Get Mystery Box with random crypto!

ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙

የቴሌግራም ቻናል አርማ sineislam — ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙 ኢ
የቴሌግራም ቻናል አርማ sineislam — ኢማን 🌙тυℬℰ™🌙
የሰርጥ አድራሻ: @sineislam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.09K
የሰርጥ መግለጫ

<< `በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።` >>
ሱረቱል ዐስር፦(1፥3)
For comment an& cross
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
@Alhamdulilah25

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 82

2022-07-16 17:54:00 ጥያቄ

➠ ለ ንብ {bee} ካልን
➠ለ ዝንብ ___???

መልሳቹን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ
677 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 17:49:31 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ ዘጠኝ)
.
.
ከጁምዐ መልስ ምሳችንን እዛው ፒያሳ ከተመገብን በኋላ ወደ ኮልፌ አቀናን። ጋሼ ባለፈው ስንመጣ ያሳዩኝን ቦታዎችና ታሪኮች እየጠየቁኝ ጨዋታችን ሳይገታ መንገዱን አገባደድነው። እዛ ስንደርስ የተሰጠንን አድራሻ እያፈላለግን ቤቱን ካገኘነው በኋላ ማንኳኳት ጀመርኩ።
"ማነው?..." የሴት ድምፅ ከውስጥ መለሰልን። ወደ በሩ ጠጋ ብላ መቆሟ በበሩ መስታወት ይታያል።
"አሰላሙ ዐለይኩም.... አብዱረዛቅን ፈልገን ነበር።"
"አብዱረዛቅ?.... አብዱረዛቅ?.... አ....አይ ተሳስተዋል.... መሰለኝ....እዚ እንደሱ የሚባል ሰው የለም።" መለሰችልን።
"ኦ... አፍወን በጣም..." ከበሩ ላይ መለስ ብዬ ጋሼን ግራ በመጋባት ተመለከትኳቸው፤ አድራሻው ይሄ መሆኑን እርግጠኛ ነበርን። ወደ ጊቢው በር እያመራን እያለ አንድ ትንሽ ልጅ የተወሰኑ እቃዎችን በፌስታል ይዞ ወደ ጊቢው ገባ።
"ባባ.... የነአብዱረዛቅን ቤት ታውቀዋለህ እንዴ? እዚ ጊቢ ነው?"
"አቡ የኔ ወንድምን ነው?" ግራ ተጋብቶ ጠየቀኝ። ጥያቄው ያስቃል....
"አብዱረዛቅ ነው የወንድምህ ስም?" የስም መመሳሰል እንዳይሆን ተስፋ እያደረኩ ጠየኩት።
"አዎ.... ግን ቤት የለም፤ ሱቅ ነው። ልጥራላቹ?"
"አዎ ቶሎ በል..." ምላሼን እንደሰማ እየሮጠ በመጣበት ተመለሰ። ጋሼ መኪናው ውስጥ እንደሚጠብቁኝ ነገረውኝ ወጡ.... የጥበቃ ነገር ያደክማቸዋል። ብቻዬን ጊቢው ውስጥ እንደቆምኩ የላኩት ልጅና አንድ ወጣት አብረው ወደኔ ተመለሱ። ሰላምታ ተለዋውጠን እሱ መሆኑን ካረጋገጥኩ በኋላ ራቢያን ያውቃት እንደሆነ ጠየኩት፤ ትውውቃቸው ከእህቱ ጋር መድረሳ መሆኑን አስረዳኝ...
"እና ቤት እንግባና አረፍ በላ...." ወደ ቤቱ ጋበዘኝ። እኔም ገንዘቡን መንገድ ላይ ቆሜ መስጠቱ ምቾት አልሰጠኝም ነበር።
"ቅድም ስመጣ የናንተ ያንኛው ቤት መስሎኝ ተሳስቼ ነበር...." የሆነውን እየነገርኩት ተከተልኩት።
.
"ሃሃህ.... እና የሚባል ሰው የለም አለችህ.... ወይ እቺ ልጅ። አፉ በለኝ ታላቅ እህቴ ናት የምትሆነው፤ ትንሽ ትረሳለች..." ሳቅ እያለ ቤቱ ጋር ደረስን። ብትረሳ ብትረሳ እንዴት የወንድሟ ስም ሊጠፋት እንደሚችል አልገባኝም። ካንኳኳ በኋላ ድምፁን ስትሰማ ከፈተችለት።
"አቡ.... ቆየህ እኮ፤ ደግሞ ኢምሩ የት ሄዶ ነው? ድንገት ስፈልገው የለም... ለአባዬ ልነግረው ስደውል ደግሞ ስልኩ አይሰራም።" ጥያቄውን ደራረበችበት፤ የተጨነቀች ይመስላል። ትከሻዋን ደገፍ አድርጎ እንዳቀፋት አልጋው ላይ አስቀመጣት። ቤታቸው አንድ ክፍል ብትሆንም አልጋና ፍራሽ ተሟልቶባታል።
"ሱቅ ልካኝ ነው አቡ...." የገዛውን እቃ አስቀምጦ ከጎኑ ተቀመጠ። አብዱረዛቅ አንዴ ለሷ አንዴ ደግሞ ለወንድሙ ሲመልስ ቆየ። ዝብርቅርቁ ህይወታቸው እየደነቀኝ ቆሜ መታዘብ ጀመርኩ.... ትንሽ ረጋ ሲሉ ከማስጨንቀው ደጅ እንደምጠብቀው ነግሬው ወጣሁ።
*
"አፍወን በጣም.... ሃሊማ አልዛይመር ስላለባት ነው። ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰባት ሄዶ አሁን የምትረሳበት ጊዜ ከምታስታውስበት በልጧል። ራሷን ወደመርሳት እንዳትሄድ መድሃኒቶቿን እየተከታተልን ነው... ግን እኔንጃ። ብቻ አላህ ይጨመርበት።" ደጅ ላይ ከወጣ በኋላ ያስረዳኝ ጀመር፤ ሁኔታው በጣም ያሳዝናል።
"3ታቹ ብቻ ናቹ?"
"አዎ.... 5 አመት ሆነን አባዬ ካረፈ። 3ቱን አመት ሃሉ ራሷ ነበረች እየሰራች የያዘችን፤ አሁን እሷ ስለባሰባት ሱቁን የያዝኩት እኔ ነኝ።"
"ኸይር አላህ ያሽራት አብሽሩ። ራቢ ይሄን እንድሰጥህ ነበር የላከችኝ... ውስጡ መልዕክትም አለው።" ፖስታውን አውጥቼ ሰጠሁት። ገንዘቡን ካየ በኋላ ፊቱ ላይ ያለው መደንገጥ ያስታውቃል.... ሳይመልስልኝ በፊት መልዕክቱን አውጥቶ ማንበብ ጀመረ። አይኖቹ በእምባ ሲሞሉ.... እንዳይፈሱ ሲታገላቸው ተመለከትኩት። አንብቦ ሲጨርስ ማንበብ እችል እንደሆነ ጠየኩት... ሰጥቶኝ ፊቱን አዙሮ ሰማይ ሰማዩን መመልከት ጀመረ።
.
<<አሰላሙ ዐለይኪ ሃሉ.... ራቢ ነኝ፤ አልረሳሽኝማ በአላህ? ወደ አዲሱ ሰፈራቹ ከገባቹ በኋላ እግር የቀነስኩት ረስቼሽ አይደለም፤ ወላህ ሃጃዎች አጨናንቀውኝ ነው። መቼስ ረመዳን ሲባል ለኔ ካንቺ ጋር ያሳለፍናቸውን ብዙ ትዝታዎች ይዞብኝ እንደሚመጣ አይጠፋሽም አይደል? <ለይለተል ቀድርን ከአላህ ምንዳ እንደሚያገኝ አምኖ የቆመ ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።> የሚለውን ኡስታዝ የነገሩን አመት ላይ 27ኛውን ለሊት ሙሉውን ከሰማይ ላይ የሚወርድ ኮከብ ያለ ይመስል ሰማዩን በመመልከት ስንጨርሰው ይዝ ይልሻል? ሱሁርን እየደወልኩ ስቀሰቅስሽ <በለሊት ደውለሽ አባ ጮኸብኝ> በሚል በማግስቱ ኪታቤን ይዘሽ ቀርተሽ ያስቆጣሽኝ ትዝ ይልሻል? ተራዊህ እንድንሄድ ስጠራሽ <ሱና ነው ለዊትሩ እንደርሳለን...> እያልሽ ስታስረፍጂብኝ ትዝ ይልሻል?.... ረመዳን ካንቺ ጋር የማሳልፈው ውብ ጊዜም ጭምር ነበር። ድሮ ለዒባዳ ብዙ ጊዜ ነበረን፤ እውቀቱ ግን አልነበረንም። ስናድግ ደግሞ ትውስታ ለመፍጠር የሚትረፈረፍ ቀርቶ ጥቅሙን አውቀን ለምንሳሳለት ዒባዳም ጊዜ አጠረን። ሃሉ.... ገንዘቡ ያን ያህል ባይሆንም፤ ለነኢምሩ ወጪ ከመጨነቅ ገለል ብለሽ ጊዜሽን በቁምነገር ለዒባዳ የምታውይው አድርጊው። ለአጎቴና ለአክስቴም አላህ የጀነት እንዲሆኑ የምትለምኚበት አድርጊው። ለአቡ ያስላኩት አምና ገንዘብ መያዝ ላይ ካንቺ የተሻለ እንደሆነ ስላየሁት ነው፤ አንቺም ለጤናሽ ሲባል መጨናነቅ የለብሽም። አልፎ አልፎ የምትረሺው ነገር ፆምሽን ቢያስተጓጉለውም ባስታወስሽ ሰዐት ቀጥዪ..... ነቢዩ {ሰ.ዐ.ወ} :- <ከናንተ አንዳችሁ መፆሙን ረስቶ ከበላ ወይም ከጠጣ ፆሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።> የሚለውን ከተማርን ጀምሮ 'አላህ እኔን ብቻ በቀን 3ቴ የሚያበላው ነገር ነው የሚገርመኝ' እያልሽ ታስቂን እንደነበረው..... ሃሃህ እንደዛ ጊዜው ፆምሽን እየጨረስሽ አላህን ምህረቱን ለምኚው። አፊያሽንም ለምኚው። ደግሞ ሙስዐብን አየሽው? ድሮ ካለምነው ጋር ይመሳሰላል አይደል? ካንቺ ጋር በስንቱ መበሻሸቅ እንደናፈቀኝ ባወቅሽ.... ወላህ እወድሻለሁ። በቅርቡ በአካል እስክዘይራቹ ለኔም ለሙስዐብም ዱዐ አድርጊልን። ወሰላሙ አለይኪ ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።>>
.
.... መልዕክቱ እዛ ጋር ያበቃል። የነበራቸውን ቅርርብ እሷ ካለችው ብቻ በመገመት አሳዘኑኝ፤ ያን ሰላማዊ የልጅነት ህይወት ሃሊማም እንደሚናፍቃት አልጠራጠርም። ችግሩ እንኳን ራቢን የገዛ ወንድሟን ሙሉ ስምና የአባቷን ማረፍ እንኳን አታስታውስም። አብዱረዛቅ ሲዞር እምባዎቼን ጠራርጌ ወረቀቱን መለስኩለት።
"አይዟቹ ያልፋል ኢንሻአላህ፤ ይሻላታል..."
"ኢንሻአላህ.... አላህ ጀዛቹን ይክፈልልኝ፤ ለኔም ለሃሉም በጣም የማይረሳ ውለታ ነው። ደግሞ አብሽሪ እቺን ቀውስ እንዴትም ብዬ እንድታስታውስሽ አደርጋለሁ በላት። ከዱዐችን አትጠፉም..." ፈገግ አለልኝ።
"ሹክረን.... እና የባንክ ሂሳብ አለህ?"
"አዎ አስገባዋለሁ አሁን ስወጣ ኢንሻአላህ..."
"አቡ.... ና ምን ትሰራለህ ደጅ?" የሃሊማ ጥሪ ከውስጥ ይሰማል። አቡን ደጅ ላይ አቁሜ ሁለት ልብ ያደረኩት መሰለኝ።
"መርሃባ.... መሄዴ ነው በቃ፤ ኢምሩን ሰላም በልልኝ.... ወሰላሙ አለይኩም" ተሰናብቼው ወደ መኪናዋ አቀናሁ።
.
.
ይቀጥላል...⓴

