Get Mystery Box with random crypto!

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

የቴሌግራም ቻናል አርማ commandoandairbornecommand — የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command
የቴሌግራም ቻናል አርማ commandoandairbornecommand — የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command
የሰርጥ አድራሻ: @commandoandairbornecommand
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.60K
የሰርጥ መግለጫ

Addis abeba Ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-21 08:31:47
#ኢድ_ሙባረክ

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም የጤና የፍቅር የአንድነት ያድርግልን።

የዒድ አልፈጥር በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የ2015 ዓ.ም የዒድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።

የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የመተዛዘን እና የመረዳዳት እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል።

በታላቁ የረመዷን ወር መጨረሻ የሚከበረውን የዒድ አልፈጥር በዓልን በሰላምና በመተሳሰብ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ማሳለፍ እንደሚገባም ጥሪ አቅርቧል።

#ቴሌግራም
https://t.me/CommandoAndAirborneCommand

#You_Tube


16 views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 06:55:12
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያልን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን፡፡

ኢድ ሙባረክ!

ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

https://t.me/CommandoAndAirborneCommand

YouTube


36 viewsedited  03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 17:23:58
የመንግሥት ማስጠንቀቂያ

~"በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሠሩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል "-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

"በኢትዮጵያ እና በሱዳን ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሠሩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ጉዳዩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ሕዝቦች ብዙ ፈተናዎችን እየተጋፈጡ በሚገኙበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ የሐሰት ውንጀላዎችን በማሰራጨት የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማሳካት የሚጥሩ ወገኖች እንዳሉ ጠቁመዋል።

እነዚህ አካላት "ኢትዮጵያ በሱዳን ድንበር አካባቢ ወታደሮቿን አስጠግታለች" የሚል የሐሰት መረጃ እያሰራጩ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

ይህን የወንድማማች ሀገራትን ግንኙነት የሚያሻክር የሐሰት ውንጀላም ኢትዮጵያ በጽኑ እንደምታወግዘው አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ያለው ጉዳይም በውይይት እንደሚፈታ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

https://t.me/CommandoAndAirborneCommand

YouTube


163 viewsedited  14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 17:17:11 የኢፌዴሪ መከላከያ ሚያዚያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም

ለሰላም ስምምነቱ ስኬት-የሁሉም ወገን ቁርጠኝነት

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት የቆየውን ጦርነት በድርድር ለመፍታት በፌዴራል መንግስትና በሕወሃት መካከል በደቡብ አፍሪካና ናይሮቢ የሰላም ስምምነትና ማስፈፀሚያ ሰነዶች መፈረማቸው ይታወሳል፡፡

ይህ ርምጃ በዋነኝነት ጦርነት በተካሄደበት አከባቢ ያሉ ነዋሪዎችንና በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ በእጅጉ ያስደሰተ ቢሆንም የስምምነቱን ዘላቂነት በጥርጣሬ የሚመለከቱ ወገኖች ቁጥር ግን ቀላል የሚባል አይደለም፣ በዚህ ላይ በአንዳንድ ወገኖችና ሚዲያዎች የሚቀርቡ አሉታዊ ዘገባዎች የሕዝቡን ጥርጣሬ ይበልጥ አሳድገውታል፡፡

‹‹ ዕውን የሰላም ስምምነቱ በአንዳንድ ወገኖች እንደሚባለው ተስፋ ቢስ ነው ወይንስ የሚጨበጡና ተስፋ ሰጪ እርምጃዎች እየታዩበት ነው?

በሠላም ስምምነቱ መሠረት እስካሁን ምን ምን ተግባራት ተከናወኑ?

የስምምነቱን ተፈፃሚነት የሚያመለክቱ ምን ተጨባጭ እውነታዎች አሉ?

በአንዳንድ ወገኖች እንደሚወራው ሕወሐት የሰላም ስምምነቱ ዕውን እንዳይሆን የማደናቀፍ ተግባር እየፈፀመ ነው ወይንስ ለስኬታማነቱ እየሰራ ነው?

