Get Mystery Box with random crypto!

ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙

የቴሌግራም ቻናል አርማ sineislam — ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙
የቴሌግራም ቻናል አርማ sineislam — ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙
የሰርጥ አድራሻ: @sineislam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.09K
የሰርጥ መግለጫ

<< `በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።` >>
ሱረቱል ዐስር፦(1፥3)
For comment an& cross
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
@Alhamdulilah25

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 83

2022-07-14 17:10:28 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ አንድ)
.
ጠዋት ላይ እንዳለፉት ሁለት ቀናት በጊዜ ተገናኝተን ወደ ስራ ገብተናል። የተሰጠን አድራሻ የጥቁር አንበሳው ሆስፒታል በመሆኑ ግራ የሚያጋባ ነበር።
"ታማሚ ነው እንዴ?" ጋሼ ወደ ጊቢው እየተቃረብን ስንመጣ ጠየቁኝ።
"እኔንጃ.... ስሙ 'ረሻድ ሙጂብ' መሆኑን ብቻ ነው የገለፀችው። ወይ እንደውልላት?"
"አዎ ይሻላል.... ደውልላት".... ተስማሙ። አነጋገራቸው እስካሁን ምን ያስጠብቅሃል ይመስላል። ስደውልላት እየሳቀች ቴሌግራም ላይ የሁሉንም ቁጥር እንደላከችልኝ ነገረች፤ ከነጋ ከፍቼ አላየሁትም ነበር። ስልኩን ዘግቼ ከላከቻቸው ስሞች መሃል የሱን ስም ፈልጌ ደወልኩለት። በመጀመሪያው ጥሪ ዘጋብኝ... ግራ ተጋባሁ። ደግሜ ስደውልለት መልዕክት ላከልኝ.... 'I'm in class'።
"Ohhhh ተማሪ ነው ጋሼ..."
"እዚ?"
"መሆኑ ነዋ እንግዲ..." ግራ እየተጋባሁ መለስኩላቸው።
"እና ምን ይሻላል? እዚ አንውል... ወይ እስከዛው ቡና ነገር እንጠጣ..."
"ሳይሻል አይቀርም..." በጋሼ ሃሳብ ተስማማሁ። ከክፍል ሲወጣ እንዲደውልልኝ እና ከጊቢው ፊትለፊት ካሉት የመንገድ ላይ ሻይቤቶች ጋር መሆናችንን በፅሁፍ መልዕክት ልኬለት ወደ ሻይቤቱ አመራን።
.
ከጋሼ ጋር ተቀምጠን ስለ ሲጋራው አንስቼ ላወያያቸው ፈልጌ ነበር፤ ፊታቸው ግን ለመምከር ያስፈራል። በማመንታት ላይ እንደሆንኩ 4 ሰዐት ሲጠጋ ደወለልኝ፤ ረሻድ። የጊቢው በር ጋር ቆሞ በአይኑ ሲያማትር ላየሁት ወጣት እጄን አውለበከብኩለት፤ እሱ ሳይሆን አይቀርም። እንዳየኝ ገልፆልኝ ስልኩን ዘግቶት ወደኛ አመራ።
"አሰላሙ ዐለይኩም.... ብዙ አስቆምኳቹ እንዴ?" ትህትና በተሞላበት አነጋገር ሰላምታ አቅረበልን።