@sineislam
622 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 17:48:35 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ ስምንት)
.
"ቀጣዩ ቤት ወዴት ነው?" ጋሼ የሸይኽ አህመድን ባለቤት ተሰናብቼ ወደ መኪናው ከተመለስኩ በኋላ ጠየቁኝ። ወደአኼራ መሄዳቸውን ነግሬአቸው ለደቂቃዎች መኪናውን የሃዘን ድባብ ወርሶት ነበር። ቀጣዩን ፖስታ ከፍቼ ተመለከትኩት...
"ኮልፌ ይላል ጋሼ..."
"አዪ ተመልሰን እዛ ልንሄድ?... ባለፈው ሙዐዝን ልናገኝ ስንል በዛው አድርሰን መምጣት እንችል ነበር።"
"ኦ አፉ በሉኝ ጋሼ። ፖስታዎቹን ቀድሜ አይቼ አንድ ሰፈር የሆኑትን አንድ ላይ የማስተካከሉ ሃሳብ አልመጣልኝም ነበር... እና እንዴት ይሻላል? ሰግደን እንሂድ ወይስ..."
"አዎ እንደዛ እናድርግ እንጂ። መንገድ ከጀመርንማ እዛ እስክንደርስ ያልፈናል... እዚሁ በኒ መስጂድ እንግባ።"
"መርሃባ እሺ። ለጁምዐ ገና ብዙ ይቀረዋል.... እስከዛ ወይ ቁርዐኖቹን እንግዛና እዚሁ እንስጣቸው።"
"ይቻላል..." መኪናውን ከቆመበት አስነሱት።
*
ቁርዐኖቹን ከገዛዛን በኋላ ወደ ኑር (በኒ) መስጂድ አቀናን። እንደሁሌው ከሰጠናቸው በኋላ ለኛም፤ ለሸይኽ አህመድም ዱዐ እንዲያደርጉልን ጠየቅኳቸው። ስንጨርስ ወደ መስገጃ ቦታችን ተመልሰን ሱረቱል ካህፍን መቅራት ጀመርን። ጋሼን በግድ አብረውኝ እንዲቀሩ ገፋፍቻቸው.... ሲሳሳቱ እያረምኳቸው ጎን ለጎን እየቀራን ቆየን። በስተመጨረሻም የጁምዐው ሁለተኛ አዛን ከተሰማ በኋላ ኹጥባ መደረግ ተጀመረ። ለረመዳን ጥቂት ቀናት ብቻ ስለቀሩት ኹጥባቸው ያንን ያማከለ ነበር...
.
"....እንደምታውቁት ያለንበት የሻዕባን ወር ወደ ማብቂያው እየደረሰ ነው፤ ቀጣዩን የበረካ ወር ልንደርስበት የቀናት ጊዜ ብቻ ቀርተዋል። ረመዳን ሲባል በኛ ዘመን የሌላ ዕምነት ተከታዮች እንኳን እየሳሉን እንደመጡት 'ለሊት ሙሉ ሲበላ የሚታደርበት ወር' ወደ መሆን እየመጣ መሆኑ ያስፈራል። የምግብ አይነት ሽታ ከየቤቱ እየወጣ መግሪብ ሲደርስ ሰፈሩ ሁሉ ሬስቶራንት ይመስላል። ኸይር... 'አንብላ ልትለን ነው እንዴ ታዲያ?' እንድትሉ አይደለም፤ መብላቱ አይከፋም አልሃምዱሊላህ። ግን ቢያንስ የመተሳሰብ ወር ነውና በዙሪያችን ያለ ሌላ ወንድማችን ጠግቦ ማደሩን ሳናረጋግጥ የምግብ አይነት የምናማርጥበት አይሁን ለማለት ነው። ከዚ ጋር ተያይዞ ብዙ ጊዜ የምናውቃት የሃቢቡና {ሰ.ዐ.ወ} ንግግር አለች:- <ሙዕሚን ማለት ጎረቤቱ ተርቦ እያደረ ለራሱ ጠግቦ የሚያድር አይደለም።> አይደል? መጪውን ወር ይህችን ቃል በተግባር የምንኖርባት እናድርጋት።" አነጋገራቸው ረጋ ያለ ከመሆኑ ጋር ቀልብ ይስባል፤ እንቅልፍ ጥሎት ይሄ ንግግር የሚያልፈው እንዳይኖር በልቤ ተመኘሁ።
.
"አሁን አሁን አልሃምዱሊላህ የተወሰኑ ጀመዐዎች አቅም የሌላቸውን ደጉመው አጅር ለማግኘት በዚህ ሰዐት እየተሯሯጡ ይገኛሉ፤ በተግባርም በሚድያዎችም እርዳታዎችን ሲያሰባስቡ እንመለከታለን ማሻአላህ። ሌሎቻችን ግን የቱ ጋር ነን የሚለውን አሁንም ራሳችንን መፈተሽ ይፈልጋል። የባንክ ሂሳባችን ላይ ስንትና ስንት ሺ ገንዘብ ተከምሮ የተቸገረ ወንድማችን ገንዘብ ሲጠይቀን ነፍሲያችን ጥብብ ትላለች፤ 'ከዛፍ ላይ አይደለም ያገኘሁት የምበትነው' የምንል ብዙዎች አለን። ሳህ ከዛፍ አይደለም.... ካንተም ሃይልና ጥበብም ግን አይደለም ያ ሪዝቅ የተገኘው፤ አላህ አስፋፍቶ ከፍቶልህ ቢሆን እንጂ። አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሃዲስ የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} ምን ብለዋል:- <የሰው ልጆች የሚያገኙት አንድም ቀን የለም፥ በዚያ ቀን ሁለት መላዕክት (ከሰማይ) የሚወርዱ ቢሆን እንጂ። አንደኛው:- <አላህ ሆይ! ለመፅዋች ምትክን ለግሰው> ሲል፥ ሌላኛው:- <አላህ ሆይ! ለንፉግ ጥፋትን አውርድ> ይላል።>.... በመሰሰት ውስጥ ነው እንደውም ያን ሪዝቅ የምትከለከለው። ንፉግ ሰው አይደሰትም፤ ምክኒያቱም አላህ ከሰጠው ኒዕማ ላይ በረካውን ያነሳበታል። ያ ገንዘብ ከሞት በኋላ አይከተለውም፤ ከሞተ በኋላም ዳግም ይከስራል ማለት ነው።
.
"ገንዘባችንን ለኸይር እናውለው ኢኽዋኒ፤ ገንዘብ ዱንያ ላይ ዘላቂ ደስታን አይገዛም.... ለአላህ ብለን ስናውለው ግን አጅርን ይገዛል፤ የአላህን መሃባ ይገዛል፤ የልብን መረጋጋትን ይገዛል። ግን ገንዘብ የለንም ማለት እነዚህን ነገሮች መግዛት አንችልም ማለት አይደለም፤ ባለን አቅም እኛ የወደድነውን ለወንድማችን በማድረግ መግዛት እንችላለን። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ}:- <እናንተ ሙስሊም ሴቶች ሆይ! የፍየል ሸኮናን የሚያክል አነስተኛ ነገር ቢሆንም እንኳ ጎረቤት ለጎረቤቱ (ስጦታ) ማበርከትን አትናቅ።> ነበር ያሉት። በዙሪያችን ያሉትን እስኪ ልብ እንበላቸው። አመቱን ሙሉ ፆሞ እያደረ ነው ረመዳን የደረሰበት? እኛ የምንሰራው ጣፋጭ ምግብ ሽታ ረሃቡን እያባባሰበት ነው? የያዘቻቸው አይታም ልጆች በኛ ልጆች መታደል ቀንተው እያለቀሱባት ነው? እኛን ለመጠየቅ ሃያዕ ይዟት እየተቸገረች ነው? ኑሮአችንን እንፈትሸው። ረመዳን ሲመጣ አምና ቤቱ ድል ባለ ፊጥራ የጋበዘንን ባለሃብት ሳይሆን ከጎናችን የተቸገረ ወንድማችንን ጠርተን እናስፈጥረው። <ፆመኛን ያስፈጠረ ፆመኛው ያገኘውን ያህል ምንዳ እርሱም ያገኛል። ይህ ሲሆን ግን የፆመኛው ምንዳ ቅንጣት ሳይጎድልበት ነው።> ብለውናል ሃቢቡና {ሰ.ዐ.ወ}። ለሌላ ሰው ዘካ የሚወጅብባቸውን እንግዶች ለማስተናገድ እየተሯሯጥን ደጃችን ላይ ፌስታል ይዞ ለቆመው ሚስኪን ለአይናችን የጠላነውን ትራፊ አንዘርግፍለት፤ ወስዶ ከልጆቹ ጋር ቀናትን ሊመገበው ጓጉቶ ይሆናል። አላህ ዘንድ የሱ እምባ ወይስ የወዳጆቻችን ሳቅ፤ የቱ በላጭ እንደሆነ አናውቅም።" ሸይኹ ንግግራቸውን ቆም አድረገው ተመለከቱን፤ የጥፋተኝነት ስሜት ያነበቡብን ይመስላል። ቀጠሉ...
.
"እሱ ቢቀር ጎረቤቶቻችን እየሰራን ሲመጡብን ፊታችንን አናጥፋ ወንድሞቼ... እንዲያውም ባለን በዛ አርገን ሰርተን ራሳችን እንጥራቸው። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} <መረቅ (ሥጋ) በቀቀልክ ጊዜ ውሃውን አብዛ፤ ከዚያም የጎረቤቶችህን ቤተሰቦች አስተውል (አቋጥር)፤ አንዳችን በጎ ነገርም (ማባያንም) ላክላቸው> በማለት ኑዛዜ ነግረውኛል ሲሉ አቡዘር (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል። ጎረቤት በሚል ስንጠራም ደግሞ ከጎናችን የሚኖረው ከኛ ያነሰ ኑሮ እየገፋ በመሆኑ ንቀነው አስፋልት ተሻግሮ ያለን የሌላ እምነት ተከታይ፤ በሙያችንና በመስተንግዷችን ለመደነቅ ስንል አንጥራ። እናታችን ዓኢሻ(ረ.ዐ) <የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} ሆይ! ሁለት ጎረቤቶች አሉኝ፤ ወደ የትኛው (ዋ) ስጦታ ልላክ> ብላ በጠየቀቻቸው ጊዜ <በራፉ (ቤቱ) ላንቺ ይበልጥ ቀረብ ወዳለው> በሚል ነበር የመለሱላት። ሰደቃ ስለነፍሲያችን መደሰት አይደለም፤ አላህን ስለማስደሰት ነው.... ጥንቃቄን ይፈልጋል። አላህ ሸይጧን በሚታሰርበት በዛ ወር ነፍሲያችንን አሸንፈን መልካም ስራችንን የምናበዛ ያድርገን። ወር ሙሉ በግድየለሽነታችን የጎረቤቶቻችን እምባ ሰበብ ከመሆን አላህ ይጠብቀን። ወሰለላሁ ወሰለም አላ አሽረፊል ኸልቂ ሰዪዲና ሙሃመዲን ወዐላ አሊሂ ወሷህቢሂ ወመን ዋላሁ ቢኢኽላሲን ኢላ የውሚ ዲን።" አማርኛውን ኹጥባ በዚሁ አጠናቀው የተዘጋጀላቸው ወንበር ላይ ተቀመጡ። ሌሎቻችንንም ያሉትን ወደራሳችን ወስደን የማስተንተን በሚመስል ዝምታ አረብኛው ኹጥባ እስኪቀጥል መጠባበቅ ያዝን።
.
.
ይቀጥላል...❶❾