በሚሉት ጥያቄዎችና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መከታ መፅሄት ከክቡር የኢፌዲሪ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ቃለ ምልልስ አካሒዷል፡፡

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ሂደቱን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ የሚከተለውን ብለዋል ፦

"የሰላም ሒደቱን አስመልክቶ አንዱ መነሳት ያለበት ጉዳይ ወደ ሰላም የመጡት ሁለቱም ወገኖች የነበራቸው መንፈስ ምን ይመስላል? የሚለው ነው ይሕ መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ይሕንን አስመልክቶ ብዙ ውዥንብር አለ:"ስምምነቱ የተፈረመው ለጊዜ መግዣ እንጂ ከልብ ተግባራዊ ሊደረግ ታስቦ አይደለም፤ የሕወሐት ሐይሎች ምሽግ በመቆፈርና ተዋጊዎቻቸውን በማሰልጠን ለአራተኛ ዙር ጦርነት እየተዘጋጁ ነው" የሚል ውዥንብር በስፋት የሚያሰራጩ ወገኖች አሉ::÷ እነዚህ የተሳሳቱ መረጃዎች ከተጨባጭ ሁኔታው ጋር  ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸውና  ሕዝብን ዕምነት ለማሳጣት ታልሞ የሚነዙ የሀሰተኛ ኘሮፓጋንዳዎች ናቸው ።

ወሬዎቹ ስምምነቱን ከማይፈልጉና፣ ከጦርነቱ ከሚያተርፉ  ሐይሎች የሚመነጩ ናቸው።
ኢትዮጵያ ሳትፈልግና ተገዳ የገባችበት ጦርነት ተቋርጦ ሰላም እንዲሰፍን በኢፌዴሪ መንግስት በኩል ከመጀመሪያው ጀምሮ ከፍተኛ ፍላጎት፣ ተነሳሽነትና  ቁርጠኝነት ነበር:፣ ዘግይተውም ቢሆን የሕወሐት አመራሮችም ጦርነቱን በድርድር ማቆም አማራጭ የሌለው ርምጃ መሆኑን ተገንዝበው ወደ ሰላም መጥተዋል፡፡

በአንዳንድ ምክንያቶች መዘግየቶች ቢታዩም ሁለቱም ወገኖች ለስምምነቱ ተፈፃሚነት እየሰሩ ናቸው፤የሐገራችንን ሰላም በዘለቄታው በማረጋገጥ የወደሙትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተቋማትን መልሰን በመገንባት የሕዝቡን ሕይወት የመለወጥ ጉዳይ ሁሉም ወገኖች ሊረባረቡበት የሚገባው የሕልውና ጉዳይ ነው፡፡

በመጀመሪያ በደቡብ አፍሪካ፣ ቀጥሎ በኬኒያ ናይሮቢ በተደረጉ ስምምነቶችና የማስፈፀሚያ ሰነዶች መሰረት በሁለቱም በኩል ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል። ፌዴራል መንግስት ሰብዓዊ እርዳታ፣ ባንክ፣ ስልክ፣ መብራት እና የመሣሠሉ አገልግሎቶች እንዲመለሱ አድርጓል። ሠራዊቱን ከውጊያ አላቋል።

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን እና የሀገር ሽማግሌዎችን ወደ መቀሌ በመላክ መተማመን እንዲፈጠር ብዙ ርቀት ተጉዟል።

በህወሐት በኩልም  በጎ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ። ሠራዊቱን ወደ ካምኘ አስገብቷል። ከባድ መሣሪያዎችን ለመንግስት ማስረከብ ጀምሯል። ስምምነቱ በሚፈለገው ልክ ተግባራዊ እንዲሆንና ተቀባይነት እንዲያገኝ ህዝቡን አወያይቶ መግባባት ላይ ደርሷል።

