Get Mystery Box with random crypto!

አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ snetsehuf — አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚
የቴሌግራም ቻናል አርማ snetsehuf — አጫጭር ግጥሞችና መጣጥፎች 📚
የሰርጥ አድራሻ: @snetsehuf
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 351
የሰርጥ መግለጫ

✔️📚ማንበብ ያሻግራል ❗️❗️❗️
በዚህ ቻናል እናንተን የሚመጥኑ የተለያዩ ግጥሞችን ፣ አጫጭር ና መሳጭ ታሪኮችን ታገኛላችሁ። እናንብብ ፤ በማንበባችን እናተርፋለን እንጂ ፤ ከቶ አንከስርም። @snetsehuf

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 21:29:23 #ስለምወድሽ_አላገባሽም

የምልሽ ነገር ፥ ቢገባሽም ባይገባሽም
ስለምወድሽ አላገባሽም።

የምን ችቦ አይሞላም? ፥ የምን አሸወይና?
በሰው አፍ መፈተል ፥ በሰው አፍ ሽመና
የምን ሽማግሌ? ፥ የምን ጥሎሽ መጣል?
የምወደው ልብሽ ፥ ስንት ብር ያወጣል?

ስንት ብር? ፥ ስንት ወርቅ?
ስንት ከብት? ፥ ስንት ጨርቅ?
ስንት ምን ብሰጥሽ ፥ አንቺን ይመዝናል?
አንቺን ይወክላል ፥ ያንቺን ስም ያክላል?
ድካም ነው ይቅርብን! ፥ ጉዳጉድ ማብዛቱ
የሳቅሽ አፀድ ነው ፥ መኖሬ ግዛቱ።

ልክ እንደዚህ...
ክራር በጣቶቼ ፥ ባልችልም መደርደር
አንቺን እየነካው
ሙዚቃ ባይሆንም
የሰማው መሰለኝ ፥ ጥቂት ዜማ ነገር
ቃላትን በሃሳብ
ተርኬ መንዝሬ ፥ ሰውን ባላሰጥም
ከአጠገቤ ሆነሽ
የሰማው መሰለኝ ፥ አንድ ትንሽ ግጥም

በነፍስ የተፃፈ ፥ በነፍስ የሚነበብ
በነፍስ የሚገለጥ ፥ ደግሞም የሚከተብ
በነፍስ የተሳለ ፥ በነፍስ የተኳለ
ልክ እንደዚ ያለ

አንቺዬ...
እድሜ ላንቺ እድሜ
ቅዳሴ አስካድሺኝ ፥ ኪዳን አስረሳሺኝ
"ሰው ቀን የለውም! ፥ ቅጽነት ነው!" እያልሺኝ
እድሜ ላንቺ እድሜ...
ያነበብኩት ገድል
ያ የእልፍ ድርሳን ፥ የቃረንኩት መጣፍ
ብነካሽ ሄድኩበት ፥ እንደመሬት ምንጣፍ

አቤት! አቤት! አቤት!
ይህንን ቢሰሙ ፥ የኔታ ምን ይሉ?
ያኖርኩትን ኪዳን ፥ ድንግልና አንግሼ
"ታቦቴ ነሽ" አልኩኝ ፥ መቅደሴን አፍርሼ
እንኳን ከአንድ ካህን ፥ ከአንድ አማኝ
የማይሆን ድርጊት ፥ እየፈፀምኩ እየተኮነንኩኝ
ያን ሁሉ እምነቴን ፥ ምን ስትዪኝ ካድኩኝ?

እንተዋወቅ!
ገዳሙን ልዘንጋው ፥ ባንቺ እንድመነኩስ
ከአዲስ ቤቴ ገቢ
ከመፍራቴ ብዛት
ውሃ ልጣድልሽ ፥ ቡታጋዝ ሳለኩስ
ልፈር በውርደቴ! ፥ ዳግም ልንተፋተፍ
የማረገው ይጥፋኝ ፥ የተላጠ ልክተፍ
"ሳቂ ከት ብልሽ!" ፥ አከራዬ ይስሙ!
አገኘ መባል ነው ፥ ሰው የመሆን ስሙ

