Get Mystery Box with random crypto!

Agape Love❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ shineyourbrightt — Agape Love❤ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ shineyourbrightt — Agape Love❤
የሰርጥ አድራሻ: @shineyourbrightt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.50K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
☞ክርስቶስ ብቻ ይሰበካል
☞ስነጽሁፍና ሌሎችም ክርስቶስ ተኮር ስራዎች ይቀርባሉ፡፡
አብረን ለመስራት አሁኑኑ ይቀላቀሉ ለሌሎችም ያካፍሉ፡፡
@shineyourbrightt ብርሃናችን እንግለጠው፡፡
"አላማችን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡"
❀ብርሃናችሁ ለአለም ሁሉ ይብራ!❀
ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ
👇👇👇
Channel Creator @zi4me
Call: 251922732143
ተጠቀሙ

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 07:35:11 * ዕድልን ጠብቃት! *

ዕድል
ቱታ ስለለበሰች እና ሥራን ስለምትመስል ለብዙ ሰዎች አትገለጥም። ቶማስ ኤዲሰን

እንቅስቃሴ ላይ ከሆንክ ዕድልን በቀላሉ መለየትና መጠቀም ትችላለህ። እንዲሁ ቁጭ ብለህ የምትጠብቃት ከሆነ ግን እድልን አታገኛትም። ምክንያቱም ዕድል የምትገለጠው በእንቅስቃሴ ላይ ለሆኑ ሰዎች ብቻ ነው።

እናም ወዳጄ ሆይ ዕድለኛ ለመሆን የምትፈልግ ከሆነ ሁልጊዜም ሥራ ላይ መሆን አለብህ። ሥራ ላይ ሆንክ ማለት ዕድል እየጠበቅህ ነው ማለት ነው። እሷም አታሳፍርህም ትመጣልሃለች።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
@Kibirenaw
57 viewsBini Tsidatu, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:16:13 ታዋቂው ሰባኪና ጸሃፊ ሪክ ዋረን ከ43 አመታት አገልግሎት በኋላ የመጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ማቅረቡን ክርስቲያን ሄድ ላይንስ ዘገበ።
‘አላማ መር ህይወት’ የተሰኘው በበርካታ ቋንቋዎች የተተረጎመው ታዋቂ መጽሃፍ ጸሃፊ መጋቢ ሪክ ዋረን ለ43 አመታት የሳድል ባክ ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን የአገልግሎቱ መጨረሻው የሆነውን ስብከቱን ከ40 አመታት በፊት በአገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ ‘ህይወታችሁን ዘለአለማዊ ዋጋ ባለው ላይ አውሉት’ በማለት በድጋሚ ሰብኳል።
በአሜሪካ ካሊፎርኒያ የሚገኘው ሳድል ባክ ቤተክርስቲያን 40,000 አባላት ያሉት ሲሆን ከ 40 አመታት በፊት በፈረንጆቹ 1980 ዓ.ም በሪክ ዋረን እና ባለቤቱ ኬይ ዋረን በላግና ሂልስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረ ቤተክርስቲያን ነው።
መጋቢ ሪክ ዋረን የአገልግሎቱ መጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ያቀረበው በአንድ የቤተክርስቲያኒቱ አባል በተሰራውና በመጀመሪያዎቹ 15 ዓመታት ይጠቀምበት በነበረው የእንጨት ፑል ፒት ላይ ሲሆን "ለ43 ዓመታት እናንተን መውደድ፣ ለእናንተ መጸለይ፣ ማገልገል ፣ መቃብር አጠገብ ቆሜ ማጽናናት ፣ አልጋ አጠገብ ቆሜ ማበረታታት፣ ሰርጋችሁ ላይ መሰበክ ፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት መምከር እና ማስተማር እግዚአብሄር ለእኔ የሰጠኝ ትልቅ ዕድል ነበር በማለት ምዕመናኑን አመስግኗል።


@shineyourbrightt
105 viewsAbush, edited  07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:27:07
" ኢቫንጀሊካል ቲቪ "

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ኢቫንጀሊካል ቲቪ  ነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም የሙከራ ስርጭት እንደሚጀምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት አሳውቋል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው በቄስ ዶክተር ገመቺስ ደሰታ ባለቤትነት ስር የነበረ ሲሆን በቅርቡ ለኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብተክርስቲያናት ካውንስል ተበርክቷል።

