Get Mystery Box with random crypto!

Agape Love❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ shineyourbrightt — Agape Love❤ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ shineyourbrightt — Agape Love❤
የሰርጥ አድራሻ: @shineyourbrightt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.50K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
☞ክርስቶስ ብቻ ይሰበካል
☞ስነጽሁፍና ሌሎችም ክርስቶስ ተኮር ስራዎች ይቀርባሉ፡፡
አብረን ለመስራት አሁኑኑ ይቀላቀሉ ለሌሎችም ያካፍሉ፡፡
@shineyourbrightt ብርሃናችን እንግለጠው፡፡
"አላማችን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡"
❀ብርሃናችሁ ለአለም ሁሉ ይብራ!❀
ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ
👇👇👇
Channel Creator @zi4me
Call: 251922732143
ተጠቀሙ

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-14 21:59:18 ስለ ጉራጊኛው ይቅርታ ከዛሬ 10 አመት በፊት ነፍሴ የሚያርፍባቸውና የምፅናናባው ለኔ ትልቅ ስፍራ ስለነበራቸው" የሻካች ኤማ ናሁቸር" በሚል ርእስ ዛሬም የማስታውሳት ካሴት የማታጫውተው ሬዴዮኔ እነዚህ
መልእክቶች የምታደርስልኝ ነበረች
96 viewsBini Tsidatu, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:37:17 @kibirenaw
106 viewsBini Tsidatu, 18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:45:01 #ለቻናላችን_ቤተሰቦቾ_በሙሉ

ተወዳጁ ፖስተር አገኘው ይደግ ከተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ በሁዋላ ዘማሪ ሳሚን አውርቶታል
#ዘማሪ ሳሚ በፍፁም መዝፈን እንደማይፈልግና ትላንት የሰጠውም interview ከመጠን በላይ ተስፋ ስለቆረጠና ምንም አማራጭ ስላጣ በባዶ ቤት ውስጥ መቀመጥ ራስ ምታት ሆኖበት ስለተጨነቀ መሆኑን ሰምተናል፥ ትንሽ ከተረጋጋም በሁዋላ ዩቲዩበሮችን እንዳትለቁት ቢላቸውም እነሱ ግን ከምንም ሳይቆጥሩት በንቀት መንፈስ ለቀውታል፥ እናም በአጠቃላይ አሁን ስላለበት አሳዛኝ ሁኔታ እንዲ ስል ለአገኘው አጫወተው፤ ከዚህ በፊት የኮተቤ ሙሉወንገል በቴክርስቲያን ምንም ደሞዝ አትከፍለኝም ነበር በወር ለትራንስፓርት ብለው የሚሰጡኝ 800 ብር የትኛውንም ጉድለተን አይሸፍንልኝም ነበር እርሱንም Covid ከገባ በሁዋላ አቆሙት:ቤት ክራይ መክፈል አቅቶን አከራዮቻችን ያለንን እቃ አውጥተው ሽጠው የቤት ኪራዩን ወሰዱ ባለቤተም የዲስክ መንሸራተት የሚባል በሽታ አስቸግሮአት ከስራ ተባራለች አሁን አንድ አመት ያልሞላው ልጄ ምግብ አቶ እጄ ላይ ሞቶ ከማይ ከ እናቱ ጋር ወደ ቤተሰቦቿ ልከአታለሁ፥ በዚህ ሁሉ ሳልፍ የተወሰኑ አገልጋዮችን ለማውራት ሞክረ ነበር ሊረዱኝ ግን ፍቃደኛ አልነበሩም! በፍፁም የልጅነት እና ወጣትነት አባተን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መካድ አልፈልግም ቅዱሳን እኔ ላይ ከምትፈርዱ በየፀሎታችሁ አስቡኝ ብሎአል!
#አስተዳድራታለው ብዬ ከቤተሰቦቿ በ ክብር የወሰድኳት ሚስቴ አቅም አጥቼ ወደ እናቷ ቤት ስትመለስ እንደማየት ውርዴት የለም ብቻ ፀልዩልኝ በፍፁም እጄን አልሰጥም ጌታ አለልኝ ማለቱን ሰምተናል!
በዘላቂነት እንዴት መረዳት እንዳለበት እየተነጋገርን ስለሆነ የደረስንበትን ውሳኔ በዚህ ሚዲያ እና በተወሰኑ ታማኝ ክርስቲያን ሚዲያዎች እንገልፃለን! ለጊዜው በቀጥታ ዘማሪ ሳሚን እስከአላገኛችሁት ድረስ ገንዘባችሁን ለማንም አትላኩ! ለማጭበርበር የተዘጋጁ መኖራቸውን ደርሰንበታል!
ይሄን በመስማቴ ደስተኛ ነኝ



@Shineyourbrightt
129 viewsአራባሪየና!, edited  05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:11:19
ሰበር እና #አስደሳች ዜና

