Get Mystery Box with random crypto!

ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙

የቴሌግራም ቻናል አርማ sineislam — ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙 ኢ
የቴሌግራም ቻናል አርማ sineislam — ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙
የሰርጥ አድራሻ: @sineislam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 37.57K
የሰርጥ መግለጫ

<< `በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።` >>
ሱረቱል ዐስር፦(1፥3)
For comment an& cross
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
@Alhamdulilah25

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 80

2022-09-01 08:25:02
'' ዱንያ ''

ክፍል ሰባት ❼

ሰርፕራይዙ ምን ይሁን በእውነተኛ ታሪክ ላይ ይተፃፈ ታሪክ ኮሜንት ላይ ሀሳብ አስታዪታቹሁን አስቀምጡልኝ በክፍል በሳት ምን ይፈጠር ይሆን ማታ 2 ሰዓት ላይ ይጠብቁን ሼር ማድረግ አትርሱ

↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
ይቀላቀሉን⇊ ይቀላቀሉን⇊
https://t.me/sineislam
https://t.me/sineislam

share
1.7K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:43:42 ​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
            ".  
#ዱንያ  ".
         ፀሐፊ፦ ሂባ
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ስድስት ❲❻❳
╰───── • ❊ • ─────╯

{በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተፃፈ}

ዛሬ በጣም ጨንቆኛል ምክኒያቱ ምን መሰላችሁ ትላንት ኬና ደውሎ ነበር እና <<ዱንያዬ ነገኮ ልደቴ ነው እና ቲኒሽ ፕሮግራም ነገር አዘጋጅቻለሁ ትመጫለሽ አ?>> አለኝ
<<ኬናዬ ልደት እኮ በእስልምና የተከለከለ ነው>>
<<እመኚኝ ማሬ ይህ የመጨረሻ ልደቴ ነው ካሁን ብኋላ ሌላ ልደት አላከብርም...... እና ደግሞ እስልምናንም ለመቀበል ወስኛለሁ....... በአላህ ይሁንብሽ ዱንያ የዛሬን ብቻ እሺ በዪኝ እውነት ካልመጣሽ ደግሞ እቀየምሻለሁ>>
<<እሺ በቃ ኬናዬ ለመምጣት እሞክራለሁ>>
<<እሞክራለሁ አትበይ እመጣለሁ ብለሽ ቃል ግቢልኝ>>
<<እሺ በቃ እመጣለሁ ቃል ነው>>ብዬ ቃል ገባሁለት መሄድ አልፈለኩም ግን ደሞ ከቀረው ኬና ይቀየመኛል ብዬ ሰግቻለሁ።
እረ ቆይ እሺ ልሂድ ብልስ የት ልሄድ ነው ብዬ ነው ከቤት የምወጣው?........በእርግጥ አሰፍ ቤት ስለማይውል የሱ ችግር የለውም ግን ታቲዬንስ የት ልሄድ ነው ብያት ነው የምወጣው?
እዲሁ በሃሳብ ተውጬ ሳለሁ የውጪ በራችን መንኳኳት ጀመረ ሄጄ ስከፍተው የመጣችው ሂኩዬ ነበረች
<<አስሰላሙ አሌይኪ አንቺ እስካሁን አልተዘጋጀሽም እንዴ ወይስ ቀርተሽ ነው?>>
<<ወአሌይኪ ሰላም ሂኩ እረ ባክሽ እቤት ታቲዬን ምን ብዬ እንደምወጣ ግራ ገብቶኝ ነው እኮ>>
<<አንቺ ደሞ የማያሳስበው ነገር ነው የሚያሳስብሽ......ታቲዬን ለኔ ተያት እኔ ነኝ ማስማማት የት ናት?>>
<<ቤት ውስጥ ናት....... ቆይ ግን ምን ልትያት ነው?>>
<<ምን አገባሽ አንቺ ዝም ብለሽ ተከተዪኝ>>ብላ ወደ ቤት ገባች
<<ታቲዬ አስሰላሙአሌይኩም>>
<<ውአሌይኩምሰላም ሂኮ እንዴት ነሽ የኔ ልሽ>>
<<አልው አልሃምዱሊላህ ታቲዬ እርሶስ እንዴት ኖት?>>
<<አልሃምዱሊላህ የኔ ልጅ ደህና ነኝ>>
<<ታቲዬ ግን እርሶ አይወዱኝም እንዴ?>>
<<እረ እወድሻለሁ የኔ ልጅ ለምን አልወድሽም?>>
<<እና ለምንድነው ዱንያን አንድም ቀን ወደኛ ቤት ልከዋት የማያውቁት?>>ብላ እንደ ማኩረፍ አለች እኔ ሳቄን መቆጣጠር አቅቶኝ ወደ ውጪ ወጥቼ መሳቅ ጀመርኩ ከዛ ታቲዬ <<ዱንያ>> ብለው መጣራት ጀመሩ
<<ወዬ ታቲዬ ጠራሽኝ>>
<<አዎ ልጄ እስኪ ልብስሽን ቀያይሪ እና ከሂኮ ጋር እነሱ ቤት ሄደሽ ቲኒሽ ተጫወቺ ግን እንዳታመሺ በጊዜ ተመለሺ እሺ>>
<<እሺ ታቲዬ>>ብዬ ከልብሶቼ መሃል አሪፍ ልብስ ነው የሚባለውን ከሂኩ ጋር መርጠን ከለበስኩ ብኋላ ከቤት ወጣን።
ተቻኩለን ስለነበር ስልኬን ረስቼው ነበር የወጣሁት ከዛም ለኬና በሂኩ ስልክ ደውለን ከቤት መውጣታችንን አሳወቅነው እሱም የአንድ ሆቴል አድራሻ ቴክስት አረገልን።
ከሂኩ ጋር ተያይዘን ወደተባለው ሆቴል ስንደርስ ወደ ሆቴሉ ብቻችንን መግባት ስለፈራን ደግመን ለኬና ደውለን እንዲወስደን ጠየቅነው እሱም ብዙም ሳይቆይ መጣና ሰላም ካለን ብኋላ ወደ ውስጥ ይዞን ገባ።
በሆቴሉ ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ በሚገርም ሁኔታ ግን ሙስሊም የነበርነው እኔ እና ሂኩ ብቻ ነበርን ሂኩ ደስ ብሏታል እኔ ግን በጣም ይጨንቀኝ ጀምሯል።
ይጨፍራሉ ይጮሀሉ ግማሹ መጠጥ ይጠጣል ሌላው ያጨሳይ ብቻ በጣም ቀፈፈኝ ቢሆንም ግን ለኬና ስል መቋቋም ስላለብኝ በግድም ቢሆን ፈገግ ለማለት እሞክራለሁ።