የሠላሙ አስፈላጊነት በእጅጉ የታመነበት በመሆኑ ለስኬታማነቱ ከልብ የሚሠሩ የህወሐት አመራሮች አሉ።  በርግጥ ከጉዳዩ ክብደት አንፃር አሁንም የሚቀሩና ጊዜ የሚፈልጉ በርካታ ስራዎች መኖራቸው እሙን ነው።

ስምምነቱ ምህረትን የሚያካትት በመሆኑ የተከሰሱ ሰዎችን ክስ ማንሳትና የመሳሰሉትም ቀጣይ ተግባራት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡  የቀሩ ትጥቆችን የማስፈታቱ ሂደትም የሚቀጥል ይሆናል።

የህወሀትን ተዋጊ ሀይል ወደ ካምፕ ማስገባት ፣ትጥቅ ማስፈታትና  ከህዝቡ ጋር እንዲቀላቀሉ የተሀድሶ ስልጠና መስጠት DDR /disarmed dimoblized and rehablitate/ የስምምነቱ አካል ናቸው። ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተተግብሯል ማለት የሚቻለውም እነዚህ ስራዎች ከተከናወኑ በኋላ ነው።

እስካሁን ህወሀት ተዋጊ ሀይሉን  ወደ ካምፕ በማስገባቱ  የመጀመሪያው ስራ ተተግብሯል።
ትጥቅ ማስፈታትና የተሀድሶ ስልጠናዎቹ  ደግሞ የሚቀጥሉ ናቸው ።

በአጠቃላይ የሰላም  ስምምነቱ አተገባበሩ በፌዴራል መንግስቱም ሆነ በሕወሃት በኩል በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ይገኛል ማለት በሚቻልበት ደረጃ ላይ ነው ያለው። ይሁንና በአንዳንድ መገናኛ ብዙሀን በተለይም በማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚነዙ አፍራሽ አሉባልታዎች አሉ።

አሁን ላይ ህዝቡም ሆነ አመራሩ ጦርነትን አይፈልጉም። ጉዳቱንም በሚገባ ተረድተውታል።
ይሁንና በዜጎች መካካል አንድነት እንዳይኖር፣ ልዩነት እንዲፈጠር፣ ኢትዮጵያ እንድትዳከም የሚሠሩ የውጭ ጠላቶቻችንና የውስጥ ባንዳዎች የሰላም ስምምነቱ ስኬታማ እንዲሆን አይፈልጉም  ለሆዳቸው የተገዙ ባንዳዎችን እኩይ ድርጊትና የቀጣሪዎቻቸውን ፍላጎት በመረዳት በጋራ መመከት የህልውና ጉዳይ መሆኑ መታወቅ አለበት።

ለሠላም ሲባል የሚተገበሩ በርካታ ጉዳዮች ይኖራሉ። በመንግስት እና ህውሐት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ጦርነቱን የሚያባብሱ ተግባራት ይቅሩ ብለናል።
ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ አካሄድ መከተል ግድ ስለሚል ፉከራ፣ ሽለላና የአሸናፊነት መፈክር ማንፀባረቅ አይፈለግም። ከቆምንበት መጀመር እንደሚያስፈልግ ሁለታችንም ተግባብተናል።
የሠላም ስምምነቱን በተፈራረሙት ሐይሎች በኩል  ነገሮችን የማባባስና ሠላምን የሚያደፍረስ ፍላጎት የለም። በዚህም ሆነ በዚያ በኩል ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም ሠላም የማይፈልግ ሐይል መኖሩ ግን እየታየ ነው።

የኢትዮጵያን ጠላቶች ማድመጥ አያስፈልግም። ባንዳም ቢሆን በታሪካችን ጠፍቶ አያውቅም።
ሌላው ቀርቶ በታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል የአድዋ ጦርነት ወቅት እንኳ በሺህዎች የሚቆጠሩ ባንዳዎች ነበሩ።

