከመፃፍ እንቆጠብ። ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ንቅንቅ አንልም።

በቴሌግራም ይከተሉኝ
https://t.me/SuleimanAbdellaNews14

ሱሌማን አብደላ
3.2K viewsedited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:56:31
ሀገሬ ስታሸንፍ ብቻ ሳይሆን ስትሸነፍም ከጎኗ እቆማለሁ !
በድል ወቅት ሳይሆን በፈተና ወቅት ከመንግስቴ ጎን የበለጠ እሰለፋለሁ !

ደግሞም አልጠራጠርም ኢትዮጵያየ ታሸንፋለች !!!
አሸናፊነት እንጅ ሌላ ነገር የሚመጥናት ሀገር አይደለችምና !!

አንድ ሰው ስለሀገሩና ክብሩ ቢሰዋ ክብሩ ነው ቢኖርም ክብሩ ነው !
ባ*ንዳ ግን ሁሌም ወራዳ ነው ! ቢሞትም ተዋርዶ ነው ! ቢኖርም ተዋርዶ ነው ! የሀገሬ ባንዳዎችም ከዚህ የዘለለ ገጥሟቸው አያውቁም !

ሁልቀን ድል ላይገኝ ይችላል ግና የመጨረሻው ድል የኛ ይሆናል ! ደግሞም እያሸነፍን ነው !
ጠላት በሬሳየ ልረማመድና ወደ ፊት ልገስግስ ብሎ ቢመጣም ጀግኖች ልጆቻችን ከሬሳው ውስጥ ሰጥሞ እንዲቀር እያደረጉት ነው !

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች !!!!

በቴሌግራም ይከተሉኝ
https://t.me/SuleimanAbdellaNews14

ሱሌማን አብደላ
3.0K viewsedited  16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:28:36
ይህ የምትመለከቱት ቦታ ፎኪሳ ይባላል የሚገኘው የዞብልን ተራራ ወደ አፋር ስትወርዱ የሚገኝ ቦታ ነው ዞብልን ተቆጣጥረዋል የምትሉ እነዚህን የምድር ድሮኖች በአየር ላይ አልፈዋቸው ነው? ይህ ፎቶ የዛሬ ሲሆን ከክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር ነው። ኮማንዶ ያለ የሌላ አቅሙን አሟጦ እየታገለ ነው።
ፋኖ እና ልዩ ሀይሉም ቆቦ ዙሪያ እስከዚች ሰዓት ድረስ እየተዋደቀ ነው።
ከእኛ የሚጠበቀው ሰራዊቱን መደገፍ ብቻ ነው። አመራሮች ይሄን የማስተባበር ሥራ መስራት አለባችሁ።

ሱሌማን አብደላ
2.9K viewsedited  13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:40:11
ኢትዮዽያ ትቅደም። የጠላሽና የደፈረሽ ይውደም።

የዛሬ ሀሽታጋችን ይሄ ነው።
#Ethiopiafirst

ሱሌማን አብደላ
3.0K viewsedited  05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:58:42
ይሰድቡታል። ስሙን ያለስም ሰተው ይዘምቱበታል። ያንቋሽሹታል። የምዕራባውያን ሚዲያዎች ይዘምቱበታል። ከካይሮ እስከ ሱዳን፣ መቀሌ ድረስ ያሴሩበታል። እናፈርሰዋለን እንደመስሰዋለን ይሉታል። በብሔር የታጠሩ ሸማቂዎች የፓርቲ ወታደር እያሉ ሊበሉት ይፎክሩበታል። ኢትዮጵያዊ ሆኖ ትክክለኛ ሞትን በትክክለኛው ቀን የሚሞተው ግን ይህ ወታደር። ለዚህ ወታደር ያላቸሁን እንዳሰስቱ። ሁሉን የኢትዮጵያን ንብረት መከላከያ ስራዊት ቢበላው ይገባዋል እንጅ አያንስበትም። ድልና ድምቀት ሰላምና ብርታት ከናተጋር ይሁን።

ሱሌማን አብደላ
3.1K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 22:29:52
ይህ ወራሪ ቡድን ገላ አልቦን ተቆጣጥሮ ወደ በረከት እየገባ ነው። ይህ ወራሪ ቡድን ከህወሓት የሳምሪ ቡድን ጋር በመጣመር ወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ ግድያ እየፈፀመ ነው። ገላ አልቦ ለወልቃይት ቅርብ ሲሆን በረኸትን ለመያዝ ውጊያ እያደረገ ነው። ጦሩ በረኸት ያለውን የኢትዮጵያ ጦር ማዛዥ ካፕ ይዣለሁ የሚል መግለጫ ቢሰጥም ከወገን ሀይል አጣርቸ ውሸት መሆኑን አረጋግጫለሁ።

ወራሪ ድል ቀንቶት በረኸትን ከተቆጣጠረ ሁመራን ያዘ ማለት ነው። መንግስት የሚሰጠውን መግለጫ እየጠበቅን ሲሆን የሱዳን ጦር እያደረገ ያለው ዘመቻ በአየር ሀይል የታገዘ ነው። በዚህ ሰአት በረኸትን ለመያዝ የአጭር እርቀት ተተኳሽ ሮኬቶችን ወደ ወገን ሀይል እየተኮሰ ነው።
የፌደራሉን መንግስት መግለጫ ጠብቁ። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዝግጁ ሆኖ መቀመጥ አለበት።

