2022-08-26 20:56:16
በእሳት ጨዋታ!
قال الشيخ أ.د/سليمان الرحيلي حفظه الله
ሸህ ሱለይማን አሩሀይሊ (አላህ ይጠብቃቸው) እንዲህ ይላሉ።
《نصيحة للشباب أن يستغلوا هذه الجوالات في نشر العلم بين الناس ... وأن ذلك يعتبر من الجهاد العظيم وسبب لتحصيل الأجور الكريمة》
《ለወጣቶች የምመክረው ስልካቸውን ለሰዎች ኢልምን በማሰራጨት ላይ እንዲጠቀሙበት ነው። ይህ ካደረገ
ከትልቅ ጅሀድ (በአላህ መንገድ ከመታገል) ይቆጠርለታል። እንዲሁም
ብዙ የሆነ የከበረ አጅርም ያስገኛል።》
ልብ በል ወዳጄ
ስልክህ
ላፕቶፕህ
የተለያዩ የምትጠቀማቸው የመገናኛ መሳሪያዎች ከአላህ የተሰጠህ ፀጋዎች ውስጥ ናቸው። የአላህን ፀጋ በመልካም ነገር ላይ ማዋል እንደማመስገን የሚቆጠር ሲሆን በዛ ፀጋ አላህን ማመፅና ወንጀል መስራት ደሞ ያንን ኒእማ እንደመካድ ይቆጠራል። እነዚህ መሳሪያዎች ነገ አላህ ፊት በምን ጉዳይ ላይ ስትጠቀምበት እንደነበርና ምን ስትሰራባቸው እንደነበር ትጠየቃለህ። ስለዚህ በስልክህም ሆነ በሌላው መሳሪያህ ኸይር ስራበት።
ዳእዋ አሰራጭበት
ኢልምን ቅሰምበት
ሰዎችን ምከርበት
ዝምድናን ቀጥልበት
ቁርአንና ሀዲስ አዳምጥበት
ወደ መልካም ተጣራበት
ለሰዎች የኸይር ሰበብ ሁንበት
ይህ ካደረክ ከከባድ ቅጣት ድነሀል። የአላህንም ፀጋ በመልካም አውለሀል። የብዙ አጅር ባለቤትም ትሆናለህ። ነገር ግን ከዚህ አልፈህ መጥፎ ምትሰራበትና አላህን ምታምፅበት ከሆነ ለምሳሌ
ፊልም ምታይበት ከሆነ
ሙዚቃ ምትሰማበት ከሆነ
ፎቶ ምትላላክበት ከሆነ
ሰውን ምታማበት ከሆነ
ሰውን ምትበድልበት ከሆነ
ከአጅ ነብይ ጋር በልቅ ምታወራበት ከሆነ
በማይረባ ነገር ጊዜህን ምታባክንበት ከሆነ
በኳስና ጌም በመጫወት ጊዜህን ምትገልበት ከሆነ
በተለያዩ ሚዲያዎች አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ምትፈፅምባቸው ከሆነ በእጅጉ ከሰርክ። ትልቅ የማትመልሰው ጥያቄና አሳማሚ ቅጣትን ተሸከምክ። ስለዚህ ቶሎ በመመለስ ወደ አላህ ቶብት። ያላስፈላጊ የሆኑ ነገራቶችን ከስልክህና ከላፕቶፕህ ደልት። የሰበሰብካቸው የአጅ ነብይ ፎቶንም አጥፋ። ስልክህ የሙስሊም ስልክ ይምሰል። ሞት መች እንደሚመጣ አይታወቅምና ስልክህና ላፕቶፕህ ይህን ሀራም እንደተሸከመ ልትሞት ትችላለህ። ነገ አላህ ፊት ይህንን ወንጀልህ ይዛ ብቅ ትላለችና ተጠንቀቅ።
ብዙዎቻችን በአካል የማንሰራውን ከባድ ወንጀል በስልክ ሲሆን ግን በቀላሉ እንዳፈረዋለን
ሰዎች በተሰበሰቡበት መናገርና መፃፍ ሚያሳፍረንን ተግባር በስልክ ግን ምንም አይመስለንም
በድንጋጤ የህፃን ልጅ ፀጉር ሽበት የሚያስበቅል ወንጀል ነው ዛሬ በስልክ አማካኝነት እየተሰራ ያለው
ብዙዎቻችን ደሞ በስልክ የሚሰራን ወንጀል የሚፃፍ አይመስለንምና እንዘናጋለን። ይህ ሁሉ ስህተት ነው
ኧረ ይህ ስልክ
የስንቱን ሀያእ ገፈፈ
የስንቱን ኢማን አራገፈ
የስንቱን ተቅዋ ገደል ከተተ
ኧረ የስንቱን ጨዋነት ነው ያበላሸው
ኧረ ስንቱ ነው የኢማን ጥፍጥና ያጣው
ኧረ ስንቱን ነው የስሜት አምላኪ አድርጎ ያስቀመጠው
ኧረ ብዙ ሰው ነው በዚህ ሰበብ ኢባዳን የረሳው
ኧረ ስንቱ ነው ከአላህ ባርነት ወደ ሸይጧን ባርነት የቀየረው
አላህ ካዘነላቸው ከጥቂቶች በቀር
ዉዴ እኛስ ከየትኞቹ ነን እስቲ በስልካችን ጉዳይ ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ። ያለፈው አልፏል! ይብቃን ከንግዲህ። በእሳት ጨዋታ የለምና በእውነተኛ ተውበት ወደ አላህ ተመለስ ። ሙእሚን በአንድ ጉድጓድ ሁለቴ አይወድቅምና አካሄዳችንን እናሳምር። ወገን ሆይ ንቃ።
||
በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ሊንኮች ፤ በቀላሉ የምለቃቸው መረጃዎች እንዲደርሷችሁ ከፈለጋችሁ ተቀላቀሏቸው።
#በቴሌግራም
t.me/shemsu_jemal
#በትዊተር
https://twitter.com/shemsujemmal
#በፌስቡክ
https://Facebook.com/ShemsuJemmall
Join follow Sher like ያድርጉ!
299 viewsedited 17:56