በዚሁ ሁኔታ እንዳለሁ የኬክ ቆረጣ ፕሮግራም ደረሰ እና ኬና የተዘጋጀለትን ኬክ መቁረጥ ጀመረ ኬኩን ቆርጦ ስያበቃ የመጀመሪያውን ጉርሻ ወደኔ አመጣ እና ለኔ አጎረሰኝ እኔም ጎረስኩለት በዚህ መሃል የሂኩ ስልክ መደወል ጀመረ ስልኩ በኔ እጅ ስለነበር የደዋዩን ማንነት ስመለከት መስኡድ ነበር ለካስ አላስተዋልኩትም እንጂ እሱ አልመጣም ነበር ስልኩን አንስቼ ላወራው ስሞክር ልጆቹ በጣም እየተንጫጩ ስለነበር ድምፁ አልሰማ አለኝ ከዛም ሂክማን ጠርቼ ነገርኳት እሷም <<በቃ ውጪ ወጥቼ ደውዬ አውርቼው እመለሳለሁ>> ብላኝ ወጣች እሷ ልክ እንደወጣች የስጦታ መስጫ ፕሮግራም ተጀመረ <<ወይኔ ጉዴ ረስቼው...... ለካስ ልደት ሲኬድ ስጦታ መሰጠት ነበረበት አላህ ሆይ ምኑ ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት?>> ብዬ በውስጤ እያሰላሰልኩ ሳለው ኬና ወደኔ መጣና <<የታል ስጦታዬ?>> አለኝ
<<ወላሂ ኬና እኔ ከዚህ በፊት ልደት ሄጄ ስለማላውቅ ምንም ነገር አላመጣሁልህም ኢንሻአላህ በቃ ነገ ያለህበት ድረስ ገዝቼ አመጣልሀለው>>
<<እረ ፈታ በይ በቃ ችግር የለሁም ግን ባይሆን እኔ ላንቺ ያዘጋጀውት አንድ ስጦታ አለ ነይ ላሳይሽ>>ብሎ እጄን ያዘኝ በእርግጥ እኔ እና ኬና ከዚህ በፊት አንድም ቀን በእጅ ተነካክተን አናውቅም ምክኒያቱም እኔ ወንዶችን አልጨብጥም ነበር ግን ዛሬ ምን እንደነካኝ ባላውቅም አሁን ኬና እጄን ሲይዘው ምንም ነገር አልተቃወምኩም ነበር
<<ምንድነው...... ማለቴ ወዴት ነው የምንሄደው?>>
<<የትም አንሄድም እዚሁ ሆቴል ውስጥ ነው አትፍሪ>> ብሎ እጄን እየጎተተ ወደ ሁለተኛው ህንፃ አመራን።
ከዛም አንድ ክፍል ጋር ደርሶ ቁልፍ ከኪሱ አውጥቶ ከፈተው እና<<ስርፕራይዝ ስለሆነ አይንሽን ልያዝሽ?>>አለኝ እኔም እሺ ብዬ ፈቀድኩለት እና አይኔን ይዞኝ ወደ ክፍሉ አስገባኝ።
.
.
ሀሳብ አስታዬት ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

╔════•| ✿ |•════╗
 
#ክፍል_ሰባት (❼)
╚════•| ✿ |•════╝

➭
@sineislam
➭
@sineislam
2.8K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:46:11 ​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
            ".  
#ዱንያ  ".
         ፀሐፊ፦ ሂባ
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አምስት ❲❺❳
╰───── • ❊ • ─────╯

{በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተፃፈ}


እንዲህ እንዲህ እያልን ዛሬ አንደኛ ሴሚስቴር ትምህርታችንን አገባደን ደረጃችንን ለማየት ሁላችንም በክፍላችን ውስጥ ተቀምጠን መምህራችን እስኪመጣ እየጠበቅን ነው ባለፋት ቀናት ውስጥ ኬናን ወደ እስልምና ለመጥራት አንድ አንድ ጥረቶችን ማድረግ ጀምሪያለው።
ቁርኣን ተፍሲር በአማረኛ እና የተለያዩ ኢስላማዊ መፀሀፍትንም ሰጥቼዋለሁ ብቻ ባጠቃላይ የቻልኩትን በሙሉ እየጣርኩ ነው ያለሁት።

መምህራችን መጥቶ ወደሱ በየተራ እየሄድን ደረጃችንን እንድናይ ተናግሮ ከፊት ለፊታችን ተቀመጠ የኛ ግሩፕ ኋላ መጨረሻ ስለምንቀመጥ ከሁሉም ተማሪዎች ብኋላ ነበር ያየነው።
ከኛ ግሩፕ አባል በመጀመሪያ ያየው ዳጊ ነበር እና እሱ አይቶ ሲመለስ መስኡድ በተራው ለማየት ሄደ
<<እ....እንዴት ነው?>> አለው ኬና
<<አሪፍ ነው ባክህ>>
<<ዋው ብሮ አኮራሽኝ እና ስንተኛ ወጣሽ?>>
<<ባክህ አታሙቅ 28ኛ ነው የወጣውት>>ሲለው ሁላችንም ሳቃችንን መቆጣጠር አቅቶን በጣም ሳቅንበት የሚገርማችሁ ነገር ደግሞ እሱም ምንም ሳይመስለው ከኛ ጋር እያስካካ ይስቃል ሀሀሀ።
መስኡድም በተራው አይቶ ተመለሰ እና ኬና ለማየት ሄደ
<<እ....መስኡዴ እንዴት ሆንሽ?>>አለው ዳጊ
<<ኤጭ ባክህ ደባሪ ነው>>
<<አቦ አታሙቃ ቶሎ ተናገር እኔ ራሱኮ 28ኛ ነው የወጣውት>>
<<ሀሀሀ ጀለስ አንተኮ እሱም ሲበዛብህ ነው መች ለተማርከው ትምህርት ነወ....... እኔ 9ኛ ነኝ>>ብሎ ከአፉ እንደጨረሰ ኬና እየተበሳጨ መጣ እና ሂከማ በ ተራዋ ለማየት ሄደች
<<ኬኖ ምነው ችግር አለንዴ>>አለው መስኡድ
<<መስኡድ ታምናለህ.....ሁለተኛኮ ነው የወጣሁት>>
<<እንዴ...... እንዴት ሆኖ ነው ሁለተኛ የሆንከው ምን አልባት ፖዪንት ሲሰሩ ተሳስተው ዪሆናል እንጂማ..... ለማንኛውም ተረጋጋ በቃ ብኋላ ሄደን እንጠይቃቸዋለን>>አለው
ሂኩም አይታ ተመለሰች እና እኔ ብቻ ቀረው እኔም ተነስቼ ወደ መምህሩ ሄጄ ውጤቴን ሳየው በጣም ደነገጥኩ እንዴት ይህን ወጤት ማምጣት ቻልኩ እያልኩ ወደ መቀመጫዬ አመራው እና ቀጭ አልኩ ግን ልክ እንደተቀመጥኩ ኬና ወደኔ ዞሮ ያወራኝ ጀመር
<<እ....ዱንያ ስንተኛ ወጣሽ>>አለኝ እኔ ግን ባመጣሁት ውጤት አፍሬ ዝም አልኩት ከዛ ሂክማ መስኡድ እና ዳጊም ወደኔ ዞረው <<ዱንያ ምን ይዘጋሻል ስንተኛ ወጣሽ ተናገሪ እንጂ>> ዪሉኝ ጀመር በጣም ሲያጨናንቁኝ
<<እሺ በቃ አትጩሁ ነግራችኋለሁ.......... እንዴት እንደሆነ አላውቅም ግን አንደኛ ነው የወጣሁት>>
<<ምን?????>>አራቱም በአንድነት የሰጡኝ በውስጡ ጥያቄ የያዘ መልስ ነበር።
እኔም ምመልሰው ግራ ሲገባኝ ዝም ብዬ አቀረቀርኩ ከዛ መስኡድ ማውራት ጀመረ <<ወላሂ እህቴ አኮራሽኝ የኔ ጀግና ኬናን ጣልሽው ማለት ነው ወላሂ ወላሂ ወላሂ በጣም ነው የኮራውብሽ።>> አለኝ ዳጊም ቀጠል አርጎ
<<ዋው እግዚያብሄርን ስርፕራይዝ ነው ያረግሽን ዱንያ እውነትም ጀግና ነሽ>>አለኝ እና ወደ ኬና ዞሮ <<ወይኔ ኬኖ ሀሀሀ ስንት ጓሮምሳን አንበርክከሽ አሁን በዱንያ ተበለጥሽ አ>> ብሎ በጣም ሳቀበት ኬናም ፈገግ ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳና ሂክማን አንዴ የሱ ቦታ እንድትቀመጥ ጠይቋት አጠገቤ ተቀመጠና በሹሹክታ እንዲህ አለኝ
<<ባንቺ በመበለጤ ምንም አልከፋኝም በጣም ነው ደስ ያለኝ እሺ የኔ ጎበዝ>> አለኝ በዚሁ መሃል ዳጊ ማውራት ጀመረ
<<ስሙ ጀለሶች 15 ቀን እረፍት አለን እየተባለ ነው እና ማሪያምን እኔ ከናንተ ጋር ሳላወራ 15 ቀን ማሳለፉ በጣም ነው የሚከብደኝ እና በቴሌግራም የአምስታችንን ግሩፕ ክሬት አርገን ለምን አናወራም>>
<<ቤስት አይዲያ ነው ወላሂ በቃ ኬኖ የግሩፓችን መሪ አንተ ስለሆንክ አንተ ክፈትልን>>
<<እሺ ግን የሂክማ እና የዱንያ ቁጥር የለኝም እኮ>>
<<እህ አሁን ተቀበላቸዋ........ እ ቺኮች ስጡት እና መታ በግሩፕ እናወራለን በቃ>> እሺ ብለን እኔና ሂኩም ስልክ ቁጥራችንን ለኬና ሰጠነው እና ተለያየን።