‹‹ግጭት ተፈጥሯዊ ነው። በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ምክንያቶችና በተለያዩ አካላት ሊከሰት ይችላል። አለመግባባትን በሠላም መፍታት የሰው ህይወት መጥፋትንና የንብረት ውድመትን ለማስቀረት ሲባል ለሠላም መረታት ሐላፊነት የሚሠማቸው አመራሮች ተግባር ነው። በመሆኑም ለሠላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን እየተሠራ ሲሆን የእስካሁኑ ጉዞም ውጤታማ ነበር ማለት ይቻላል›› ብለዋል ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፡፡

በጦር ሐይሎች ጠቅላይ መምሪያ በየሦስት ወሩ የሚታተመው መከታ መፅሔት ቁጥር 1 ህትም ላይ  የተወሰደ

ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

https://t.me/CommandoAndAirborneCommand

YouTube


152 viewsedited  14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 17:16:54
122 views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 14:47:11 ስለሀገር የመኖር ፅናት~እንደ ወታደር
ሀገርን መውደድ ስለ ሀገር መሞገት ከማንኛውም ዜጋ የሚጠበቅ በጎ እሳቤ ነው። ነገር ግን ሀገርን መውደድና ስለሀገር መኖር ለየቅል የሚሆኑበት እውነታዎችም አሉ።
  
በስመ - ሀገር ወዳድነት ህጸጽ ብቻ እያነፈነፉ፣ የተፈጠሩ ችግሮችን ከሚገባው በላይ እየለጠጡና ከመጠን በላይ እያገዘፉ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ሲያላዝኑ መዋል የሚያስገኘው ጠብ የሚል ነገር የለም።
   
ይህ ሲባል በሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ ዝም ይባል፣ አንዳችም የግል አስተያየት አይሰጥ ለማለት ተፈልጎ እንዳልሆነ ልብ ይባል።
    
ሀገር ትውልድ እስከቀጠለ ድረስ እንደየዘመን ሁነቱ ችግሮች አሉ። ነበሩ። ይኖራሉም። ምክንያቱም ፍጹም ትክክል የሆነ ነገር ከሰው የሚጠብቅ ካለ የራሱን ሰዋዊ እውነታ የዘነጋ ነው ቢባል ስህተት አይሆንም።
   
ከፀሐይ በታች ዓለምን በማያቋርጥ ምርምርና ጥናት እየታገዘ በአስገራሚ ፈጠራዎች የሚያስደምም ግኝት እውን እያደረገ የሰው ልጅ ህይወትና ኑሮን ለእስከዛሬው ዓለማዊ ዕውነት ያበቃው የሰው ልጅ ዕውቀት በብዙ ስህተቶች ባለፈ ጉዞ የተገኘ ትሩፋት መሆኑን ማጤን ግድ ይላል።
   
በተለይ...በተለይ እንደኛዋ ኢትዮጵያችን ዓይነት በየዘመናት አንጓ እየተፈጠሩ በመጡ የታሪክ፣ የፖለቲካና መልከ - ብዙ ስብራቶች እያነከሰች ዛሬ ላይ የደረሰች ሀገር ላይ በጥቂት ዓመታት ሆይ ሆይታ ሁሉም ነገር በምናስበው ልክ ትክክል እንዲሆን መጠበቅ የዋህነት ነው የሚሆነው።
  
"እና ምን? " የሚል ጥያቄ አጭሮብን ይሆን ይሆናል። ምላሹ ከተባለ እንደኔ "ሀገርን ከመውደድ እና ስለ ሀገር ከመሞገት ባሻገር፤ ስለሀገር የመኖር ጽናት ይኑረን።" ነው።
 
