Get Mystery Box with random crypto!

የሀሳብ መንገድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yehasab_menged — የሀሳብ መንገድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yehasab_menged — የሀሳብ መንገድ
የሰርጥ አድራሻ: @yehasab_menged
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 979
የሰርጥ መግለጫ

ሀሳብ የየትኛውም ነገር መነሻ ነው፤
ሀሳብን አንዳችም የሚያቆመው ነገር የለም።
ልታገኙ ምትችሏቸው ፅሁፎች #1.አስገራሚ ግለ ታሪኮች
#2. አሁን ላይ ስለምንጠቀምባቸው ነገሮች ታሪካዊ አመጣጥ። #3.የስነ-ልቦና ምክሮች

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-30 10:15:31 አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣአልተፈቀደምና ስለነበር አንድ ሠራተኛ መጥቶ ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማኖሪያ እባክዎ ያንሱ ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡

‹‹ቢያነሱ ይሻላል እምቢ ካሉ ላለቃዬ እነግራለሁ›› ቢላቸውም ‹‹ሂድ ንገር›› አሉት፡፡ ሂዶ ሲነግረው አለቅየው መጥቶ "ያንሱ እንጂ ለምን አላነሳም ይላሉ?" ብሎ ቢነግራቸው ‹‹አላነሳም›› በሚለው ሐሳባቸው ጸንተው የማይበገሩ ሆኑበት፡፡

በመጨረሻም ለዋናው ኃላፊ ተነግሮት ይመጣና ‹‹ይህን ሻንጣ ያንሱ›› ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡ ዋና ኃላፊውም ‹‹ለምን?›› ሲላቸው ‹‹ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ፡፡ እኔ የቸገረኝ እኮ እስካሁን ድረስ ‹‹ለምን›› ብሎ የጠየቀኝ ባለመኖሩ ነበር፡፡ አንተ ‹‹ #ለምን ?›› ስላልከኝ አመሰግንናለሁ፡፡ በመሠረቱ ግን ሻንጣው የእኔ #አይደለም ሲሉት በመደነቅ ይቅርታ ጠየቃቸው፡፡

አብዛኞቻችን በሰዎች ላይ በደፈናው እንፈርዳለን፡፡ ነገር ግን ሁሌም በደፈናው ከመፍረዳችን በፊት "ለምን?" ብሎ መጠየቅም እውቀት ነው፡፡

@yehasab_menged
@yehasab_menged
305 viewsTeddy, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 22:22:59 Rophnan ft Julian marley
Merkeb
(አርምሞ)


የልቦናን መቅረፅ አብርቶ
የሚጓዝ መች ይሰምጣል ከቶ
ወደ ውስጥ ላየ ለገባው
መርከቡ ሰፊ ነው ከውሀው


ሰው ራሱን ካዳመጠ ከራስ ከታረቀ
የመኖርን ሚስጢር እውነት አወቀ
ልብ ላይ ሁሌም ድምፅ አለ እሱን ተከተለህ
በሶስተኛው በሙሉ አይንህ ታያለህ


@yehasab_menged
@yehasab_menged
399 viewsTeddy, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 07:09:32 ባውንድሪ ማለት ጨዋነትና ሚዛናዊነት ማለት ነው!

የአብዛኛው የግንኙነት ቀውስ የሚከተለው ሰዎች የራሳቸውን ባውንድሪ (ቀይ መስመር) በሚዛናዊነት ሳያስክብሩ ሲቀሩና ሰዎች እንደፈለጉ እንዲያደርጓቸው ሲፈቅዱ ነው፡፡ እነሱም ቢሆኑ የሰውን ባውንድሪ ካላከበሩ ለግንኙነት ቀውስ ምክንያት መሆናቸው አይቀርም፡፡

የራሳችንን ባውንድሪ አስከብረንና የሰውን አክብረን ልኩን ያወቀ ሕይወት እንዳንኖር የሚያደርጉን ደግሞ በሕብረተሰቡ መካከል የሚዘዋወሩ አፈ-ታሪዎች ናቸው፡፡