ማታ ላይ ግሩፑ ተከፍቶ ስለነበር ሁላችንም ስንጨዋወት ከቆየን ብኋላ ሁሉም ተኝተው እኔ እና ኬና ብቻ ኦንላይን ቀረን ከዛም ኬና ኢንቦክስ ያናግረኝ ጀመር
<<እኔ ምልሽ ዱንያ አንቺ የሰጠሽኝን መፃፎች አንብቤ ጨርሻለሁ በጣም ወድጃቸዋለሁ ሌላ መፃፍ የለሽም እንዴ?>>
<<አለኝ ግን ያው ትምህርትቤት ስለተዘጋ ኬት ተገናኝተን እሰጥሀለው ወይ ለምን አንድ አንድ ኢስላሚክ ቻናሎችን በቴሌግራም አትከታተልም>>
<<ደስ ዪለኛል በቃ ሊንካቸውን ላኪልኝኛ>> እሺ ብዬ የተለያዩ ኢስላሚክ ቻናሎችን ላኩለት አልፎ አልፎ የተለያዩ ዳውአዎችን እና ሀዲሶችንም እራሴው እየፃፍኩ እልክለት ጀምሪያለሁ።
በዚህም ምክኒያት ከኬና ጋር በጣም መቀራረብ ጀመርን ወሬአችን ከቴሌግራም አልፎ እስከ መደዋወል ደረሰ እረ እንደውም አንዳችን የአንደኛችንን ደምፅ ሳንሰማ መዋል ማደሩ ሞት መስሎ ይታየን ጀምሯል።
አሰፍ የኢንትራንስ ተፈታኝ ስለሆነ ሰሞኑን ቱክረቱ በሙሉ ወደ ጥናት ሆኗል አንድ አንዴ ቤትም አያዶርም ጓደኞቹ ጋር ሲያጠኑ ነው የሚያድረው።
በዚህም የተነሳ ከአሰፍ ጋር የነበረኝ የጓደኝነት ግኑኝነት እያነሰ መጣና ለአሰፍ የነበረኝን ቦታ ለኬና መስጠት ከጀመርኩ ቀናት ተቆጥረዋል
።
.
.
ሀሳብ አስታዬት ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

╔════•| ✿ |•════╗
 
#ክፍል_ስድስት (❻)
╚════•| ✿ |•════╝

➭
@sineislam
➭
@sineislam
3.1K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:20:44
'' ዱንያ ''

ክፍል አምስት ❺

ኬና የእውነት እምነት የለዉም ወይስ ምን አስቦ ነው እስልምናን ይቀበል ይሁን በእውነተኛ ታሪክ ላይ ይተፃፈ ታሪክ ኮሜንት ላይ ሀሳብ አስታዪታቹሁን አስቀምጡልኝ በክፍል አምስት ምን ይፈጠር ይሆን ማታ 2 ሰዓት ላይ ይጠብቁን ሼር ማድረግ አትርሱ

↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
ይቀላቀሉን⇊ ይቀላቀሉን⇊
https://t.me/sineislam
https://t.me/sineislam

share
3.5K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, edited  12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:28:26
➥. መውሊድ በዓለም ላይ ብዙ ሚሊየን ሙስሊሞች ያከብሩታል። አንዳንዶቹ አይቻልም ይላሉ።

➲. ስለ መውሊድ ብዙ ኺላፎች አሉ እናንተ ከየትኛው ናችሁ

አክባሪ ነኝ
አላከብርም
74 views hayu_smile , 05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:58:19 ስሜ ፊርዶስ ይባላል ። በጣም ቆንጆ ነኝ አልሃምዱሊላህ በዛላይ በጣም የሚስብ በፈገግታ አለኝ ።ብዙ ወንዶች ለፍቅር ጥያቄ ያቀርብልኛል ። እኔ ግን አላህን ፈሪና ታዛዠ ስለሆንኩ ፍቅር ምናምን የሚሉትን ነገር ፈፅም አልቀበለውም ።አሁን ድረስ ብዙ ወንዶች ያስቸግሩኛል ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ ያንን ቀን መቼም ቢሆን አረሳውም ።ጁመአ ቀን ነብር ከጓደኞቼ ጋር ተገናኝቼ ቀኑን ሙሉ ስደስት የዋልኩት አመሻሽ ላይ ሁላችንም ተሰነባብተን ተለያየን። ወደ ቤት እያመራሁ እያለ ያልጠበቁት ክስተት ተከሰተ በግምት ሰዓቱ ከምሽቱ 1:30 አከባቢ ይሆናል................ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ክፈት የሚለውን ይጫኑ ሀቂቃ ውሸት አይደለም





ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
161 viewsIbro Al-Amin , 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:24:24 ​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
            ".  
#ዱንያ  ".
         ፀሐፊ፦ ሂባ
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አራት ❲❹❳
╰───── • ❊ • ─────╯

{በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተፃፈ}

ዛሬ ትምህርት ከጀመርን 2 ወራትን አስቆጥረናል
ባለፉት ቀናት ውስጥ ከሁሉም የግሩፔ አባሎች ጋር ተግባብቻለሁ ሂኩዬ ሚስጥሮቼን የማጋራት ሁሉን ነገር የማማክራት ምርጥ ጓደኛዬ ሆናለች።
መስኡድ ደስ የሚል ልጅ ነው ሲታይ አወራሩ እና አለባበሱም ጭምር ዱርዬ ነገር ያስመስለዋል ግን እሱ በጣም የቀራ እና ኢማን ያለው እንዲሁም በዲኑ የማይደራደር ጓበዝ ልጅ ነወ።
ዳጊ ደግሞ እብድ ነገር ነው ትምህርት ቤት ራሱ ለፈተና ጊዜ ካልሆነ በስተቀር አይመጣም ምንም ጣጣ የሌለበት በራሱ ሙድ የሚኖር የለየለት ቀውስ ነገር ነው።
እና ኬና ደግሞ..........ኬኖ ደስ የሚል በሀሪ አለው ግን ቲኒሽ ቀበጥ ነገር ነው ቢሆንም በትምህርት እውነትም ልክ እንደተወራለት በጣም ጓበዝ ተማሪ ነው ሁሌም በፕሮግራም ያስጠናናል ያው ደግሞ እኔ ትምህርቱ ሳይገባኝ ቀርቶ ሳይሆን ከነሱ ላለመለየት ስል እሱ ሲያስጠናን እንዳልገባው ሰው ዝም ብዬ አዳምጠዋለው አስረድቶን ጨርሶ ገብቶሻል ሲለኝም አይ እዚህ ጋር አልገባኝም ብዬ እንዳልገባኝ እያስመሰልኩ ደግሞ እንዲያስረዳኝ እያረኩ እጫወትበታለሁ ሀሀሀ ያወቀብኝ ቀን ግን ጉዴ ነው የሚፈላው።
እና ሌላ ስለ ኬና ያልነገርኳችሁ ነገር ምን መሰላችሁ ኬና ሁሌም ከእጁ የማያጣት በሄደበት ሁሉ ይዧት የሚጓዘው በጣም የሚወዳት ካሜራ አለችው እና ካሜራ ማን ነው በዚህም ምክኒያት ብዙ ሴቶች ኬና ፎቶ አንሳኝ በሚል ሰበብ በጣም ዪቀርቡታል።
እሱም ሙስሊም ክርስቲያን ሳይል እንደፈለገ ከነሱ ጋር ይጨመላለቃል ይህን በሃሪውን ደግሞ በጣም ነው የምጠላው ግን ያን ያክል ቅርበት በመሃላችን ስለሌለ እስካሁን ምንም ነገር አልተናገርኩትም።

ከእለታት በአንዱ ቀን ታዲያ ከሰአት አንድ አሳይመንት ተሰቶን ስለነበር እሱን ለመስራት ሄደን ከዳጊ በስተቀር ሁላችንም ትምህርት ቤት ተገናኝተን እየሰራን ሳለን የአሱር ሶላት ደርሰ መስኡዴ የሶላት ሰአት ማሳለፍ ስለማይወድ <<ሰዎች ኑ እንስገድ እና ከዛ ተመልሰን እንጨርሰዋለን>> አለ ኬናም ቀጠለና <<ሂዱ ስገዱ በቃ>> አለን እኔ ግራ ተጋብቼ <<ኬና አንተ አትሰግድም እንዴ? >>አልኩት
<<አንቺ ልጅ ምን ነካሽ ....... ወሬሽን ተይ እና ነይ ተከተይኝ >>አለኝ እና መስኡድ ተነስቶ ወጣ ሂክማም ተከተለችው እኔ ግን ኬና የማይሰግድበትን ምክኒያት ሳላውቅ ከተቀመጥኩበት መነሳት አቃተኝ ዝም ብዬ እመለከተዋለሁ
<<እረ ዱንያ ፍቺኝ ሆሆሆ>>
<<ኬና ለምን አትሰግድም በአላህ ንገረኝ ማወቅ እፈልጋለሁ>>
<<ምን ያደርግልሻል ብነግርሽም አይጠቅምሾም እኮ >>
<<አይ ንገረኝ ይጠቅመኛል>>
<<እንግዲህ ከገገምሽ ምን ይደረጋል..... ዱንያ እኔኮ ሙስሊም አይደለሁም>>
<<ምን?.........ግን እኮ ኬና ኡመር አይደል እንዴ ስምህ እንዴት ሆኖ ነው ሙስሊም ያልሆንከው>>
<<እሱን በቃ ብኋላ አስረዳሻለው አሁን ግን ሶላት እያለፈብሽ ስለሆነ ነይ እስከ መስገጃ ቦታው ልሸኝሽ>> ብሎኝ ተነስተን ትምህርት ቤት ውስጥ ወዳለው መስገጃ ቦታ አመራን እኛ እዛ ስንደርስ መስኡድ እና ሂኩ ሰግደው ጨርሰው ነበር እና ኬና እነሱ ሄደው የቀሩትን የአሳይመንት ጥያቄ እንዲሰሩ እና እሱ ደግሞ እኔ እስክሰግድ ጠብቆኝ አብሮኝ እንደሚመለስ ነግሯቸው እነሱ ሄዱ እኔ ደግሞ መስገድ ጀመርኩ ኬና ደግሞ እኔ እስክጨርስ ቁጭ ብሎ ይጠብቀኝ ጀመር።