#አስደሳች ዜና ሳሚ ወደ ልቡ ተመልሷል ፣ በፍጹም መዝፈን እንደማይፈልግ ምላሽም ሰጥቷል ።
ያንን ቃለመጠይቅ ያደረገው በጣም ተስፋ ከመቁረጡም እንደተነሳ ገልጿል ።
የሳተ ይመለሳል የወደቀም ይነሳል !
ወንድማችንን ጌታ አጽንቶልናል ጠላትም እንዳሰበው አልሆነለትም። ፓስተር አገኘሁ ይደግ እግዚአብሔር ይባርክህ በጣም እናመሰግናለን ቅዱሳን አሁንም ጸሎታችሁ ይቀጥል ።
ስለ ወንድማችን የጸለያቹ ወንድም እህቶቼ ጌታ ብርክርክ ያርጋቹ ተባርካችኋልም።
በፍርድ ወንበር የተቀመጣቹ ግን ዋ!
ያስተዛዝባል!

ክብሩን ሁሉ ጌታ ይውሰደው!

@Shineyourbrightt
156 viewsአራባሪየና!, edited  20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 16:46:04 ከመቶ መጎች አንዱ ወንድሜ ሳሚ ነው። ቀርቤ አውቀዋለሁ ውስጡ ለጌታ ያለው ቦታ የተለየ ነው። ሰው ይደክማል እንጂ ጠፍቶ አይቀርም። እኔ እያለሁ አንተ እያለህ አንቺ እያለሽ ወንድማችን አይጠፋም።
ውድ ቤተሰቦቻችን ለወንድማችን ሳሚ ማድረግ ያለብንን ከጸሎት ጀምሮ ለማድረግ ኮሜንት ላይ ጻፋልን ወይም @zi4me ወይም @Meyabot ላይ inbox አርጉን

Go ወደ መፍትሄ
152 viewsአራባሪየና!, edited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:52:49
#ሞራሉ_አለን?
ቤተክርስቲያን ልጆቼ የት ወደቁ ምን ላይ ናቸው ብላ መከታተል በተወችበት ዘመን፣ የቸርች መሪዎች የመሬት ጉዳይ ብቻ በሚያስጨንቃቸው ዘመን፣ ገንዘብ ያለው ብቻ በሚፈለግበት ዘመን ይሄንን ሰው ዘፋኝ ሆንክ ብለን የመክሰስ ሞራሉ አለን? ያሳለፈውን እናውቃለን?
ለማንኛውም ወንድማችን ሳሚ የዘፈኑን አለም መርጦ ሄዷል። በምንም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ ከጌታጋ ፀንተን መቆም ቢገባንም ይሄ ሰው ግን ይሄንን ያደረገበት እጅግ የሚያሳዝንና ልብ የሚሰብር ምክንያት አለው።
የምንችል እንደግብዝ ፈሪሳዊ ከምንፈርድበት ተንበርክከን እንፀልይለት።


@Shineyourbrightt
167 viewsአራባሪየና!, edited  11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 07:47:34 * እንደምትችል ታምናለህ? *

እንደምትችል እመን እናም እዚያ ለመድረስ ግማሽ መንገድ ተጉዘሃል ይለናል ቴዎዶር ሩዝቬልት።

እምነት በጣም ሃያል ነገር ነው። አንድን ነገር ለማሳካት እንደምትችል ካመንክ የስኬትህን 50 ከመቶ ተጉዘሃል። ቀሪውን መጓዝ ደግሞ ቀላል ነው። ምክንያቱም ዋናው ጉዳይ እንደምታሳካ ታምናለህ ወይ? የሚለው ስለሆነ ነው።

ካመንክ ትደርሳለህ ካላመንክ አትደርስም። አየህ ወዳጄ ግብ ማሰቀመጥ መልካም ቢሆንም ያቀድከው እንደሚሳካ ካላመንክ ባታቅደው ይሻላል። እመን ወዳጄ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
@Kibirenaw
278 viewsBini Tsidatu, 04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 14:35:03 እንዳንበሳ መከበርና መፈራት ያማረው ውሻ አንድ ቀን ጏደኞቹን ይሰበስብና እንዲ ይላቸው ጀመር እኛ ውሾች ሰዎች የሚንቁንና የማያከብሩን ማንም ቡችቡች ብሎ ሲጠራን እሮጠን ስለምንሄድ ነው ይህው ከዛሬ ጀምሮ ማንም ቡች ቡች ስላለን እሮጦ መሄድ ይበቃል ብሎ ተናግሮ ሳይጨርስ ድንገት እንዱ ቡች ቡች ሲል ምላሱን እያለከለከ ሮጠ::

ታዲያ በዚህ ዘመን ቡቺ ብቻ ሳይሆን እኛስ የተናገርነውን የሰበክነውን የዘመርነውን እንኖር ይሆንን??? ምስቦኮቻችንና ሜዲያችን በሚያስደምም የቃልና የዝማሬ ትዕይንት ተሞልቶ መሬት ላይ የወረደው ኖሮ በእርግጥ አንድ ነውን? የሰው ጆሮ ጠቦ አፉ የፋ እስኪመስል ሁሉ ተናጋሪ ሁሉ አዋቂ ሁሉ ልሰማ ባይ የሆነም አይደል? አንድ ቀን ባወቅነውና ባስተማርነው ልክ በጌታ ፊት መጠየቅ እንዳለ ሳንረሳ መኖር ከብዙ ፍርድ ያድነናል::
ጌታችን እየሱስ ሲናገር እንዲህ አለ ~ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥
ሉቃ 12: 48
~ ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ያዕ 1:19