@sineislam
441 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:38:03 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ ሰባት)
.
.
ስድስተኛ ቀን.... እለቱ ጁምዐ በመሆኑ ከሌላው ቀን በበለጠ ደስታ ተሰምቶኛል። ከጋሼ ጋር የጠዋት ጉዞአችን ተጀምሯል፤ ፊታቸው ከትናንቱ ዛሬ ፈካ ያለ ፈገግታ ይታይበታል። ሁለታችንም በለበስናቸው ጀለቢያዎች መኪናው ዒድ መስሏል።
"እና የመጀመሪያው ቤት የት ነው አልከኝ?" ትንሽ እንደራቅን ጠየቁኝ።
"ሱማሌ ተራ ይላል..."
"ኦ ፒያሳ.... ከተማ ነው የምንውለዋ ዛሬ..."
"ሃሃህ መሆኑ ነው። ሸይኽ አህመድ ሷሊህ ይላል ስማቸው.... ያውቋቸዋል?"
"እንዴ እንዴ እንዴ....አዎ!..... በቅርበት ባይሆንም ግን የድሮ ሰፈራችን ያሰግዱ የነበሩ ኢማም ናቸው። እኔ ወደዛ እግር ስለማላበዛ እንጂ የማያውቃቸው አልነበረም። ባይገርምህ ልጆቻችንን ሁሉ ያስቀሩት እሳቸው ናቸው..." ስለሳቸው ሲያወሩ ፊታቸው ላይ ትልቅ ደስታ ይነበባል።
"ኧረ... ማሻአላህ፤ ዛሬ የተሟላ ጁምዐ ሊሆንልን ነዋ።" ፈገግታቸውን ተጋራኋቸው። ስለሳቸው የሰሙትንና የሚያውቁትን እያጫወቱኝ፤ እኔም በአካል ላገኛቸው እየጓጓሁ ወደ ፒያሳ አቀናን።
.
በጠዋት ስለወጣን 3 ሰዐት ሊሆን አካባቢ ወደ ተሰጠን አድራሻ ደረስን። ከጥቂት መምታታት በኋላ ሰዎችን ጠይቀን ቤቱን አገኘነው.... የዝናቸውን ያህል የተንደላቀቀ መኖሪያ የላቸውም። የጊቢያቸውን በር ከጎረቤቶቻቸው አንዱ ከከፈተልን በኋላ የሳቸው ወደ ተባለው ቤት አምርተን ማንኳኳት ጀመርን።
"ማነው?" የሴት ድምፅ ከውስጥ መለሰልን...
"አሰላሙ ዐለይኩም፤ ሸይኽ አህመድን ፈልገን ነበር.... ቤት ይኖራሉ?" ጥያቄዬን ሰነዘርኩ። አሉምም የሉምም ሳትለን ለደቂቃዎች በሩ ላይ ከቆምን በኋላ ከፈተችልን። ፊቷ በኒቃብ የተሸፈነ ቢሆንም በሩን በመጠኑ ብቻ ገርበብ አርጋው በከፊል እንደሸፈናት ቆመች።
"አፍወን.... ምናቸው ነህ የኔ ልጅ?" ድምጿ የትልቅ ሴት ይመስላል፤ ልጃቸው.... እህታቸው ወይስ ባለቤታቸው ትሁን ለመለየት አይቻልም። ልጇ እንደምሆን ከገመተች ለአክብሮቱ እኔም በአንቱታ መመለሱን መረጥኩ...
"መልዕክት እንድሰጣቸው ተልኬ ነው፤ ራቢያ ናት.... እኔ ደግሞ ባለቤቷ ነኝ።"
"ራቢያ..... አላወኳትም።" ግራ በመጋባት መለሱልኝ።
"ሸይኽ አህመድ የሚያውቋት ይመስለኛል.... በጊዜ ይመጣሉ?"
"አ....አይ አይመጡም። ማለት... ወደአኼራ ሄደዋል..... 3 ሳምንት አለፋቸው። ከሁኔታህ አለመስማትህን ስለተረዳሁ ነበር ምናቸው መሆንህን የጠየኩህ...." በማመንታት መለሱልኝ። ከንግግራቸው ጋር ልቤ ትርትር ያለ መሰለኝ። ለደቂቃዎች የማውቀው ሰው መርዶ የተነገረኝ ይመስል ደርቄ ቀረሁ። ራቢን ምን ልላት ነው? ቅርርባቸው ምንን ያህል ይሆን? ታመው ይሆን ይሞቱት? ወር ቀድሜ ይሄን ስራ ብጀምር የሚድኑበት አጋጣሚ ነበር ይሆን?
"አፍወን.... በጣም ይቅርታ። አላህ ሶብሩን ይስጦት.... በጣም ታመው ነበር?"
"አሚን... ኧረ አብሽር ችግር የለውም። የቆየ አስም ነበረባቸው፤ እሱ ነው ከሌሎች ህመሞች ጋር እያደከማቸው የሄደው።" ሲመልሱ ረጋ እንዳሉ ነው፤ ሃዘኑን የተቋቋሙት አልያም የወጣላቸው አይነት መሆኑ ያስታውቃል።
"አላህ የጀነት ያርጋቸው.... ራቢያ ይሄን መልዕክት ልካላቸው ነበር፤ ልጆች አሏቸው እንዴ? ከሆነ ለነሱ መስጠቱ ይሻላል።"
"እኔ ባለቤታቸው ነኝ። የአራት አመት እና የሁለት አመት ህፃናት ናቸው ያሉን። እኔ መቀበል እችላለሁ?" ጠየቁኝ። ከጋሼ እንደተረዳሁት እድሜአቸውን ለዲን ዕውቀት ብቻ ያዋሉ ነበሩ፤ ዘግይተው አግብተው ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ።
"ይቻላል...." ፖስታውን አውጥቼ ሰጠኋቸው። "ውስጡ ከራቢ የተላከላቸው መልዕክት ጭምር አለው...." እያቀበልኳቸው አከልኩበት።
"እንዴት ይሻላል ታዲያ? እኔ የዚ አካባቢ ሰው አይደለሁም.... አማርኛ መናገር እንጂ መፃፍና ማንበብ አልተማርኩም" ካርዷን አውጥተው አገላብጠው እየተመለከቷት።
"እኔ ላነብሎት እችላለሁ.... ቅር ካላሎት..."
"እሺ ይሁን.... ጎረቤት ከማስቸግር... ጀዛከላህ..." ወረቀቷን ሰነዘሩልኝ። ሰሙን አላቅቄ ማንበብ ጀመርኩ...
.
<<አሰላሙ ዐለይኩም ኡስታዝ.... ራቢያ ነኝ ከመስጂድ። ምናልባት ከነዛ ሁሉ ተማሪዎች መሃል አያስታውሱኝ ይሆናል ግን በእርሶ እጅ ላይ ቁርዐንን አኽትሜአለሁ፤ ብዙ ኪታቦችንም የቀራሁት ከርሶ ነው። ሰፈር ከቀየሩ ጀምሮ ህመሞት መባባሱን እና መስጂድ መመላለስ እየቻሉ አለመሆኑን ሰምቼ ነበር፤ አላህ ያሽሮት። <አንድ የአላህ ባሪያ በአላህ መንገድ በሚፆመው በእያንዳንዱ ቀን አላህ ፊቱን የሰባ ዓመት ርቀት ያህል ከእሳት ያርቅለታል።> ብለው እንዳስተማሩን በቻሉት አቅም ፆመው ለመጨረስ እንደሚጥሩ አውቃለሁ። ግን ቢሆንም መድሃኒቶትን መውሰድ ካለቦት ራሶትን እንዳያደክሙ፤ ሲሻሎት አካክሰው ይፆሙታል ኢንሻአላህ። በየቀኑ መስጂድ ተራዊህ ለመቆምም ጤናዎትን አደጋ ላይ አይጣሉ። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ}:- <አንድ የአላህ አገልጋይ በሚታመምበት ወይም ጉዞ በሚወጣበት ወቅት፥ በሀገር ውስጥና ጤነኛ እያለ በሚሰራቸው (የዘወትር ፅድቅ) ሥራዎች የሚያገኘውን ምንዳ መጠን ሳይቋርጥ ይፃፍለታል።> ብለው አስተምረውን የለ? እስከዛሬ ሳያቋርጡ የፀኑባቸው ዒባዳዎች አጅራቸው ይቀጥላል.... እርሶ ብቻ ራሶትን ማስታመም ላይ ይበርቱ። በቅርቡ በአካል እስክዘይሮት ለኔም ለባለቤቴ ለሙስዐብም ዱዐ ያድርጉልን። ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።>>
.
.....አንብቤ ስጨርስ ካርዱን መለስኩላቸው።
"እሺ ጀዛኩሙላህ.... አላህ ያክብራቹ ሁለታቹንም። እሳቸውንም የጀነት ያርጋቸው.... አላህ መልካምነታቸውን ሜዳ ላይ አልተወውም። አላህ ይሶብርሽ በላት..... የመልካም ኒያዋን ይሙላላት... መቼም በዱዐዬ አልረሳቹም" ባሁኑ ከእምባ ጋር እያወሩ መሆኑ ያስታውቃል፤ የተዳፈነ ሀዘን የቀሰቀስን ስለመሰለኝ ተረበሽኩ።
"መርሃባ.... አይዟቹ አላህ አለ። እምም.... የአምና ምናምን ፆም ነበረባቸው እንዴ? የቅርብ ዘመዶቻቸው ወይ ምናምን ይፆሙላቸዋል ወይስ..."
"አይ.... አይ የለባቸውም። እስከመጨረሻው ከኢባዳ ተሳንፈው አያውቁም፤ በዒባዳ ጉዳይ እረፉ የሚላቸውን አይሰሙም ነበር..."
"ኸይር በቃ። የባንክ ሂሳብ ካሎት ገንዘቡን አስገብተን መመለስ እንችላለን..."
"አይ ወንድሜ ይመጣል ከጁምዐ በኋላ፤ እሱ ስለሆነ የያዘን ወደሱ አስገባዋለሁ ኢንሻአላህ..."
"መርሃባ ኸይር፤ የተሻለ ብለው ያመኑትን ያድርጉ። አብሽሩ በቃ.... ወሰላሙ አለይኩም" ተሰናብቻቸው ወደ ጋሼ መኪና አቀናሁ፤ ከበሩ እስክርቅ በእምባ የታጀበው ምርቃታቸው ከኋላዬ ይሰማኝ ነበር።
.
.
ይቀጥላል...❶❽