እስቲ እንተዋወቅ!
በርዶናል እያልን ፥ አውቀን ተጠጋግተን
ልባችን ይምታብን ፥ የምንለው አጥተን
ዝምታ ነግሶብን ፥ እየተነፈስን
እቃ ጠፋን እንበል ፥ እጅ እየዳሰስን
ምነው ባልመጣውኝ! ፥ የሚያስብል ፍርሃትሽ
"ምነው ነይ ባላልኳት?" ፥ ከአፌ ሊያመልጥልሽ?
ትንሽ እየቀረኝ ፥ ትንሽ እየቀረሽ
ጆሮ ጌጥሽ ጋር ሆንኩ ፥ ማህተቤ ጋር ደረስሽ

ውዴ
ይህ ሁሉ ስብከቴ ፥ ቢገባሽም ባይገባሽም
ስለምወድሽ አላገባሽም።

የአገባሁሽ እንደው...
ባለቤት በሚል ስም ፥ አጥሬው አጥሬሽ
ከአንድ እቃ እኩል ፥ ቆጥረሽኝ ቆጠሬሽ
እንዳንረሳሳ...
እሽ በይ ዓለሜ! ፥ መጋባት እንርሳ።

ባታገቢኝ ይቅር
ባላገባሽ ይቅር ፥ ቀኔ እንዳይለያይ
ሰው ከእጁ ያለን ሰው ፥ ከመዳብ ነው የሚያይ!
ቤቴ ካገባሁሽ...
ስለምድሽ ስለምጂኝ ፥ ሃሳቤ ግድ የለው
ያው ሰው አይደለው!
መልመድ ያረክሰናል ፥ ጠዐምን ይሸኛል
"አለች" እንደማለት ፥ ንቀት የት ይገኛል!?

ልጅነቴ ይኑር ፥ እደግ ፍርሃቴ
በምን ልሙላው ያልኩት ፥ ደግሞ ይጥበብ ቤቴ
እንዳዲስ ፃፊኝ ፥ እንዳዲስ እንቀልም
ፍቅረኛ እንደሆንን ፥ ማርጀት ነው የኔ ህልም
የምን ችቦ አይሞላም? ፥ የምን ጥሎሽ መጣል?
የምወደው ልብሽ ፥ ስንት ብር ያወጣል?
ጉዳጉድ ነው ጉዱ
ባይጨፈር ይቅር ፥ የቤተ-ዘመዱ
እድሜ ላንቺ እድሜ ፥ ህልሜን አስቀየርሺኝ!
"ሰው ዘመን የለውም! ቅጽበት ነው!" እያልሺኝ
አሁን ያልኩሽ ሁሉ ፥ ቢገባሽም ባይገባሽም
ስለምወድሽ አላገባሽም።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ኤልያስ ሽታኹን
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
@snetsehuf
65 viewsፍቅር-ኤል, 18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:21:47 #የአራት_ኪሎ
#ኪሎ

በአራት ኪሎ አጸድ
ታሪክና ሥልጣን ፥ በዘመን ሲቀለም
መታዘብ አይቀርም
ግራ የገባውን ፥ የጦቢያን ዓለም
በልጅነት አመት ፥ በምስኪኗ ነፍሴ
በጀንበር ስንጓዝ ፥ ለጥር ሥላሴ
ድንገት!
ከመንገዱ በላይ...
አታልፉም እያለ ፥ ፖሊሱ ሲገታን
ሓሳብ ተሸክመን ፥ ስንርቀው ጌታን
ተከልክለን መሄድ ፥ መራመድ ካደምን
ጥያቄ ነበረን ፥ እኮ ለምን ?
መልስ
የሀገሪቱ መሪ ፥ በመንገድ ስላሉ አትነቃነቁ
እሳቸው እስኪያልፉ ፥ ቆማችሁ ጠብቁ!

ጀመርና ምርምር
ልጅ እንደው ፥ ጅል አይምር
ምርምር ፩
ያንን ሁሉ አማኝ
አታልፉም የሚሉን ፥ አታልፍም የሚሏቸው
ጸሎቱ ምሕሏው
መሪን አውርድልን ፥ መሆኑ ገብቷቸው ?