"ወዐለይከ ሰላም.... አይ ብዙም።" ሰላምታውን መልሰን እንዲቀመጥ ጋበዝነው። ከለበሰው መነፀር ጋር የሰውን አይን የሚፈራ ይመስላል.... ብዙ አያወራም።
"አብሽር ተጫወት..." ጋሼ ለሱም የሚሆን ሻይ እያዘዙ።
"አይ.... አያስፈልግም። 5 ሰዐት መመለስ አለብኝ... ካላቻኮልኳቹ"
"አሃ እሺ በቃ። ራቢያን ታውቃታለህ?"
"ራቢያ..... ታይዋን የሄደችዋን ነው?" ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነቅኩለት። "አዎ አውቃታለሁ በደምብ.... ምነው? በኸይር?"
"አዎ አብሽር። ሙስዐብ እባላለሁ.... ባለቤቷ ነኝ። መልዕክት እንዳደርስላት ልካኝ ነው የመጣሁት..." ፖስታውን አውጥቼ ሰጠሁት። ከፍቶ ካየው በኋላ እንዳለፉት ተቀባዮች ሁሉ ቀና ብሎ ተመለከተኝ... የደነገጠ ይመስላል።
"ግንኮ.... ብዙ ነው..." ግራ ተጋብቶ ተመለከተኝ።
"አብሽር የገንዘብ ብዙ የለውም... ሃሃህ" ጋሼ ዘና ሊያደርጉት ሳቅ አሉ። እንደደነገጠ መልሶ ከፈተው... እንደሌሎቹ ስለካርዱ እንድነግረው አልጠበቀም፤ አውጥቶ የተፃፈበትን በዝምታ ማንበብ ቀጠለ። መነፀሩን በየመሃሉ ወደላይ ከፍ ያደርጋል.... የኔም ሃሳብ አብሮ ከፍ ዝቅ እያለ መሆኑን አላወቀም። የተፃፈበት ያን ያህል ረጅም አይመስለኝም.... ሳይመልስልን ለደቂቃዎች ወረቀቱ ላይ እንደተመሰጠ ቀረ።
"ሰላም ነዋ?" ግራ በመጋባት ጠየኩት።
"እ... አዎ አፍወን.... ሰላም ነው..." ከተሳፈረበት ሃሳብ ደንገጥ ብሎ ተመለሰ። "መርሃባ አብሽሪ.... አንቺም እየበረታሽ፤ ዱዐ አደርግልሻለሁ በላት... ጀዛኩሙላህ፤ ወላህ ከሚገባኝ በላይ ነው።" ፈገግ ለማለት እየሞከረ። እያዋራኝ ካርዷን ወደ ፖስታው መልሶ ከተታት፤ እንዲሰጠኝ ለመጠየቅ ትህትናው ያሳሰረኝ መሰለኝ።
"እና.... የባንክ ሂሳብ አለህ?" ልሂድ ብሎ ከመነሳቱ በፊት ጠየኩት።
"አዎ አለኝ...."
"ኸይር በቃ.... አስገብተን መምጣት እንችላለን... ለ 5 ሰዐት 40 ደቂቃ ይቀራል።" እሺ እንዲለኝ የመጫን አይነት ነበር፤ ተስማማ። 3ታችንም ወደ ጋሼ መኪና ተመልሰን በቀጥታ ወደ ባንክ አመራን። ልቤ ካርዱን ማንበብ የምችልበትን ሁኔታ ወደመፍጠር ብቻ ተሰብስቧል። ፖስታውን ተቀብዬው ፎርሙን ከሞላ በኋላ ተራችን ደርሶ እስክንጠራ እሱና ጋሼ እንዲቀመጡ ነግሬአቸው ወደ ገንዘብ ተቀባዩዋ ተጠግቼ ቆምኩ። ጋሼ ስለ ህክምና ትምህርቱ የባጥ የቆጡን ይጠይቁታል፤ አሁን ባነብ ልብ አይለኝም። ሁኔታው የስርቆሽ አይነት የጥፋተኝነት ስሜት ቢኖረውም ስለራቢ ለማወቅ ያለኝ ጉጉት ግን ከዛም በላይ ነበር። አጋጣሚውን ለመጠቀም ካርዱን አውጥቼ ማንበብ ጀመርኩ....
.
