Get Mystery Box with random crypto!

Agape Love❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ shineyourbrightt — Agape Love❤ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ shineyourbrightt — Agape Love❤
የሰርጥ አድራሻ: @shineyourbrightt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.50K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
☞ክርስቶስ ብቻ ይሰበካል
☞ስነጽሁፍና ሌሎችም ክርስቶስ ተኮር ስራዎች ይቀርባሉ፡፡
አብረን ለመስራት አሁኑኑ ይቀላቀሉ ለሌሎችም ያካፍሉ፡፡
@shineyourbrightt ብርሃናችን እንግለጠው፡፡
"አላማችን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡"
❀ብርሃናችሁ ለአለም ሁሉ ይብራ!❀
ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ
👇👇👇
Channel Creator @zi4me
Call: 251922732143
ተጠቀሙ

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-05-31 16:50:32
302 viewsአራባሪየና!, 13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 19:41:50 በክርስቶስ ነህ ወይስ ጴንጤ ነህ?
**
ወዳጄ ሆይ.......
ክርስቶስ የሞተልህ ጴንጤ እንድትሆን ሳይሆን በክርስቶስ እንድትሆን ነው!!

እግዚአብሔር በክርስቶስ መሆንህን እንጂ ጴንጤነትህን አያውቀውም!!

በክርስቶስ ሆነህ እንጂ ጴንጤ ሆነህ ባለመፍትሄ አትሆንም!!

እግዚአብሔር ሁሉን በልጁ የማድረግ እንጂ ሁሉን ጴንጤ የማድረግ ሀሳብ የለውም!!

በክርስቶስ በመሆንህ ሕይወት ይኖርሃል ጴንጤ በመሆንህ ኃይማኖት ይኖርሃል!!

ወልድ ያለው ሕይወት እንጂ ኃይማኖት የለውም!!

የወንጌል እንቅፋትና የሰው ትልቁ ጥላት ኃይማኖት ነው!!

ኃይማኖት ነፍስ የወንጌሉን ብርሃን እንዳትረዳ የሚጋርድ ጥልቅ ጨለማ ነው!!

ክርስቶስ ሕይወትን እንጂ ኃይማኖትን አልሰጠም!!

በኃይማኖት ነፃነት በክርስቶስ ባርነት የለም!!

በኃይማኖት ዳንኩ የሚል በክርስቶስ ጠፋሁ የሚል የለም!!

በኃይማኖት መፅደቁ የሚሰማው በክርስቶስ ኩነኔ የሚሰማው የለም!!

በኃይማኖት እርሱ ማለት በክርስቶስ እኔ ማለት የለም!!

በኃይማኖት የሚያርፍ በክርስቶስ የሚቅበዘበዝ የለም!!

በኃይማኖት ድፍረት በክርስቶስ ፍርሀት የለም!!

ኢየሱስ የእምነታችን ራስና ፈጻሚ እንጂ የክርስትና ኃይማኖት መስራች አይደለም!!

ያመኑበትን ሁሉ ሕይወት ሰጣቸው እንጂ ኃይማኖት አልሰጣቸውም!!

ሕይወት ያለው ኃይማኖት የለውም!!..............ሕይወት ክርስቶስ ነው!!

ጴንጤ መሆንህ በክርስቶስ የመሆንህ ዋስትና አይደለም!!

እናልህ ወዳጄ በክርስቶስ ነህ ወይስ ጴንጤ ነህ?
ማስታወሻ

ጴንጤ የሚለው ሁሉንም ሐይማኖት ይወክላል!

#በክርስቶስ_ነኝ!! #In_Christ!!