ለ4 አመታት ያህል የስርጭት ላይ ቆይቶ የነበረው ጣቢያው ለ1 አመት ያህል ስርጭቱ ተቋርጦ ከቆየ በኃላ ወደ አየር ተመልሶ ነሃሴ 26/2014 ዓ.ም የሙከራ ስርጭቱን እንደሚጀምር ተገልጿል።

መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ መደበኛ ስርጭቱን ይጀምራልም ተብሏል።

ኢቫንጀሊካል ቲቪ መደበኛ ስርጭቱን ሲጀምር ልዩ ልዩ ትምህርቶች፥ ስብከቶች፥ ወቅታዊ ዝግጀቶች፥ ቶክ ሾዎች፥ እለታዊ ዜናዎችን ጨምሮ የተለያዩ አስተማሪና ገንቢ ዝግጅቶችን ለተመልካቾቹ እንደሚያቀርብ ለቲክቫህ በላከው መልዕክት ገልጿል።

የጣቢያው ስርጭት በኢትዮ ሳት- Frequency  11105  - Symbol rate 45000 - Polarization Horizontal እንደሚተላለፍም ተጠቁሟል።

@tikvahethiopia
44 viewsAbush, 12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 17:10:46 1500 አመት እድሜ ያለው የሐዋሪያው ጴጥሮስን መኖሪያ ቤት የሚጠቁም ጽሁፍ ማግኘታቸውን አርኬዎሎጂስቶች ገለጹ።
የእስራኤል እና የኣሜሪካ ኣርኪዎሎጂስቶች ቡድን በገሊላ ባህር ኣቅራቢያ ባደረጉት ቁፋሮ 1,500 አመታት እድሜ ያለው ህንጻው የሐዋሪያው ጴጥሮስ መኖሪያ ቤት በነበረበት ቦታ ላይ መሰራቱን የሚጠቁም ጽሁፍ አግኝተናል ብለዋል።
በግሪክ በተጻፈው በዚህ ጽሁፍ ላይ ‘ቆስጠንጢኖስ የክርስቶስ ኣገልጋይ’ የሚል በ4ተኛው ክፍለ ዘመን ክርስትናን የተቀበለው የሮማ ንጉሰ ነገስት ስም የሚጠቅስ ቃላት የተጻፈ ሲሆን ‘የሰማያዊ ሐዋሪያት መሪና አለቃ” የሚል ስም አንደተካተተበት ተገልጿል።
ይህ ‘የሐዋሪያት መሪና ኣለቃ’ የሚለው መጠሪያ የቤዛንታይን ክርስቲያን ጸሃፊዎች ሐዋሪያው ጴጥሮስን ለመግለጽ የሚጠቀሙበት መጠሪያ እንደነበር ዜናው ጠቅሷል።
ቁፋሮውን ያደረጉት የእስራኤል ኪነሬት ኮሌጅ እና የኒውዮርክ ኒያክ ኮሌጅ አጥኚ ቡድን ኣባላት በጴጥሮስ እና በወንድሙ በእንድሪያን ቤቶች አቅራቢያ ተገንብቷል ተብሎ የሚታመን የቤዛንታይን ዘመን ቤተክርስቲያን ህንጻ ማግኘታቸውን ኣስታውቀው ነበር።ዜናውን የዘገበው ክርስቲያን ሄድ ላይንስ ነው።
163 viewsAbush, 14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 09:54:55 #ዘማሪ_በቸኒ_ከአምላኩ_በመሟገት_ያንጎራጎረው መዝሙር!!
ሰብ እንመታ የዝራኸወ
ብዘ ሽም ኦጣም የጫወደወ
እያም የኽንቃር አኸም ትኽንቃር
ጅጓረ ነረ ቢያሄ ደራር ታቅመና በፈር።
#ኧሰኸ ብቡን አንሰኽ የባሬ
.........
ጔቶ ኔኸኒ እያህ ሟን ነሬ።