አፈ-ታሪክ #1:- “የቀይ መስመር ወሰን ማበጀት ማለት ራስ ወዳድነት ነው”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የቀይ መስመር ያለው ሰው ራስ ወዳድ ሳይሆን ራሱን በሚገባና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የሚያከብር ሰው ነው፡፡

አፈ-ታሪክ #2:- “የቀይ መስመር ሲኖረኝ ከሰዎች ጋር ያለኝ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ እውነታው፣ የቀይ መስመሩን በተገቢው መልኩ ያሰመረ ሰው ከሚኖረው መርህ-ተኮር ግንኙነት የተነሳ በአካባቢው ያሉ ጤና-ቢስ ሰዎችን ምቾት ላይሰጣቸው ቢችልም ሁኔታ ግን ጤና-ቢሶቹን ሲያርቃቸው፣ ጤናማዎቹን ግን የበለጠ ሊያቀርባቸው ይችላል፡፡

አፈ-ታሪክ #3:- “የቀይ መስመር ሲኖረኝ በሰዎች እንድጠላ እሆናለሁ”፡፡
ትክክል ነው፣ የቀይ መስመርን ማስመር የአንዳንዶችን ፍላጎት ስለሚነካ እንድንጠላ ቢያደርገንም፣ የቀይ መስመራችንን በማስመራችን ምክንያት ይልቁንም የበለጠ የሚያከብሩን ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡

አፈ-ታሪክ #4:- “የቀይ መስመርን ማስመር የስሜት ቀውስን ይፈጥርብኛል”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የቀይ መስመርን በማስመር ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት መርህ-ተኮርና የጋራ የሆነ መከባበር የሞላው እንዲሆን ማድረግ በመጀመሪያ ምቹ ስሜት ላይሰጠን ቢችልም ብዙም ሳይቆይ ግን ለሕይወታችን ጤና-ቢስ በሆኑ ግንኙነቶች ላይ ለመሰልጠን እንድንችል ስለሚያበቃን ደስተኞችና የተረጋጋን እንሆናለን፡፡

አፈ-ታሪክ #5:- “የቀይ መስመር ማስመር የሚባለው ሃሳብ ድርቅና ይመስላል”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የቀይ መስመር ሰው መሆን ማለት የመርህ ሰው በመሆን ከማን ጋር ምን አይነት መስመር ማስመር እንዳለብን ማወቅ ማለት ነው እንጂ ግትር፣ የማይደፈርና በአጥር የታጠረ ሕይወት መኖር ማለት አይደለም፡፡

@yehasab_menged
@yehasab_menged
148 viewsTeddy, 04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 06:32:29 መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ!

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መኖራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እሞታለሁ በሚልፍ ፍርሃት ታስራችሁ ከምትኖሩ ቀና ብላችሁ ብትኖሩ ይመረጣል፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መነገዳችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እከስራለሁ በሚል በፍርሃት ታስራችሁ ከምትነግዱ በአዎንታዊነት ተነቃቅታችሁ በትነግዱ ይሻላል፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መማራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ፈተና እወድቃለሁ በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምትማሩ እችለዋለሁ በሚል እምነትና ትጋት ብትማሩ የላቀ ነው፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም አንድን ሰው ማፍቀራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ይገፉኛል በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምታፈቅሩ ጤናማ በራስ መተማመን ይዛችሁ ብታፈቅሩ እጅግ ተመራጭ ነው፡፡

መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ! ቀና ብላችሁ መኖር ስትጀምሩ ደግሞ መፍራት ታቆማላችሁ!

@yehasab_menged
@yehasab_menged
324 viewsTeddy, 03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 21:49:59 አለመጣደፍ….!!!