@sineislam
715 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:34:38 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ ስድስት)
.
.
ዐስርን ሰግደን ረመዳንን ቃል በገባሁለት መሰረት ወስጄ አዲስ ልብስና የፈለጋቸውን ምግቦች ከገዛዛሁለት በኋላ ወደ ቤት መለስኩት። ጋሼ እስካሁን ድረስ እንደሌላው ቀን አይጫወቱም.... ሲመስለኝ ትናንት ማታ የሰማነውን ዳዕዋ ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፤ ከነጋ 'መጣሁ' ብለው ሲሄዱም አላየኋቸውም። እኔም ጣልቃ ገብቼ በንግግሬ ላበሳጫቸው ስላልፈለኩ ላዋራቸው ጥረት አላደረግኩም። በዚሁ ሁኔታችን ስንዞር ሰዐቱ ወደ 12 ሰዐት በመጠጋቱ እግረመንገዳችንን ቁርዐኖቹን ገዝተን ወደ ተውፊቅ መስጂድ አቀናን። ከሰጠናቸው በኋላ ዱዐዕ አድርገውልን መግሪብ እስኪደርስ ከጀመዐው ጋር ተቀላቅለን መጠባበቅ ጀመርን።
*
"رُبَّ صَائِمٍ لَيْسَ لَهُ مِنْ صِيَامِهِ إِلاَّ الْجُوعُ

<ስንትና ስንት ጿሚዎች አሉ ከፆማቸው ረሀብን እንጂ ሌላን የማያተርፉ> ብለውናል የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ}" ሸይኹ ከመግሪብ ሰላት በኋላ ዳዕዋቸውን ቀጥለዋል። ሰላምታ አቅርበው ከጀመሩበት ቅፅበት ጀመሮ ሁሉም ተመስጦ በዝምታ ይከታተላቸዋል። ".... አላህ ከነሱ መሃከል ከመሆን ይጠብቀን። በረመዳን ላይ አንጀታችን ተርቦ ውሎ ፆማችንን የምናፈርስባቸው ትናንሽ ጥፋቶች እጅግ ብዙ ናቸው። ፆም ማለት አይንና ጆሮአችንም ከሃራም የሚከለከሉበት መሆን አለበት..... በመከልከል ውስጥ አላህን ለማምለክ ብቻ መፈጠራችንን የሚያስታውሰን መሆን አለበት። ፆማችን ከምግብ በፊት አይናችንን ከሃራም ነገር ላይ ከመሰብሰብ ይጀምር። ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ በአንዱ መፅሃፋቸው ላይ ምን ይሉ ነበር:- "አላህ አይንን የልብ መስታወት አድርጎታል፤ አንድ ባርያ እይታውን ከገራው (ሃራምን ነገር ማየትን ከከለከለ) ልብም ፍላጎቷን ትገራለች (ትቀንሳለች)። እይታውን ለቀቅ ካደረገው ደግሞ ልቡም ፍላጎቶቿን ለቀቅ ታደርጋለች።"..... ልክ ብለዋል። አይናችንን እንደልቡ ስንለቀው ዒባዳን ማጣጣም ይቀርና 'አዪዪዪ ሃራም ባይሆን ኖሮ.... እንዲ ማድረግ ነበር። ፆም ባይሆን ኖሮ...' ወደማለት እንመጣለን። ፆማችን የመማ'ራችን ምክኒያት መሆኑን ዘንግተን እስርቤት ይሆንብናል። በአይናችን ያልተፈቀደችልልንን ሴት ያልተፈቀደን አጅነቢይ ከየፊልሙና ሚድያው ላይ ስንከታተል ውለን የቂያም ለት ባዶ እጃችንን ስንመጣ፤ ከባድ ነው.... አንዴ ተመልሼ አስተካክዬ መፆም ብችል የምንልበት ቀን ይመጣል።" በትካዜና ቁጭት ነበር የሚናገሩት፤ በዙሪያዬ በብዛት ወጣቶች ከመሰብሰባቸው ጋር ከልባቸው እየሰሙት እንዲሆን ተመኘሁ።
.
"ሌላው ደግሞ ምላስና ጆሮዎቻችን ናቸው። አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሃዲስ ነቢና {ሰ.ዐ.ወ}:- <ሐሰት መናገርንና በርሱ መስራትን ያልተወ ሰው ከምግብና ከመጠጥ ታቅቦ ከመዋሉ አላህ ምንም ፍላጎት የለውም።> ማለታቸው ተነግሮናል። ግልፅ ነው አይደል?.... የሰማያትና የምድር ካዝናዎች ያሉት ሃያል ጌታ የኔና ያንተ በረሃብ ተሸማቆ መዋል ምንም የሚጨምርለት ነገር የለም። ፆም እኛ በመከልከላችን ከመጥፎ ስራ ልንጠበቅበት፤ ሸይጧን በመታሰሩ አላህን የተሻለ ልንገዛበት ብቻ ነው። ፆሜአለሁ ብለን ስናበቃ መልሰን ሰው ስናማ ከዋልን፤ ምግብ ከመብላት የሞተ ወንድማችንን ስጋ ወደመብላት ብቻ ነው የተሸጋገርነው.... መዐዘላህ! እንደውም በረመዳን 'አፍ ስራ ሲፈታ ወዳጁን ያማል' የምናስመስለውም እኮ ብዙዎች አለን አላህ ይጠብቀን..... ከፊሎቻችን ደግሞ የተሻልን መስሎን 'እንዲ ቦታ እየዋለች የሷ ፆም እኮ ቢቀር ነው የሚሻለው.... ተጀመረ ደግሞ ረመዳንን ጠብቆ ሊሰግድ ነው' እያልን በአሳቢነት የተሸፋፈነ ሃሜት እናማለን..... አላህን እንፍራ! <ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱ እና ከእጁ አደጋና ክፋት የዳኑ (ሰላም የሆኑ) ሰው ነው> አይደል እንዴ ነቢና {ሰ.ዐ.ወ} ያስተማሩን? የቂያም ቀን ስለፆማችን እንጂ ስለነሱ ሰላት አንጠየቅም። ስለዚ መጪው የዒባዳ ወር የራሳችን ወንጀል ብቻ የምናተኩርነት ይሁን።
.
"ከነዚህ ደግሞ ለየት ብለን በጆሮአችን ፆማችንን የምናፈርስ አለን። የተከለከሉ ሃራም ዘፈኖችና ድምፆችን መስማት አንዱ ጥፋት ነው፤ ቀልባችን ለቁርዐን ና ለኹሹዕ ክፍት እንዳይሆን እንደፍነዋለን። ከዛም ውጪ ደግሞ ልብ የማንለው ወንጀል ሌሎች በክፉ ሲወሱ ማዳመጥ ነው። ሃሜቱ ላይ ባንሳተፍም ነግ በኔ እያሉ መስማት ሃራም መሆኑን ዘንግተን ባህል አርገነዋል። ከቻልን እንዲያቆሙ መከልከል ካልሆነም ደግሞ ከሃሜቱ ስፍራ መራቅ ዲናዊ ግዴታችን ነው። አላህ በአል-ሙዕሚኑን ምዕራፍ ላይ ሙዕሚኖች ማን እንደሆኑ ሲተነትንልን 3ኛው አንቀፅ ላይ...

وَٱلَّذِينَ هُمْ عَنِ ٱللَّغْوِ مُعْرِضُونَ

{እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፡፡} ብሎ ነበር የገለፃቸው። በማዳመጣችን ውስጣችን ጥርጥር ይፈጠራል፤ ባንፈልግ እንኳን ስለሱ ማብሰልሰል እንጀምራለን። ለዚህ እኮ ነው ብዙዎቻችን ሰላታችን የሚበላሸው! አፋችን ፆሞ ውሎ ልባችን ግን በሰማው ሃሜት.... አልያም ስለ አጅነቢይ ሴት ስለሰማው ገለፃ እያሰላሰለ ወንጀል ሲሰራ ይውላል። አላህን እንፍራ! እነዚህ ጥፋቶች ከባድ ናቸው.... ምክኒያቱም ግድያ አልያም ስርቆት ቢሆን ማጥፋታችንን ስለምናውቀው ወዲያው ተውባ እናደርጋለን። ይሄ ግን ሳንፆም ፆመናል ብለን ባዶ እጃችንን ወደ አኼራ እየሄድን ነው! ነቢና {ሰ.ዐ.ወ} :- <ከኔ ኡመት ድኃ ማለት ነገ የቂያም እለት ሶላቶቹን፣ ጾሙን፣ ሶደቃውን ይዞ የሚመጣና ነገር ግን ያን በመሳደቡ፤ ይሄኛውን በማዋረዱ፣ እሱን ደግሞ ብሩን በመብላቱ፣ የዚህያውንም ደም በማፍሰሱ፣ ይሄንን በመምታቱ ሰበብ ከሐሰናቱ ተወስዶ ለተበዳዮች ይሰጥና የሱ ሐሰናት ሲያልቅበት ከተበዳዮች ኃጢአትን በምትኩ ተሸክሞ በጀሐነም የሚወረወር ነው> ብለው ከገለጿቸው ህዝቦች መሃከል እንዳንሆን። ስንጀምር እንዳልነው ከፆማቸው ረሃብን እንጂ ሌላን ያላተረፉትን ህዝቦች እንዳንሆን። አላህ ይጠብቀን!..... ለዛሬ እዚሁ ላይ እናቁም። አላህ ወደሱ እየገሰገስን ያለነውን የዒባዳ ወር ደርሰው ከሚፆሙት፤ ፆመውም ከሚጠቀሙበት ያድርገን። ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።" ንግግራቸውን አጠናቀቁ። ከተናገሩት ውስጥ አንድም የሚዘለል የለውም፤ አላህ ሂዳያውን ይስጠን።
.
"ሙስዐብ.... እየመሸ ነው፤ በጊዜ መንገድ እንጀምር... ወደ ውጪ ልቅደምህ..." የሸህኹን ንግግር መጠናቀቅ ተከትለው ጋሼ በችኮላ ነገረውኝ ወደ ውጪ ወጡ። ፊታቸው ላይ ምቾት እይነበብም.... 'እንዲ በቀላሉ አይተውም...' ያሉኝ ታወሰኝ። በእርግጠኝነት መቅደሙን የፈለጉት ሊያጨሱ ነው፤ ቢሆንም በመጀመሪያው ቀን ይሄን ያህል መዋል ከቻሉ ትልቅ ተስፋ ነው። ለጥቂት ደቂቃዎች ዱዐእ ካደረግኩ በኋላ ጋሼ ጨርሰው እንደሚሆን በመገመት ከመስጂዱ ወጣሁ።
.
.
ይቀጥላል...❶❼