ኢየሩሳሌም ነጊያ

@Shineyourbrightt
456 viewsአራባሪየና!, edited  11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 13:27:03 አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች ፦
አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመፀለይሽ ምን # ትርፍ ታገኛለሽ?
……………………………………………………
እሷም መለሰች ፦
ብዙውን ጊዜ"ምንም አላገኘሁም"ይልቁንም ነገሮችን አጣለሁ"
እናም ወደ እግዚአብሔር በመፀለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፦
"ኩራቴን" አጣሁ።
"ትዕቢቴን" አጣሁ።
"ስግብግብነቴን" አጣሁ።
"ክፉ ፍላጎቴን" አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
"ፍትወትን" አጣሁ።
"የመዋሸት ደስታን" አጣሁ።
"የሀጢአትን ጣዕም" አጣሁ።
"ተስፋ መቁረጥን" አጣሁ።
ሀያላን በፊቱ መገኘት ሁሌም ማትረፍ ነውና ጥያቄዎቻችሁ ያልተመለሱ ቢመስሏችሁ
እንኳን ከእግዚአብሔር ፊት አትታጡ!!
ስላጣችኋቸው ነገርሮች እግዚአብሔርን አመስግኑ!!


@Shineyourbrightt
569 viewsአራባሪየና!, edited  10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 16:50:34 ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለህ ከመሾምህ በፊት ነቢዮ ኢሳይያስ እኛ አሁን እየታነጽንበት ላለው
ወንጌል በመጋዝ ሁለት ቦታ ተሰንጥቆ መሞቱን ታውቃለህ!?
ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለህ ከመሾምህ በፊት ለዚህ የወንጌል እውነት ሐዋሪያው ዮሐንስ
በሚፈላ ዘይት በርሜል ውስጥ ተዘፍዝፎ መሞቱን: እንዲሁም ሐዋሪያው ጴጥሮስ "እንደ
ጌታዬ በቁሜ አልሰቀልም" ብሎ ወደታች ተዘቅዝቆ በመሰቀል መሞቱን ታውቃለህ!?
የጥንቱ ሐዋሪያት ዘመናዊ ውድ መኪና የመንዳት: ዘመናዊ ቪላ የመስራት: የቱርክ ሱፍና
የፈረንሳይ ሽቶ የመቀባት አባዜና ጥማት አልነበረባቸውም::
የጥንቱ ሐዋሪያት በጥቁር ገበያ በተጭበረበረ ዶላር: ዮሮና ፓውንድ: ከድሆች መቀነት
በተዘረፈ ብር ቢሊየነር የመሆን ሕልም አልነበራቸውም::
የጥንቱ ሐዋሪያት ዘይት: ውኃና ጨርቃ ጨርቅ ሽጠው ባለጠጋ የመሆን ሕልም
አልነበራቸውም:: ትልልቅ አዳራሾች አልገነቡም:: የተሸቃቀጠ ወንጌል ሰብከው ዝና
አላካበቱም:: ሐሰትን ከእውነት ቀላቅለው እንደ ሸቀጥ ለገበያ አላቀረቡም!!
ዛሬ ዛሬ ነቢይ: ሐዋሪያ: ቢሾፕ እያሉ የተለያዩ ስሞችን ለራሳቸው የሚሰጡ ሰዎች የስሙን
ዋጋና ክብር አላወቁም:: ስሙን የያዙ የጥንቱ እውነተኛ አገልጋዮች ስሙ የሚጠይቀውን
እውነተኛ የሕይወት መስዋዕትነት እንደከፈሉ እነዚህ መክፈል አይፈልጉም!!
ዛሬ ማንም ስሙን የያዘው ሰው ስሙ ለሚጣይቀው እውነት ኑሮና ሕይወት መከራ መቀበል:
ዋጋ መክፈል አይፈልግም:: የገዛ ምኞታቸው አገልጋይ እንደመሆናቸው መጠን
እግዚአብሔርን ማገልገል ለሚያመጣው መስዋዕትነት ዝግጁ አይደሉም:: ፈቃደኛም
አይሆኑም!!
የጥንቱ ነቢያትና ሐዋርያት ዓለማና ግብ ለወንጌሉ እውነት መጋደልና ነፍሳቸውን መስጠት
ነው:: የዘወትር ትጋታቸው ነፍሳትን ለጌታ መመረክ: የክርስቶስ ክብር: ደቀ መዝሙራዊ
ሕይወትና ተግባራዊ ክርስትና ነው!!
ከ Alex Zetsa'at ተባረክ brother


@Shineyourbrightt
602 viewsአራባሪየና!, edited  13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