የጥድፊያ መንፈስ ይታይብናል፡፡ በብዙ ነገሮች መረጋጋት የከዳን ይመስላል፡፡ ሰከን ማለትን ሳንጠላው አልቀረንም… ጥቂት አፍታ ወስዶ የሰዎችን የልብ መሻት፣ ወይም የነገሮችን ስረ-ግንድ ለማስተዋል የተዘጋጀን አልሆንም…፤ እጅግ ጥቂት የበለጡን ግለሰቦች ይኖራሉ፤ እነሱን አይመለከትም ጉዳየ፡፡

በብዛት ግን… የተጣደፈ ወጨፎ አይነት ባህሪ እየናጠን ነው……

ሳስብ የሚሰማኝ፤ ሰው ስሜቱን ሳይሻገር የሚያቀርበው አስረጂ ሁሉ ወደ ልክነት የመድረስ ንጥረቱ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው፡፡ ስሜቱን መሻገር ከቻለ እንደጥላቻ፣ ንቀት፣ ማጥላላት፣ ማኮሰስ ወዘተ አይነት አሉታ አጸፋዎችን አያስተጋባም፡፡ ሰዎች በሚኖሩት ህይወት፣ በሚያነሱት ሀሳብ ወይም ባላቸው ማንነት እያስታከከ ጥቁር መልክት አይዘራም፤ ፊቱን አያጮናም፡፡


ስሜትን መሻገር ለምሳሌ በማህበራዊ ሚዲያ ‹ፕላት ፎርሞች› ላይ የስድብ ወይም ዘለፋ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ በመረጃ መቃወም፤ ወይም በመረጃ ማጠናከር አይነት ስሜት ካለን እንደማለት ይሆናል፡፡ በተጨማሪም አስተያየት ሳይሰጡ ዝም ማለትንም ይይዛል፡፡

በየቀኑ ከሚኖረን መስተጋርና ውሎ አንጻርም ለሌሎች ያለን እይታ፣ የሚሰማን ስሜት እልህ፣ ቁጭት፣ ንቀት ጥላቻ በአንድ ጎናችን ሲታጨቅበት አልያም ከወሰን የበዛ አድናቆትና መደመም ውስጥ ሲከተን እዚህም ላይ ያልተሻገርነው የስሜት ባህሪ አለ ማለት ነው፡፡
….
እናም…

በአንዳች ጉዳይ ላይ የተሰማን ስሜት… በአወንታም ይሁን በአሉታ ስሜታዊ ካደረገን ራስን ታግሎ ሰከን ማለት ጥሩ መፍትሄ ነው፡፡ ለማድነቅም ለመተቸትም አለመቸኮል… ከፍሬያማ ውጤት ያደርሳል፡፡


@yehasab_menged
@yehasab_menged
426 viewsTeddy, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 09:23:34 መነጠል እና መጀመል

... ይልቅ አንድ ታሪክ ልንገርህ፡፡

እ.ኤ.አ በ1750ዎቹ በለንደን ከተማ ጎዳናዎች የሆነ የሚያስገርም ሰው ብቅ አለ፡፡ ስሙ ጆናስ ሀንወይ (712-1786 እ.ኤ.አ) ይባላል፡፡ የሆነ ቀን ከጨርቅና ከቆዳ ቀጣጥሎ የሠራውን ዘባተሎ ግዙፍ ጃንጣለውን ይዞ ብቅ ሲል "ምን ጉድ ነው? "በሚል ስሜት ሰዎች ተከተሉት፡፡ ጃንጥላውን ይዞ በወጣ ቁጥር አንድ ገበያ ሕዝብ ያጅበው ጀመር፡፡ ምናልባት የሚሸነቁጥ የሚያዋርድ ስድብም ይከተለው ይሆናል፡፡ ለሠላሳ ዓመታት ይሄው ምቾት የሚነሳ አጅብ አልቀረለትም፡፡

እነሆ ዛሬ በአሜሪካ ብቻ በዓመት 33 ሚሊዮን ጃንጥላዎች ይሸጣሉ፡፡ 365 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ለግብይቱ ይውላል፡፡ ከኛም ሀገር የመከላከያ በጀት እንደሚወዳደር ልብ በልልኝ፡፡ በዘመናዊው ዓለም በዓለማቀፍ ደረጃ እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ጃንጥላ ተጠቃሚዎች እንደሆኑ ይገመታል፡፡ ዛሬ ጃንጥላዎች ከዝናብና ሀሩር መከላከያነታቸው በተጨማሪ የውበት፣ የፋሽን መሳሪያዎች ሆነው ያገለግላሉ፡፡

ሌላም ነገረ ሀቲታችን የሚያሰፋ ተረክ እነሆ..

በአሥራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን አንድ ቀን የሙዚቃው ጠቢብ ቪትሆቨንና ወልፍጋንግ ገተ በእግር እየተንሸራሸሩ ሳለ ድንገት አንድ መስፍን በመንገዳቸው ላይ እስከ አጃቢዎቹ መጣ፡፡ ገተ መንገድ ለቆ ሲሽቆጠቆጥ ቪትሆቨን ግን ከመንገዱ ንቅንቅ አላለም፡፡ መስፍኑ ለምን መንገድ እንደማይለቅ ቪትሆቨንን በጠየቀወም ጊዜ አለ

«ልዑል ሆይ አንተ ልዑልነትን የተቀዳጀኸው በመወለድ ብቻ ነው፡፡ አዕላፍት ልዑላን ነበሩ፡፡ ሌሎች ሺዎች ልዑላን ወደ ፊት ይኖራሉ፡፡ ነገርግን አንድ ቪትሆቨን ብቻ...›› ቪትሆቨን ቪትሆቨንን ለመሆን ግን አርባ ዓመታት ፈጅቶበታል፡፡ የመስማት ችሎታውን አጥቷል፡፡ ይህ በሞዛርት አንደበት ሳይቀር አድናቆት የዘነበለት የረቂቅ ሙዚቃ (classical music) ጠቢብ ቪትሆቨን
በዕድሜ ዘመኑ አጋማሽ ቀስ በቀስ መስማት አቆመ፡፡ ነገሩ እጅግ አስደንጋጭ ሆነበት፡፡ ራሱን እስኪጠላ ድረስ ተረበሸ፡፡ በዝናብ ውስጥ ለረጃጅም ሰዓታት ጠዓረ ሞት መስሎ ተመላለሰ፡፡ ተቅበጠበጠ፡፡ ራሱን ለማጥፋት ዳዳው፡፡

በመጨረሻ አዲሱን ማንነቱን ለመቀበል ተገደደ፡፡ ከዓለም ተገለለ፡፡ ተነጠለ፤ የሌለ ያህል ተረሳ፡፡ ራሱን ሙዚቃዊ ፈጠራዎቹ ውስጥ ቀብሮ እሱ የማይሰማውን የረቂቅ ሙዚቃ ጥዑም ውህድ ማረቀቁን ተያያዘው፡፡ አስደናቂዎቹን ፈጠራዎቹን የሠራው መስማት ካቆመ በኋላ ከዚህ ሕመም፣ ከዚህ የመነጠል፣ የመገለል ጥልቅ ውስጥ ነበር፡፡ የተጋፈጠው ፈተና ግን የምንጊዜም ምርጥ የረቂቅ ሙዚቃ (classical music) ሰዎች ተርታ ከመመደብ አላገደውም፡፡ ከገጠመው መራር ዕጣ ጋር ተናንቆ እንዴት የሕይወት መንገዱን እንደቀየረ ሲናገር ‹‹ዕጣ ፋንታዬን ጉሮሮው ላይ ፈጠረቅሁት፡፡ ብሏል፡፡ ዛሬ ትውልድ በየዕለቱ በሥራዎቹ እየተደነቀ የዓለምን መልክ ከቀየሩ መቶ ሰዎች መሃል ደምሮ ያስታውሰዋል፡፡

ስሙን ለማስታወስ የተቸገርኩት አንድ ሰው ሳነበው የገረመኝ አንድ ሀሳብ አለው፡፡ በአንድ ዐረፍተ ነገር ብቻ ሲቀርብ «human mind is a gigantic duplicating machine)) ይሆናል፡፡ ዘመኑን በሚሊዮንም ስፈረው በሺኅ የሰው ልጅ ከአደን ዘመን ጀምሮ ያሳየው የኑረት ዘይቤ መሻሻል በጣም ጥቂት ነው፡፡ ብዙው ሰው ኢምንት ሳያበረክት በስህተት እንደተጠራ ተጀምሎ ሲቆጠር ኖሮ ያልፋል፡፡