<<አሰላሙ ዐለይክ ረሻድ.... ራቢያ ነኝ ከጀመዐ አስታወስከኝ? ትምህርቱ ቢያለፋም ጥሩ እየተሟገትከው መሆኑን ሰምቻለሁ.... ጀመዐ ውስጥም እንደድሮው ፈጣን መሆንህን ነግረውኛል ማሻአላህ። ስለጠፋሁ አፉ በለኝ... ሃጃዎች በዝተውብኝ እንጂ የደረስክበት ሳያሳስበኝ ቀርቶ አይደለም። ገንዘቡ ያን ያህል እንደማያቆይህም አውቃለሁ.... ግን ቢያንስ መጪውን የረመዳን ወር ለነኡሚ በመጨናነቅ ላይ ታች ስትል እንዳያመልጥህ በሚል ነው። የረመዳንን ልቅና ላንተ አላስረዳም መቼም፤ ግን ደግሞ የትጋት ወር መሆኑንም አትርሳ። ከሁላችንም የላቁ የሆኑት ነቢና {ሰ.ዐ.ወ} እንኳን <ከማንም በላይ ቸር ነበሩ። ይበልጥ ቸር የሚሆኑት ግን ጂብሪል በሚያገኛቸው የረመዳን ወር ውስጥ ነበር። ጂብሪል በረመዷን ወር ውስጥ በእያንዳንዱ ሌሊት ያገኛቸውና ቁርዐን ያስተምራቸው ነበር። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} በዚህ ወቅት በበጎ ነገር መቸገራቸው እንደ ነፋስ ፈጣንና ሁለንተናዊ ይሆናል።> ተብለው አይደል በሃዲሶች የተገለፁልን? ስለዚህ አንተም ከምን ጊዜውም በላይ ትጋበት.... ሂፍዝህን መልሰህ ከልሰው፤ ያልቀሩ የጀመዐና የዶርም ልጆችህንም አቅራቸው። አደራ! በቻልከው አላህን ይበልጥ መገዛትና ማውሳት ላይ ጠንክር። በቅርቡ በአካል እስክዘይራቹ ለኔም ለሙስዐብም ዱዐ ያድርጉልን። ወሰላሙ ዐለይክ ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።>> የመጨረሻዎቹን መስመሮች እያነበብኩ እያለ የረሻድ ስም ሲጠራ ደንገጥ ብዬ ወረቀቱን ወደ ፖስታው መለስኩት።
*
ከባንክ ቤት መልስ ረሻድን ወደ ጊቢው አድርሰን ተሰናብተነው እኔና ጋሼ መንገዳችንን ቀጠልን።
"ጋሼ..... ያውቁታል እንዴ? ማለት... ወይ ራቢ ስታወራ ሰምተው ከሆነ?" ከካርዱ ላይ ከሱ መልካም ተርቢያ ውጪ ለማወቅ ስላልቻልኩ ጉጉቴ አልሰከነም።
"አይ አላውቀውም.... ግን ቅድም ባንክ ተቀምጠን ራቢን የት እንደሚያውቃት ሲያጫውተኝ ነበር። የ10ን ፈተና ጨርሰው ውጤት እየጠበቁ በነበረበት ጊዜ ላይ እናቱንና እህቱን ለመደገፍ ጎን ለጎን የታክሲ ረዳትነት ይሰራ እየነበር ነው የተዋወቁት። ከዛ ጎበዝ ተማሪና ባለ ጥሩ አኽላቅ መሆኑን ስትሰማ ጊቢ አብረዋት ለሚሰሩት ጀመዐ አገናኝታው እየተረዳ መማር ቀጠለ። አሁን ማሻአላህ 4ኛ አመት ህክምና እያጠና ነው.... ማታ ማታ አንድ ሱፐር ማርኬት ውስጥ ከ12- 2 ሰዐት በሻጭነት እንደሚሰራም አጫውቶኛል.... ኧረ ልጁ ስለራሱ ለማውራት አይንቀለቀልም እንጂ ጠንካራ ነው፤ ፊቱ ይናገራል.." ጋሼ ድምፃቸው ውስጥ ደስታ እየተደመጠኝ ተርከው ጨረሱ። ከሱ ሁኔታ ጋር እኔም ተማሪ ሆኜ ስሰራ የነበረበት ሁኔታ ታውሶኝ፤ ለኔ ያኔ ቢደረግልኝ የምመኘው የነበረውን ድጋፍ ዛሬ ለሱ ለማድረግ በመቻሌ ደስ ተሰኘሁ...
"አላህ ያግዘው። እሱ የሚለፋን ሰው ጥሎ አይጥልም... ትልቅ ደረጃ ይደርሳል ኢንሻአላህ።"
"አሚን ኢንሻአላህ...." ጋሼ ፈገግ ብለው መንዳታቸውን ቀጠሉ፤ ጊዜ ለመቆጠብ ሳይጠይቁኝ የቀጣዩን ቤት አድራሻ አቀበልኳቸው።
.
.
ይቀጥላል...❶❷