ሱሌማን አብደላ
2.3K viewsedited  19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 22:02:19
ቡረሀን አልፋሽጋ ነው። ከመጠን በላይ እየደነፋ ነው። ጦራችን አሳማኝ የሆነ እርምጃ ይወስዳል ብሏል። በርግጥም ጀነራሉ ይሄንን ባለበት ቅፅበት ጦሩ የንፁህ ኢትዮጵያዊያን ቤት በከባድ መሳሪያ እየደበደበ አምሽቷል። ተዋጊ ጀቶቹ ዝቅ ብለው አልፋሽጋ መሬት ላይ ሲበሩ አምሽተዋል።
.
ይህንን ጦርነት በቀላሉ ማየት የለብንም። 30"ሺ በግብፅና በሱዳን የሰጠነው የህወሓት ሳምሪ ቡድን ከፊት ሆኖ በግብፅ መሳሪያ እየተዋጋን ነው። አላማው የወልቃይትን በር አስከፍቶ ከህወሓት ጋር መገናኘት ነው። በተቻለ መጠን ጥንቃቄም ይሁን የመልስ ምት መስጠት አለብን። አሁን መንግስት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት እየጣረ ነው። የማይሳካ ከሆነ ግን ሁላችን እናልቃታለን እንጅ አገራችንን ሲያፈርሱት ማየት የለብንም። የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስት የሚሰጠውን መግለጫ በተጠንቀቅ ሆነህ ጠብቅ።
ሱሌማን አብደላ
የሱዳን የጦር ታጣቂ በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ማምሻውን ወደ
ወደ አቦጢር
ወደ ግላል ውኃ
ወደ ኮረደምና
ወደ አብራጅራ ከባድ መሳሪያ መተኮስ ጀምሯል።

ሱሌማን አብደላ
2.2K viewsedited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 23:05:08
ደቂቃዎች እየቆጠሩ የሰአቶችን መሙላት እየጠበቁ ነው። ከነዚህ ሰአትና ደቂቃዎች አልፎም በትንሽ ቀኖዎች ውስጥ ባይደን ያኖሩትን ፊርማ ካልሰረዙት የነገሮች መቀያየር ለኢትዮጵያ ስጋት ነው።
.
ጆ ''ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሊበሩ'' ሽር ጉድ ዕያሉ ነው። ኢትዮጵያ ደሞ ከታገደችበት የአጎዋ ንግድ እንድትመልስ እየወተወተች ነው። በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከአረብ ሊግ ጋር ውዝግብ የገባችው ኢትዮጵያ « ጆ » ፍቃዱን ሳይሰጡ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ከመጡ ነገሮች ሊቀያየሩ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች መነሳት የለበትም 160 ሚሊየን አረቦችን የውሃ ደህንነት አደጋ ላይ ጥላለች የሚል የውስጥ ለውስጥ ትግል የገጠማት ኢትዮጵያ ጆ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሳይበሩ ቀድመው ኢትዮጵያን የአጎዋ ንግድ ተጠቃሚ እንደትሆን ከፈቀዱ እድለኛዋ ኢትዮጵያ እድለኛነቷን ታረጋግጣለች። ወጣቱ መሪ ግን ፍቃዳቸውን ሳያኖሩ ከሄዱ የአጎዋ ጉዳይ የናይል ወንዝ አጀንዳ ማሳለጫ መሆኑ አይቀርም።
.
በነገራችን ለአጎዋ ንግድ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የመጉዳት አቅም የለውም ግን አይጎዳንም። ኢትዮጵያ በውጭ ባንኮች የተያዘባት ዶላር ለማስለቀቅ ግን እጅግ ወሳኝ የሆነ እድል ነው። አጎዋ የታገድነውን ዶላር በማስለቀቁ ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዋጋ ንረት የማረጋጋት አቅም አለው። እንጅ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ይልቅ ከአረቦች ጋር ያላትን የንግድ ልውውጥ ብታሳድግ ከአጎዋ በላይ እጥፍ እጥፍ የውጭ ንግዷን ማጎልበት ትችላለች።

ሱሌማን አብደላ
2.2K views20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 23:28:13
ይህ የጃዋር ምክር ብቸኛ መዳኛችን ! ሁሉም ሰው ሁሉ አክቲቪስትና ፖለቲከኛ ባይ ባይ ሁሉ ይህንን ሊሰማ ይገባዋል !
2.3K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 23:04:30
#ወለጋ
#መንግስት የጠረጠራቸውን የወለጋ ባለስልጣናት በቁጥጥር አውሎ ምርመራ እያደረገ ነው።

አካባቢው ላይ ሰፍሮ የቆየው የፌዴራል ፖሊስና የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ለቆ እንዲወጣ አድርጓል። በምትኩ ባለ ቀይ ቦኔቱ ልዩ ኮማንዶ ወደ ቦታው አቅንቶ ኦፕሬሽን መስራት ጀምሯል። አዳሩን ውጊያ ላይ ያደረገው ልዩ ኮማንዶ ወደ ካምፕ ተመልሶ ተጨማሪ ሀይል አሁን ገብቶለታል። ውጊያ እስከዚህ ሰአት ድረስ እንደቀጠለ ነው።
.
መንግስት ትክክለኛ ኦፕሬሽን አድርጎ የሌላ ብሔር ተወላጆችን ታርጌት ያደረገ ጥቃትን ሊመክት የሚችል ቦታው ላይ የሚቆይ ወታደር ማቋቋም አለበት። ሌላው 4 አመት ሙሉ ያንን አካባቢ በተለያዩ የስራ ድርሻ ሲያስታድሩ የነበሩ አመራሮች ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለባቸው።
እየተደረጉ ያሉ ኦፕሬሽኖችን መንግስት ለህዝብ ማሳወቅና አካባቢ ላይ ትክክለኛ መንግታዊ መዋቅር ተካቶ ቀየኑ ያለ ወኪል የሚገደሉ ህዝቦች ተፈጥሯዊ የመኖር መብታቸውን ሊያስከብርላቸው ይገባል።

ሱሌማን
2.1K viewsedited  20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