ሱሪያሊቱ ሠዓሊ ሳልቫዶር ዳሊ የሴትን ልጅ ውበት ከአበባ ጋር ያመሳሰለው የመጀመሪያው ሰው እሱ ፈላስፋ ነው፡፡ የደገመው ግን ደደብ ነው፡፡» ይላል፡፡ አልበርት ካሙም በካሊጉላ አንደበት ‹‹አያትህን መብለጥ ካልቻልክ አስቀድሞውኑ ሞተህ መቀበር ነበረብህ፡፡›የሚል ግልምጫ ሰንዝሯል፡፡ ብዙ ሰው በኑረት ለዛው እንደ ተፈጥሮ ስህተት የሚቆጠር ምንም ነው፡፡ የአያቱን ዳዊት የሚደግም የአባቱን ሙታንታ የሚታጠቅ ስርዝ ድልዝ ነገር፡፡ ይኼን ጽሑፍ የማንበብ ተነሳሽነቱ ያለህ አንተ ይኼን እንደ ስህተት መቆጠርን የምትጸየፍ ይመስለኛል፡፡

አሜሪካዊቷ አብስትራክት ሠዓሊ አንግሥ ማርቲን ።በሕይወትህ ውስጥ እጅግ መልካም የሚባሉት ነገሮች የሚከሰቱልህ ብቻህን ስትሆን ነው፡፡›› ትላለች፡፡ አየህ ዛሬ እኛ የምንኖርበትን ንቅሳታም አለም የገነቡት ነጠል ብለው መቆም የቻሉ፣ ሌላ ዓይነት የህይወት ቅኝት የነበራቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፡፡ ዛሬ ያለውን ዘመናዊ ስልጡን ዓለም አንድ በአንድ የቀረጹት ሕይወትን በተለየ እንግዳ ዓይን የታዘቡት፣ ከተራ ምልከታ ተነስተው ነባሩን ዘልማዳዊ ዓለም የሚቀይር ሀሳብ ያረቀቁት ነበሩ ።

ምንጭ-ከባዶ ላይ መዝገን
ደራሲ- ያዕቆብ ብርሀኑ

@yehasab_menged
@yehasab_menged
516 viewsTeddy, 06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 20:32:14 ....
ብዙ የማውቃቸው ሰዎች ሀይማኖት ያላቸው ሲኦል እና ገነት አለ ስለተባሉ ነው። ከክፋት የሚቆጠቡት ሲኦልን ፍራቻ እንጂ መልካም መሆን ምንም ሽልማት የለውም ክፉ መሆንም ምንም ቅጣት የለውም ቢባሉ ለክፋት የሚግደረደሩ ናቸው። በሰውነት ሰው ስለመሆን ሳይሆን እግዚአብሔር ወይም አላህ ወይም ሌላኛው አምላክ በክፋታቸው ይቀጣናል ፤ በመልካም ስራቸው ይሸልመናል ብለው ስለሚያምኑ ነው ሚዛን የሚሰሩት። እስኪ እውነት እናውራ ከተባለ የብዙ ሀይማኖቶች መደምደሚያ ከሞት በኋላ ያለ ሽልማት ወይ ቅጣት ባይሆን ምን ያህል ሰው ሀይማኖት ይኖረው ነበር? ምን ያህል ሰው ቅዱስ የሚለውን ስራ ለመስራት ይጋጋጣል? ምን ያህሉስ ሰው ወደሀይማኖት ተቋማቱ እየሄደ አቴንዳንስ ያስመዘግብ ነበር?

@yehasab_menged
@yehasab_menged
386 viewsTeddy, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 18:18:41 #ታካችነት_ኃይልህን_አሳልፈህ_የምትሰጠው_ጠላትህ_ነው


"ታካች ሰው። አንበሳ በሜዳ ነው ሲባል በመንገዱ ላይ እሞታለሁ ይላል።" (መጽሐፈ ምሳሌ 22:13)

የሆነ ሰው አእምሮህን በመጠቀም ከካንሰር ጭምር መፈወስ እንደምትችል ቢነግርህ፤ ታምነዋለህ ወይስ ትስቅበታለህ?