@sineislam
2.4K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:44:07 ፈዳኢል...
(ክፍል አስር)
.
.
ሳዕዲያን ገንዘቧን በአካውንቷ አስገብተንላት ወደ ቤቷ ከመለስናት በኋላ ወደ ሱመያ መስጂድ አቀናን፤ የዐስር ጀመዐ አልፎ ነበር። እኔና ጋሼ ለብቻችን በጀመዐ ከሰገድን በኋላ ጋሼ ተጣድፈው ከመስጂድ ወጡ.... እኔ እዛው ትንሽ ከቆየሁ በኋላ ጋሼ ተመልሰው ሲመጡ አብረን ሄደን ቁርዐኖቹን ገዛዝተን ወደ መስጂዱ ተመለስን። ከሙሉ ውሎው ቅመም የሆነው ማጣፈጫ ክፍል ይሄ እንደሆነ ይሰማኛል። የመስጂዱ ወጣቶች ካስተናገዱን በኋላ መግሪብ እስኪደርስ አንድ አንድ ቁርዐን ይዘን እዛው መስጂዱ ውስጥ ተቀመጥን። ራቢ እንዳለችው ባሰላሁት መሰረት በየቀኑ 2 ቤት እየሸፈንን መሄድ ከቻልን... በ10 ቀን ውስጥ ለመጨረስ በቂ ነው፤ ስለዚህ ጊዜ ቢኖረንም ቀጣዩን ቤት ነገ ጠዋት ስለምንቀጥለው አሳሳቢ አልነበረም። በሌላ ጎኑ የመግሪብ በኋላ ዳዕዋዎቹ የተወሰነ ኢማኔን እንዲያጠናክሩት ፍላጎት አድሮብኛል።
.
መግሪብ ከተሰገደ በኋላ ሱናን ሰግደን እንዳለፉት ቀናት የሚኖረውን ዳዕዋ ለመታደም መጠባበቅ ጀመርን። ሸይኹ በአጠቃላይ ስለሚመጣው ወር በላጭነት ሲያስታውሱን ከቆዩ በኋላ ረመዳን ላይ ምግብ ካለመብላቱ በተጨማሪ ልንጠነቀቅላቸው ስለሚገቡ ነገሮች መዘርዘር ጀመሩ። ዳዕዋቸው በየመሃሉ ጣል ከሚያደርጉት አዝናኝ ንግግር ጋር ማራኪ አይነት ነበር። እኔን ጨምሮ ሁሉም በዝምታ ማዳመጡን ቀጥሏል...
.
"....ስለዚህ ይሄንን ወር ተርበን አሳለፍነው ማለት ብቻ እንደ ፆም አይቆጠርም። እንደውም ስንፆም ኢማናችን ከምን ጊዜውም በላይ የሚፈተንበት ነው። አንዳንዴ 'ሸይጧን ይታሰራል' መባሉን ብቻ ይዘን ትንሽ እንዘናጋለን። አይደለም አንሸወድ!..... ነፍስም እኮ በክፉ ታዛለች አይደለም እንዴ? እኛ ራሳችንን ብንጠብቅ እንኳን ሌላ ነፍሲያውን ማሸነፍ ያልቻለ ሰው እኛም ላይ ጫና ይፈጥራል። አመቱን ሙሉ የተከለከሉ ነገሮችን ሲፈፅም የኖረ ሰው.... ልክ ረመዳን ላይ ነፍሱን 'አቁሚ' ቢላት ቶሎ አትታዘዘውም። ስለዚህ አይታወቀውም....