@sineislam
543 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:33:12 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ አምስት)
.
ከዙሁር በኋላ ምሳችንን በልተን ወደ ቀጣዩ ቤት መንገዳችንን ቀጥለናል። ጋሼን ከምጨቀጭቃቸው አይኔን በመስኮቱ አሻግሮ ወደሚታዩት ሱቆች ሰንዝሬ አላፊ አግደሚውን ማማተር ጀመርኩ። ከአንዱ ዛፍ ስር የጫማ መጥረጊያ እቃዎችን የያዘ ትንሽ ልጅ ተመለከትኩት፤ አቀርቅሮ የተከፋ ይመስላል።
"አንዴ.... አንዴ አቁሙት ጋሼ..."
"አሁን? ደርሰናል እኮ..." ግራ ተጋብተው በመስታወቱ ተመለከቱኝ...
"አዎ... አዎ አሁን...." መኪናችን ልጁ ጋር ደርሶ እያለፈው በመሆኑ ልቤ ተሰቅሏል። ጋሼ ባይገባቸውም አቆሙልኝ፤ ተጣድፌ ወረድኩ።
.
አጠገቡ ስደርስ ፍጥነቴን ገታ አድርጌ ተጠጋሁት.... ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ተመለከተኝ፤ ሳልፍ ከገመትኩትም በላይ ልጅ ነው። ለጊዜው እየሰራም ቢሆን ላዋራው ስለፈለኩ እግሬን የሊስትሮ ሳጥኑ ላይ ሰቀልኩለት።
"ስንት አመትህ ነው?...." ፊቱን ለማየት እየሞከርኩ።
"አስር"
"የምር? ግን አትመስልም"
"ወላሂ...." አንደበቱ ሲምልበት ደስ ይላል፤ በዛውም ሙስሊም መሆኑን አወኩ።
"ትማራለህ?".... ጭንቅላቱን በአሉታ ነቀነቀልኝ። "እሺ መድረሳስ?" ቀና ብሎ በመኮሳተር ከተመለከተኝ በኋላ መልሶ አቀረቀረ...
"መግባት አልፈልግም"
"ለምን?"
"አላህ ረስቶናላ!..... ከሃብታም ብቻ ነው ዱዐ የሚሰማው..." ይበልጥ ብስጭትጭት እያለ መጥረጉን ቀጠለ፤ አሳዘነኝ። እግሬን አውርጄ ጎንበስ ብዬ ለማውራት ብቻ ተስተካከልኩ።
"ምን ጠይቀኸው ነው አልሰማም ያለህ?"
"ብዙ ነገር..... እንደሌሎች ልጆች ሳላቆራርጥ ት/ቤት እንድሄድ እንዲያደርገኝ፤ እማዬ እግሯ ተሽሏት እንደድሮው መስራት እንድትችል፤ እህቴ ውጪ ስትሄድ ቶሎ እንድታስታውሰኝ፤ የሰራሁበትን ከሚቀሙኝ ልጆች በላይ ጠንካራ እንዲያደርገኝ ጠይቄው ነበር። እህቴ 'በማታ ጠይቀው ይሰማሃል' ትላለች.... ግን በቀንም በማታም ጠይቄው አልሰማም" እምባዎቹን ከእልህ ጋር እንደጉድ ይፈሳሉ። የሚያወራለት ሰው ተርቦ የከረመ ይመስላል። በምን ቃላት ህመሙን እንደማስታግስለት ግራ ገባኝ...
"ታዲያ እኮ ይሰጥሃል..."
"አይሰጠኝም..... እሱ ሃብታም ነው፤ ሃብታሞች ደግሞ ደሃ አይወዱም...." ከልቡ ተበሳጭቶ ነበር የሚናገረው። ቦርሳዬ ውስጥ ካሉት ፖስታዎች አንዱን ሰጥቼው ባስፈነድቀው ተመኘሁ.... ግን አልችልም። ጥቂት በዝምታ ካሰብኩ በኋላ በራሴ አቅም እምባውን ላብስለት ወሰንኩ...
"ማን ነበር ስምህን ያልከኝ?"
"ረመዳን..."
"ለምን መጥቼ የጠየኩህ ይመስልሃል ረመዳን? ዱዐ ስላደረገ የፈለገውን ግዛለት ተብዬ እኮ ነው። አሁን ሂድና እቃህን ቤትህ አስቀምጠህ ተመለስ.... እኔም ደረስ ብዬ የምመጣበት ቦታ አለ፤ እዚሁ ተገናኝተን የፈለከውን እንገዛለን"
"ውሸትህን ነው.... ስመለስ አትኖርም።" ጉንጮቹ እንተነፋፉ ህቅታ እየታገለው ያለማመን አስታየየት አየኝ።
"ወላሂ እመጣለሁ..." ቃል ገባሁለት። እጁን አስመትቶኝ ጭምር ካስማለኝ በኋላ እቃዎቹን ሰብስቦ እየሮጠ ወደ መንደሩ ውስጥ ገባ። ደስታው ተጋባብኝ.... በእርምጃ ወደ መኪናው አመራሁ።
*
ከጋሼ ጋር ቤቱ ጋር ደርሰን ያረጀውን የእንጨት በር ማንኳኳት ጀመርኩ....ልቤ ረመዳን በአላህ ላይ ያለውን ተስፋ ይበልጥ እንዳላሳጣው ተጨንቋል።
"ማነው...?" የትልቅ ሴት ድምፅ ከውስጥ ተሰማ።
"አሰላሙ አለይኩም.... ወ/ሮ ራህማን ፈልገን ነበር.."
"ቆይ አንዴ..." ምላሽ ሰታን ለደቂቃዎች ድምፅ ሳይሰማ ቆየ፤ ፊቴን አዙሬ መጠበባበቅ ጀመርኩ። በስተመጨረሻም ከጀርባዬ በሩ ሲከፈት ሰማሁት... ፊቴን ሳዞር ያየሁት ነገር ግን ተዐምር ይመስላል።
"እንዴ.... ረመዳን?" ደንግጬ ባለማመን ከላይ እስከታች ተመለከትኩት።
"ቤታችንንም ነገሮሃል እንዴ ለካ?" እሱም በግርምት እያየኝ። ጋሼ መኪናው ውስጥ እንደተቀመጡ ናቸው፤ ብቻዬን ወደ ውስጥ ዘለቅኩ... ወ/ሮ ራህማ ፍራሹ ላይ እንደተቀመጠች ነበር። ለደቂቃዎች በደስታ ምንም ሳልናገር ከቆየሁ በኋላ ራሴን አስተዋወኳቸው። ረመዳን ተነስቶ ተጠምጠመብኝ፤ 'እህቴ' ሲላት የነበረችው የኔው ራቢ መሆኗን የገባኝ ይሄኔ ነው። ፖስታውን ለእናቱ ከሰጠኋት በኋላ መልዕክት እንዳለው ነግሬአት አውጥታ ማንበብ ጀመረች። በእጅጉ ረጋ ያለች ሴት ናት....
"ሃሃህ... ላንተ ነው ረሙዬ..." ካርዱን አቀበለችው። ትንሽ ከሞከረ በኋላ እሱ ያንብብልኝ ብሎ ሰጠኝ...
.
<<አሰላሙ ዐለይክ ትንሹ አባወራ.... እህትህን አስታወስካት? ስለ ት/ቱ ከማማ ጋር ስለምናወራበት ካንተ ጋር ሌላ ቁምነገር ልናወራ ነው። እንደ ስምህ የተዋበው ወር መንገድ ላይ መሆኑን ታውቃለህ አይደል? አላህ በዛች ቀን ምንም ነገር ብትጠይቅ እንደሚሰጥህ ደጋግሜ የነገርኩህ ቀንም አብራ ትመጣለች። የካች-አምና ዱዐእህን ታስታውሰዋለህ አይደል?.... ይኸው ተሰሚ ሆኖ አላገኘኸውም? ዘንድሮ ደግሞ ማማ እንዲሻላት ያቺን ቀን ተጠባብቀህ ዱዐ አድርግላት፤ ሃላፊነትህ ነው!.... ማንም ማያውቀውን አንድ ሚስጥር ልንገርህ? ነቢና {ሰ.ዐ.ወ}:- <ለይለተል ቀድርን በረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት ውስጥ በጎደሎ (ዊትር) ቀናት ተጠባበቁት።> ብለው ነበር። አንተም እንዳታመልጥህ አስሩንም ቀናት ለሊት እየሰገድክ በሚስጥር ዱዐ አድርግ። <አልላሁምመ ኢንነከ ዐፉውዉን ቱሒብቡል ዐፍወ ፈዕፉ ዐንኒይ> (አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ። ይቅርታንም ትወዳለህ። ስለዚህም ይቅር በለኝ።)> ብለህ ዱዐእህን ጀምር፤ እንዲሰማህ የሚስጥር ቃሉ ነው። ሽሽሽሽ..... ሙስዐብ ራሱ አልነገርኩትም ላንተ ብቻ ነው>>
.
"ወይኔ..... ቲሽሽ..." ካርዱን ተቻኩሎ ቀማኝ። እኔና ወ/ሮ ራህማ ሳቃችንን መቆጣጠር አልቻልንም።
"ልጨርስልህ እንጂ?" የተቀረው ስንብቱ መሆኑን በአይኔ ቀድሜ ስለዳሰስኩት አሳዘነኝ።
"አይ አይ.... ራሴ ማንበብ ተለማምጄ እጨርሰዋለሁ። ለራቢ እንዳትነግራት እ? በጣም ታኮርፋለች..." ከልቡ ነበር።
"ሃሃህ እሺ በቃ..... አንተም ያለችህን ካደረግክ ለማንም አልናገርም።" ልክ እንደቅድሙ እጁን መትሼ እየማልኩለት። ካርዱን ሻንጣው ጋር ሊደብቅ ወደ ውስጥ ይዞት ገባ። "አክስቴም ዒባዳው ላይ አደራሽን እ? ራቢ የሚመጣውን ወር በዒባዳ ብቻ እንድታሳልፉት ነይታ ነው የላከችው። ኢንሻአላህ ዱዐሽን ሰምቶ አፊያሽን የሚመልስበት ይሆናል..."
"ኢንሻአላህ.... እኔስ ረመዳን ከተስተካከለልኝ ምንም አልፈልግም፤ ውጪ ሲውል እያበላሹብኝ ነው..." ትክዝ ብላ አቀረቀረች።
"አብሽሪ... የሂሳብ ቁጥር ካለሽ ንገሪኝና የሱን ወጪ እኔ እሸፍናለሁ.... ት/ቱና ዲኑ ላይ ብቻ ያተኩር።" ስልኬን አውጥቼ የምትለኝን ቁጥር መመዝገብ ጀመርኩ። ከደስታዋ ብዛት እምባዎቿን ከመፍሰስ ልታግዳቸው አልቻለችም። እኔም መንገድ ላይ አስቁሞ ዱዐውን እንድሰማ ያደረገኝ የኢላሂ ሙጂብነት መሆኑን ሳስበው እምባዎቼን መቆጣጠር አቃተኝ።
"ወንድሜ...." ረመዳን እየተቻኮለ መጋረጃዉን ከፍቶ ሲወጣ እምባዎቼን ጠረግኳቸው። "የምር ግን ራቢ እንደምትለው በደንብ ካጠናሁ ይገባኛል? ሊስትሮ ዶክተር መሆን ይችላል እንዴ እ?" ተስፋና ጉጉት አይኖቹ ላይ እየተነበበ ጠየቀኝ።
"አዎ በደምብ! ከታክሲ ረዳትነት ተነስቶ ዶክተር የሆነ ልጅ አውቃለሁ። ግን አላህ የሚለምኑትን ነው የሚያግዘው...." እንዲያጠናክረው ትናንት ከረሻድ የተማርኩትንና ሌሎች የማውቃቸውን ሷሊህ ሰዎች ስኬት አጫውተው ጀመር።
.
.
ይቀጥላል...❶❻