አእምሮ ሃይል አለው!!!

በጭንቀት፣ በስጋት ውስጥ ከቶ ከሰውነት ተራ እስክትወጣ ድረስ ያከሳሃል…

በተስፋ እና በሃሴትም ሞልቶ ህይወትህን ያበራልሃል።

የምትችላቸው እና የማትችላቸው ነገሮች ያሉት አእምሮህ ውስጥ ብቻ ነው።

በቀጣዮቹ ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ የምትችለውን ሁሉ አድርገህ አስር ሺ ብር ይዘህ ና ብልህ ‘አልችልም - ገንዘቡን ከየት ማምጣት እንዳለብኝ ምንም ሃሳቡ የለኝም’ ትለኛለህ።

ሆኖም በሳንቲሞች የተሞላ ካልሲ በእጄ ይዤ “አስር ሺ ብር ካላመጣህ፣ በዚህ እመታሃለሁ” ብዬ ባስፈራራህ እና መንገድ ለመንገድ ባሯሩጥህ፣ አማራጮችን ማሰብ ትጀምራለህ -

ምናልባትም ትበደራለህ፣

ምናልባትም ከቤትህ እቃ አውጥተህ ትሸጣለህ ወይም ለእርዳታ ትጣራለህ።

ሁሌም ቢሆን አእምሯችን አማራጮች አሉት፤ እኛ እንዳላየ ሆነን ማለፍን እንመርጣለን፣ ሃላፊነቶችን እንሸሻለን እንጂ ተአምረኛው አእምሯችንን በትክክል ከተጠቀምንበት ለእድገት የሚጠቅሙንን ነገሮች ሁሉ ለማቅረብ ዝግጁ ነው።

ከታካችነት ወጥታችሁ አእምሯችሁን ልትጠቀሙበት ዝግጁ ናችሁ?

#ከተአምረኛው_አእምሮህ መጽሐፍ የተቀነጨበ

@yehasab_menged
@yehasab_menged
602 viewsTeddy, 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 21:10:43 የአሪስቶትል ምናባዊ ሰው (Aristotle's Imaginary Man)
፨ " በአለም ላይ ለመኖር የሚያስፈልጉት ነገሮች እጅግ በጣም ጥቂቶች
ናቸውና አላስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ራሱን አያጋልጥም፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ
እራሱን ቢያገኝ እንኳን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀና ቆራጥ ነው።
በእንዲህ ያለ ኑሮ ውስጥ ሕይወት አላስፈላጊ መሆኗን አምኖ ተቀብሏል።
ለታይታ ሲል አይኖርም፤ የሚወደውንና የሚጠላውን ነገር መደበቅ አይችልም፤
ሲናገርም ሲያደርግም በግልጽ እንጂ በድብቅ አይደለም፤ በእርሱ አይኖች
የሚደነቁ ነገሮች የሉምና ስለምንም ነገር አይደንቅም፤ ብዙ አያወራም፤ ሰዎችን
ለማስደሰት ሲል የማይገባውን አያደርግም፤ በሌሎች ይመሰገን ወይም ይደነቅ
ዘንድ ግድ የለውም። ጠላቶቹን ጨምሮ ስለ ማንም ሰው ክፉ አያወራም፤
አቋሙ የፀናና አነጋገሩም የተላከ ነው። በዓለም ላይ ጉዳዬ የሚለው ነገር ጥቂት
ስለሆነ ለምንም ነገር አይቸኩልም፤ የሕይወትን ክፉ አጋጣሚዎች በፀጋ መቀበል
ይችላል። እሱ የራሱ ጓደኛ እንጂ ሌላ ጓደኛ የለውም፤ በብቸኝነቱም ተደሳች
ነው።"
አሪስቶትል "ሰው" የሚለው እንግዲህ እንዲህ ያለውን ነው።
ታዲያ በዚህ ሚዛን ስንቶቻችን ሰው ሆነን ይሆን?
ዋቢ መፅሐፍ ጥበብ ቅፅ ፩
ከጲላጦስ ( ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)