#ተግር_ኧግረና የትኼታተሬ
......
የበረካና ቆፋ የኸረ
....#ዝሶህ_ንቅኒ...አፍካኒ
በመጨረሻም የመዝሙሩ መደምደሚያ
#ባኸ_ተስፋ ስርም ኤያርጪ
ያጠዊ ወዝገብ አኸ ትትቸን ሀዊም ይከፉቺ
#አት_ከረ_ከረ ነረ
#መከራና_ይትረሴ_ከረ
#ዮረ_እሀ_ኸማ_አዥን_ከረ!
ዘማሪው በመዝሙሩ የዳሰሰው ሀሳብ:-
መከራ ከመሬት አይበቅልም ከየት እንደመጣ ባላውቅም ጓዳዬ ውስጥ ሀገር ያወቀው ፀሀይም ያሞቀው ይባሱንም አንተም ዘንድ የታወቀ ደግሞም አድነኝ እያልኩ እየነገርኩህ ያለው ነው።
እኔ ለመከራ የተወለድኩ ይመስላል በእርግጥ ኢዮብ እንዲህ ብሎም አነበር? <<ምነው መከራዬ #ልክ_ሚዛን በኖረው በተመዘነ! ደግሞም ለስቃይ የተወለድኩ ይመስላል>>ይህ ቃል እኔም ደገምኩት ይለናል ዘማሪ በቸኒ
ሰዎች ሁሉ ለችግሬ ስም እያወጡ ይተርትበታል
እኔም አንገት እደፋለሁ ~ያስነውረኛል አይኖቼ ከማንባት~አንከቴም ከመድፋት~ልቤንም ከመቁዘም አልተቆጠቡም ጉልበቴ ዛለ ይባሱንም አሞቴ ፈሰሰ የምችለው ታገልኩ ወጣሁ ወረድኩኝ ወደ አንተም አቀረቡኩኝ መከራዬ ሲብስበት እንጂ ፈውሱን አልታየኝም
ብቻ ልጅህ እኮ ነኝ ምነው ተውከኝ ዝምታህ ገነነ ለመከራ የተወለድኩኝ ይመስል በዙርያዬ ከበበኝ እያለ ከአምላኩ እየተሟገተ ይዘምራል።
በነገራችን ላይ የመዝሙሩ እንጉርጎሮ በራሱ ሌላ ስሜት አለው
ስንኞቹ በሚገባ የተጠኑ ሰምና ወርቅ የታጨቁ በብዙ ጠንከር ባሉ ቃላቶች የታጀቡ ሲሆን
የመዝሙሩም ዘይ ደግሞ እጅጉ ጥበብ የተላበሰ ነው።
ከመዝሙሩ ስንኝ መሀል <<እያሽ አተጋ ቁርጠና አንጥሁም ባኸ ታመርሁም ይለናል!>> ምን ለማለት ፈልጎ ነው?? የኔና ያንተ ቁርኝነት የአባትነትና የልጅነት ዝምድና እንጂ አሁን ስለመጣብኝ መከራ አይደለም። ከመከራው ብታድነኝ መልካም ባታድነኝ እንኳን ያመንኩህ መከራው ስለመጣብኝ አይደለም ቀድሞም አባቴ ነህ ባታድነኝም አምኜሀለሁ አምላኬ ነህ እያለ ማዜሙ ነው!!
#የመዝሙሩ_መደምደምያና መቋጫ!
ኢዮብ 12:5 መከራህን ትረሳለህ እንዳለፈ ውሀ ታስታውሰዋለህ። የሚለውን ውድ የእግዚአብሔር ቃል ተስፋ በመስጠት ይቋጨዋልወይም ያስረዋል።
አሁን ካለበት ትልቁ ችግር ከእግዚአብሔር የትም ሳይሸሽ እሱን በመታመን እንደሚጠብቅ ነገሮቹን እንደሚያስተካክልለት እምነት በማኖር #አንድ _ቀን እንደሚመጣ የፀሀይ ወገግታ እንደሚያይ ተስፋ አድርጎ ይቋጫል። እባቆ እንዳለሁ <<በመጠበቅያዬ እጠባበቃለሁ የመድሀኒቴ አምላክ ተስፋ አድርለሁ >>
ዘማሪ በቸኒ የግል አቋሙ ኢዮብ በኖረው እየኖረ ይሆናል ልክ እንደ ኢዮብም በእግዚአብሔር ለመፅናት ለመኖር አቋሙ መፅሀፍ ቅዱስ መሰረት ባደረገ በዚህ መልክ አስቀምጧል እግዚአብሔር ይመልስለት ይርዳውም!
እኛም የዘመኑ ቅዱሳን ካለንበት መከራ እንድንታገስ ይህ መዝሙር ያስተምረናል ይመክረናልም እንስማው በሰማነውም እንድፀና ጌታ ይርዳን!!!
መዝ 34:6 ይህ ችግረኛ ጮኸ እግዚአብሔር ሰማው ከመከራም ሁሉ አዳነው!
ካለንበት ችግር ባያድነንም ፦ #ቁርጠንራ_ሀነም_ጔታ_አመነም።
መዝሙሩን እንድትሰሙት ግብዣዬ ነው

@shineyourbrightt


186 viewsAbush, 06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 09:54:55 @shineyourbrightt
135 viewsAbush, 06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 12:24:19 Guragigna
329 viewsአራባሪየና!, 09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 11:51:19
271 viewsአራባሪየና!, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 21:24:17 ሰዎች የነዱት ሰው ጸጸት

“ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!”