ምርምር ፪
የምእመን ልመና
ደግ ንጉሥ አምጣ ፥ በጎ መሪ እንኳን ላክ ?
ወትሮስ ምን ሊጠየቅ
ቤተ-መንግሥት ጎን ፥ የተገኘን አምላክ።

ምርምር ፫
የፖለቲካ ጽንስ ፥ በጊዜ ሲታቀፍ
በህዝቡ መቆም ነው
የንጉሥ አካሄድ ፥ የማይደናቀፍ
ጠቢብ ገዢ ማለት ፥ ቅኔው ሲተረተር
እስከሚያልፉ ድረስ
ተራማጅን ሁሉ ፥ በአለበት መገተር።

በአራት ኪሎ አጸድ
ታሪክና ሥልጣን ፥ በዘመን ሲቀለም
መታዘብ አይቀርም
ግራ የገባውን ፥ የሀገሬን ቀለም
ከመንግሥት ፓርላማ
መካከል የቆመ ፥ የሥላሴ ዋርካ
ጠመንጃ አጅቦት ፥ ከቶ ማይነካ
ከካህኑ ይልቅ
ጦረኛ የበዛው ፥ የደብሩ ኪዳን
የአማኙ ጸሎት
ከሲኦል አይደለም ፥ ከሰደፍ ነው መዳን።
በፓርላማው ጫፍ ላይ ፥ ከበላይ ከአናቱ
ሰቅለው ያስቀመጡት ፥ አይሰራም ሰዓቱ።
እንደ መሥሪያ ቤቱ ።

በመሥሪያ ቤት ውስጥ
እጅ እየተነሳ ፥ እንባ እየወደቀ
ከቤተ-መቅደሱ
ወርሰው ነው መሰለኝ
ያገኙትን ሁሉ ፥ የሚሉት ጸደቀ
ቅኔ ማህሌቱ
ከቤተ-ፓርላማው ፥ ስለተሳከረ
የአምናውን አርሞት
ባለሱፍ በሙሉ
አይኑን እንደገለጠ ፥ መተኛት ጀመረ
ተሻሻለ...
በረቂቋ ሀገር
በፖርላማው ጓዳ ፥ ካገኘን አማካይ
አባሉ አይደለም
ድምጽ ቆጣሪው ነው ፥ የህዝቡ ተወካይ።

መቁጠር ነው...
መቁጠር ነው...
መቁጠር ነው...
ያጸደቀን መዳፍ ፥ የወሰነን ወንበር
ስንት እጅ ነው? ፥ በእጅ ወድቆ የሚሰባበር
በአራት ኪሎ አጸድ
ቅድስት ሥላሴን ፥ የሻተ መሳለም
ማየቱ አይቀርም
ግራ የገባውን ፥ የጦቢያን ዓለም
በሥላሴ አጸድ
እማማ ጦቢያ
ሰብስባ ስትቀብር ፥ በታንቡር በዕንባ
ቀብር ይፋለሳል
ከመቅደሱ አጠገብ ፥ ከፓርላማው ጀርባ
ሰው ስሙን ቀይሮ ፥ አፈር ተጠልሎ
በአራት ኪሎ ሰማይ
ማየትህ አይቀርም
የጦቢያም ዋርካ
የጦቢያም እሾህ ፥ በአንድ አፈር ተጥሎ።

የዓለም ፈጣሪ
በአንድ እያደሩ ፥ ከሀገር ከመሪ
የተረሳ ወገን
በቢጫ አረንጓዴ ፥ አጥር የታጠረ
የህዝብ ተወካይ
ከፊቱ አቁሞ ፥ ሳይገኝ የቀረ
ከአርበኛ ህንጻ ሥር
ማንነቱን ያጣ ፥ ቀልቡ የቀለለው
አራት ኪሎ ራሱ
ኪሎው ፥ ምን ያህል ነው?

ቅኔ ነው!
ምስጢር ነው! ፥ ለንጉሥ ፍርሐት
ረቂቅ ግንዝ ነው
መፈታት የሚሻ ፥ የዘመን ፍትሐት
በፍትሐት እውነት
የወታደሩን ደንብ ፥ ቃሉን ተቀብዬ
ይኸው እቆማለሁ
የዘመኔ መሪ ፥ እስኪያልፉ ብዬ
ተራማጅ አራማጅ ፥ በአንድ ላይ ሲያስቆም
ትርጉሙ ብዙ ነው!
መሪያችን እስኪያልፉ ፥ ህዝብ ሆኖ መቆም
ባለጊዜ እስኪሄድ
አንዱ በሌላው ላይ ፥ ጣት እየጠቆመ
ዘመን እንደመሪው ፥ እስኪያልፍ እየቆመ
የሐበሻ ምሱ...
ቀጥ ብሎ ከርሞ ፥ ቁም በተባለበት
ንጉሥ አልፎም እንኳን
ሂድ ቢባል አይሄድም ፥ መገተር ለምዶበት።
ቁም በል በቆምክበት።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ኤልያስ ሽታኹን
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••
62 viewsፍቅር-ኤል, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:36:48 "በኔ መንገድ ካልሔድክ
መንገድህ ገደል ነው" ፥ ማለት የሚከጅል
"እንደኔ ካላሰብክ
ማሰብ አትችልም" ፥ ሊል የሚዳዳው ጅል
በህይወት መንገድ ላይ...
እንደራሴ ስጓዝ ፥ ነፍሴ ምትሞግተው
ስንት ገደል አለ
"ድልድይህ ነኝ" የሚል ፥ መሻገር ሲያቅተው ።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
በላይ በቀለ ወያ
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
@snetsehuf
142 viewsፍቅር-ኤል, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:35:08 የቀጠለ