@sineislam
602 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 12:46:18 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ አራት)
.
.
በረንዳዬ ላይ ቆሜ የጠዋቷን ፀሃይ በፈገግታ እየተቀበልኩ ነው፤ ሳይታወቀኝ ቀናቶቹ ነጉደው 5ኛው ቀን ላይ መድረሳችን ይደንቃል። ወደ ክፍሉ ተመልሼ ከተቀሩት ፖስታዎች መሃል ሁለቱን አንስቼ ቦርሳዬ ጋር ከከተትኩ በኋላ ቁርስ ለመብላት ወደ ካፌው ወረድኩ፤ ጋሼ ጋዝ ለማስሞላት አንድ ማደያ ጋር መቆማቸውን ስለነገሩኝ ሳይቆዩ አይቀሩም።
.
ካፌው ጋር ተቀምጬ ጋሼ እስኪመጡ ስልኬን አውጥቼ የገቡልኝን መልዕክቶች መፈተሽ ቀጠልኩ፤ ልምድ እየሆነብኝ እንደመጣው... የምጀምረው ከራቢ ነው። 'የምትፅፊላቸው መልዕክቶች ደስ ይላሉ፤ ያለፈው ህይወትሽ አድናቂ ነኝ' ብዬ ልፅፍላት አስብና ተደብቄ ማንበቤ ትዝ ሲለኝ እተወዋለሁ። አሁንም 'ከዛሬ ጀምሮ'ኮ መልዕክቶችሽን ሳላስፈቅዳቸው ላላነባቸው ወሰንኩ' ብዬ ልልክላት ካልኩ በኋላ በራሴ ሃሳብ ስቄ ተውኩት። ፍቅር ከኒካህ በኋላ ደስ ይላል.... ስለሷ በማወቅ ውስጥ ሰምጬ ስቀር፤ በየአጋጣሚው እሷን ማዋራት ሲናፍቀኝ ሃራም ላይ እንዳልወድቅ አልሰጋም። ከራሴ ሃሳብ መለስ ስል የላከችልኝን ምላሽ ከፈትኩት....
'ማሻአላህ ለረሻድ ደስ ብሎኛል፤ ሰዐዲም ደስታዋ የሚመለስበት ጊዜ ያርግላት። ታውቃለህ? ዛሬስ የማንን ይሆን ያነሳው የሚለው ለኔም እያጓጓኝ መቷል.... ሃሃሃህ' ከመልዕክቷ ውስጥ ለጥቂት ቀናት ብቻ የሰማሁት ሳቋ ይደመጠኛል። በየምሽቱ ቤት ስደርስ የነበረኝን ውሎና ያሳዩኝን ምላሽ እፅፍላታለሁ.... ለደስታቸው ተደስታ አትጠግብም።
'እኔም እንደዛው... ማታ አሳውቅሻለሁ ኢንሻአላህ' መልሼላት ያዘዝኩትን ማክያቶ ተጎነጨሁ። ብርጭቆውን ወደ ቦታው እየመለስኩ ቀና ስል የጋሼ መኪና ወደ መግቢያው ተጠግታ ስትቆም ተመለከትኳት። መግባት እንደማይፈልጉ ባለፉት ቀናት ደጋግመውልኛል፤ ሂሳቡን ከፍዬ ወደ መኪናው አመራሁ።
.
ከጋሼ ጋር እየተጨዋወትን ወደዛሬው አድራሻችን ደረስን፤ ካራ። መንደሩ ውስጥ ካሉት ትናንሽ ቤቶች መሃል ወደ አንዱ አመራን፤ ጋሼ ከዚህ በፊት መጥተውበት የሚያውቁ ይመስላል። አንዱ በር ጋር ስንደርስ እሱ መሆኑን ነግረው አስቀደሙኝ፤ አንኳኳሁ። ጥቂት ከጠበቅን በኋላ በሩ በትንሹ ተከፈተ...
"አቤት?" ከበሩ ጀርባ የሚሰማው የሴት ድምፅ ነበር።
"አሰላሙ ዐለይኪ.... ቢላል ይኖራል?" ፖስታው ላይ የተጠቀሰልኝ የወንድ ስም ጠራሁላት።
"አይ.... ለስራ ወጣ ብሏል።"
"ያመሻል?"
"አላውቅም፤ ግን ከዙህር በኋላ ሰግዶ መምጣቱ አይቀርም.... ትንሽ ቆይታቹ ኑ" ሃሳቧ ለኛ እቅድ የሚመች ባይሆንም ሌላ አማራጭ አልነበረንም። ተስማምተን ተሰናብተናት ወደ መኪናው መመለስ ጀመርን...
"አገባ ማለት ነው?.... ማሻአላህ፤ አላህ ያግዘው።" ጋሼ ነበሩ።
"ያውቁታል እንዴ በደምብ?"
"አዎ.... የድሮ ሰፈራችን በምንኖርበት ጊዜ ለማንም ሰው ሃጃ ተሯሩጦ የሚያስፈፅመው እሱ ነበር። እዚ ከገባ በኋላ ግን ስለሱ ብዙ አልሰማሁም..." ከመንደሩ ወጣ እያልን እያለ ጋሼ ንግግራቸውን ቆም አድርገው አንዱን ወጣት ትኩር ብለው መመልከት ጀመሩ። "እሱ ይሆን እንዴ?.... አዎ ነው.... ቢላል!" ጮክ ብለው ተጣርተው እጃቸውን አውለበለቡለት። ወደ ጭነት መኪና ሲጭን የነበረውን ሲሚንቶ አስቀምጦ ወደኛ ገሰገሰ።
"አሰላሙ ዐለይኩም.... ጋሼ.... ሃሃህ.... ምን እግር ጣሎት" ልብሱን ያለበሰው አቧራ የሳቸውንም እንዳያበላሽ እየተሳቀቀ አቀፋቸው። በቆሙበት ሰላምታ ሲለዋወጡ... እኔን ሲያስተዋውቁት... እየተመለስን እንደነበር ሲያስረዱት ምናምን ቆሜ ከፈገግታ ጋር ማዳመጥ ጀመርኩ። ቅን ሰው መሆኑ ገና ከአነጋገሩና ሁኔታው ይንፀባረቃል።
"ራቢ ይሄን ልካልሃለች.... ውስጡ መልዕክትም አለው።" ፖስታውን አውጥቼ ሰጠሁት... ከፍቶ ከተመለከተው በኋላ በመጀመሪያ አይሆንም ብሎ ተቃውሞኝ ነበር፤ ከጥቂት ክርክር በኋላ አሳመንኩት። መልዕክቱን አውጥቶ ማንበብ ጀመረ፤ ከእያንዳንዱ ድርጊቱ ጋር ፈገግታ አይለይም።
"መርሃባ.... አብሽሪ ያንቺ ሃጃ የኔም ነው በላት። አላህ ጀዛቹን ይክፈልልኝ፤ በጣም አመሰግናለሁ።" ደስታውን ከፊቱ ላይ መደበቅ አልቻለም።
"ኢንሻአላህ.... አንዴ ማንበብ እችላለሁ?" ጠየኩት።
"አዎ አዎ.... ይቻላል አብሽር።" ወረቀቱን ሰጠኝ። ሳልጨናነቅ ማንበብ ጀመርኩ...
.
<<አሰላሙ ዐለይክ ቢላል... ራቢያ ነኝ አስታወስከኝ? የመጨረሻ የደወልክልኝ ጊዜ ልታገባ ማሰብህን ነግረኸኝ ነበር.... በርታ አላህ ሪዝቁን ያመጣዋል ያልኩህ ትዝ ይልሃል? ይሄም ገንዘብ ብዙ ባይሆንም አላህ ለመነሻ እንደላከልህ ሪዝቅ ቁጠረው። የፊታችንን የራህማ ወር አንተም ቤቱን ለመሙላት በስራ፤ እሷም ሱፍራውን ለመሙላት በማብሰል የምትጠመዱበት እንዳታደርገው። ትዳራቹን አላህን አብራቹ ራህመትን የምትጠይቁበት አድርጉት፤ ለዚህ ደግሞ ከረመዳን የበለጠ የመተሳሰብ ወር የለም። <የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} ተከታዮቻቸውን በረመዷን እንዲቆሙ ያበረታቷቸው ነበር። ቁርጥ የሆነ ትዕዛዝ ግን አላዘዟቸውም። እንዲህ ይሉ ነበር:- <ረመዷንን፥ ምንዳ ከአላህ እንደሚያገኝ አምኖ የቆመ ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።> > አይደል ሃዲሱ የሚለን? አንተም ተበራትተህ አበራታት.... ወንጀልሽ እንዲማር፤ ወደ ጀነት እንድትከተዪኝ ነይ አብረን ተራዊህ እንሂድ በላት። ግን ይሄን ስልህ በአንድ ለሊት ቁርዐንን ጨርሰን ማደር አለብን ብለህ ራስህንም እሷንም እንዳታደክማት። ዒባዳውን የአቅማቹን ያህል፤ ግን በመጀመሪያዎቹ የረመዳን ቀናት ላይ በነሻጣ ተጀምሮ የማይቆም አድርጉት። <...አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ዲን (ዒባዳ) ሰውየው አዘውትሮ የሚሰራው ነው።> አይደል ሃዲስ ላይ የሰፈረልን? አደራ.... የትዳራቹን መጀመሪያ በዒባዳ የምታቃናበት ወር አድርገው። በቅርቡ በአካል እስክዘይራቹ ለኔም ለሙስዐብም ዱዐ ያድርጉልን። ወሰላሙ ዐለይክ ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።>> አንብቤ እንደጨረስኩ መለስኩለት፤ ከፈገግታ ጋር ተቀበለኝ። እንደራሱ ሁሉ በዙሪያው ያለውም.... የተፃፈለት መልዕክትም ሰላም የሰፈነበት ነው።
.
"የባንክ ሂሳብ አለህ?" ጋሼ ነበሩ ለጥያቄው የቀደሙኝ።
"አዎ አለኝ.... እዛ ጋር ወረድ ብዬ አሁን አስገባዋለሁ።"
"ኸይር... በል ይዘህ ስትሄድ የዋህ ነው ብለው ይቀሙሃል.... አብረን ደርሰን እንመጣለን። ና... የኛ መኪና እዛ ጋር አለች..."
"ኧረ ጋሼ.... ወላሂ አያስፈልግም..." እንደቅድሙ መከራከሩን ቀጠለ፤ ሆኖም መስማማቱ አልቀረም። "እሺ በቃ.... ጠብቁኝ ደርሼ ልመጣ መሆኑን ላሳውቃቸው፤ ስራ ጥዬባቸው ነው የመጣሁት..." ፖስታውን አቀብሎኝ እየሮጠ ሲሸከምበት ወደነበረበት መኪና ገሰገሰ። ተስፋና ሃምድ ከሁለመናው ላይ ይነበባል.... በውስጡ የተሸከመው ሌላ ሃሳብ ኖሮም ከሆነ ኢላሂ እንዲያገራለት እየተመኘሁ ፖስታውን ወደ ቦርሳዬ መለስኩት። እንደመጣ ወደ መኪናው ጉዟችንን ጀመርን...
.
.
ይቀጥላል...❶❺