ንዴት ንዴት ይለዋል። በጠዋቱ 'አሰላሙ ዐለይኩም...' ስትሉት 'ምን ሰላም አለ....' ብሎ በአፀያፊ ስድብ ሊዘልፋቹ ይችላል። ይሄ ብቻ አይደለም.... እናንተም አንዳንዴ ረሃቡ ደከም ያደርጋቹና ነፍሲያ የምግብ ነገር አላስችል ሲላት በሆነው ባልሆነው ቁጣ ቁጣ ይላችኋል.... አይደለም እንዴ?" ብዙዎቻችን በአዎንታ መለስንላቸው...
.
" አዎ!.. ያስብላል.... ፆም ሸይጧን ቢታሰርም ትንሽ ከበድ ይላል። ስለዚህ አህባቢ እኛም ለፈተናው ብቁ ሆነን መዘጋጀት አለብን። አቡ ሁረይራ እንዳስተላከፉት የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ}፦ <ከናንተ አንዳችሁ በፆመ ጊዜ ፀያፍ አይናገር፤ አይጩህም። አንድ ሰው ከሰደበው ወይም ከተጋደለውም 'እኔ ፆመኛ ነኝ' ይበል።> ነበር ያሉት። ወዳጅህ መጥቶ ያልሆነ ነገር ቢናገርህ እንኳን አትስደበው.... የማይሆን መሆኑን ካወክ አትከራከረውምም፤ ትተህ እለፈው። እህቶችም ብትሆኑ አንዳንዴ ያጋጥማል.... ባሎቻቹ ወይ ወንድሞቻቹ ፆሙ ከስራ ጋር አድክሟቸው ይመጡና የናንተንም በቤት ውስጥ መድከም ረስተው የሆነ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ። ግን አትመልሱላቸው.... እለፏቸው። 'እኔ ፆመኛ ነኝ' በሏቸው ነው ያሉት ነቢና..... ግን ክርክሩ ውስጥ አትሳተፉ እንደማለት ነው። በደከመሽ ሰዐት 'ኸዲጃ ነይ ይሄን አድርጊ' ብለው ሲቆጡሽ ሁሉ 'እኔ ፆመኛ ነኝ' በይ ማለት አይደለም.... 'እኔ አፍጥሬአለሁ ያለሽ ማነው?' የሚል ሌላ ፀብ ያጭራል... ኡስታዝ ነው የመከረኝ እንዳትዪ በኋላ..." ሁላችንም በንግግራቸው ፈገግ አልን።
.
"ሃሃህ... ሌሎች መንገዶች ሞልተዋል ለማለት ነው። ለስለስ ያሉ ቃላት ንዴትን ያበርዳሉ። ከመከራከር ይልቅ 'ፆመኛ ስለሆንኩ ትንሽ ደክሞኛል... ከመግሪብ በኋላ እናውራበት' ብሎ ማራዘም ይቻላል። አንድም ፆማቹ አይፈርስም... አንድም ጉዳዩ ይበርድና ይረሳል። እሺ ኸይር.... እንደኔ ደግሞ ተናዳጅ ናቹ እንበል። አልያም ፆመኛ ነኝ በሚል ልታስቆሙት ያልቻላቹት ሰው ንዴት የፈጠረባቹ እንደሆነሳ?.... አሁንም በድጋሚ አትመልሱለት። አላህ ያስቀመጠልን መፍትሄ ምንድነው?

وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ ٱلشَّيْطَٰنِ نَزْغٌ فَٱسْتَعِذْ بِٱللَّهِ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ

{ከሰይጣንም ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጠባይም ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡} (ፉሲለት 36) አይደል ያለን?.... ኢስቲዐዛ እያደረግክ ሶብር ማድረግ ነው፤ በዚህም ላንተ 'ንዴታቸውን መቆጣጠር ከሚችሉት' በመሆንህን አጅር ይኖርሃል።
.
"ኢስቲዐዛም አደረግክ አልሰራም.... እሺ ታዲያ ምን ይሁን? ካናደደህ ሰው ፊት ዞር በልና ውዱዕ አድርግ። ነቢና ውዱዕ ንዴትን እንደሚያሰክን ገልፀውልናል.... ማንም ደግሞ 'ለምን ውዱዕ ታደርጋለህ?' ብሎ የሚተሳሰብህ አይኖርም። ግን ፆመኛ ስትሆን ውዱዕም ጥንቃቄ ይፈልጋል.... በአፍህም በአፍንጫህም እንደልብህ ውሃ እየላክ ጉሮሮህን የምታርስበት አይነት መሆን የለበትም። ለቂጥ ኢብኑ ሶቢራህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት:- <የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለ ውዱእ ይንገሩኝ> አልኳቸው። <የተሟላና አካልህን ያዳረሰ ውዱእ አድርግ። በጣቶችህ መካከል ያለውን ቦታ እጠብ። ወደ አፍንጫህ ውስጥ ውሃ በደንብ አስገባ፤ ፆመኛ ካልሆንክ በቀር> አሉኝ።> ብለዋል። ስለዚህ ጥንቃቄ የተሞላበት ረጋ ያለ ውዱዕ አድርገህ ራስህንም ፆምህንም ጠብቅ።
.
"ከዚ ውጪ ደግሞ ቁመህ ከሆነ ተቀመጥ፤ ተቀምጠህ ከሆነ ተኛ ነው አይደል መፍትሄው? ግን በዚ አሳበህ ፆሟ ከበድ ባለችህ ቁጥር 'እንዳልናደድ' እያልክ ተጋደም ማለቴ አይደለም..." ፈገግ ብለው ወደያዙት ወረቀት አቀረቀሩ፤ እኛም ሳቅ አልን። "...አአአአዎ... ያን ያህል የሚያናድድህ ደረጃ ላይ ከደረስክ ራስህን ጠብቅ ለማለት ነው። ይሄ ሁሉ የሚዘረዘረው እኮ በከንቱ አይደለም አህባብ.... 'ጨው አበዛሽ' በሚል ተናዶ በመሃል ረመዳን 'ፈትቼሻለሁ... ወደ ቤተሰቦችሽ ሂጂ' ብሎ ቤቱን የሚያፈርስ ስለሚኖር ነው። ሌላው ደግሞ ራሱን ከፎቅ ላይ ይጥላል... አላህ ይጠብቀን። ንዴት አላህን የሚያስቆጡ ውሳኔዎችን የሚያገራልን ነው.... ስለዚ በተለይ ረሃቡም ድካሙም ትንሽ በሚበዛበት በዚ ወር ላይ ጥንቃቄ ይፈልጋል። እኔም እያሳቅኩ የማዋራቹ እንዳትቆጡ ለመጠንቀቅ ነው.... ቅድም ስገባማ ፊታቹ ያስፈራ ነበር..." በድጋሚ አሳቁን። "ሃሃህ....ኸይር.... ሰዐቴን ብዙ ሳልጠቀመው አልቀረሁም፤ ስለሁለተኛው ባህሪ ኢንሻአላህ ነገ እንቀጥላለን። ለዛሬ ይብቃን.... ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ..." ተሰናብተውን፤ ማጠቃለያ ዱዐቸውን አድርገው ወደ ውስጥ ገቡ። ዳዕዋቸው በመጠኑ ዘና የሚያደርግ ቢሆንም ልብ ላይ የሚቀር ነበር። የዒሻእ ሰዐት ስለደረሰና የያዝኩት ሆቴል በጋሼ መኪና ከዚ በጣም ስለማይርቅ ዒሻእን እዚሁ ሰግደን ለመውጣት ተስማማን።
.
.
ይቀጥላል...❶❶