" እንደ ማን?" ከተባለ ደግሞ "እንደ ወታደር" እላችኋለሁ።
   
የሀገሬ የሀገራችሁ ወታደር አሁን ላይ ከየትኛውም ፖለቲካዊ ሆነ ሌሎች ውግንና ነጻ ሆኖ፤"ከራስ በፊት ለሀገርና ህዝብ" በሚል መርህ ሁለንተናውን በሙያዊ ዲሲፕሊን ለሀገሩ ፍቅር አውሎ በሳምንት ሰባት ዕለታት በቀንም ሃያአራት ሰዓታት ያለ ዕረፍት እየሰራ ይገኛል።ሲሰራም እስከሚደክመው ሳይሆን እስከሚሞት ድረስ።
   
በነገራችን ላይ የውትድርና ሙያ በራሱ በስብዕናና ዜግነታዊ ዕምነት ላይ የበዙ በረከቶችን ለግሶ፣ በችግሮች ማላዘንን ሳይሆን፤የመፍትሄ አካልነትን፣ በስሜት ከመንተክተክ ይልቅ ስክንነትን፣ ከሆይ ሆይታ ይልቅ አስተዋይነትን፣በትንሽ ነገር ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ጽናትን የሚያላብስ የሞያዎች ሁሉ በኩርና ክቡር ነው።
   
የውትድርና ህይወት በማያቋርጥ የዕውቀት ዑደት ውስጥ ዕለት በዕለት ማለፍም ነው።በዘላቂ ሳይንሳዊ ተጨባጭ ዕውቀትና ጥበባዊ አመራር እየተገነባ የሚራመድ ተቋም አባል የመሆንን ወርቃማ ዕድል የሚያጎናፅፍም ነውና፤አያልቄ ገጸ - በረከት የሚገኝበትም ነው።
   
ለዚያም ነው  ወታደር በጠባብ ደረቱ በምትገኝ ልቡ ውስጥ ታላቋንና ግዙፏን ኢትዮጵያ ይዟት ለጸና ሰላሟ ሲያካልላት የሚኖረው።
   
በሀገሩ ምንም ቢፈጠር ምን፤ መፍትሄ እንደሚኖር ተስፋ አድርጎ ብቻ ሳይሆን አምኖም ጭምር ስለሰላም ይሰራል።በመስዋዕትነት ታጅቦ።
   
ታዲያ ስለድካሙና ቃላት ሊገልጹት አቅም በሚያንሳቸው ብርቱ ልፋትና ድካሙ ምትክ ክፍያ አይሻም።ክፍያው የሀገሩ መጽናት መከበርና የታላቅነት ጉዞ መቀጠል ነው።
   
እናም ወታደር ሀገሩን ከመውደድ ተሻግሮ ስለሀገር ይኖራል። በታመነና ከእውነተኛ ልባዊ ፍቅሩ በመነጨ ኢትዮጵያዊ እምነት።
   
ይህንን ጽኑ እምነት አይተን፣ ሀገራዊ ችግሮችን ለግላዊ ጥቅም የሚያውሉ ቀላማጅ ዩቱዩበሮች 'እውን የሀገር ተቆርቋሪ ናቸውን?' ብለን ራሳችንን እንጠይቅ።
   
አንድ ነገር ግን ማለት ግድ ይላል። ሁሉም ዜጋ ባለው ሙያ፣ ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት እንደ ወታደሩ ሁሉ፤ ፖለቲካውን ለፖለቲከኞች ትቶ፤ የበኩሉን ዜግነታዊ አበርክቶ ለሀገር በመኖር መርህ ቢወጣ ምን ውጤት እንደሚገኝ ለመገመት አይከብድም።
  
እንዲህ ያሉ ዜጎች የሉም ማለት ሳይሆን እልፍ አዕላፍ ቢሆኑ አስባችሁታል?
ክብር ስለሀገሩ በፅናት ለሚኖረው ወታደር

ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

https://t.me/CommandoAndAirborneCommand

YouTube


142 viewsedited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 14:47:03
122 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 11:35:01
#ሱዳን

" ቤተሰቦቻችን ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ አልቻልንም ፤ጭንቀት ላይ ነን "