@Shineyourbrightt
376 viewsአራባሪየና!, edited  16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 00:58:46 ሰላምታ ሲጠየቅ በተለምዶ ሁሉም ሰው መልሱ ደህና ነኝ ነው! እየከፋው፣ እያዘነ፣ ውስጡ
ተጎድቶ፣ ለህይወት ትርጉም አጥቶ፣ ዲፕሬሽን ውስጥ ሆኖ፣ 'ደህና ነህ?' ስንለው ወግ
ነውና 'ደህና ነኝ!' ይላል! እያለቀሰ ብታገኘው 'ደህና ነኝ' ይልሀል! ቆዝሞ ብታገኘው 'ደህና
ነኝ!' ይልሀል ... ስንት የምናቃቸው ወጣቶች ዛሬ ሰላምታ ስንሰጣቸው 'ደህና ነኝ!'
ብለውን.. በንጋታው ራሳቸውን አጥፍተዋል! ስንቱ ለቅሶ ላይ ተገኝተን... ትላንትኮ፣ የዛሬ
ሳምንትኮ፣ የዛሬ ወር ኮ አጊኝቼው... 'ደህና ነኝ!' ብሎኝ ነበር... ምነው ለዚህ ውሳኔ
ያበቃውን ባማከረኝ ብለን አልቅሰናል ስንቱ ጠዋት 'ደህና ነኝ!' ብሎን ከሰዓት
ራሱን አጠፋ ተብለናል! ምክንያቱም እንዴት ነህ? ለሚለው የለመድነው፣ ያደግነው፣
'ደህና ነኝ!' እያልን ነው! መርምሮ፣ ቀርቦ፣ ያለንበትን ሁኔታ ተረድቶ፣ አጥብቆ ካልጠየቀን
'ደህና ነህ?' ለሚለው መልሱ የቱን ያህል ቢከፋን፣ ብናዝን፣ መልሱ ደህና ነኝ ነው! እስኪ
ራሳችንን እንጠይቅ?! ስንቱ ደህና አለመሆኑን እያወቅን.. 'ደህና ነኝ!' ስላለ ብቻ
አልፈነዋል.... ስንቱ ራሱን ሊያጠፋ በኪሱ መርዝ፣ ገመድ ይዞ 'ደህና ነኝ!' የሚል ቃል
እያወጣ... ደህና አለመሆኑ ሁኔታው እያሳበቀ አልፈነው የሞቱን ዜና ሰምተናል?! ደህና ነኝ!
ያለ ሁሉ ደህና ነው? ደህና ነኝ! የሚል ቃልስ ደህንነትን ይገልፃል?? ስለዚህ ምናልባት
ደህና ነኝ! ከሚለው ቃል ጀርባ ያለውን ህመም ተረድተን ወይም ገምተን.... ደህና መሆኑን
አጥበቀን ብንጠይቀው..... ደህና አለመሆኑን ነግሮን... ምናልባት ላለበት ችግር መፍትሔ
ማስቀመጥ ችለን ካለበት ዲፕሬሽን ወይም ራስ የማጥፋት ስሜት እንታደገው ይሆናል ኮ!
እስኪ እንጠይቅ.... ስንቱ ሀሳቡን፣ ጭንቀቱን፣ የሚያካፍለው አቶ ደህና ነኝ! እያለ አተነዋል!
ምናልባት ቤታችን ውስጥ አንድ ጣሪያ ስር እየኖርን.... ቀርቦ ባለመጠየቁ፣ አይዞህ
ያልፋል ባለመባሉ ከባድ ጊዜን ብቻውን እያሳለፈ ነው? ከጊዜ በኋላ ወይ በሽታ ላይ ወይ
ሞት ወስዶብናል? ብዙ ባለማውራታችን፣ ባለመወያየታችን፣ ባለመጠየቃችን፣
ባለመረዳታችን..... በአከባቢያችን ያለን ሰው እያጣን ነው? አሁን እየተበራከተ የመጣው
የወጣቶች ሱሳይድ ቀርቦ የሚጠይቃቸው አተው፣ ችግራቸው የሚያዋዩት አተው.... 'ደህና
ነህ?' 'ደህና ነኝ!' በሚል ቃል እያለፍናቸው በጣም ከተጎዱ በኋላ ያኔ ባወራሁት! ብለናል!
በተለይ ጉዳታቸውን፣ ስሜታቸውን፣ ስብራታቸውን... ለሰው ማዋየት ልምድ እንደሌላቸው
የምናውቃቸው.... ምናልባት የቤተሰባችን አካልም ሊሆን ይችላል እሱ/ሷ እንደዛ ነው!
እንደዛ ናት! ማውራት አትወድም! አይወድም! ብለን አንለፋቸው!! የሰው ልጅ በተፈጥሮ
መፍትሔ ማግኘት ባይችል እንኳ ... ችግሩን በአፅኖት የሚያዳምጠው ካገኘ ይቀለዋል!

መፍትሄው ኢየሱስ ነው
ማውራት የኛ ድርሻ ነው

Join and #Share
@shineyourbrightt
311 viewsአራባሪየና!, edited  21:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 00:58:43
284 viewsአራባሪየና!, 21:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 21:39:09




አይዞሽ ኢትዮጵያዬ
ዘማሪ ኤደንና ባለቤቷ
404 viewsአራባሪየና!, edited  18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 23:14:20
ለ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ!

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለምትሄዱ ተማሪዎች የሚቀበሏችሁ የካምፓስ ሕብረት መሪዎች እና አገልጋዮች አድራሻዎች

#EvaSUE #New_Students
ለበለጠ መረጃ እና ትምህርቶች ለማግኘት


@shineyourbrightt
537 viewsአራባሪየና!, edited  20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 23:14:20
ለመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ!

መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለምትሄዱ ተማሪዎች የሚቀበሏችሁ የካምፓስ ሕብረት መሪዎች እና አገልጋዮች አድራሻዎች

#EvaSUE #New_Students
ለበለጠ መረጃ እና ትምህርቶች ለማግኘት

@shineyourbrightt
453 viewsአራባሪየና!, edited  20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 23:14:20
ለቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ!

ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ ለምትሄዱ ተማሪዎች የሚቀበሏችሁ የካምፓስ ሕብረት መሪዎች እና አገልጋዮች አድራሻዎች

#EvaSUE #New_Students
ለበለጠ መረጃ እና ትምህርቶች ለማግኘት

@shineyourbrightt
378 viewsአራባሪየና!, edited  20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 23:14:20
ለጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ!

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለምትሄዱ ተማሪዎች የሚቀበሏችሁ የካምፓስ ሕብረት መሪዎች እና አገልጋዮች አድራሻዎች

#EvaSUE #New_Students
ለበለጠ መረጃ እና ትምህርቶች ለማግኘት

@shineyourbrightt
327 viewsአራባሪየና!, edited  20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 23:14:20
ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ!

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለምትሄዱ ተማሪዎች የሚቀበሏችሁ የካምፓስ ሕብረት መሪዎች እና አገልጋዮች አድራሻዎች

#EvaSUE #New_Students
ለበለጠ መረጃ እና ትምህርቶች ለማግኘት

@shineyourbrightt
284 viewsአራባሪየና!, edited  20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