ሰግጄ ስጨርስ <<ተነስ ኬና እንሂድ>>አልኩት ኬናም
<<ቲኒሽ እንቀመጥ?>>ብሎ እንድቀመጥ ጋበዘኝ እኔም አላሳፈርኩትም ቲኒሽ ርቀት በመሃላችን እንዲሆን አድርጌ ተቀመጥኩ።
<<ታውቂያለሽ ዱንያ የኔ ህይወት ትርጉም አልባ ከንቱ ህይወት ነው እኮ>>
<<ለምን እንደዛ አልክ?>>
<<ያለ ምንም እምነት መኖር ምን አይነት ስሜት የሚኖረው ይመስልሻል?>>
<<ማለት አልገባኝም.......ቆይ ኬና እምነት የለኝም እያልከኝ ባልሆነ>>
<<አዎ የለኝም ሙስሊም ክርስቲያን ፕሮቴስታንት ኦርቶዶክስ ምንም አይደለሁም እኔ በቃ ልክ እንደ አንድ እንስሳ ነው የምቆጠረው አአአ?>>
<<አይ ግን ኬና እንዴት እንደዛ ሊሆን ቻለ?>>
<<አባቴ ሙስሊም ነው እናቴ ደግሞ ክርስቲያን ናት ሁለቱም ደስ እንዳላቸው ነው የሚኖሩት ለእምነታቸው ግድ የላቸውም ይገርምሻል በህይወታቸው ሁለቱም አንድም ቀን አባቴም መስጂድ ወስዶኝ አያውቅም እናቴም እንደዛው አንድም ቀን በህይወቷ ቸርች አልወሰደችኝም ሌላው ቀርቶ በቤታችን ውስጥ እንድም መፅሀፍ ቅዱስ እና ቁርኣን ራሱ የለም እና ንገሪኝ እስኪ የኔ እንዲህ መሆን የኔ ጥፋት ነው ብለሽ ታስቢያለሽ ወይስ የቤተሰቦቼ ጥፋት ነው?>>
<<በእውነቱ ኬና በወላጆች መፈተን በጣም ይከብዳል ግን አንተ ወዴትኛው ታደላለህ?>>
<<በክሽ ለኔ ሁሉም አንድ ናቸው ምንም ልዩነት የላቸውም>>
<<ስለ እስልምናስ ምን ያህል ታውቃለህ?>>
<<ምንም አላውቅም ስለ ዬትኛውም ሀይማኖት ምንም የማውቀው ነገር የለም>>
<<እሺ ማወቅስ ትፈልጋለህ?>>
<<አዎ እፈልጋለሁ በጣም ነው ማወቅ የምፈልገው>>
<<እሺ በቃ እኔ እረዳሃለው ኢንሻ አላህ ነገ አንድ አንድ ስለ እስልምና የሚያስተምሩ መፀሃፎችን ይዤልህ እመጣለሁ።>>
<<ደስ ዪለኛል እና ደግሞ አንድ ላሳይሽ የምፈልገው ነገር አለ ግን መጀመሪያ በፍፁም እንደማትቆጪኝ ቃል ግቢልኝ>>
<<አብሽር አልቆጣህም ምንድነው አሳ.........>>ብዬ ከአፌ ሳልጨርስ የኬና ስልክ ተደወለ
<<ወይኔ ዱንያ ቆየን መሰለኝ መስኡድ ነው እየደወለ ያለው>>
<<ተው አታንሳው ዪጮህብሃል ተነስ እንሂድ በቃ ነገ ታሳየኛለህ>>ብዬው ወደነ መስኡድ ጋር አመራን መስኡድም ቲኒሽ ከጮህብን ብኋላ አሳይመንቱን ሰርተን ወደየቤታችን ገባን።
.
.
ሀሳብ አስታዬት ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

╔════•| ✿ |•════╗
 
#ክፍል_አምስት (❺)
╚════•| ✿ |•════╝

➭
@sineislam
➭
@sineislam
2.3K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:40:01
'' ዱንያ ''