ምስኪኒቷ እናቴ!
በሞላ ጎዳና
ባልጠበበ ድንበር ፥ በዘር ገመድ ታግዳ
ነጻ ነኝ ትላለች
መንጋነት ያሰረው ፥ ባሪያ ትውልድ ወልዳ፡፡
የጀግንነት እብሪት
ልባችንን ደፍኖት ፥ ማሰብ እየከዳን
እንዴት ነው ነጻነት
እንዳበደ ፈረስ ፥ ስሜት እየነዳን፡፡
ገድሎ የመንገስ ጥማት
ጩኀት ላገነነ ፥ አመጽ ላጀገነው
ለዚህ ምስኪን ትውልድ
በጅምላ እየነዱት
በመንጋ እያሰበ ፥ ነጻነት እንዴት ነው?
ነጻነት ምርጫ ነው!
አምሮ ቢደላደል
ጥፋት ያመነነው ፥ የመንጋዎች መንገድ
እንቅፋቱን ወዶ
ለኖሩለት እውነት ፥ ለብቻ መራመድ!
ነጻነት ማመን ነው
ቀን ወዶ ቢያጀግን ፥ ቀን ጠልቶ ቢከዳም
ቢቆሽሹም ቢደምቁም
እራስን መቀበል
ራስን መምሰል ነው ፥ የነጻነት ገዳም!
ነጻነት ማሰብ ነው
በአንድነት መለምለም
የኔነትን አረም ፥ ከህሊና ማጥፋት
ዘር ሆኖ ከማነስ
ሀገር ሆኖ ማበብ ፥ ዓለም ሆኖ መስፋት።

ንገሯት ለሀገሬ ...
በጀግኖቿ ትግል
ድንበር ባታስደፍር ፥ ከእጀ ገዥ ብትወጣ
ነጻ ነኝ እንዳትል
በገዛ ልጆቿ ፥ በእጅ አዙር ተሸጣ ፡፡
ስሩን ካልሸመነው
በመዋሃድ ጥለት ፥ በማስተዋል ሸማ
ታሪክ አናደምቅም
በጭብጨባ ድግስ ፥ በሆይ ሆይታ ዜማ፡፡
ምን ብናቀነቅን
በየሰልፉ ሜዳ ፥ ወኔ ብንደግስም
በፈረሰ አይምሮ
በደቀቀ አንድነት ፥ ሀገር አናድስም፡፡
በጭፍን ከመሮጥ
አስቦ ማዝገም ነው ፥ የመራመድ ውሉ
ሁሉም እንቅፋቶች
እስኪጥሉን ድረስ ፥ ምርኩዝ ይመስላሉ፡፡
በድፍን ግልብ እሚያጋድል
ህዝብ የመሆን ፥ መንጋ አይንዳን
በማሰብ ስር እንፈወስ ፥ በሰውነት ፀበል እንዳን፡፡
ከእግዜር ልንወዳጅ
ለምህረቱ ጥላ ፥ እምባ ብንደግስም
ልብን ሳይመልሱ
ለንስሃ መሮጥ ፥ ከጽድቅ አያደርስም፡፡
ውብ ነገን እናውርስ
ትላንትን አክመን ፥ በይቅርታ ፀበል
ትውልድ ይጨርሳል
ያረገዝነው እምባ ፥ የቋጠርነው በቀል
ከመስጠት አንጉደል
ከቀማኞች ገደል ፥ ተረግጠን ብንጣል
ካሸከሙን በቀል
ምናወርሰው ፍቅር ፥ ሀገር ይለውጣል፡፡