ብሮኒ በመጀመሪያ የምትተርከው ግሬስ ስለምትባል በታላቅ ጸጸት ውስጥ ስላለች ሴት ነው፡፡ ግሬስ ከሃምሳ አመታት በላይ በጋብቻ ሕይወት አሳልፋለች፡፡ ግሬስ ከልቧ ከምትወዳቸው ልጆቿ ከምታገኘው ደስታ ባሻገር “የአስራዎቹ” አመታት ወጣት የልጅ ልጆች ማግኘቷ የማይጠገብ የደስታ ምንጭ ሆኖላታል፡፡ ሆኖም፣ ይህ ደስታዋ ሙሉ እንዳይሆን ያደረገባት አንድ ጥቁር ነጥብ ግን በሕይወቷ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ የባለቤቷ ጉዳይ ነበር፡፡

አምባ ገነንና ጨካኝ የሆነው ባለቤቷ ባሳለፉት አመታት ውስጥ ጋብቻን አስቸጋሪ ያደረገባት ሰው ነበር፡፡ ወደጋብቻ ከመጡበት እለት ጀምሮ የቅስም ሰባሪ ቃላትና የተለያዩ የክፉ ተግባሮች ሰለባ አድርጓታል፡፡ ይህንንም ሁኔታውን ለማስተካከል መውሰድ የነበረባት እርምጃዎች እንዳሉ ብታውቅም፣ አንዱንም ምርጫ ለመውሰድ ድፍረቱ ሳይኖራት ለአመታት ተቀጥቅጣ ኖራለች፡፡ የባለቤቷ አስቸጋሪነት እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ ከጥቂት አመታት በፊት ከእርጅና የተነሳ በአረጋውያን መጦሪያ ማእከል በመግባቱ እርሷ ብቻ ሳትሆን ሁኔታውን የሚያወቁ ሰዎች ሁሉ ደስተኛ ነበሩ፡፡

ግሬስ በትዳር አመታቶቿ በሙሉ አንድ ቀን ከባሏ ክፉ ተጽእኖና ጨካኝ ሁኔታ ውጪ ሆና ደስተኛ ሕይወትን ለብቻዋ የምታጣጥምበትን ቀን እንደናፈቀች ኖራለች፡፡ አሁን በሰማኒያዎች አመታት ውስጥ ብትሆንም፣ ለእድሜዋ የሚመጥን መጠነኛ ጤንነትና የአካል ብቃት ነበራት፡፡ ወደማእከሉ ስትመጣ ወዲህ ወዲያ ለማለት የሚያበቃት አቅም ነበራት፡፡

እድሜዋን በሙሉ “በድብደባ” ያሳለፈው አእምሮዋ አሁን ለዚህ ሁኔታ ከዳረጋት ባለቤቷ በመለየቷ ምክንያት የእረፍትን ጭላንጭል ያየ ይመስላል፡፡ ለብዙ ዘመናት የጠበቀችውን ይህንን ለብቻ የመሆንና ካለምንም የውጪ ሰው ተጽእኖ የማሰብ “ነጻነት” ባገኘች በአጭር ጊዜ ውስጥ በድንገት በጽኑ መታመም ጀመረች፡፡ ሕመሙ ከተሰማት ከጥቂት ቀናት በኋላ ብዙም እድሜ እንደማይኖራት የሚጠቁም ምልክት ተገኘባት፡፡ ሁኔታውን እጅግ ልብን የሚሰብር ያደረገባት፣ የህመሙ መንስኤ ለብዙ አመታት ባለቤቷ በቤት ውስጥ ሲያጨስ ከነበረው የሲጃራ ጭስ እንደሆነም ማወቋ ነው፡፡ የበሽታው ደረጃ እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ በአንድ ወር ውስጥ አቅሟን ሁሉ አጥታ የአልጋ ቁራኛ ሆነች፡፡