@sineislam
3.2K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:17:34 ፈገግታ ሱና ነው

መምህር፡''የዛሬ ርዕሳችን ሙስና ነው።''
ተማሪ፡''እሺ መምህር''
መምህር፡''እሺ ሙስና ምንድን ነው?''


ተማሪ፡ ''#የዛሬ_ርዕሳችን!''

ብሎት እርፍ
ተ ላ ሉን
@sineislam

@sineislam
3.2K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:20:15 አነስ ኢብኑ-ማሊክ (ረ፡ዐ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሰ፡ዐ፡ወ)እንዲህ አሉ፡-ወደ-ሰማይ) ባረግሁ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ፡፡ጂብሪልንም፡-ማናቸው እነዚህ?ስለው፡ እነዚህ(በሐሜት) የሰዎችን ስጋ የሚበሉና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው አለኝ" (አቡ ዳዉድ)፡፡ሐሜት በውዱና በተፈላጊው ዓለም በአኼራ ባለቤቱን ከከሳሪዎች የሚያደርግ በሽታ ነው፡-

ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡(ቁርአን-49:10)

@sineislam @sineislam
3.3K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 20:20:57 °•ለሰዎች የምትመክረውን ቅድሚያ ራስህን/ነፍስያህን ፈትሽበት ሰዎችን መምክር ቀላል ሊሆን ይችላል ነገር ግን ለሰዎች የምንመክረው እኔ ተግብሬዋለሁኝ ወይ እኔስ የት ነኝ ብሎ ራስን መገምገም ብዙዎቻችን የዘነጋነው ጉዳይ ነው!

።።ብዙ ሰዎች ሰውን ይመክራሉ ለሰዎች እንደሻማ ናቸው ነገር ግን ዘወር ብለህ ስታያቸው ለራሳቸው ምክር የሚያስፈልጋቸው ሆነው ታገኛለህ ይህ ማለት ለሰዎች ብርሃን ሆነው ለራስ ልክ ሻማ መቅለጥ ማለት ነው እናማ ወዳጆቼ እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ ለራሳችን ትኩረት እንስጠው !!

@sineislam @sineislam
4.5K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:36:18 ➧. #ኢላሂ! ስሜቴ አሸናፊ አቅሌ ተሸናፊ ነፍሴ ነውረኛ ምላሴ ነገረኛ ታዛዥነቴ አናሳ ወንጀሌ ብዙ ሆነው የልቤን ብርሃን ጋርደውታል።

➧. አንተ ደግሞ ደካማነቴን አዋቂ ነውሬን ደባቂ ወንጀሌን መሀሪ መልካምን አሰሪ ነህና እኔን ለኔ አትተወኝ ያረብ ።

@sineislam @sineislam
4.9K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 12:46:15 አደራ

➣ዛሬ ሰኞና ማክሰኞን መፆም አይቻልም

የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፦ [ (ሶስቱ) የተሽሪቅ ቀናቶች የመብላት የመጠጣት እና አላህን የማውሳት ቀናቶች ናቸው። ] (ሙስሊም ፥ 1141).

ሼር ማድረግ አትርሱ ሁሉም ሙስሊሞች ማወቅ ይኑርበት!

@sineislsm @sineislam
5.3K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 10:17:05 አንድም ሴት በሜካፕ ምክንያት የወፍጮ ቤት ሰራተኛ መምሰል የለባትም አራት ነጥብ።
5.0K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:10:05 ➲"ልብ የአይን ተከታይ ( ተጎታች) ነው ይባላል ፣

....... ያስለመደውን ይለምዳል ።
አይን መጥፎ ነገርን በለመደ ግዜ ቀልብም ይህንኑ መጥፎ የሚለምድና የሚመኝ ይሆናል ። መልካሙም ላይ እንዲሁ ነው ። እናም አይኖቻችንን ከሓራም እንጠብቅ ። መልካም ነገርን እናስለምዳቸው ።

መልካም ምሽት

@sineislam @sineislam
5.6K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 22:02:25 ለፈገግታ

.......ለ ኡዱሂያ ምን አረድክ ያ ቢላል አሉት (ረሱለላህ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም )

ዶሮ አላቸው ቢላል (ረዐ)...

ሙአዚን ሙአዚንን ያርዳል አሉት ረሱል(ሰዐወ)

መልካም ዒድ ይሁንላችሁ

@sineislam @sineislam
6.0K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