@yehasab_menged
@yehasab_menged
774 viewsBabi, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 08:29:48 • በህይወቴ ዘመን ሁሉ ቤተሰቦቼ እንደ ልጅ ቆጥረዉኝ አያዉቁም፡፡ ጠንቋይ ቤት ሄደዉ ያላቸዉን ሀብት 'እኔ ላይ ካፈሰሱ ዉድቀትና ድህነት ቤታችን ዉስጥ እንደሚገባ ነገር ግን ወንድሜ ላይ ካፈሰሱ ቤታችን በበረከት እንደሚሞላ' ዘባረቀላቸዉ፡፡

ይህን ካዘዛቸዉ ቀን ጀምሮ እኔን እንደለማኝ ወንድሜን ደግሞ እንደንጉስ አሳደጉን፡፡ ወንድሜ 'አለ የተባለ ትምህርት ቤት' ሲያስገቡት እኔን ግን የመጨረሻ የድሃ ትምህርት ቤት ወረወሩኝ፡፡ ግን ምን እንደሆነ ልንገርህ ተከተለኝ...

• አስተማሪዎቼ ቤተሰቦቼን ጠርተዉ 'ደደብ ተማሪና ተደብዳቢ እንደሆንኩና ለዚህም እንደመቀጫ የትምህርት ቤቱን ሽንት ቤት ማፅዳት እንዳለብኝ' መወሰናቸዉን ነገሯቸዉ፡፡ ቤተሰቦቼ ደስ አላቸዉ...አዎ የወለዱኝ ቤተሰቦች!!

ስራ ስጀምር ከሽንት ቤት ማፅዳት መሆኑ ለኔ የኋላ ኋላ ለመልካም ሆነልኝ፡፡ ይኸዉ አሁን ከ 20 አመት በኋላ የትልቅ ካምፓኒ ባለቤት ነኝ፡ ይብላኝ ለነሱ! አሁንም ተከተለኝ...

• ከልቤ የማፈቅራት ሴት ‘አንተ እንኳን ለፍቅር ለጉርብትናም ትደብረኛለህ!’ ብላኝ ትታኝ ሄደች፡፡ ግን ከ 10 አመት በኋላ እሷ ካለችበት ኢኮኖሚ 10 እጥፍ 'ሀብታምና የተሳካለት ሰዉ' ሆኜ ከች አልኩ! እሷ ግን እንደማንም ተራ ሆና አሁንም አለች!

እኔን ጥላ በሄደችበት ጊዜ የዛኔዉ 'የልቧ ትርታ' አሁን ከሷ ጋር የለም...አዉላላ ሜዳ ላይ ‘አንቺን ብሎ ፍቅረኛ !’ ብሏት ላጥ! ገና አልጨረስኩም...

• የሆነ የህይወቴ አስቸጋሪ ሰአት ሁሉን ከስሬና ባዶ ሆኜ ስመጣ የተማመንኩባቸዉ ሰዎች በሙሉ ካዱኝ፡፡ ‘አቅሙን የማያቅ!’ ብለዉ ተዘባበቱብኝ!

ቀን ተገለበጠና እኔ ‘አንቱ’ የተባልኩ ሀብታም እነዛ ደግሞ 'ደፋ ቀና የሚሉ' የተለመደዉ አይነት ሆነዉ አሉ፡፡ ይኸዉ ነዉ የኔ ታሪክ!

ሰዎች ሲጎዱኝ፣ ሲጫወቱብኝና እጃቸዉን መቀሰር ሲጀምሩ ያንኑ የተሰበረ ስሜት ተጠቅሜ ወደ ስኬት እለዉጠዋለሁ፡፡ ዉስጤ በቁጭትና በታታሪነት ይሞላል፡፡ ከዛም በህይወቴ የሚገርም ለዉጥ አያለሁ! አንተስ እንዴት እየኖርክ ነዉ??

@yehasab_menged
@yehasab_menged
701 viewsBabi, 05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