ከዕድሏ ጣሪያ ላይ
ዘር የቀዳደው ፥ ሽንቁሯ ቢበዛም
ያ ከንቱ ፎካሪ
ባፈጀ ቀረርቶ ፥ ሺህ ጉራ ቢነዛም
ሚሊዮን ዘር ቢሸጥ ፥ አንድ ሀገር አይገዛም፡፡
ኢትዮጵያዊነት ነው
የትርታችን ልክ ፥ የነፍሳችን ግጥም
መልስ ቤት በራቀው
በከረመ ፀሎት ፥ ሰርክ ብታንጋጥም
አጎንብሳ ድሃ
ባፀናችው ጉልበት ፥ ብትረጋገጥም
ነፍሷን አደህይታ
ባሻረችው ቁስል ፥ ብትገሸለጥም
ሀገር ሆና ገዝፋ
በየ ጎጣጎጡ ፥ አትርመጠመጥም፡፡
የዘመን እውነት ነን
ከደግነት ሰማይ ፥ በጥበብ የኖርን
ትዕግስትም ልክ አለው
ፈርተን እንዳይመስለው ፥ ስላቀረቀርን፡፡
ማተብ አስሮን እንጂ
ተጣልተን እንዳንቀር ፥ በክፍፍል ገደል
ከሀገር ክብር በልጦ ፥ ሞት ብርቃችን አይደል፡፡
ንገሩት ለዛ ሰው
ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ
ኃይል እንደ ተራራ ፥ ገዝፎ ቢከመርም
ክንዱን አፈርጥሞ
እልፍ የሰገደለት ፥ ጀግና ቢሰድርም
ዓለም የሞተበት
የጠላት ማርከሻ ፥ ጦር ቢደረድርም
በአንድ ዓይናችን ሰላም
በኢትዮጵያችን ክብር፥ አንደራደርም !!!

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ሕሊና ደሳለኝ
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
፳፻፲፪ ዓ.ም
131 viewsፍቅር-ኤል, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:34:30 #የማጀት_ሥር_ወንጌል

ሙያተኛ ሀገሬ
ከማጥገብ ጎደለ
በረከት እራቀው ፥ የገበታሽ ለዛ
ተሻምቶ ለመጉረስ
ከበላነው ይልቅ ፥ የደፋነው በዛ፡፡
ሙያሽ ባያስደፍር ፥ አጀብ ቢሰኙበት
ማዕዱ ቢሙላላ ፥ ዓይነቱ ቢያምርበት
አበዛዙ አይደለም
አበላሉ ላይ ነው ፥ የገበታሽ ውበት፡፡
እየተማመንን!
የፉክክር ቅሚያ ፥ በርሃብ እየናጥን
ከደፋነው ጠግቦ ፥ ውሻችን በለጠን፡፡
ከምርት አላነስን
ጎተራችን ሙሉ
ጀግና አራሽ ፥ መች አጥተን?
ማሰብ የጎደለው
አያያዛችን ነው ፥ ገደል የከተተን፡፡
ይልቅ ግዴለሽም!
ከምግባር ምጣድ ላይ
ሳንበስል አንጋግተሸ ፥ ከማዕድ አትምሪን
ገበታሽ እንዲያምር
ከእግዜር የሚያስታርቅ ፥ ፍቅር አስተምሪን።

ገበታ ዕድሜ ነው ፥ ባለ ማሰብ መክነን
ሳንፀነስ ጃጀን ፥ ሳንጣድ አረርን
ከዘመን ገበታ
ከፊደል አቅድመን ፥ ዘር እየቆጠርን
ገበታ ሀቅ ነው
በክፋት ሊጥ ጋግረው ፥ ያሻገቱት እውነት
በሆዳም እስክስታ
ረግጠው ያፈኑት ፥ የምስኪናም ጩኸት
እስከ ልጠይቅሽ...
በጥም ደዌ ደቆ
የረሃብ ጠኔ ደፍቶት ፥ እልፍ ትውልድ ያልፋል
ቢራ ለመጥመቂያ
ሚበተን ገብስ ግን ፥ ከሀገር መች ይጠፋል፡፡
ከሆድ በማይሻገር
የማጀት ቤት ዕውቀት ፥ አጥብበሽ አትለኪን
እስቲ መኖር ይግባን
ከማስተዋል መቅደስ ፥ ሰው መሆን ስበኪን።