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ውጊያ ዛሬ 6ኛ ቀኑን መያዙ ይታወቃል።

በሱዳን ያሉ ቤተሰቦቻችን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ካርቱም ወዳለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ ብንደውልም ምላሽ አላገኘንም ሲሉ እዚህ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት ልከዋል።

በሱዳን ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ባለመቻላቸው እንደተጨነቁ የገለፁት እንዚሁ የአባላት ፤ ማንን መጠየቅ እንዳለብን ግራ ገብቶናል ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አካል ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።

ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ቤት በሆነችው ሱዳን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለስራ እና በቋሚነት ለኖሮ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የሰሞኑ የሱዳን ውጊያ ደግሞ እዛ ያሉትን ብቻ ሳይሆን እዚህ ያሉ ቤተሰቦችንም ጭምር ጭንቀት ውስጥ ጥሏል።

ከትላንት በስቲያ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፤ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ሲቪሎች ለጉዳት መዳረጋቸውና ህይወትም እየተቀጠፈ መሆኑን በመግለፅ ከእነዚህ መካከል #ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች እንደደረሱት አሳውቋል።

ኤምባሲው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ እና እንደተጎዱ በዝርዝር ባይገልፅም ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ ኢትዮጵያዊን የተቻላቸውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

መረጃ ለመለዋወጥ እና ለምክክር የኤምባሲው ባልደረባ የሆኑትን አቶ ነጅብ አብደላ በስልክ ቁጥር +249911646547 ማነጋገር እንደሚቻልም ገልጿል።

YouTube


150 views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 11:19:46
#ሰበር

ሱዳን ኢትዮጵያ ድንበሯን እንድትዘጋላት ጠየቀች።

ሾልኮ ያገኘነው መረጃ
እንደሚያሳየው የሱዳን መንግስት ለኢትዮጵያ ያቀረበው ጥያቄ የፈጥኖ ደራሽ ታጣቂዎች በድንበር በኩል ወደ ጎረቤት ሃገራት ሾልከው ሊያመልጡ ይችላሉ ከሚለው ስጋት የመነጨ ነው ተብሏል።

በሱዳን መንግስት ሰራዊትና በፈጥኖ ደራሽ የሃገሪቱ ሃይል መካከል የተከፈተው ግጭት ሳምንት ሊሞላው ነው።

በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ የሱዳን ህዝብ ወደ ሰላም እንዲመለስ ለማድረግና ልዩነቶችም በንግግር እንዲፈቱ ድጋፍ እንደምታደርግ በይፋ ማስታወቋ ይታወሳል።

አንዳንድ ሃገራት በሱዳን ግጭት ጣልቃ በመግባት የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር እየሞከሩ መሆኑን ደግሞ ሁለቱም የሱዳን ተፋላሚዎች ሲከሱ እንደነበር ይታወሳል።

ወታደሮቻቸውን መሃል ሱዳን ውስጥ አስፍረው የተገኙት  ሃገራት ደግሞ የራሳቸውን ግልፅ የጣልቃ ገብነት ሴራ ለመሸፈን ኢትዮጵያንም ወደ እኩይ ሴራቸው ስበው ለመክተትና ስሟን ለማጠልሸት የበሬ ወለደ ወሬያቸውን መንዛት ጀምረዋል።

ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

https://t.me/CommandoAndAirborneCommand

YouTube


130 viewsedited  08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 11:17:33 ሱዳን 200 የሚደርሱ የግብጽ ወታደሮችን ማስወጣቷን አሳወቀ

የግብጽ ወታደሮች ለጋራ ወታደራዊ ልምምድ ተልእኮ በሱዳን ነበሩ ተብሏል። የግብጽ ጦር ወታደሮቹ ሱዳንን ለቀው እንደወጡ እስካሁን አላሳወቀም። 
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ያንብቡ፤ https://am.al-ain.com/article/egyptian-troops-evacuated-from-sudan

https://t.me/CommandoAndAirborneCommand

YouTube


133 viewsedited  08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