ክፍል አራት ❹

የእህትና ወንድም ፍቅር ትጠላላቹ ኡኡኡኡኡ በቅናት ልሞት ነው ብታዩ ሀሀሀሀ አስቲ ኮሜንት ላይ ሀሳብ አስታዪታቹሁን አስቀምጡልኝ በክፍል አራት ምን ይፈጠር ይሆን ማታ 2 ሰዓት ላይ ይጠብቁን

↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
ይቀላቀሉን⇊ ይቀላቀሉን⇊
https://t.me/sineislam
https://t.me/sineislam

share
3.1K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:59:12 ​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
            ".  
#ዱንያ  ".
         ፀሐፊ፦ ሂባ
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ሶስት ❲❸❳
╰───── • ❊ • ─────╯

{በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተፃፈ}

በመጨረሻም የግሩፓችን መሪ ተብዬው ማውራት ጀመረ
<>አለ
ቅድም መምህሩ የሀገራችንን ትልቅ ውጤት ያስመዘገበው ኬና ኡመር ሲል ሰምቼ ስለነበር የሀገራችንን ጂነስ ተብዬ ለማየት ካቀረቀርኩበት ቀና አልኩ እና ተመለከትኩት ቸኮሌት ከለር ያለው ፣ ፀጉሩ ተፈርዞ የተጠቀለለ ግን ሹሩባ ቢሰራ ከኔ ከሴቷ ፀጉር የሚበልጥ የሴቶችን ፀጉር የሚያስንቅ ውብ ፀጉር አለው ልጅ ነው በቃ ከዚህ በላይ ለማየት ድፍረት ስላጣው ተመልሼ አቀረቀርኩና የሚያወራውን ነገር ዝም ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ
<<እና ውዶች ፈታ በሉ.......ምንም ነገር ከከበዳችሁ ሳትፈሩ እና ሳትጨናነቁ ጠይቁኝ እኔ ሁሌም ልረዳችሁ ዝግጁ ነኝ>>አለ
<<እረ ብሮ ጣጣ የለሁም እኔ በበኩሌ የፈለኩትን ነገር ምንም ሳላንገራግር ነው የምጠይቅሽ>>አለ ዳጊ ሙሰኣብም ከዳጊ ቀበል አርጎ
<<ደግሞ የፈለጋቹትን ስትባሉ የፈተና መልስ ጠይቁ አሏችሁ እናንተኮ አታፍሩም>>ብሎ ሁላችንንም ፈገግ አስባለን
ከዛም መምህሮች ተራ በተራ እየመጡ ስለሚያስተምሩት ትምህርት አንድ አንድ ሀይላይት ሰተውን ወጡ።

ከሂክማ ጋር ደግሞ ተግባብተናል ደስ የምትል ጥሩ ልጅ ናት ደግሞ ሰፈሯም እኛ ሰፈር ስለሆነ ካሁን ብኋላ ትምህርት ቤት ስንመጣም ሆና ስንገባ አብረን ለመግባት ተግባብተናል።
ከትምህርት ቤት ስንለቀቅ ከሂክማ ጋር ወደ ቤት እየገባን ሳለን አሰፍን መንገድ ላይ አገኘነው
<<አስሰላሙአሌይኩም ማማዬ>> ብሎ አቀፈኝ ሂክማ ሰላምታውን መልሳ ከኛ ቲኒሽ ራቅ ብላ ቆማ ትጠብቀኝ ጀመር
<<ወአሌይኩም ሰላም አሱዬ ምሳ በላህ ወይስ እንደለመድከው ሳትበላ ነው የመጣህው>>
<<ማማዬ ካላንቺኮ ምግቡ አልበላ ሲለኝ በቃ ከትምህርት ቤት ስመለስ አብሬሽ እበላለሁ ብዬ ትቼው መጣው>>
<<ድሮስ መች አጣሁት ያንተን ስራ ቆይ ግን እስከመች ነው እንዲህ የምትሆነው>> ብዬ እነደማኩረፍ አልኩ
<<ውይ የኔ ልእልት ስታኮርፊኮ እንዴት ውብ እንደምቶኚ ማን በነገረሽ ሀሀሀ........ደገሞ ጓደኛ አገኘሽአ>>
<<አዎ ሂክማ ትባላለች አንድ ክፍል ነን ደግሞ እኛ ሰፈር ነው የምትገባው ካሁን ብኋላ እኔን መሸኘት አዪጠበቅብህም ከሷ ጋር እሄዳለሁ።>>
<<እሺ ማማዬ ረፈደብኝ እኮ ቻው በቃ>> ብሎ ግምባሬን ስሞኝ እየሮጠ ከአጠገቤ ሄደ እኔም ፈጠን ፈጠን ብዬ በመራመድ ወደ ሂክማ አመራሁ እና <<አፍወን በአላህ አቆምኩሽአ?>>አልኳት
<<እረ ችግር የለሁም ግን ምንሽ ነው........ማለቴ ካልደበረሽ ልትነግሪኝ ትችያለሽ?>>
<<እረ አብሽሪ ችግር የለሁም......አሰፍ ዪባላል ወንድሜ ነው >>
<<እስኪ ወላሂ በይ?>>
<<ወረቢ ወንድሜ ነው ምነው ችግር አለንዴ>>
<<እረ ምንም ችግር የለም........ግን ምናቹም አዪመሳሰልም እኮ ለዛ ግራ ተጋብቼ ነው>>
<<አዎ እሱ አባዬን ነው የሚመስለው እኔ ደግሞ እናቴን ነው የምመስለው ለዛ ነው>>
<<ወላህ በጣም ደስስ ትላላችሁ>> ብላ ስለራሷም አንድ አንድ ነገሮችን አጫወተችኝ እኔም ስለራሴ ነገርኳት እና ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን።