@sineislam
859 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 12:46:18 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ ሶስት)
.
ለሰአዳ መልዕክቱን ካደረስን በኋላ በቀጥታ ወደ ጡሩ ሲና መስጂድ ሄደን አስርን በጀመዐ ሰገድን። ያነበብኩት መልዕክት የፈጠረብኝ ስሜት ከውስጤ ሊወገድ አልቻለም። ምሳችንን አለመብላታችን ራሱ የታወሰኝ ጋሼ ሲያነሱት ነበር። በአቅራቢያው የሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ከተመገብን በኋላ ቁርዐኖቹን የምንገዛበት ቤት ማፈላለግ ጀመርን። ሰዐቱ ወደ 12 ሰዐት ሲጠጋ ገዛዝተን ጨርሰን ወደ መስጂዱ ተመልሰን ቁርዐኖቹን ሰጠናቸው.... ባሁኑ ጥያቄዬ ልክ እንደ ራቢ ፍላጎት ሁሉ "ዱንያ የከበደችባት አንድ እህት አለችኝ.... ትዳሯና ሪዝቋ እንዲቀናላት ዱዐ አድርጉልኝ" የሚል ነበር። እግረመንገዳቸውን ለኔም ማድረጋቸው አልቀረም፤ ልቤ ግን ለሷ በተደረገላት ይበልጥ የረካ መሰለኝ። እንዳለፉት ቀናት ሁሉ የመግሪብ ወቅት እስኪገባ ከጠበቅን በኋላ መግሪብን እዛው በጀመዐ ሰገድን።
.
"ቢስሚላህ... ወሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ..." ሸይኹ በሰለዋት አጅበው ዳዕዋቸውን ጀመሩ። ስላለፉት ቀናት የተወሰነ ማጠቃለያ ካሉ በኋላ ወደ ዛሬው ዳዕዋቸው ገቡ። "....በአጠቃላይ የፊታችን ረመዳን ሳንጠቀመው እንዳያልፈን፤ መልካም ስራዎችን እናብዛበት! 'በብዛት ለምንድነው ረመዳን ሲመጣ ለመለወጥ መጣር ያለብን? ከዛ በፊትስ አይቻልም ነበር ወይ?' ካላቹ ይቻላል.... ነገር ግን ረመዳን ሸይጧን የሚታሰርበት በመሆኑ አዳዲስ ልምዶችን ለመፍጠር፤ መጥፎዎቹን ለመተው የተሻለ ነው። ስለዚህ መጥፎ ልምዶቻችንን በአዲስ መልካም ልምዶች እንቀይራቸው..." ለጥቂት ደቂቃዎች በዝምታ አይናቸውን ወደያዙት ወረቀት ሰበር ካደረጉ በኋላ ቀጠሉ...
.
"መልካም መሆን ያን ያህል ከባድ አይደለም። <እያንዳንዱ መልካም ተግባር ሰደቃ ነው> ብለው ነበር ያስተማሩን አሽረፉል ኸልቅ {ሰ.ዐ.ወ}። ኢንሻአላህ ራሳችንን የምናገኝበትን መልካም ተግባር ከተከታዩ ሃዲስ አብረን የምንፈልግ ይሆናል። አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሃዲስ ነቢዩ {ሰ.ዐ.ወ}:- <እያንዳንዱ ሙስሊም የመለገስ ግዴታ አለበት> አሉ። <የሚመፀውተው ካላገኘስ?> አለ (አንድ ጠያቂ)። <በእጁ ሰርቶ ራሱን ይጥቀም፤ ይመፅውትም> አሉ። ሁለት መልካም ተግባራትን ያዙልኝ። ቀጠሉ.... <ካልቻለስ?> ሲል ጠየቃቸው። <የተቸገረን ባለጉዳይ ይርዳ> ሲሉ መለሱ። <ካልቻለስ?> አላቸው። <በፅድቅ ወይም በመልካም ይዘዝ> ሲሉ መለሱ። <ይህን ካልፈፀመስ> አላቸው። <ከተንኮል ይቆጠብ። ይህም ምፅዋት ነው።> የሚል ምላሽ ሰጡ። ከነዚ 5 ቡድኖች ራሳችንን ሳናደክም፤ ጊዜያችን ሳይባክን መሳተፍ እንችላለን... 'እንዴት?' የሚለውን እያንዳንዳቸውን ነጥለን እንመልከት።
.
"የመጀመሪያው ላይ ለሌሎች መመፅወት ሲባል የግድ ትልቅ ነገር መሆን የለበትም። በየቀኑ ለወፎች የተወሰነ ጥሬ መበተን ሰደቃ ነው፣ የተራረፈን ምግብ ለእንስሳት መስጠት ሰደቃ ነው፣ ዛሬ ረፍት ስታገኝ በምትተክለው ዛፍ ነገ ሌሎች ሰዎችም ሆኑ እንስሳት ቢመገቡበት ዛፏ እስካልተቆረጠች ድረስ እስከ ቂያማ ቀን የማይቋረጥ ሰደቃ ነው። <ርጥብ በሆነች (በሕያውያን) ሆድ ሁሉ ምንዳ ይገኛል።> ነው ያሉን ነቢና {ሰ.ዐ.ወ} አይደል እንዴ? በኒ'ያ ከያዛቹት ደግሞ ካሁን ጀምሮ የምትመፀውቱት ገንዘብ ከየውሏቹ ላይ ቀንሳቹ፤ በየቀኑ አነሰም በዛም መንገድ ላይ ላሉት ወንድሞቻቹ ብትሰጡ ሰደቃ ነው። ረመዳን ሙሉ ወሩን ብትተገብሩት ከዛ በኋላ እናንተም የነሱን ደስታ ማየት ሱስ ይሆንባቿል ኢንሻአላህ። ይህን ካልቻልን ደግሞ ራሳችንን መቻል ነው ሁለተኛው አይደል? አዎ....ወተህ ለመንቀሳቀሻ የሚሆንህን ገንዘብ የምታገኝበት ስራ ብትይዝ፤ ቤተሰብህ አንተን በሚችልበት ገንዘብ ራሱን አልያም ሌላን ሰው መጥቀም ይችላል። አንተም ደግሞ የጀመርከው ነገር ከተሳካልህ ሌሎችን ትጠቅማለህ ኢንሻአላህ።
.
"ሶስተኛው መልካምነት ምንድነው አልን? የተቸገረን ባለጉዳይ መርዳት!..... እስኪ በዚህኛው ረመዳን በልባችን 'ለአላህ ስል በቀን የአንድ ወንደሜን ሃጃ እፈታለሁ' ብለን እንነሳ። መቼስ ቻሌንጅ ትወዳላቹ.... ቻሌንጅ አድርጉት! በትርኪምርኪው ራሳቹን አዛእ ከምታደርጉ ወንድማቹን ለመርዳት ራሳቹን ብተስቸግሩ ወላሂ ለናንተ በላጭ ነው። ነቢና {ሰ.ዐ.ወ}:- <በወንድሙ ጉዳይ የዋለ፥ (የወንድሙን ጉዳይ የፈፀመ) ሰው አላህ በርሱ ጉዳይ ላይ ይውልለታል፥ ከሙስሊም አንዲትን ጭንቀት ያስወገደ፥ በርሷ (ሰበብ) አላህ ከቂያማ ጭንቀቶች አንዲትን ጭንቀት ያስወግድለታል።> አልበር እንዴ ያስተማሩን? ወንድምህ ነገ ፈተና ተፈታኝ ከሆነ ከአላህ ምንዳን ማግኘትን አስበህ ሄደህ አስጠናው፤ አልያም እህትሽ ናት.... ሄደሽ የቤቷን ስራ ሸፍኚላት እሷ ታጥና። ወይ ደግሞ ነገ ስብሰባ አለው የሚለብሰው ጨንቆታል፤ ልብስህን አውሰው። ስለ ሃጃው ማማከርም አንድ ጭንቀትን ማስወገድ ነው። በየቀኑ የአንድ ሰውን ጭንቅ ለመፍታት ቆርጠህ ተነሳ.... ኢንሻአላህ በዚህኛው የሰደቃ አይነት ወሩ ሲያበቃ ራስህን ከመልካሞች መሃል ታገኘዋለህ።
.
"ሌላው በፅድቅ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ነው። በዙሪያህ ያሉትን ወደ ዒባዳ መጣራት.... መስጂድ ስትመጣ ጎረቤትህም አብሮህ እንዲሄድ መጋበዝ፤ እህትሽን ሂጃቧን እንድታስተካክል መምከር፤ አልያም በስልክሽ በየእያዳንዱ የረመዳን ምሽት ለተወሰኑ ጓደኞችሽ አንድ አንድ ሃዲስ መላክ ሊሆን ይችላል። የሚድያ ገፅህ ላይ ዘፈን አጋርተህ ከሞትክ በኋላም የማያቋርጥ ወንጀል ከመሰብሰብ አንድ ዳዕዋ አስተላልፈህ የሚጠቀምበትን የእያንዳንዱን ሰው አጅር ተካፈል። ይሄም አንድ የሰደቃ አይነት ነው... ራሳችንን እናጠናክረው። የመጨረሻው ከተንኮል መቆጠብ ነው! ጉዳታችንን ከሌሎች ላይ መሰብሰብም ሰደቃ ነው። ራሳችንንም መጉዳት አይፈቀድም አይደል? ስለዚ በዚህ ረመዳን አንድ ጉዳት እንቀንስ.... ወላጆቻችንን አዛ እናደርግ ከነበረ አሁን ምላሳችንን የምንሰበስብበት ይሁን። ሱስ ከነበረብን ረመዳንን ፆመን ስለምንውል በእያንዳንዱ ቀን የተወሰነ መጠን እየቀንስን ለመሄድ እንሞክር፤ ለሱ የምናወጣውን ገንዘብ እንመፅውተው። በእያንዳንዱ ጥረታችን አጅር ይኖረዋል ኢንሻአላህ። ስለዚ ባሁኑ ረመዳን ከነዚህ ቻሌንጆች አንዱን ተቀላቅለን ለመመፅወት በኒ'ያ እንነሳ..... ኢንሻላህ?"
"ኢንሻአላህ" በጋራ መለስን። ዞር ብዬ ጋሼን ተመለከተኳቸው.... ከገቡበት መጥፎ ልማድ ለመውጣት የተወሰነ ተስፋ የታየኝ መሰለኝ።
"ኸይር..... የዛሬውን ስብስባችንን እዚህ ጋር እናጠቃለው። ቅድም ሳንጀምር በፊት አንድ ወንድማችን 20 ቁርዐኖች አምጥቶ ሰቶናል አላህ ይስጠው፤ ለእህቱ ዱዐ እንድናደርግለት ጠይቋል። አላህ ሃጃዋን ይፈርጅላት.... ጭንቀቷንም ያግራላት፤ በዱዐችን እናስታውሳት። ለወንድማቹ ጭንቀቱን ከምታስወግዱበት መንገድ አንዱ ከልባቹ ዱዐ ማድረግም ጭምር ነው። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን.... ወሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።" ንግግራቸውን አጠቃለሉ። ሸይኹ ሳልጠይቃቸው የሰዐዳን ሃጃ ለሁሉም ዱዐ ማስጠየቃቸው ገረመኝ፤ እስከዛሬ ለኔና ለራቢ ዱዐ ሳስደርግ ይህ ሆኖ አያውቅም። ምን አይነት ዱዐ ብታደርግ ነው አላህ ወዷት እንዲ ባለ ሰፊ ጀመዐ መሃል ለዱዐ ስሟ እንዲነሳላት ያጫት? ከራሴ ጋር ይሄን አጋጣሚ በማስተንተን ውስጥ ሳለሁ የዒሻዕ አዛን ተሰማ.... ዛሬ ጋሼም ለመሄድ አልወተወቱኝም። ሳንነጋገር በልቦቻችን ዒሻዕን ሰግደን ለመውጣት ተስማማን።
.
.
ይቀጥላል...❶❹