ዘመን ካልገበረው
ከችጋር ተራራ ፥ ከሲኦል ዳር ኑሮ
እንዴት ነው መሻገር
ከመርፌ ቀዳዳ ፥ በጠበበ አይምሮ።
ከምስኪን ዘመን ላይ
የማይኖሩበትን ፥ ዕድሜ መበዳደር
ለአንዲት ማምሻ ደስታ
በአያት እስትንፋስ ላይ ፥ ቁማር መደራደር
ያሳፍራል አይደል?
እያደጉ ማነስ ፥ እያነሱ መዝቀጥ
አጎንብሶ ያፀናን
የድሃ እናት ጉልበት ፥ በጭካኔ መርገጥ
ያሳምማል አይደል?
መንገስ ከሚያባላስ
መጥገብ ከሚያቃቅር ፥ ማግኘት ከሚያጎለን
ማጣት ውሎ ይግባ
ባርነት ይሰንብት ፥ ድህነት ይግደለን፡፡
ከረፈደ ፀፀት
ደረት እየደቁ ፥ ከእግዜር ቢዋቀሱ
ትርጉሙ ምንድነው ?
ሲኖር ተቃቅሮ ፥ ሲሞት መላቀሱ።
በእናታችን አድባር ፥ በፍቅሯ ይሁንብን
መድመቅ ካጋደለን ፥ ቆሽሸን ይመርብን
በመጠማት ሲቃ
እስትንፋስ እስኪያንቃት ፥ ነፍሳችን ትርበትበት
ብቻህን ከመጥገብ
አብሮ መራብህ ነው ፥ ሰው የመሆን ውበት፡፡
በድፍን ግልብ እሚያጋድል
ህዝብ የመሆን መንጋ ፥ አይንዳን
በማሰብ ስር እንፈወስ ፥ በሰውነት ፀበል እንዳን።
አየህ! ሰው ስትሆን
ከመንጋነት ሚያግድ
እረኛ አያሻህም ፥ ከህሊናህ በላይ
ስታስብ መሪ ነህ
በብስለት ከፍታ ፥ በማስተዋል ሰማይ፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን
የጎጥ አረም ነቅለህ
በአንድነት መስክ ላይ ፥ ፍቅር ትዘራለህ፣
በወረወሩብህ የጥላቻ ድንጋይ
ትውልድ የሚያፋቅር ፥ ድልድይ ታበጃለህ፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን
ዝምታህ ኃያል ነው
ጀግና የሚያንበረክክ
ከፈሪ ቀረርቶ ፥ ከባዶ ሰው ጩኀት
ሀገር ላምስ ከሚል
በመንደር አጀንዳ ፥ በአሽኮለሌ ተረት፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን
ነጻ ነህ እያሉህ
መታሰር ያምርሃል
መቀመቅ መበስበስ
የኖርክለት እውነት ፥ ሀገር እስኪፈታ
በሀቁ እስኪመዘን
ስለ በርባን ክብር
የቆሸሸው ፍቅር ፥ የታሰረው ጌታ
ከድል ታሪክ ሰማይ
ከሥልጣኔ ዳር ፥ ከጥበብ ከፍታ
እንሻገራለን
ህዝብነትን ትተን ፥ ሰው የሆንን ለታ፡፡

በትረ ጥበበ ቢካን
ዓለም ሊያንቀጠቅጥ ፥ ድል ሥልጣን ቢሰጠው
ጀግና መሪ አይደለም
ብርቱ ተመሪ ነው ፥ ሀገር ሚለውጠው፡፡
አስተውል ወዳጄ
ጠልተን ላንጣላ
ችለን ላንጋደል ፥ ነደን ላንፋጀው
የኛው ትርምስ ነው
በልቶ ለሚያባላ ፥ ጠላት ሚበጀው፡፡
ስጋና ደም እንጂ
የአንድነታችን ውል ፥ የፍቅራችን ቀለም
ያሰመርነው ክልል
የታጠርንበት ዘር ፥ ቋንቋችን አይደለም፡፡
ከመዋሃድ መቅደስ
ትውልድ እናስተምር ፥ ዘመን ይመርቀን
ፍቅራችን ምን ጎድሎት ፥ ደማችን ያስታርቀን፡፡
በልጆቿ አጥንት
በደም ኪዳን ምለን ፥ የገባንላት ቃል
ከጩኀት ያለፈ
ዘመን የሚሻገር ፥ ተግባር ይጠይቃል፡፡
በአንድ ሃሳብ ተጋምደን
በድል ድር እናብር
ውድቀታችን ያንቃን ፥ ሠርተን እናሳምን
ሆነን ድል እንንሳ ፥ የአፍ ጀግንነት ይብቃን፡፡
98 viewsፍቅር-ኤል, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:30:31 #ተነሳ_ተራመድ

