Get Mystery Box with random crypto!

እንዳንበሳ መከበርና መፈራት ያማረው ውሻ አንድ ቀን ጏደኞቹን ይሰበስብና እንዲ ይላቸው ጀመር እኛ | Agape Love❤

እንዳንበሳ መከበርና መፈራት ያማረው ውሻ አንድ ቀን ጏደኞቹን ይሰበስብና እንዲ ይላቸው ጀመር እኛ ውሾች ሰዎች የሚንቁንና የማያከብሩን ማንም ቡችቡች ብሎ ሲጠራን እሮጠን ስለምንሄድ ነው ይህው ከዛሬ ጀምሮ ማንም ቡች ቡች ስላለን እሮጦ መሄድ ይበቃል ብሎ ተናግሮ ሳይጨርስ ድንገት እንዱ ቡች ቡች ሲል ምላሱን እያለከለከ ሮጠ::

ታዲያ በዚህ ዘመን ቡቺ ብቻ ሳይሆን እኛስ የተናገርነውን የሰበክነውን የዘመርነውን እንኖር ይሆንን??? ምስቦኮቻችንና ሜዲያችን በሚያስደምም የቃልና የዝማሬ ትዕይንት ተሞልቶ መሬት ላይ የወረደው ኖሮ በእርግጥ አንድ ነውን? የሰው ጆሮ ጠቦ አፉ የፋ እስኪመስል ሁሉ ተናጋሪ ሁሉ አዋቂ ሁሉ ልሰማ ባይ የሆነም አይደል? አንድ ቀን ባወቅነውና ባስተማርነው ልክ በጌታ ፊት መጠየቅ እንዳለ ሳንረሳ መኖር ከብዙ ፍርድ ያድነናል::
ጌታችን እየሱስ ሲናገር እንዲህ አለ ~ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥
ሉቃ 12: 48
~ ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ያዕ 1:19


ኢየሩሳሌም ነጊያ

@Shineyourbrightt