@sineislam
1.0K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 09:24:24 ጁመአ

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ። [ሱረቱ አል-አሕዛብ,56]

እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚያስከፉ በቅርቢቱ ዓለም በመጨረሻይቱም አላህ ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም አዋራጅን ቅጣት ደግሶላቸዋል፡፡➎➐
አላህ ሆይ! በነብዩ ላይ ሰላምታ አውርድ፡፡ ሰላም አስፍንም፡፡››
"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"

@sineislam @sineislam
2.3K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:13:14 ፈዳኢል...
(ክፍል አስራ ሁለት)
.
.
ዙህርን ሃጂ አህመድ መህሊ መስጂድ ከሰገድን በኋላ ቅድም ለጋሼ ወዳሳየኋቸው አድራሻ አመራን፤ ቦሌ። እዚ አካባቢ ሃብታሞች ባሉበት ደሃዎችም እንደሚኖሩ ማሰብ ከባድ ነው።
"አድራሻውን ግን እርግጠኛ ናት?" ጋሼ መንገዱን ከጀመርን ጀምሮ ይሄን ሲጠይቁን 3ኛቸው ነው።
"እንግዲ ብትሆን ነዋ.... ምነው ግን?"
"አይ የነበሩት የጨረቃ ቤቶች ስለተነሱ ማንም የለም ሲባል ነው የማውቀው።"
"እርግጠኛ ኖት?... ታዲያ ወይ ልደውልላት ለሰዐዳ?"
"ደርሰናል እሱስ.... ግን ደውልላት..." መኪናውን አንድ ጥግ ላይ አቁመውት ወረዱ። ለሰዐዳ ደወልኩላት.... ጋሼ ልክ ነበር፤ ሰፈር ቀይራለች። ሆኖም 24 ጋር ካሉት ኮንዶሚንየም ቤቶች አንዱ ጋር ተመላላሽ ስለምትሰራ ቅርብ መሆኗን ነገረችኝ። የቆምንበት አካባቢ ጋር በትልቁ የተለጠፈ የካፌ ስም አንብቤ እንደ ምልክት ነገርኳት፤ ራሷ ብትመጣ የተሻለ እንደሚሆን ነግራኝ ስልኩ ተዘጋ።
.
ጋሼ ከተመለሱ በኋላ ስለሰፈሩ እያጫወቱኝ መጠበቃችንን ቀጠልን። በመሃል ስልክ ተደወለልኝ.... ሰዐዳ ነበረች። በመስኮት ስመለከት ካፌው ጋር ግራ በመጋባት የቆመች ሴት ስልክ እያወራች ነበር፤ እሷ መሆኗን ካረጋገጥኩ በኋላ ወደ መኪናው እንድትጠጋ ነገርኳት።
"አሰላሙ ዐለይኪ.... ነይ ግቢ..." የመኪናውን መስታወት አውርጄ አናገርኳት።
"አ...አይ.... እቸኩላለሁ.." ሰላምታዬን ሳትመልስ አጭር መልስ ሰጠችኝ፤ ፊቷ ላይ ምቾት አይነበብም። ለነገሩ ሁለት ወንዶች ያሉበት መኪና ውስጥ እንድትገባ መጠየቄ ድፍረት ሳይሆን አይቀርም። በራሴ አፍሬ መኪናውን ከፍቼ ወረድኩ፤ በሌላኛው እጄ ፖስታውን እንደያዝኩ ነው። በመጠኑ ወደ ኋላ ሸሸት ያለች መሰለኝ.... አይኔን በሰበርኩበት እጆቿ ያለማቋረጥ ሲፍተለተሉ ያስታውቃሉ። የለበሰችው ሰፊ ሻርፕ የሰውነቷን ቅርፅ እንጂ መጎሳቆሏን አልደበቀም።
"ወይ... ወደ ካፌው እንግባ..." ባለሁበት ቆሜ ማውራት ጀመርኩ።
"አይ.... እዚሁ ተመችቶኛል።"
"መርሃባ እሺ.... ራቢያ ናት የላከችኝ፤ እኔ ባለቤቷ ነኝ... ሙስዐብ። ይሄንን እንዳደርስልሽ ትፈልጋለች..." የያዝኩትን ፖስታ አቀበልኳት። ከተቀበለችኝ በኋላ ከፍታም አላየችውም፤ አመስግናኝ ወደ ሻርፗ ስር ሸጎጠችው።
"....እሺ አላህ ያክብርልኝ በላት። አላህ ያስታውሳት.... ከጨረስን ልሂድ በቃ፤ አፉ በሉኝ..." በሩጫና እርምጃ መሃል ባለ አረማመድ ፈጠን እያለች መንገዷን ጀመረች። ያላት መርበትበት ከስካሁኖቹ ይለያል። ፖስታውን ሳቀብላት ከውስጡ አውጥቼ ያስቀረሁትን ካርድ ማንበብ ጀመርኩ... ሰሙ ሳይላቀቅ እንዲደርሳት በሚል ራሷ እስክትከፍተው ከጠበኳት እንደ ረሻድ እድል ሳትሰጠኝ ልትወስደው እንደምትችል በማሰብ ነበር ያወጣሁት።
.
<<አሰላሙ ዐለይኪ ሰዐዲ.... ራቢያ ነኝ፤ አወቅሺኝ? አፉ በዪኝ በጣም ሳልጠፋብሽ አልቀረሁም.... ያንቺ ሃጃ ከኔ ቢበልጥም አልተመቻቸልኝም ነበር። ገንዘቡ ያን ያህል ብዙ እንዳልሆነ አውቃለሁ.... ግን የሚመጣውን የበረካ ወር ቤት ለቤት እየተዘዋወርሽ ልብስ ከማጠቡ አርፈሽ በዒባዳ እንድታሳልፊው በማሰብ ነው። ረመዳን ልመናሽ ይበልጥ ተቀባይነት የሚያገኝበት ነው ሰዐዲ.... በተቻለሽ አቅም ፈርድ ሰላቶችንም ለይልንም ጨምረሽ ለመቆም ሞክሪ፤ በእርግጠኛነት በአንዱ የዱዐሽን ምላሽ ታያለሽ። ያኔ ቤትሽ ስመጣ የጡሩሲና አዛን እና ስግደት ከቤትሽ ሆነሽ ይሰማ ነበር፤ ልሂድ ብትዪ አቡበከር ጋር ፀብ ውስጥ እንደምትገቢ ይገባኛል.... ግን በቻልሽው አቅም እሱ አምሽቶ እስኪገባ ተራዊህን ከቤትሽም ሆነሽ ስገጂ። <የሶስት ሰወች ዱዓ ተቀባይነት አለው፣ ወላጅ ለልጁ የሚያደርገው ዱዓ፣ ፆመኛ የሚያደርገው ዱዓ እና ሙሳፊር የሚያደርገው ዱዓ> አይደል ሀዲሱ የሚለን? አቡበከርንም እንዲሰግድና ተራዊህ እንዲሄድ አበረታቺው፤ ዱዐ አድረጊለት። ያንቺን መበ'ደል እንዲበቀልልሽ ሳይሆን እንዲምረው፤ ከሱሶቹ እንዲመልሰው ዱዐ አድርጊ። ምናልባት በዚ ወር ባንቺ ሰላትና ዱዐ ትዳራቹ ውስጥ ያለው ጭቅጭቅ የሚስተካከልበት ይሆናል። ራህማ እና መተሳሰብ ያለበትን ቤት መላዒካዎችም ያርፉበታል። አብሽሪ በዱዐ ሁሉም ያልፋል.... አደራ ይሄ ወር እንዳለፉት በእምባና በጭንቀት፤ በስራም እንዳይባክን። ገንዘቡን ወደ ባንክ አስገቢው፤ ከየት አመጣሽው የሚል ነገርም ላጭርብሽ አልፈልግም። አፉ በዪኝ.....በቅርቡ በአካል እስክዘይርሽ በዱዐዬ አልረሳሽም፤ አንቺም በዱዐሽ አስታውሺን። ወሰላሙ አለይኪ ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።>>
.
.....የመልዕክቱ ማብቂያ ነበር። ስለኛ ትዳር በግልፅ አንስታ ዱዐ ከመጠየቅ እንኳን ያቀባት ይመስላል። ሰዐዳ የሚታይባት ፍርሃት የሃያዕ ብቻ ሳይሆን ባለችበት የዱላና የጭንቅ ህይወት መሆኑን ገመትኩ። ከሱም በላይ የምታጥብላቸው ሰዎችስ ስራዋን እንዳይከለክሏት ፈርታ ቢሆን? ኒያዬ የሰውን ገመና ማንበብ አልነበረም..... የሰዐዳ ተስፋ የሚሆነውን መልዕክት መስረቅም አልነበረም። ራቢም ብትሆን እኔ እንደማልከፍታቸው ስለመነች መሆኑን በዝርዝር የምትፅፈው የተገለፀልኝ አሁን ነበር። መልዕክቶቿ ተራ ማነቃቂያዎችም ብቻ ሳይሆኑ ህይወታቸውን የማቃኛም ብቸኛ መላዎች ናቸው። ስለሷ ለማወቅ በሚል ካመነችኝ በተቃራኒ ሆኜ መገኘቴ አሳፈረኝ። በትህትና ከመጠየቅ ወረቀቱን ወደማስቀረት የሄድኩበት ለውጥ ለራሴም አስደነገጠኝ....
"ሰዐዳ..." ሳላስበው ከአፌ የወጣ ቃል ነበር። ወረቀቱን ለሷ ማድረስ እንዳለብኝ ትዝ ሲለኝ ቀና ብዬ ፈለኳት.... መንገዱ ቀጥ ያለ ረዥም በመሆኑ እስካልታጠፈች በመኪና እንደምንደርስባት አምኜ ወደ መኪናው ተመለስኩ።
.
"ሄሎ.... ሰዐዳ...." ጋሼ መኪናውን ማዞር እንደጀመሩ ደወልኩላት። "እምምም... ቤት ካልደረሽ ሌላ የቀረ መልዕክትም ነበር።.... እሺ.... እዛው ቁሚ በቃ አንቆይም..." ስልኩን ዘግቼ የመንገዱን ዳር መመልከት ጀመርኩ። ከሩቁ ቅድም ያየሁትን ሻርፕ የተመለከትኩ መሰለኝ። እንደደረስን እንደቅድሙ ሁሉ መልዕክቱን ሰጠኋት....እፎይታ ተሰማኝ። ሳላስበው አይኖቼ ለአፍታ ወደ ፊቷ ተሰነዘሩ፤ የቀሉ አይኖች፣ ቀናትን ያስቆጠረ የሚመስል የደበዘዘ ብልዝ.... ፊቷ ብዙ ይናገራል። ምንም ሳትናገር ተቀብላኝ መንገዷን ቀጠለች፤ ባሁኑ የምትታየኝ ህመሟ ሌሎች የዱንያ ማታለያዎችን እንዳታይ የከለሏት ሴት ነበረች። የቀሩትን ቤቶች ስለ ራቢ ለማወቅ ሳይሆን ለችግራቸው መፍትሄ ለመሆን ስል በፍጥነት ለማዳረስ ወሰንኩ።
.
.
ይቀጥላል...❶❸

@sineislam
2.5K views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