ቤት ገብቼ ምሳ ከበላሁ እና ለአያቴ ቡና ካፈላሁ ብኋላ ወደ ቂርአት ቤት አመራሁ ግን ብዙም ሳልቆይ ሆዴን እና ጀርባዬን ህመም ዪሰማኝ ጀመር በጣም ሲጠናብኝ ኡስታዛችንን አስፈቅጄ ወደ ቤት ተመለስኩኝ።

ከዛም ወደ ክፍሌ ገብቼ ተኛው አያቴ ለምን እንደተመለስኩ ስጠይቀኝ እንዲሁ ደብሮኝ ነው የተመለስኩት አልኳት <<እእ...ደብሮኝ ነው ነው ያልሽኝ.....ሆ ጉድ እኮ ነው የዘመኑ ልጅ ውሃ ቀጠነ ብሎም ዪደብረዋልኮ በይ እንግዲ ያ ወንድምሽ እስኪመለስ ድረስ ተኚ እና እሱ ሲመለስ ውጪ አውጥቶ ያዝናናሽ>> ብላኝ ወጣች እኔም በጣም እያመመኝ ስለነበር እንቅልፍ ቶሎ አልወሰደኝም ቢሆንም በመጨረሻ ተኛው።

<<ማማ......ማማዬ>>እያለ አንድ ሰው ፀጉሬን መደባበስ ጀመረ በስንት መከራ አይኔን ከፍቼ ስመለከተው አሱዬ አጠገቤ ተቀምጧል
<<አሱዬ መጣክ እንዴ>>ብዬ ጭንቅላቴን ከትራሴ ላይ አንስቼ የሱ እግሮች ላይ ተኛው እሱም ፀጉሬን እየዳበሰ <<ምን ሆንሽብኝ ማማዬ...... ታቲዬኮ ደበረኝ ብላ ተኝታለች አለችኝ ምን ሆነሽብኝ ነው የደበረሽ?
በነገራችን ላይ ታቲዬ ማለት አያቴ ናት ታቲ እያልን ነው የምንጠራት
<<አዎ ቲኒሽ ደብሮኛል እና ደግሞ እያመመኝም ነው>>
<<ምንሽን በአላህ?........ተነሺ በቃ ሀኪም ቤት እንሄዳለን.......ቆይ እንደውም እኔ ልሸከምሽ>>
<<እረ አሱዬ አረጋጋው ሀኪም ቤት መሄድ አያስፈልግም ሀይድ ላይ ነኝ ለዛ ነው ያመመኝ>>
<<ኦ...እንደዛ ነው እንዴ........እሺ ታዲያ ምን አባቴ ላርግልሽ ማማዬ>>
<<ምንም አልፈልግም አሱዬ ምንም አታርግልኝ>>
<<እሺ ሞዴስ አለሽ?>>
<<አዎ አለኝ ግን አይበቃኝም>>
<<እሺ በቃ እዚሁ ጠብቂኝ ገዝቼ እመጣለሁ>>ብሎኝ ወጣ እና 10 ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ መአት ነገር ገዝቶ ተመልሶ መጣ የያዛቸውን እቃ ስንመለከት እኔ እና ታቲዬ ሆዳችንን እስኪአመን ድረስ ሳቅንበት
<<አንተ ሰውዬ አራስ የወለደች ሴት ለመጠየቅ የመጣ ሰው ነው እኮ የምትመስለው......ሞዴሱስ ይሁን እሺ ለስላሳው ጁሱ እና ሙዙስ ለምን አስፈለገ? ሀሀሀ>>
<<ታቲዬ ደሞ ለምን ታካብጂያለሽ ለ እህቴ ከዚህ በላይ ራሱ ብገዛላት ሲያንስባት ነው እኮ>>
<<ለማንኛውም እኔን በጣም ደስ ብሎኛል አምጣ እስኪ አቀብለኝ>>ብዬ ተቀብዬው ሁላችንም በልተን ከጠጣን ብኋላ ከአሱዬ ጋር ወክ ወጣን እና አመሻሽ ላይ ወደ ቤት ተመለስን።.
.
.
ሀሳብ አስታዬት ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

╔════•| ✿ |•════╗
 
#ክፍል_አራት (❹)
╚════•| ✿ |•════╝

➭
@sineislam
➭
@sineislam
3.9K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:43:47
'' ዱንያ ''

ክፍል ሶስት ❸

በክፍል ሶስት ምን ይፈጠር ይሆን ማታ 2 ሰዓት ላይ ይጠብቁን

↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
ይቀላቀሉን⇊ ይቀላቀሉን⇊
https://t.me/sineislam
https://t.me/sineislam

share
4.2K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, edited  08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