ተነሳ ተራመድ ፥ ክንድህን አበርታ
ላገር ብልፅግና ፥ ለወገን አለኝታ

ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም
ሀሁ ኢትዮጵያ ተትቅደም

ወንዞች ይገደቡ ፥ ይዋሉ ለልማት
በከንቱ ፈሰዋል ፥ ለብዙ ሺ ዓመታት
ይውጡ ማእድናት ፥ ለሃገራችን ጥቅም
ህዝቧ ታጥቆ ይስራ ፥ በተቻለ አቅም።

አሸብርቃ ታይታ ፥ በተፈጥሮ ሃብት
ተብላ እንዳነበር ፥ የአፍሪካ መሬት
ብለው እንዳልጠሯት ፥ የዳቦ ቅርጫት
እንዴት እናታችን ፥ ይጥማት ይራባት፡፡

ይቅር ማንቀላፋት ፥ ያበቃል መኝታ
ይጥፋ ከሃገራችን ፥ ድህነት በሽታ
ይነገር ይለፈፍ ፥ ይታወጅ በይፋ
አንድነት ሃይል ነው ፥ የሁላችን ተስፋ፡፡

የእናት ሃገራችን ፥ ጥቃቷን አናይም
ህዝቧ ተበድሎ ፥ ማየት አንፈልግም
የዘር የሃይማኖት ፥ ልዩነት አንሻም!
ይላሉ ልጆችሽ ፥ ኢትዮጵያችን ትቅደም!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

@snetsehuf
102 viewsፍቅር-ኤል, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 23:05:12 ኦርቶዶክሳዊ አዳዲስ እና የቆዩ መዝሙሮችን የሚፈልግ በዚህ ሊንክ ያገኛል።

https://youtube.com/channel/UCH-ySyaIEpsyXSMesboJFUw
238 views🇦 🇧 🇽 ✞࿄, 20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 22:37:57 ስምንተኛው ንጉስ ስሙ ማሞ ነው !
(በአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ የብሔር ዘረ መል ተመራማሪ አሌክስ አብርሃም)

ሰሞኑን ግን የማያቸው የምንም ነገር ተንታኞች ምን እያጨሱ ነው የሚገቡት? ...ማለቴ ሄሮይን ምናምን ተፈቀደ እንዴ ?… በቃኮ አንደኛ ክፍል እያለን በጨዋታ መልክ የምናወራውን የቃል ጨዋታ ሱፍ ለብሰው ከረቫት አስረው የሚያወሩ ‹‹አባባ ማሙሾች›› ናቸው የወረሩን! እንዴ ለምሳሌ … ‹‹ጎደሎ›› ከሚለው አማርኛ ቃል ‹‹ባትሪ ሎ›› የሚል እንግሊዝኛ ተፈጠረ ዓይነት! አያችሁ በዚህ አይነት ጉዳዮች ከመሳቅና ከመሳለቅ ይልቅ ህዝብና ህዝብን ለማቀራረብ ብንጠቀምብት አዋጭ ይመስለኛል!እኔም ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ብቻ ከላይ ለራሴ በሰጠሁት ማእረግ በመጠቀም ስለአማራና ኦሮሞ ብሔሮች አሰያየም …ስለስሞቹ ታሪካዊ ዳና …ወቅታዊ ቃና …እንዲሁም አንድነት እና ልዩነት ጥልቅ ማብራሪያ እሰጣለሁ!

well ! እንደምታዩት አ ማ ራ በ (አ) ይጀምራል ኦሮሞ በ (ኦ) ይጀምራል !
(አ) ኡ ኢ ኣ ኤ እ (ኦ) ጥግና ጥግ ይዘው ለምን እንደሚጠዛጠዙ ከፊደሎቹ አቀማመጥ አልተረዳችሁም?
በሁለቱ መሀል በ አ እና ኦ (ኢ) አለች ኢትዮጵያ ማለት ነው! ኢትዮጵያ ተጨነቀች ወገኖቸ! …ኤ ትታያችኋለች? ኤርትራ ማለት ነው! ይሄ ጭንቀት እስከኤርትራ የዘለቀ ነው ! ሌላ ኣ አለች አሜሪካና አውሮፓ ማለት ነው … እ አለች እንግሊዝን በተለይ ሲጠቅሳት ነው! (አያችሁ ስለማታስተውሉ እንጅ ቀላል ነው!) አሁን የስንት አገራት ጣልቃ ገብነት እንዳለና የእነዚህን የሁለት ብሄሮች ምሁራን በስውር እጅ እያጋጩ እንዳሉ ሚስጥሩ ፊደሎቻችን ውስጥ አለ! አናስተውልማ!