“ለምን ያንን ዘመን ሁሉ እኔ ያመንኩበትንና የፈለግሁትን ነገር አላደረኩም? ለምን እንደፈለገ እንዲገዛኝና እንዲያንገላታኝ ፈቀድኩለት?” የሚሉት ጥያቄዎች ካለማቋረጥ ከግሬስ አንደበት ሲወጣ ይደመጥ ነበር፡፡ ያመነችበትን ትክክለኛ ሕይወት ለመኖር ድፍረት ሳይኖራት ዘመኗ በማለፉ ምክንያት በራሷ ላይ እጅግ በጣም ትበሳጭ ነበር፡፡ ልጆቿም ቢሆኑ እንደፈለገ ባደረጋትና ባደረገባት ባሏ ምክንያት ስላሳለፈችው ከባድ ሕይወት በግልጽ ይመሰክሩ ነበር፡፡

“አንቺ ማድረግ የምትፈልጊውን ትክክለኛ ነገር ከማድረግ ማንም ሰው እንዲከለክልሽ አትፍቀጂለት” በማለት ለተንከባካቢዋ ለብሮኒ ደጋግማ ትነግራት ነበር፡፡ “እባክሽን ይህንን እኔ የሰራሁትን ስህተት እንዳትሰሪ ቃል ግቢልኝ” በማለት ታሳስባት ነበር፡፡ አንድ ቀን ግሬስ ይህንኑ ምክር ደግማ ከነገረቻት በኋላ፣ ብሮኒ በእሺታ ምክሯን ተቀብላ እንደምትተገብረው ቃል በመግባት፣ “ራስን የመቻልና ያመኑበትን ትክክለኛ ነገር የማድረግን ትምህርት ያስተማረችኝ እናት ስለነበረችኝ እድለኛ ነኝ” በማለት ለግሬስ ነገረቻት፡፡

“አሁን ያለሁበትን ሁኔታ ተመልከችው” አለች፣ ግሬስ በመቀጠል፡፡ “በመሞት ላይ ነኝ፡፡ በሞት አፋፍ! እንዴት ቢሆን ነው እነዚያን አመታት ሁሉ ነጻና ራሴን የቻልኩ ሆኜ ለመሆን ስጠብቅ ኖሬ፣ አሁን እዚያ የተመኘሁበት የሕይወት ምእራፍ ላይ የደረስኩ ሲመስለኝ ጊዜው ያለፈብኝ?” እነዚህን መራራ ቃላት የሰማችው ብሮኒ የግሬስ ሁኔታና ጸጸት እንድታስብ ያነሳሳትን እውነታ ማሰላሰል ጀመረች፡፡

የደረሰችበትም ድምዳሜ፣ “ማንኛውም ሰው የራሱን አመለካከት ማወቅ፣ ትክክለኛውን መንገድ መለየትና ያንንም ያመነበትን ትክክለኛ ጎዳና መከተል አለበት” የሚል ነበር፡፡

ግሬስ በውስጧ የምታምንበትንና የሚሰማትን ስሜት ሳይሆን የዚያን ተቃራኒ ገጽታን በውጪ እያንጸባረቀች ዘመኗን አባከነች፡፡ እድሜዋን በሙሉ እርሷ ያመነችበትንና ከነበረባት የጭካኔ ሰለባ የሚያወጣትን ሕይወት ሳይሆን ሌሎች ሰዎች ከእርሷ የሚጠብቁባትን አይነት ሕይወት ስትኖር ካሳለፈች በኋላ፣ አሁን በመጨረሻዎቹ አመቶቿ ምርጫው የእርሷ እንደነበርና፣ ፍርሃት ከትክክለኛው ምርጫ እንደገታት ተገነዘበች፡፡ ራሷን ይቅር የማለት አስፈላጊነት ቢነገራትም እንኳን አሁን ሌላ ምርጫ ያለውን ሕይወት ለመኖር ጊዜው ያለፈባት መሆኑን ስታስብ ከአቅሟ በላይ የሆነ ስሜት ይወርሳታል፡፡

ብሮኒ በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎች በሚኖሩበት ማእከል ውስጥ ስትሰራ ካጠናቻቸው የሰዎች ጸጸቶች ይህኛው፣ “ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!” የሚለው ጸጸት አብዛኛዎቹን ሰዎች የሚያጠቃውና ቀንደኛው ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የሕልማቸውን ግማሽ እንኳን ሳያጣጥሙ ዘመናቸው የሚያልፈው ያመኑበትን ትክክለኛ የሕይወት አቅጣጫ ለመከተል ምርጫ እንዳላቸው ካለማወቅና ወይም ትክክለኛውን ምርጫ እያወቁ ያንን ምርጫ ለመከተል ጉልበት ከማጣት የተነሳ ነው፡፡
@Kibirenaw
266 viewsBini Tsidatu, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