ይታያችሁ ወገኖቸ አ ማ ራ ኦ ሮ ሞ ሁለቱም ውስጥ የ መ ዘር አለ …ስታገጣጥሙት ማ ሞ (ወደፊት ማሞ የሚባል ሁሉን ያማከለ ንጉስ ይመጣል) ሁለቱም ውስጥ የ ረ ዘር አለ … እንዴት ይሄ ሁሉ ነገር ሊመሳሰል ቻለ ካላችሁ ከልዩነታችን አንድነታችን ስለሚበዛ ነው …የቅርፅ እንጅ የዘር ልዩነት የለንም ወገኖቸ !

እና አሁን እነዚህን ሁለት ብሔሮች በስያሜ ደረጃ እንዴት እናስማማቸው ለሚለው ቀላሉ መፍትሄ ወይ አ ፊደልን እግሯን ማሳጠር ነው ወይም ኦ ፊደልን እግሯን ማስረዘም ነው! አመሰግናለሁ! በቀጣይ በምጋበዝባቸው መድረኮች ቀሪዎቹን ሁለት ፊደሎች እንዴት ማስተካከል እንደምንችል አብራራለሁ …ፈጣሪ አገራችንን ይባርክ !
@snetsehuf
256 viewsፍቅር-ኤል, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 22:50:36 "የሕይወት ትርጉም ምንድ ነው? እንወለዳለን፥ እድለኛ ከሆንን እናድጋለን፥ እናረጃለን፥ እንሞታለን። ከእንሰሳት የተለየ ሕይወት አይደለም። ልዩነት ቢኖር የሰው ልጅ ስለመኖር ያለው የማሰብ ችሎታ ብቻ ነው። ማሰብ ባይኖር ኖሮ ክፉን ለበጎ ለይቶ ለማወቅ ሕሊናችን አይጨነቅም ነበር። ህይወት አጭር እና ጅል ነገር ናት! ግን ታስጨንቃለች። የጭንቀቱ መሠረት የማሰብ ችሎታችን (conscious) ነው። ሌላ አይደለም። የማሰብ ችሎታችን ሲቆም እፎይታ፥ ሠላም፥ ዘላለማዊ ፀጥታ! የሰው ዘር ሞኝ ነው፤ ጅል ነው። ለሚኖረው አጭርና ጅል ሕይወት፥ ገና ለገና የማሰብ ችሎታ አለኝ ብሎ፥ ለእንሰሳት ባህርይው የረቀቀና የላቀ ትርጉም ሊሰጠው ይሞክራል። የስቃዩ ዋነኛ ምንጭ ነው…"



"የቀይ ኮከብ ጥሪ" ከበዓሉ ግርማ (241)
@snetsehuf
267 viewsፍቅር-ኤል, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 22:49:42 በጀርመን ሐገር የሒትለር ልጅ አብሮ ከሚማርበት ክፍል አንድ መምህር "ተማሪዎች በክንፋቸው ከሚበሩት እንሰሳት መኻል አንድ ጥቀሱ?" ብሎ ይጠይቃል።

በዚህ ቅፅበት የሒትለር ልጅ እጁን አውጥቶ "ዝሆን!" በማለት መለሰ።

አስተማሪውም "አጨብጭቡለት! ሞቅ አድርጋችሁ አጨብጭቡለት…የኔ አንበሳ!" ይላል። ክፍሉም በጭብጨባ ብዛት ቀውጢ ሲሆን ይሄን የሰማ ርዕሰ-መምህር ይመጣና "ምንድነው?" ሲል ቢጠይቅ አስተማሪው ጉዳዩን ሹክ ይለዋል።

ከዚያም ርዕሰ-መምህሩ "ደግማችሁ አጨብጭቡለት እንዲህ አይነት እሳት የሆነ ተማሪ ከየት ይገኛል!" እያለ ጠጋ ብሎ ለመምህሩ በጆሮው "ወንድሜ እኛ ከምንበር ዝሆኑ ቢበር ይሻላል!" አለው።

•••

"ሉባር" ከበረደድ ገዳሙ (115)
@snetsehuf
231 viewsፍቅር-ኤል, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